2000 የፍቅር ደብዳቤዎች
መጋቢት 2, 2000
ኒል እንደምን አለህ ኒል
እጅግ አድርጌ እወድሃለሁ:: ለመሆኑ እንደምን ከርመሃል? ያመመህ ይመስለኛል:: ለመሆኑ ምንድነው የሚያምህ? ጓደኛህስ እንዴት ነው? በእርግጥ እኔ ባልተለመደ ሁኔታ እጅግ የሚከብዱ እንግዳ ነገሮችን እያየሁ ነው:: ነገር ግን እግዚአብሄር ከእኔ ጋር ነው:: በእርግጥ አንተንም እንደምጠብቅህ አውቃለሁ:: ከእኛ የምጠበቀውንና እፈፅመው ዘንድ እግዚአብሔር የላከኝን በትክክል እንደምፈፅም እንደምታምነኝ ተስፋ አደርጋለሁ:: አንተን በተመለከተ እያደረክ ያለውን ነገር እግዚአብሔር ካልረዳውና ካላገዘው በስተቀር ማንም ሊያደርገው አይችልም:: መዓዛ ትላንትና ይህንን ጉዳይ አስረግጣ ነበር የነገረችኝ:: እዚህ ያሉ ሰራተኞች ሁሉም አብዝተው ስለአንተ ያስባሉ፤ይጨነቃሉ:: ባለፈው ሳምንት በእኛ ፕሮግራም ምክንያት ሁለት የቅርብ ጓደኞች ተለያይተዋል። ሴቷ የምትሰራው በአበባ እንዱስትሪ ውስጥ ሲሆን ወንዱ ደግሞ እዚህ በእኛ ድርጅት ውስጥ እንዲሰራ ቀጥሬዋለሁ።
እንግዲህ ወንዱን የመቅጠሬ ጉዳይ ነው ሁለቱ ጥንዶች በተለያየ ቦታ እንዲኖሩ ያደረገው። ሁለቱም እጅግ በጣም አዝነው፤ ይላቀሳሉ። እኔም ቢሆን በእነርሱ ሁኔታ በጣም አዝኛለሁ። ዳሩ ግን እኔና አንተም እንዲሁ ጥንዶች ነን ፣ ነገር ግን ተለያይተን በተራራቀ ስፍራ ነው የምንኖረው። በዚሕም ከመጠን በላይ ነው የማዝነው። በዚህም ምክንያት እነዚህ የተለያዩ ጥንዶቸ ሲያለቅሱ እኔም አብሬያቸው አለቅሳለሁ። እናም በዚህ አስቸጋሪ ወቅት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ስለሆነ ቶሎ ያገናኘናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ከናይጄሪያ የሆነች አንዲት ጠንካራ ክርስቲያን እህት አልፎ አልፎ ከእኔ ጋር ትፀልያለች። ይህች እህት ስለአንተ ስትፀልይ ነግራኝ በመልካም ጤንነትና ሁኔታ በጥቂት ወራት ውስጥ እንደምትመጣ እና እንደምንገናኝ ነግራኛለች። ይህም በጣም አበረታቶኛል። ኒል በርታ። የእኛ ብርታትና ጥንካሬ ከሁሉም በላይ አስፈላጊ ነው። እግዚአብሔር ስለ እኛ ስለሚሰራ ሁሉንም በአሸናፊነት እንወጣለን። የእርሱን ስራ ደግሞ በእኛ እውቀት ልንቃወም አንችላለን እንዴ? አብዝቼ እወድሃለሁ!
ቤኪ
መጋቢት 4, 2000
ቤኪ
ለወር ያክል ከአንቺ ኢ-ሜይል ባለማግኘቴ ግራ ተጋብቻለሁ። ከዚህ ጋር ሁኔታዎች ተጨማምረው ተስፋ አስቆርጠውኛል። የሚከፈል ገንዘብ ባለመኖሩ ምክንያት ስልኮቻችን ወደ መዘጋቱ ደርሰዋል። በሹፍርና ከሚረዳኝ ሰው ጋር ሆነን ግማሸ ጊዜያችን በሀዘን ሆነን ያለ ስራ ነው የምናሳልፈው። በዚህን ጊዜ በእጄ ላይ ያለው ገንዘብም በጣም ጥቂት ነው። በዚህ ምክንያት ቲ ሸርት እንኳ መቀየር ባለመቻሌ በግራ እጄ ላይ የተቀደደ ቲ ሸርት ነው ምለብሰው። መኪናችንም ችግር አለበት። በቻታኑጋ ሳለን ችግሩን ያገኘን እኛው ነን። በዚህ በቻታኑጋ ያለውም የስራ ስነ-ስርዓት ከሌሎች ቦታዎች የተለየ ነው። እናም ይህንን የመኪናችንን ችግር ለመፍታት ማንን ማናገር እንዳለብኝ ጠይቄ ነበር። ሶስተኛ ፎቅ ሄጄ ሊያስተናግደኝ በሚችል መልኩ ህጉን እንዲቀይሩልኝ የሆነ ሰው መናገር እንዳለብኝ ተነገረኝ። ወደ ተጠቀሰው ፎቅ ሄደን ፀሐፊ ካነጋገርን በኋላ የኮቬናንት የጭነት ማመላለሻ ድርጅት ፕሬዚዳንት የሆኑትን ሚስተር ጆይ ሆገን እንዳገኛቸው ተነገረኝ። እሳቸውን ሳነጋግራቸው በጋዜጣ ላይ ስለ ኢትዮጵያ ያሳተምነውን እንዳነበቡ አስታወሱ። ስለዚህ ጉዳይ ጥቂት ካወራን በኋላ ወደ መኪናቸው ወሰዱኝ፤ በመኪናቸውም ውስጥ ሆነን አንድ እኔ እማላውቀውን ሰው በስልክ ጠሩ። ሰውዬውም እየተጣደፈ መጣ። ተዋወቁ፣ ሚስተር አር ኤች ላንቭ ይባላሉ አሉ ሆገን። እኔም ስሜን ነግሬያቸው ተዋወቅን። እኚሕ ሰው ሁለት ሳምንታት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚሄዱ ነገሩኝ። እናም ሆገን ከሁለታችን ጋር ስብሰባ እንድናደርግ ቀጠሮ ይዞ ተለያየን።
አር ኤች ላቭን በኢትዮጲያ ውስጥ በምንሰራው ስራ በጣም ተደስቷል። ፕሬዝዳንቱና አር ኤች ቀጠሮ ይዜ ድቪድ ቤካርንና ጆይ ሆገንን እንዳነጋግረው መክረውኛል። አሜሪካ ውስጥ አስካለሁ ድረስ በማንኛውም ጊዜ ቀጠሮ በማስያዝ ምን እንደምሰራ እና ፍላጎታችን ምን እንደሆነ እንዳስረዳቸው መክረውኛል። እንደሚረዱኝም አረጋግጠውልኛል። ይህ ትልቅ አጋጣሚ ነው። ሌሎችን በመርዳት ውስጥ የኮቬናንት የማመላለሻ ድርጅት ከኛ ጋር የመተባበሩ ነገር ትልቅ እድልና በረከት ነው። እንግዲህ መጥፎ አጋጣሚዎችን ወደ መልካም እድል መቀየር የሚቻለው ለእግዚአብሔር ብቻ ነው። እንግዲህ ከመጋቢት 27 እስከ ሚያዝያ 5 ባሉት ቀናት ወደ ሀገሬ እመለሳለሁ። በዚያ በቻተኑጋም ዊንዲ ቤት እቆያለሁ። አር ኤች ላቪን መጋቢት 26 አዲስ አበባ ይደርሳል። ሚያዝያ 9 ደግሞ ደብረዘይት የሚገኘውን ወላጅ አልባ ሕፃናት ማሳደጊያ ጣቢያ ይጎበኛል። እባክሽ ቀጥሎ በተመለከተው ኢሜይል በመጠቀም የስልክ ቁጥርሽን ስጭው። ከዛውም ስደውልልሽ ሁሉንም ገልጸሽ ንገሪው። Loviymkiah@transport.com:: የሚገርምሽ ነገር ከኮቬናነት ማመላለሻ ድርጅት ፕሬዚዳንትና ከድርጅቱ የአስተዳደር ክፍል ምክትል ፕሬዚዳንት ጋር በኢትዮጵያ በምናደርገው ስራ ጉዳይ ላይ ማነጋገሬን በፍጹም ማመን አልቻልኩም። በነዚህ ባለስልጣናት ፊት መቅረብ የቻልኩት በእግዚአብሔር እቅድና ዓላማ እንጂ እኔ ተራ ሰው ቀርባለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም። ፕሬዚዳንቱ ሪቤካ ወደ አሜሪካ ስትመጣ ፕሬዚዳንቱ ጋ በመደወል ቀጠሮ በማስያዝ ዓላማዋንና የሚያስፈልጋትን እርዳታ ለማግኘት ማነጋገር ትችላለች ብሏል።
ከዴቪድ ፓርከር ጋርም እንዲሁ በሚያስፈልጋት ነገር ሁሉ መነጋገር ትችላለች ብሏል። ይህም በአስቸኳይ በሚያስፈልጋትና በየወሩ በሚያስፈልጋት የገንዘብ ዝርዝር ዕቅድ በማቅረብ መጠየቅ ትችላለች ብሎኛል። የማሽከርከሩን ስራ በተመለከተ የዕለት መዝገብ አያያዝ ላይ ትንሽ ግራ ገብቶኝ ስለነበር ግንዛቤ ለማግኘት ብዬ ለመማር ሄጄ ነበር። ወደ ክፍል ሄጄ ባለሙያውን ለማነጋገር ተራዬን በመጠበቅ ላይ ሳለሁ አንድ ሰው ወደ እኔ ቀርበው ሚስተር ላቪን ሊያነጋግረኝ እንደሚፈልግ ነገረኝ።ትንሽ ቆይቶ ደግሞ ያው ሰው እንደገና መጥቶ ሚስተር ላቪን በ3፡30 እንደሚያገኘኝ ነገረኝ። ተራዬን በመጠባበቅ ላይ ሳለሁ የሆነች ሴት ተራዬን በመጠባበቅ ላይ መሆኔን ለማረጋገጥ መጣች። ይህንንም እንዳረጋገጠች የመጀመሪያው ተረኛ እንድሆን ሁኔታዎችን አመቻቸችልኝ። ትምህርቱን እየተከታታልኩ እያለሁ የዚያ ክፍል ከፍተኛ ኤክስፐርት ወደ እኔ ቀርቦ ፕሬዚዳንቱ ከእኔ ጋር ለመገናኘት በእንግዳ መቀበያ ውስጥ እየጠበቁኝ እንደሆነ ነገረችኝ። ሰዎች ሁሉ በጥሩ ሁኔታ እንዲቀርቡኝ፤ የነካሁት ሁሉ እንዲቃናልኝ፤ የማናግራቸው ሰዎች ሁሉ ውድና የማይረሱ ወዳጆች እንዲሆኑልኝ በመንፈሴ ዝግ ብዬ አሰብኩ። ይህም የማይረሳ ትውስታዎቼ ሆነው ይቀራሉ። አፍቃሪሽ ነኝ,
ኒል
መጋቢት 4, 2000
ኒል
ሆጋንና ላቪን ጋር የሆነውን ጉዳይ በተመለከተ የጻፍክልኝን ኢሜይል ደግሜ ደጋግሜ እያነበብኩኝ ነበር። በተጨማሪም አሁን የኮቨናንት ማመላለሻ ድርጅት ይህን ያህል ዕውቅና ስለሰጠህ እጅግ ተደስቻለሁ። እስከአሁን ባልተሳካ ሁኔታ ውስጥ ሆነህ አሁን ግን እግዚአብሔር በበረከት ስለጎበኘህ እጅግ ተደስቻለሁ። አንተ የካበተ የማሽከርከር ልምድ ይዘህ ከኮቨናነት የማመላለሻ ድርጅት ጋር በጥሩ ሁኔታ መስራት በመቻልህ ለእኔ ታላቅ በረከት ነው። በዚህ መንፈስ ውስጥ ሆኜ የሚስተር ላቪን ወደዚህ ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ማለት ምን አንድምታ እንዳለው ሳስብ እጅግ ደስታ ይሰማኛል። ወደ ፊት በኢትዮጵያ ውስጥ ለምናደርገው መልካም ስራ አመላካች ነው። በእውነት እወድሃለሁ። ፈጥኜ ላይህም እናፍቃለሁ። አፈቅርሃለሁ
ቤኪ
መጋቢት 6, 2000
ኒል ከአር.ኤች በሁለት ሳምንታት ውስጥ እንደሚመጣ ታውቃለህ። ምን አለበት አብራችሁ ብትመጡ? እባክህ ከአሁኑ ተዛጋጅና ለመምጣት ሞክር። በዚህን ጊዜ ወደ 1300 ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ አለን። የቤታችንን ኪራይ ባታገኝም ግድ የለኝም። እባክህ ለመምጣት ሞክር። ትኬት እንድታገኝ አደርጋለሁ።ዊንዲ ፓስፖርትህ ታድሶ እንደሆነ ታረጋግጥልህ። እባክህ የመምጣቱን ነገር ከዛሬ ጀምሮ ማቀድ ጀምር። እዚህ ያለን ሁላችን መምጣትህን በእጅጉ እንፈልጋለን። በተለይም እኔ እጅግ እፈልጋለሁ። እባክህ ቶሎ አሳውቀኝ። እወደሃለሁ!
ቤኪ
ግንቦት 23, 2000
እንደምን አለህ ኒል
እባክህ በያሁ ኢሜሌ በመጠቀም ኢሜል ጻፍልኝ። ይህንን አድራሻዬን ለሌላ ሰው ሰጥተህ ነበር እንዴ? አንተ እንዴት ነህ? በጣም እወድሃለሁ። እግዚአብሔር ለእኛ መልካም ነው። በፍጥነት እኔ ዘንድ ብትደርስ እመኛለሁ። ምን አዲስ ነገር አለ? የኮቨናንት ማመላለሻ ድርጅት እንዴት ሊረዳን እንደፈለገ ለማየት ጓጉቻለሁ። ምናልባትም ትንሸ ገንዘብ ካገኘን ወደ አሜሪካ ቶሎ መመለስ የሚያስፈልገኝ ይመስለኛል። ነገሮችን ህጋዊ ለማድረግ መስራት ያለብኝ ይመስለኛል። ለምሳሌ አንድ የአስተዳደር ዳይሬክተር ማስቀመጥ አስፈላጊ ይመስለኛል። በፍትህ ሚንስቴር መስፈርት መሰረት እኔ ለዚህ ቦታ ብቁ አይደለሁም። ምክንያቱም 1. ኢትዮጵያዊ አይደለሁም 2. በኮሌጅ ትምህርት ውስጥ አላለፍኩም። ስለዚህ ወንድወሰንን በዚህ ቦታ ላይ ቶሎ መሾም አለብኝ። ይህም በህጉ መሰረት ስራዎቼን ለማከናወን ያስችለኛል። ከእግዚአብሔር በቀር ሁሉን የሚያውቅ የለም። እኔም እንደዚሁ እርሱ ያውቅልኛል እንጂ ብዙ የማልረዳቸው ነገሮቸ አሉ:: በሚቀጥለው ሳምንት መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች ብሄራዊ ፈተና ይወስዳሉ። እንደቀደመው ሁሉ በዚህም ዓመት ጥሩ ውጤት ያመጣሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ከአንተ በኩል ያለውን ሁሉ አሰማኝ። እጅግ አድርጌ እወድሃለሁ።
ቤኪ
ግንቦት 23, 2000
ቤኪ
ከተማችንን ሪኪነን ለሰባት ቀናት ልንርቃት ትላንት ወደ ቻታኑጋ ደርሰናል። መኪናችን ጥገና ያስፈልግ ስለነበረ እዚህ መቆየት አለብን። ዛሬ በ5፡00 ሰዓት ገደማ አስፈላጊው መለዋወጨ ዕቃ ለማስመጣት አምስት ቀናት ይፈጃል ብለው ስለነገሩን ለተጨማሪ 5ቀናት እዚህ እንቆያለን ማለት ነው። ይህም አስከ ግንቦት 29 ወይም 30 ይሆናል። ለዊንዲ ደውዬ ነበር ነገር ግን እነርሱ እስከ ግንቦት 26 ድረስ ከከተማ ውጭ እንደሆኑ ነግራኛለች። ዛሬ የጉዞ መዝገብ አያያዝ ትምህርት ተከታትያለሁ። ከዚህም ሌላ መኪናዬን አጽድቻለሁ። ለጽዳት የምንጠቀምባቸውንና የቆሸሹት ቁርጥራጭ ጨርቆጭ ሁሉ ከመኪናዬ አስወግጃለሁ። ወለሉንም ወልውዬ በማጠብ አጽድቻለሁ። ለመኪናው መጠነኛ ጥገናመ አድርጌያለሁ።ለሾፌሮች እውቅና ለመስጠት በተደረገው የዕራት ግብዣ ላይ አር ኤችን አግኝቼያለሁ። በዚያን ወቅት አንቺ የላክሽለትን የዲቪዲ ግልባጭ ሰጥቶኛል። የኮቨናንት ማመላለሻ ድርጅት ጋዜጣ አዘጋጅ ከሆነችው ጎዲፈሬ ጋር አስተዋውቆኛል። እርሷም ፎቶ አንስታኛለች። የአንቺንም ፎቶግራፍ ትፈልጋለች። ከጀርባሽ ተማሪዎች እንዲሆኑ አድርገሽ ተነሽና ላኪላት። ጎዲፈሬ የላከችልኝ ኢሜይል በያሁ ኢሜልሽ ስለላኩልሽ በዚያ በኩል ተገናኚያት። ሲያስፈልግሽ እንድታገኚያት የኢሜይል አድራሻዋንም በዚያው መዝግበሽ ለራስሽ ያዢ። ይህንን መልዕክት የምጽፍልሽ ለሁለተኛ ጊዜ ነው ምክንያቱም በስህተት ልክ ያልሆነ ቁልፍ ነክቼ ስለተደመሰሰብኘኝ ነው። ትላንትና ቺኤፉ የሚባል ምግብ በልቻለሁ:: ይህ ምግብ ከአትክልትና ከዶሮ የሚሰራ ነው። የወሰድኩት አንድ ፒንት ያክል ሲሆን ይህም በቂዬ ነው።
ከ5 ወይም 6 ቀናት በፊት ከሪኪ ጋር ሆነን የተመገብነው በፖንዳ ሮሳ ነበር። በዚያን ቀን የበላሁት ሁሌ ከምበላው በላይ ነበር። በስምምነታችን መሰረት መዳረሻችን የምንደርሰው ከአንድ ቀን ተኩል በኋላ ስለነበር ድካምና ሕመሜን ለማስታገስ በ40 ዶላር ማረፊያ ተከራይቼ አረፍ አልኩ። በዚህ በተከራየሁበት ክፍል ትንሽ የሚያሳርፈኝ የሙቅ ውሃ ሻወራቸው ነበር። እናም 5ቴ ወይም 6ቴ ታጥቤ ወደ መኝታዬ ሄድኩ። እጅግም ተኛሁ። የነቀሁትም በጣም አርፍጄ ከጥዋቱ 3፡00 ነበር። ወዲያውም ጉዞ ነበር የቀጠልነው። በሕመሜ ምክንያት እጅግ ተስፋ ቆርጬ ነበር። ነገር ግን ሕመሜ የቆየብኝ ለ7 ሰዓታት ነበር። ይህን የምነግርሸ ላስጨንቅሽ ሳይሆን ትክክኛውንና እውነት የሆነውን ላሳውቅሽ ብዬ እንጂ። ከምናደርገውም ነገር ምንም እንዲቀየር ፈልጌም አይደለም። ምንም ችግር በዝቶ ቢመጣ እግዚአብሔር እንደምቀይረው አውቃለሁ። በዚህን ሰዓት በልቤ ውስጥ ከአንቺ ጋር ነኝ። እኮራብሻለሁ። ስለ አንቺ ለሌሎች ሳወራ እጅግ እየኮራሁብሽ ነው። አንቺ ከምትከውኝውና ከምታስመዘግቢው መልካም ውጤት ውጪ የማስበው ነገር የለኝም። በማንኛውም ጊዜ እወድሻለሁ። መልካም በሰራሁ ጊዜ እወድሻለሁ፤ ምናልባት አጥፍቼ በጸጸት ውስጥ ቢሆንም እወድሻለሁ። ሁሉ አልቆ በእጄ ላይ ምንም ባይኖርም እወድሻለሁ። እጄ በበረከት ሞልቶ ስለ እኔ መልካም ነገር በሚወራበት ጊዜም እወድሻለሁ። ምክንያቱም ሁሉም በእኔ አይደለም በአንቺም አይደለም። ነገር ግን ሁሉም ስለ እኛ ነው፤ ሁሉንም ያደረገው ደግሞ እግዚአብሄር ነው። በየቀኑ እወድሻለሁ።
ኒል
አሁን በቻታኑጋ ውስጥ ስለ ሆንክ ለምን ቶምን አታናግረውም? እባክህ የቦርድ ስብሰባ የምታደርግበት ሰዓት አሁን መሆኑን ንገረው። እባክህ አንተ እዚያ መሆንህን ንገረውና ኡገኔን ይዞ የቦርድ ስብሰባ አንተ በተገኘህበት የቦርድ ስብሰባ እንዲጠራ ለማድረግ ሞክር። ስብሰባ የምታደርጉት በስንት ሰዓት እንደሆነ በትክክል ንገረኝ። ለዲቦራም በኢሜይል ንገራት። ለቶም አሁኑኑ እጽፍለታለሁ። እባክህ አንተ እዚያ እያለህ ቶም ለስብሰባው ዝግጅት እንዲያደርግ ንገረው። ከእርሱም ጋር እንደተነጋገርክ ምን እንደተባባላችሁ ንገረኝ። በስብሰባው ላይ የወንድወሰን ጉዳይ መነሳት አለበት። እንደምታውቀው ቀጣዩ የሚሽናችን ዳይሬክተር አድርገን ለመሾም አስቤያለሁ። ይህንንም በዚያ በስብሰባው ላይ እንዲወሰን አድርጉ። ይህ ጉዳይ በጣም አስቸኳይ ስለሆነ እዚያው ቻታኑጋ እያለህ ፈጽም። እወድሃለሁ አመሰግንሃለሁም።
ቤኪ
ሰኔ 2, 2000
እንደምን አለህ ኒል
ዴኒስ እጅግ ታላቅ ነገር ሰርታለች። በጋዜጣቸው ላይ ባስቀመጠችው ታሪክ ውስጥ ታላቅ ነገር ሰርታለች። እንደምኮራብህ ልታውቅ ይገባል፤ ምክንያቱም በጋዜጣ ውስጥ ዴኒስ የተጠቀመችው ታሪክ የአንተ ነውና። እግዚአብሔር ያንን ጋዜጣ በመጠቀም ሌሎች ብዙዎችን እንደሚያነሳሳ ተስፋ አደርጋለሁ። ታሪኩን በኢሜይል ልኬልህ ነበር፤ ነገር ግን በኢንተርኔት መረብ መቋረጥ ምክንያት ጠፍቶብኛል። እንዲያው በአጭሩ እንድትገነዘብ ጉዳዩን ገልጬ ለኡገኔ ጽፌላታለሁ። በቦርድ ስብሰባ ላይ እንድትገኝ ጥረት እንድታደርግ ነግሬያታለሁ። በአሜሪካ ውስጥ እስከ አሁን ምንም የቦርድ ስብሰባ አልተደረገም። ይህ ደግሞ መልካም አይደለም። ስለሆነም ለዓመታዊ የቦርድ ስብሰባ ይህ ወር የመጨረሻ ነው። እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ህጋዊ የሆኑ ስራዎች ለመስራት አልቻልኩም። ምክንያቱም ዳይሬክተር ስላልተሾመ ነው። ዳይሬክተር ቢኖረን ኖሮ የምንሰራቸው ብዙ ህጋዊ ስራዎች ነበሩ። ኩቢ እንደ ዳይሬክተር እንዲንቀሳቀስ ብጠይቀውም ሊቀበለኝ አልቻለም። ምናልባት እግዚአብሔር በዚህ መንገድ የምሰጠውን ተልዕኮ ተገንዝቦ ሀሳቡን ይቀይራል የሚል እምነት አለኝ። ካልሆነ የዚህን ስፍራ ሀላፊነት እኔው ራሴ ለመያዝ እገደዳለሁ። ካልሆነም ወንድወሰን ቦታውን የሚይዝ ይሆናል። ለማንኛውም የቦርድ ስብሰባ እጅግ ጠቃሚ በመሆኑ እንዲካሄድ ጫና ፍጠር። እልፍነሽ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች። የሞተችው ትላንትና ነው። ከኤድስ ጋር የኖረችው ለረጂም ዘመን ነበር። ይህ ሁኔታዋ ሳስበው ያመኛል። ከሌሎች ሀዘንተኞችና ለቀስተኞች ጋር ወደ ቤቷ እሄዳለሁ የሚል ተስፋ አለኝ። እወድሃለሁ!
ቤኪ
ግንቦት 29, 2000
ቤኪ
በእርግጥ ሶስት ሰዎች ሆኖ ስብሰባ መቀመጥ ቀላል አድርገሽ እንደምታስቢ አውቃለሁ። እኔ ግን በጣም ሰልችቶኛል። በክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ከቶም ጋር ሆኜ ኡግኔን ብዙ ጠብቀናል። እንደ ገባሁ እደውልልሃለሁ ብሎኝ ነበር። ነገር ግን ከእርሱ ምንም ነገር ሳልሰማ ሁለት ቀን ሆኖኛል። ከዚህም ሌላ ከ15 እስከ 20 ጊዜ ደውያለሁ፤ ነገር ግን ስልኬን አይመልስም። በዚህ ምክንያት ቶምም ተስፋ እየቆረጠ ነው። በሌላ መልኩ በሁለት ቀናት ውስጥ ወደ ስራዬ መመለስ አለብኝ። ከአሁን በኋላ እኔና ሪክ ለ14 ሳምንታት በቤታችን ለመቆየት የምናቅድ አይመስለኝም። እወድሻለሁ!
ኒል
ሰኔ 5, 2000
ብቸኛ አፍቃርዬ የሆንሽ ለውድ ፍቅሬ
ከአር ኤች ጋር በመሆን የላክሽውን ቪዲዮ አይቸ ለመገንዘብ ችያለሁ። ከዚህ ቪዲዮ ቅዱስና ከባድ ስራ እየሰራሽ መሆንሽን የሚያሳምን መልዕክት አግኝቻለሁ። በኬንትና በዊንዲ ቤቶች በተደጋጋሚ ጊዜ ይህንን ቪዲዮ ተመልክቻለሁ። ረዳቴም ሁለቴ ወይም ሶስቴ አይቷል። አሁንም ለመመልከት ይፈልጋል። ለእናቱ፣ ለእህቱ እና አያቱ ለማሳየት ይፈልጋል። እኔም ስመለከተው የተለየ ስሜት ፈጥሮብኛል። እናም መግለጽ በማልችል ከፍ ባለ መጠን እወድሻለሁ። በርቀት ላይ ብትሆኝም በቅርበትሽ በመሆኔ ተባርኬያለሁ። ከሚሰማሽ ወይም አንቺ ለሌሎች የምታደርጊውን ነገር ከሚያውቅ በረከት ልቀበል የተገባሁ አይደለሁም። በዚህን ጊዜ ፀሎት እያደረግሽልኝ ከሆነ እባክሽ አታቋርጭ። ዛሬ ጠዋት የአንድ ሰባኪ ንግግር አዳምጥ ነበር፤ በቀጥታ እኔን የሚመለከት ነበር። ይህ ሰዓት የመተኛዬ ሰዓት ነበር። እናም በሰማሁት ነገር ስቅስቅ ብዬ አለቅስ ነበር። የተሰማኝን ነገር መግለፅ አልችልም ነገር ግን ከነበርኩበት ማንነቴ መለወጥ አለብኝ እያልኩኝ ነበር። እግዚአብሔር ከሰውነት ክፍሎቼ ወስዶ በሚሻል አካል እንደቀየረልኝና እንዳደሰኝ ታወቀኝ፤ እግዚአብሔር የሰጠኝን ሰውነት የሚገባኝ ሆኖ ሳይሆን እንዲያው በቸርነቱ ነበር። የዚያ የተሰጠኝ አካል ዋጋም ከምገምተውና ከሚገባኝ እጅግ የበለጠ ነው። እወድሻለሁ!
ኒል
ሰኔ 5, 2000
ኒል እንዴት ነህ
ኢሜይልህን በማንበቤ እጅግ ተባርኬያለሁ። አዎን እንደጠየከኝ በአሁኑ ጊዜ እየፀለይኩልህ ነው። በፀሎት መበርታት አለብን፤ ማቋረጥ የለብንም።እግዚአብሔር መልካም ስለሆነ ይጠብቀናል። በተለይም ለእኔ በተለየ ሁኔታ ነው የሚጠብቀኝ። እግዚአብሄር ምን ያክል እንደለወጠህ ስትነግረኝ የሚያስደነቅ ነገር ነው!!!! ቪዲዮውን በመመልከትህና እዚህ ምንሰራው ነገር ምን ያክል ለውጥ ሊያመጣ እንደሚችል በመገንዘብህ በጣም ደስ ብሎኛል። 5 መስማት የተሳናቸውን ልጆች ቢሾፍቱ በሚገኘው ጀነሲስ ፋርም ማስገባታችንን ስትሰማ ትደሰታለህ። ይህንን ቦታ ከዚህ ቀደም ጎብኝተኸው ስለነበር ታስታውሰዋለህ ብዬ እገምታለሁ። መንፈሳዊና ስጋዊ ነገራቸውን የሚያገኙበት ቦታ ነውና ይህ ቦታ ለእነዚህ ልጆች እጅግ በጣም አስፈላጊ ቦታ ነው። ለማንኛውም እዚህ ስትደርስ ገበሬ ለመሆን መመኘት ብቻ ሳይሆን እስከ አሁንም በሆንኩ ብለህ ትመኛለህ። ከዚህም ሌላ ብዙ መስማት የተሳናቸው ልጆች በዚህ ዘርፍ እንዲጠነክሩ ታበረታታቸዋለህ። ጠበቃችን የሆነው ስቲቭ ኢሜይል ልኮልኛል። እናም አሁን ማድረግ ስለሚገባን ጉዳዮችን በተመለከተ የበለጠ ግልጽ ሆኖልኛል። እሱ ከነገረኝ በመነሳት እንግዲህ አንተ ማድረግ ያለብህ ሁለት ነገሮች ናቸው፤ ወደ ቻታኑጋ መመለስ ወይንም ኡጌኔን ጨምራችሁ ወይም ትታችሁ አንተና ቶም ከእኔ ጋር በስልክ የቦርድ ስብሰባ ማድረግ። ቢያንስ ሶስት ሰዎች በአካል ወይም በስልክ በስብስባ ላይ መሳተፍ ከተቻለና ይህንን ማረጋገጥ ከቻልን ስብሰባውን ማስኬድ ይቻላል። እኔ የድርጅታችን የኢትዮጵያ ተወካይ ብሆን መልካም ይመስለኛል። ይህንንም በቦርዱ ስብሰባ የሚወሰን ይሆናል። ሁሉም በእግዚአብሔር ፈቃድ ይሆናል። ለማንኛውም እግዚአብሔር በህይወትህ ውስጥ እየሰራ ያለውን ፃፍልኝ፤ ስንደዋወልም እንድትነግረኝ ይሁን። እጅግ አድርጌ እወድሃለሁ።
ቤኪ
ሰኔ 8, 2000
ሃይ ኒል እንደምን አለህ?
እዚያ እናንተ ጋ ካለው ጠበቃችን በተነጋገርነው መሰረት ከኡጌኔ ወይንም ዲቦራ ውጭ የቦርድ ስብሰባችንን ማካሄድ እንደምንችል በግልጽ ተረድቻለሁ። ነገር ግን አንዴ ማሳወቅ እንዳለብን ነግሮኛል። ስለዚህ እባክህ በተቻለ መጠን ወደ ቻታኑጋ በፍጥነት በመመለስ ስብሰባውን ለማድረግ ሞክር። እናንተ እዚያ ስብሰባ ስታደርጉ እኔ በስልክ ከእናንተ ጋር እሳተፋለሁ። ነገር ግን ይህንን በፍጥነት ማድረግ አለብን። እናም በፍጥነት ወደዚያ ለመመለስ ሞክር። ይህን መቼ ማድረግ እንደምትችል አሳውቀኝ። እወድሃለሁ!
ቤኪ
ሰኔ 9, 2000
ቤኪ
አሁን ለቶም መደወል ትችያለሽ። ስብሰባውንም ዛሬ ማታ ማድረግ እንችላለን። እኔ አሁን የአንቺን የስልክ ቁጥር ቢኖረኝም ልደውልልሽ አልችልም። ባለሁበት አካባቢ ይህን ማድረግ የሚያስችለኝ ካርድ ማግኘት አልቻልኩም። መኪናችንም ቆሞብናል እናም አሁን ያለነው ጆርጅያ ውስጥ ዊልድ ዉድ አካባቢ ነው። ይህ ቦታ ከቻታኑጋ መዳረሻችን 3 ማይሎች ርቀት ላይ ነው። እዚህ ቦታ ካርድ ማግኘት ስለማይቻል ልደውልልሽ አልችልም።
ኒል
ሰኔ 9, 2000
ሃይ ኒል
ቶም ደውሎልኛል። እርሱ እኛ በምናስበው መሰረት ነው ያለው። ስለዚህ ሁሉም ደህና ነው ማለት ይቻላል። ስብሰባውን ዛሬ ማታ እንደምተደርጉ ተስማምተናል። ነገር ግን በ2፡30 ከቶም ጋር ሆናችሁ እንደምትደውሉልኝ ስለተነጋገርን በዚሁ መሰረት ደውሉልኝ። ምናልባት ኤሌክትሪክ ካለ በኢንተርኔት መስመር በመጠቀም መደዋወል እንችላለን ካልሆነ በስልክ መደዋወሉ የበለጠ ይሆናል። ለማንኛውም ሁሉንም ከአንተ ለመስማት በጉጉት እየተጠባበኩኝ ነው። ከኮቨናንት የማመላለሻ ድርጅትም እጅግ ታላላቅ ነገሮችን ሰምቻለሁ። እጀግ የሚያስደስት ነገር ነው። በጣም እወድሃለሁ!!!
ቤኪ
ጭነት ለማሰረከብ ተራዬን አየተጠባበቅኩ ነው። ካሰረከብኩም በኋላ ዩታ ወደሚገኘው ሳልት ሌክ ከተማ እሄዳለሁ። ከኮቨናንት የምናገኘውን እርዳታ በተመለከተ እስከ አሁን ድረስ ምንም የሰማሁት ነገር የለም። በተረፈ የምሰራው ያለእረፍት ነው:: በነዚህ ቅርብ ቀናት ምንም እረፍት ብሎ ነገር በእኔ ዘንድ የለም። በማይታመን መልኩ ብዙ ጭነቶችን እያጓጓዝኩኝ ነው። እናም በጣም ደክሞኛል። በነዚህ አራት ቀናት ውስጥ በማደርገው የመጨረሻ ጉዞዬን ካጠናቀቅሁ ሁለት ሰዓታት እረፍት አለኝ። እወድሻለሁ!
ኒል
ሰኔ 11, 2000
ቤኪ
ለሞባይሌ አዲስ ባትሪ እንደሚያስፈልገኝ ተነግሮኛል። ነገር ግን እዚህ አሁን በቆምኩበት ቦታ ባትሪ የለም። እናም ባትሪ ታዞ እጄ እስኪገባ ድረስ ሁለት ቀናት ይወስዳል። ሞባይሌ ቶሎ ቶሎ ይጠፋል። ሙሉ ለሊት ኤሌክትሪክ ስሞላ ባድርም በ15 እና 20 ሰኮንዶች ውስጥ በራሱ ጊዜ ይጠፋል። አልፎ አልፎ ደግሞ ለአንድ ወይም ሁለት ቀናት ሳይጠፋ ይቆያል። ይህንን መልዕክት እየላክሁ ያለሁት ስልኩ ይሰራ እንደሆነ ለመፈተሽ ነው። እወድሻለሁ!
ኒል
ሰኔ 11, 2000
ኒል
አዎን በትክክል ይሰራል። መልዕክትህን በማግኘቴ በጣም ደስ ብሎኛል። እጅግ በጣም ስለምወድህ ቶሎ እኔ ዘንድ እድትደርስ እመኛለሁ።በቡድን ስለምንፀልይና ዘወትርም ስለምንፀልይ እግዚአብሔር ፀሎታችንን ሰምቶ ይኸውና ወደዚህ እንድትመጣ መንገድህን እያመቻቸልህ ነው። እኔ በስልክ ላነጋግርህ እየሞከርኩኝ ነበር። ነገር ግን ጥሪየ ሊደርስህ ስላልቻለ አሳስቦኝ ነበር አሁን ግን ምክንያቱን ምን እንደሆነ አውቄያለሁ። እወድሃለሁ!
ቤኪ
ሰኔ 11, 2000
ቤኪ
አሁን ያለሁት አይዋ ውስጥ ነው። ከዚያም ወደ ነሽቪል እመለሳለሁ። ቀጥሎም ብቻዬን የምነዳ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ዋሽግንተን ውስጥ ወደሚገኘው ኦሎምፒያ እሄዳለሁ። አብሮኝ የሚሰራ ረዳት ሾፌሬ ከሳምባ ምች ጋር በተያያዘ በህክምና ላይ ነው። ከዚህም ሌላ ተጨማሪ የጤና ችግር እንዳለበት ሰምቻለሁ። ለማንኛውም ስለምንደዋወል ስለ እሱ ሁኔታ እየተከታተልኩኝ ነው። የጤንነቱ ሁኔታ ዳግም ወደ ሾፌርነት የሚመልሰው አይመስለኝም። ጥሩ የስራ ጊዜ አሳልፈናል። ረዢም ጉዞ ነው ያደረግሁት፤ ያለማቋረጥ 11 ሰዓት ከነዳሁ በኋላ ለ15 ደቂቃ ነዳጅ ለመሙላት ቆምኩ። ከዚያም ለ10 ሰዓት ያህል ተኝቼ ሌላ ተመሳሳዩን ረጂም ጉዞ እየቀጠልኩኝ ነው። የዚህን ዓይነት ጉዞ ለብቻዬ ማድረግ ከጀመርኩ በተከታታይ ይኸው 4ኛ ቀኔን ይዣለሁ። መቼ ነው የምንገናኘው። የተለያየን ያክል ይሰማኛል። ይህን ያክል ረጂም ጊዜ መለያየታችን ወደ ብስጭት የሚወስደኝ ይመስለኛል። ባለፈው ከእኔ ውስጥ ስለወጣው የኩላሊት ድንጋይ ነግሬሽ ይሆን? ድንጋዩ ሲወጣልኝ ዊንዲ ቤት ነበርኩ። የድንጋዩ መጠን 1/8 ኢንች ያክል ነበር። እወድሻለሁ!
ኒል
ሐምሌ 10, 2000
ኒል
ስለ ረዳት ሾፌርህ መታመም በጣም አዝናለሁ። ምናልባት ሌላ ሰው ብትፈልግ የተሻለ ይመስለኛል። ለማንኛውም በጥቂት ቀናት ውስጥ እዚህ ትደርሳለህ ብዬ ስለማስብ ብዙም አትጨነቅ። የነገርከኝ የኩላሊት ድንጋይ ጉዳይ ገና ዛሬ መስማቴ ነው። አዝናለሁ፤ አሁን ተሽሎሃል የሚል ተስፋ አለኝ። እንግዲህ ኢዮብን አስታውስ። ለሁሉ ችግሮች በኋላ ብዙ በረከቶች ነበሩት። የተሰጠው በረከት ቀደም ሲል ከነበረው ሁሉ በላይ እጅግ የሚልቅ ነበር። እናም ስለመገናኘታችን አታማርር። አሁን በቅርቡ እንገናኛለን። አብዝቼ እወድሃለሁ!
ቤኪ
ሰኔ 11, 2000
ኒል
ከጥቂት ቀናት በፊት ከኮቨናንንት የትራንስፖርት ማመላለሻ ድርጅት አሁን 2,0085.00 ዶላር ደርሶኛል። እናም እያንዳንዱን ሳንቲም በጥንቃቄ ነው ስራ ላይ የማውለው። ከዚህም ሌላ በኢትዮጵም ሆነ አሜርካ ያሉብን እዳዎች እንዴት መክፈል እንዳለብን እያሰብኩኝ ነው። በዓመቱ መጨረሻ የሚመለስልን ታክስ ጉዳይ ምን ደረሰ? ለዩኤስ ባንከ መከፈል የሚገባው ታክስ ተከፍሏል? እባክህ ስትነዳ ጥንቃቄ አድርግ። በሙሉ ጤንነትህ እኔ ዘንድ እንድትደርስ እፈልጋለሁ። በሚገርም ሁኔታ እየሰራህ እንዳለ ተረድቻለሁ። በጥሩ ሁኔታ ስራ እያገኘህ ነው። እዚህም የሚደንቁ ነገሮች ተከናውነዋል። ለምሳሌ ከ49 የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ውስጥ 46 ተማሪዎች ብሄራዊ ፈተና አልፈዋል። ይህም በእኛ ፕሮግራም ውስጥ ስላለፉ ነው። የሌሎችን ክፍል ውጤት እስከ አሁን አልተቀበልንም። ይህ ውጤት አስደናቂ ነው። እወድሃለሁ!
ቤኪ
ከሳምንት ወዲህ የላኳቸው ኢሜሎች ሞባይሌን ቻርግ ለማድረግ ኤሌክትሪክ ላይ አድርጌ እና ቻርጁ ከሞላ በኋላ ነው። እናም ይደርስሻል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ይህን ያልኩበት ምክንያት በዚህ ሳምንት ውስጥ ምንም መልስ ከአንቺ ስላላገኘሁ ነው።
ኒል
ሐምሌ 11, 2000
ኒል
የኢሜይል መልእክት ከእኔ ያላገኘህበት ምክንያት ከኢሜይል ፋንታ በስልክ ላናግርህ በመፈለግ ነበር። ለዚህም በዚህ ሳምንት በተደጋጋሚ ጊዜ ብሞክርልህም ስልክህ ዝግ መሆኑን ተገንዝቤያለሁ። ከአንተ ርቄ በመኖር በእርግጥ ተሰላችቻለሁ። ተገናኝተን እንደገና አብረን የምንሆንበት ቀን እግዚአብሔር እንዲያፋጥነው ፀሎት እያደረግሁ ነው። ይህ ተራርቀን የመኖራችን መንገድ ለምን እንደሆነ እግዚአብሄር ያውቃል። ነገር ግን ስንገናኝ ለሁለታችንም መልካም እንደሚሆንልን እተማመናለሁ። ለማንኛውም የስልኩ ነገር ይሳካልናል የሚል ተስፋ ይዤ ዛሬም እሞክርልሃለሁ። እወድሃለሁ!
ቤኪ
ሐምሌ 14, 2000
ቤኪ
2,085.00? ወይን 20,085.00? መለየት አቃተኝ።
ኒል
ሐምሌ 14, 2000
ኒል
አይደለም በየወሩ 2,085.00 ዶላር ይልኩልናል። ስለዚህ አሁን በጀትን በተመለከተ ወደ ነበርንበት ልንመለስ ነው። እግዚአብሔር የተባረከ ይሁንና ኮቨናንት የማመላለሻ ድርጅት እየረዳን ነው። እናም ኒል በአስቸኳይ ልትመጣ ይገባል። እዚህ ሆኜ ፈንድ ለማግኘት የተቻለኝ ሁሉ እያደረግሁ ነው። አምና ከባድ ጊዜ ነበር ያሳለፍነው። በዚያን ዓመት ጥቃቶች ከሁሉ አቅጣጫ ይሰነዘርብን ነበር። በጀት ተፈቅዶልን ልንቀበል በተቃረብንበት ጊዜ ሁሉ ት/ቤታችንን ልናጣ የተቃረብንበት ወቅቶች ነበሩ። በእውነት ዓምና ከባድ ዓመት ነበር። በተቃራኒው ደግሞ ዘንድሮ ያለምንም ጥርጥር የበረከት ዓመታች ይሆናል። የሚያስፈልገው ትንሽ መታገስ ብቻ ነው። ይህን የምልህ በተደጋጋሚ ከእኔ ስለሰማህ እንደምትሰላች አውቃለሁ። ለማንኛውም ትንሽ ታገስ። ምክንያቱም በረከታችን በእጃችን መግባት ሲጀምር ከምትገምተው በላይ እጅግ የገዘፈ በረከት ይሆናልና። ፕሮጀክታችን መስማት በተሳናቸው ወገኖች ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ላይ በጎ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር ብዙዎች ይናገራሉ። ይህ ደግሞ እንደሚሆን አልጠራጠርም። አንተን በተመለከተ ብቻህን ከምትነዳ አንድ ረዳት እንዲኖርህ እመኛለሁ። እንዲያው ሌላ ሰው ስለማግኘት ምን ታስባለህ? አይቻልም እንዴ? እዚህ የምንሰራውን ስራ በተመለከተ በጋዜጣ ላይ የተፃፈው ምን ተፅዕኖ ፈጠረ? ሰዎች ምን ዓይነት ግብረ መልስ ሰጡ? በጣም እወድሃለሁ!
ኒል
ጳጉሜ 1, 2000
ቤኪ
ዛሬ ከታክስ ተመላሽ ከተደረገልን ላይ 4,123.00 ዶላር እንዲሁም 600.00 ዶላር ከኢኮኖሚ ቼክ በጥቅሉ 4,723.00 ዶላር በቁጠባ ሂሳባችን አስገብቻለሁ።
ኒል
ሃይ ኒል
እንደምን አለህ? ዬት ነው ያለኸው? እወድሃለሁ!!!! በጥቅምት እዚህ እኛ ዘንድ እንድትደርስ ሁላችንም እንፈልጋለን። ለመምጣት አስበሃል? አንተ መምጣት ትችል ዘንድ ከታክስ የተመለሰልንን ገንዘብ አልነካም። ይህንን ገንዘብ መጠቀም የምችለው ምናልባት የሆነ ሰው ለአንተ መምጫ የሚሆን ገንዘብ ከላከልን ብቻ ይሆናል። በቁጠባ ሂሳባችን ውስጥ የማየው ከታክስ ተመላሽ የሆነውን ገንዘብ ብቻ ነው። ነገር ግን ቀሪው 600.00 ዶላር በሂሳባችን ውስጥ አይታይም። እስኪ እንደገና አረጋግጥ። ግን በትክክል አስገብተሃል? እወድሃለሁ!!!
ኒል
በዚህ ገንዘብ ምን ለመስራት አስበሃል? ወደዚህ ለመምጣት እንድትጠቀምበት እፈልጋለሁ። ያው መምጫህ በጥቅምት ይሆናል ብዬ አስባለሁ። ምናልባት ሌላ ገንዘብ ለዚህ ጉዳይ ካልተገኘ በስተቀር ይህንን ገንዘብ ለዚህ ጉዳይ ተጠቀም። እርግጠኛ ነኝ በሀሳቤ ትስማማለህ። እናም በዚህ ሀሳቤ ከተስማማህ ፓስፖርትህን መታደሱን አሁኑኑ ማረጋጋጥ አለብህ። ይህንንም ዊንዲ እንድትፈፅምልህ አድርግ። ትኬትህን እኔ ራሴ በኦንላይን ገዝቼ የበራራ ቀጠሮህን ልይዝልህ እችላለሁ። እናም እኔ አደርግልህ ዘንድ የምትፈልገውን በቶሎ አሳውቀኝ። እወድሃለሁ!!! እወድሃለሁ!!! እወድሃለሁ!!!
ቤኪ
መስከረም 5, 200ዐ
ቤኪ
ባለፈው ስራ በዝቶብኝ ነው የሰነበትኩት። እናም ሁለቴ እረፍት ካደረግሁ በኋላ ወደ ቻታኑጋ ነበር የሄድኩት። አንድ ረዳትም አግኝቻለሁ። አዲሱ ረዳቴ የማያጨስ፣ አማኝ የሆነ ነው። አስም አለበት። የሚኖረውም በአትላንታ ጆርጅያ ቻታኑጋ አቅራቢያ ነው። ከዚህ ከረዳቴ ጋር መጀመሪያ ከቻታኑጋ ወደ አትላንታ ከዚያም ካልፎርኒያ ውስጥ በሳክራሜንቶ ጭነታችንን ካራገፍን በኋላ ከዚያው ከፈረንሳይ ካምፕ ለዎልማርት ጭነት ይዘን አሁን ኒውዮርክ ወደሚገኘው ፔጂላንድ እያመራን ነው። ረዳቴ ህንድ አጠገብ ከምትገኘው ብሁታን ነው። ቤተሰቡ ሁሉም የሂንዱ ዕምነት ተከታዮች ናቸው። እርሱ ክርስቲያን ነው። ግማሽ ቤተሰቡም ክርስቲያኖች ሆነዋል። ሁል ጊዜ ስራ ከመጀመራችን በፊት ፀሎት እናደርጋለን። ከእርሱ ጋር ስሰራ ደስ እያለኝ ነው። ሁሉንም ነገር በንፅህና መያዝ ያስደስተዋል። ሁለቱን የእጅ ፎጣዎቼን ጭምር በጽዳት ሰበብ አስወግዷቸዋል። በቶሎ ወዳንቺ መምጣት እችል ዘንድ ገንዘብ መቆጠብ እንጀምር። ለበረራዬ እኛ ተዘጋጅተናል። ላለፉት 3 ወራት ከሙቀት የተነሳ ምቹ ጊዜ አላሳለፍኩም። ለነዚህ ሶስት ቀናት አየሩ ምቹና ትክክለኛ የሙቀት መጠን ነበረ:: ደስተኛ ነኝ። ትላንትና ሌሊት እስከ 10፡45 ድረስ ነበር ያሽከረከርኩት። የአየር ሙቀት ወደ 45 ድግሪ ቀንሷል። እስከ ታህሳስ አጋማሽ መስራት የመረጥኩት ሌላኛው ምክንያቴ ይህ የሙቀት መቀነስ ነው። በቶሎ ላይሽ እወዳለሁ። እወደሻለሁ!
ኒል
ጳጉሜ 4, 2000
ቤኪ
በጣም እወድሻለሁ። ወደ አንቺ ለመምጣትም በጣም እፈልጋለሁ።ከአንቺ ርቄ በመኖሬ ተሰላችቻለሁ። ከእዳ ያለመውጣታችን ጉዳይ የሞራልና ራስን የመውደድ ችግር እንዳለብኝ ይሰማኛል። እኔና አንቺ ወደን የመረጥነው መንገድ ነው እዳ ውስጥ የከተተን። ይህ ደግሞ ሌሎችን ለማኖር ስለሆነ ለእግዚአብሔር ክብር ነው። ይህን ነገር እግዚአብሔር ከእኛም የሚፈልገው ጉዳይ ነው። ይሁንና ለሁሉም ጊዜና ቦታ አለው። አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር የማንፈልገውን ነገር አስቀድመን እንድንፈፅፈመው ይጠይቀናል። ይህም ለራሱ ዓላማ ነው። ይህንን ጥያቄውን ቸል የምንል ከሆነ የራሳችንን በረከት ከማጣታችንም በላይ በታዘዝነው ስራ ምክንያት ሌሎች ማግኘት የሚገባቸውን በረከት እናስቀራለን። ለመሆኑ እንደ ወንድምሽ አጋርሽ ብቻ ነኝ ብያለሁ እንዴ? በሌላ ዓለም እየኖርኩ ልክ አንቺ ባለሽበት ዓለም እንደሆንኩ ያህል አስቤያለሁ እንዴ? እንደ ዶን ኮህቴ ንፋስን የማሳድድ በቅዠት ዓለም ውስጥ ነኝን? የኮቨናንት ትራንስፖርት ድርጅትስ ንፋስ እንደሚከተል ሆኖ የሚያሳድደኝ ይመስልሻል? አንቺና እኔ ኮቨናንት የትራንስፖት ድርጅት አሳምነን እንዲረዳን ያደረግነው ንፋስ የምንከተል ሆነን ነው? ምናልባት ስህተት ቢኖርም በቅንነት ተግቶና ደክሞ በመስራት መንግስተ ሰማያት የሚገኝ ከሆነ እኔ ማረጋጋጫ አለኝ። ከላይ የጠቃቀስኳቸው ሁሉ እውነት እንዳልሆኑ አውቃለሁ። ሁላችንም የቆምነው በአደጋ ውስጥ ነው። ለማንኛውም የምንገናኝበት ቀን ሩቅ እንዳልሆነ አውቃለሁ። ይህ የሚሆነው ግን ህዳር ወይም ታህሳስ ይመስለኛል። እስከዚያው መታገስ አለብን። ሀይል የሆነኝ እና በእኔ ውስጥ የሚሰራው የጌታ ደም፤ የፈሰሰልኝ ደም ነው። ይህም በደሙ ባለኝ እምነት ነው። ሌሎች ሀገሮች የሚከተሉ ቢሆንም እምነት ግን እኛነታችንን ከድርጊታችን ጋር የሚያገናኝ ነው። እወድሻለሁ!
ኒል
ጳጉሜ 5, 2000
ኒል
እባክህ ይህን ጉዳይ ንፋስ ከመከተል ጋር አታመሳስል። ወይም ደግሞ አንተ እኔን በመደገፍ ደረጃ ብቻ አትወስን። እግዚአብሔር ለዚህ ዓላማ ጠርቶናል። ይህ ጥሪ ደግሞ እኔና አንተ ከምናስበው እጅግ የላቀ ነው። በአሁኑ ወቅት እኔና አንተ ከአዲስ አባባ ወጣ ብለን 3 ሄክታር ያክል መሬት ባለቤት ልንሆን ነው። ይህ ቦታ 2 ሰዓት ያክል ከአዲስ አበባ ይርቃል። ይህ ጉዳይ ትክክለኛ አቅጣጫውን ሲይዝ ዝርዝር ሁኔታውን እነግርሃለሁ። የሆነ ሆኖ ዘንድሮ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከፍተን ለማስጀመር በከፍተኛ ፍጥነት እየሰራን ነው። አንድ ጠንካራ የሆነ ሰው ይዤ እየሰራሁ ስለሆነ በሚቀጥለው ሳምንት ይጠናቀቃል ብዬ አስባለሁ። በተረፈ እስከ ህዳር ወይም ታህሳስ እቆያለሁ ያልከኝ አላስደሰተኝም። ነገር ግን የሆነ ሰው በጥቅምት እንድትመጣ ሁኔታዎችን ይመቻችልህ ይሆናል ብዬ አስባለሁ። ይህ ማለቴ ለጉዞ የምሆንህን ገንዘብ ያመጣልሃል ብዬ አምናለሁ። የአሜሪካ ባንክ ካርድ ከፍያለሁ። እዚህ ስትደርስ እና ሁኔታዎችን ስትመለከት በእርግጥ ንፋስ የምትከተል አለመሆንህን በሚገባ ትረዳለህ። አር ኤች ቀደም ሲል አይቷል። አንተም አይተህ ታረጋግጣለህ። ምንም ቢሆን በሁሉም ነገሮች ውስጥ ሆኜ በጣም እወድሃለሁ።
ሃይ ኒል
እንዳው ሆነ ብለህ ወደዚህ የመምጫ ጊዜህን ታራዝማለህ? ይገባኛል የምትናገራቸውን ሁሉ እረዳለሁ ረዳት ሾፌርም በማግኘትህ በጣም ደስ ብሎኛል። ዛሬ በጣም ጠቃሚ የሆነ ቀን ነው። ይህ ቀን በሰዓታት ውስጥ የትምህርት ቢሮ ትምህርት ቤታችንን ገምግሞ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መጀመር እንችል እንደሆነ ወይም የማንችል እንደሆነ የሚያሳውቅበት ቀን ነው። ለዚህ ጉዳይ ለመዘጋጀት ብዙ ጥረቶችን ስናደርግ ቆይተናል። ይህንን ኢሜል ቀድሞ የደረሰ እንደሆነ እባክህ አብዝተህ ፀልይልን። ሁኔታዎች እንዴት እየቀጠሉ እንደሆነ አሳውቀሃለሁ። ከዚህም ሌላ ቫርሶን ክፍያችንን በተመለከተ ቀደም ሲል በምንከፍለው መጠን እንድንከፍል አሳውቆናል። እባክህ ቃላቸውን እንዲጠብቁ ደውለህ ንገራቸው። አብዝቼ እወድሃለሁ!
ቤኪ
መስከረም 21, 2001
ሃይ ኒል
የኋላ ኋላ የኢንተርኔት አገልግሎት እንደገና በመጀመሩ እኔም እሄው መልእክት ልልክልህ ችያለሁ። መልእክት ከእኔ ያልደረሰህ በዚሁ በኢሜይል መጥፋት ምክንያት ነው። በየቀኑ ኢሜይል መጠቀም የምችለው በጣም አጭር ጊዜ ነው። ለዚያውም ከቤቴ ርቀት ሄጄ ነው ኢንተርኔት ካፌ የማገኘው። ኢንተርኔቱም ቶሎ ቶሎ ይጠፋል እኔም ሀላፊነቴን ለመወጣት ቶሎ ብዬ ወደ ት/ቤት መመለስ አለብኝ። በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ የሰራነውን ስራ ብታይ በጣም ትኮራበታለህ። ካለንበት ግቢ ፊት ለፊት ካለው መንገድ ማዶ ሌላ ግቢ አግኝተናል። ይህም ተጨማሪ ክፍሎች እንዲኖረን አድርጓል። ክፍያውም ቢሆን በፊት ከምከፍለው እጥፍ ያክል ነው። ይህ የሆነበት ምክንያት ት/ቤቱን ለመክፈት የመንግስትን መስፈርት ማሟላት ስላለብን ነው። ለማንኛውም በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ነው። ለዚህ ጉዳይ ከክሬዲት ካርዳችን ገንዘብ መውሰድ ነበረብኝ። ይህንን የወሰድኩትን ገንዘብ በተቻለኝ መጠን ቶሎ ብዬ እመልሳለሁ። ቻርሊ እዚህ ነው ያለው። የምንሰራቸውን ሁሉ እየታዘበ ነው። በሚያያቸው ነገሮች ሁሉ መገረም አለበት! በዚህን ጊዜ ለምን እዚህ ሊመጣ እንደቻለ እኔ አላውቅም። ምናልባት ለዓላማ ይሆናል። እንደ እርሱ ሁሉ ደግሞ አንተ ለምን እዚህ እንዳልተገኘህ አላውቅም። ሲመለስ መልካም የሆኑ ፎቶዎችንና ዘገባዎችን ይዞ ይመጣል ብዬ አስባለሁ። ይህንን ዘገባ ስታገኝ እንደምትባረክ አምናለሁ። ከዚህም ሌላ ከአንተ የሚመጣው ገንዘብ ምን ሰራ? ለሚለው ትክክለኛ ግንዛቤ ታገኛለህ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። የአንተን ፎቶ ለመጀመሪያ ጊዜ ከጆይና ቶሚ ጋር ያሳተምኩት ዛሬ ነው። በጣም ኮርቼብሃለሁ፤ ኒል። አንተ ምን ጊዜም ፍቅሬ ነህ። ራስህን ጠብቅ እናም ቶሎም ፃፍልኝ።
ቤኪ
ጥቅምት 3, 2001
ቤኪ
ቻርሊ ዛሬ ደውሎልኛል። ምናልባት የሚሰራ ከሆነ ኢሜይልም ጽፌያለሁ። ከአንቺ የኢሜይል መልዕክት ይደርሰኛል ብዬ እጠብቅ ነበር። ነገር ግን በነዚህ ቅርብ ቀናት ምንም መልእክት ከአንቺ አላገኘሁም። ከዚህም ሌላ ቁጥሩ 6038 የሆነው ስልካችን አሁን ተዘግቷል። በአሁኑ ጊዜ የስልክ መስመሮች ልውውጥ አለ። በዚህ ሽግግር ውስጥ ምናልባት የ6034 ስልክ የኢንተርኔት አገልግሎቱ ሊቋረጥ ይችላል። ይህንንም ተከታትዬ እንደሚሰራ ወይም እንደማይሰራ አጣራለሁ። ባለፉት ሁለት ሳምንታት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ነበር ስንሰራ የነበረው። ስለዚህም ከ1,000.00 ዶላር በላይ ቼክ እናገኛለን ብለን እንጠብቃለን። ባለፈው ሁለት ሳምንታት ከባድ ስራ ምክንያት በጣም ድካም ተሰምቶኛል። ስለሆነም ለ6ቀናት እረፍት ጠይቄያለሁ። እረፍት በጣም ያስፈልገኛል። ወዲያውም የምስጋና በዓልን ለማክበር አቅጃለሁ። እወድሻለሁ!
ኒል
ጥቅምት 4, 2001
ኒል
የአንተን ኢሜል አግኝቻለሁ ለማለት በመቻሌ እጅግ ደስ ብሎኛል። ከቻርሊ መልዕክት በማግኘትህም በጣም ደስ ብሎኛል። ስልክህ ባለመስራቱ ምክንያት እስከ ዛሬ ድረስ ኢሜይል ልጽፍልህ አልቻልኩም ነበር። በሌላ መልኩ በቀኝ እጄ ላይ ከባድ የመቁሰል አደጋ ስለደረሰብኝ በከባድ ችግር ላይ ነበርኩ። ነገር ግን ከመቁሰል ውጭ የመሰንጠቅ አደጋ ስላልደረሰብኝ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ። በዚህም ምክንያት እንደ ወትሮዬ ወደ ኢንተርኔት ካፌ በመሄድ ኢሜል ለመላክ አላስቻለኝም ነበር። አሁን ግን ጤንነቴ ተመልሶ ወደ መደበኛ ስራዬ ተመልሻለሁ። እዚህ በሰራተኞቻችን ዘንድ ምን እየተከናወነና ያላቸውን የስራ ተነሳሽነት በተመለከተ ቻርሊ ሁሉን እንደሚነግርህ ተስፋ አለኝ። እግዚአብሔር በስራ ላይ ነው። የአሰራሩ ሁኔታም እጅግ ድንቅ ነው። እዚህ እየተካሄደ ባለውን ነገር ላይ ቻርሊ እጅግ ይደነቃል። የሁኔታዎች በአስደናቂ ሁኔታ መለወጥ በመረዳትና ለሌሎች በማካፈል ረገድ እጅግ ግር እንደሚለው ይናገራል። ስለሆነም በዚህ ጉዳይ ላይ በተለያዩ ጊዜያት አብረን እንፀልይ ነበር። በአጠቃላይ የእግዚአብሔርን ነገር ወደ ፊት ለማስኬድ ጠላታችን የሆነውን ሰይጣን ከእግራችን በታችን እየቀጠቀጥን በሁሉ ነገሮቻችን ላይ ጌታን እያነገስን እንጓዛለን። ይህም ማለት ዛሬ ወይም ነገ ከፍተኛ ሁለተኛ ት/ቤታችንን እንጀምራለን። ለማንኛውም ቻርሊ በሚያካፍልህ ነገሮች ሁሉ እንደምትባረክ አምናለሁ። ምንም እንኳ ከቻርሊ ጋር እዚህ መምጣት ባትችልም እዚህ ስለሆነው ነገር ጥሩ መረጃ ታገኛለህ። ይህም እንደሚያበረታታህ ተስፋ አደርጋለሁ። አንተ በእኔና እዚህ ባሉት ሰራተኞች ዘንድ ታላቅ ከበሬታ እንዳለህ ልነግርህ እፈልጋለሁ። ከልክ በላይ እግዚአብሔር ይባርክህ እና በእጅጉ እወድሃለሁ!
ቤኪ
ጥቅምት 8, 2001
ኒል
አሁን መስማት ለተሳናቸው ወገኖች ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ለመክፈት ህጋዊ ሰውነት አለን። ይህም ለማመን በጣም የሚከብድ ነው። እግዚአብሔር የማይንቀሳቀስ የሚመስለውን ነገር ተራ በተራ እያንቀሳቀሰ ነው። በዚህ ሰዓት ይህን የእግዚአብሔርን ስራ ማንም ሊያቆም አልቻለም፤ ጠላት ሊያቆም አልቻለም። ፍፁም የሆነ የእግዚአብሔር ተዓምር በዚህ ስፍራ ተከናወነ ከቻርሊ ጋር ሁሉንም እንደምትነጋገር ተስፋ አደርጋለሁ። እርሱ ለአንተ የሚያካፍልህ ብዙ መረጃዎች አሉት። እኔ በኢሜይል ከምነግርህም በላይ መረጃ አለው። እርሱ የሚነግርህ በዓይኑ የተመለከተውና በተግባር የተመለከተውን ነው። አሁን ተራርቀን የምንኖርበት ጊዜ እያበቃ ነው። አብረን የምንኖርበትን ትክክለኛ ጊዜ ከላይ ከእግዚአብሄር በትግስት መጠበቅ ነው:: እግዚአብሄር ሁሉንም የሚሰራበት ጊዜ አለው። ከኮቨናንት የትራንስፖርት ድርጅት ዴኒስ በጣም ጠቃሚያችን ነች። የመረጃ መረባችንን ወቅታዊ በማድረግና ከቻርሊ በምታገኛው መረጃ ላይ በመመርኮዝ በድርጅቱ ውስጥ ላሉት ሁሉ ሪፖርት ለማድረግ ፍላጎት አላት። በቅርቡ ሁለት የቴሌቪዥን በቡኖች ወደ እኛ መጥተው ነበር። የመጡት ጋዜጠኞች ስራንና መስማት የተሳናቸውን ወገኖችን ትምህርትና ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ ጠለቅ ያለ ቃለ መጠየቅ አድርገዋል። ይህም የመስማት የተሳናቸውን ትምህርት በተመለከተ የተደረገው ቃለ መጠይቅ የኢትየጵያ ሁኔታን መሰረት ያደረገ ነው። በዚህን ሰዓት እዚህ ሆነህ የድካምህን ፍሬ ቢታይ እጅግ እደሰት ነበር!!!!!! እባክህ ቶሎ መልስ ጻፍልኝና ራስህንም ጠብቅ እወድሃለሁ!
ቤኪ
ጥቅምት 10, 2001
ቤኪ
በዚህ ሳምንት ስራው ቀዝቃዛ ነው። በፍሎሪዳ እንኳ ለሁለት ቀን ነው ያለ ስራ የተቀመጥኩት። ረዳቴም ከጥቂት ወራት በፊት በቀኝ እጁ ላይ በደረሰበት ጉዳት የተነሳ ወደ ቻታኑጋ መሄድ ነበረበት። ምክንያቱም ጉዳቱ ምንም ያልተሻለው ስለሆነ እዚያ ሄዶ ማመልከትና መፍትሄ ማግኘት ስለነበረበት ወደዚያ ሄድን። እዚያ ከደረስን በኋላ የመኪናችን ሞተር የሚያሮጠው ኮምፒውተር ተበላሽቶ ኖሮ መለወጥ ስለነበረበት እዚያም ለሁለት ቀናት ተቀመጥን። ዶ/ር ሎራ እንዳለችው ትክክለኛውን ነገር በትክክለኛው ሰዓት ማድረግ እንዳለብን አውቃለሁ። ነገር ግን ይህን ማድረግ እንዲሁ ቀላል አይደለም። እንደምታውቂው እስራኤላዊያን ከግብጽ ለመውጣት ወዲያው በተነገሩበት ሰዓት ዝግጁ ሊሆኑ አልቻሉም ነበር። ሩትም ቦዓዝን ለማግባት ወዲያው ራስዋን አላዘጋጀችም። አንቺም ብትሆኝ ወደ አዲስ አበባ ሄደሽ መስማት ለተሳናቸው ት/ቤት ለመክፈት በአንዳፍታ አልወሰንሽም። ወደዚህ ውሳኔ የደረስሽው እያደር ከምታደርጊያቸው ትናንሽ ውሳኔዎች በኋላ ነው። እነዚያ ለዓመታት ያልጎበኘሻቸው በኋላም የህይወታቸውን አቅጣጫ የሚለውጥና በኑሯቸው ላይ እሴት ሊጨምር የሚችል፤ እነርሱም ቢሆኑ በፍጹም የማያስቡትን ስራ ለመስራት የወሰንሽው። እናም ባለቤትሽ በመሆኔ ክብር ይሰማኛል። እኔ ከእግዚአብሔር ፍቅር ተካፋይ የሆንኩ ሰው ነኝ። ለወደፊት ሽልማቴ ተስፋ የሆነኝና ያንን ከእግዚአብሔር የምቀበለውን ሽልማት በሩቅ እንድመለከት ያደረገኝም ይኸው ነው። ሙሴ የተስፋይቱን ምድር በሩቁ እንደተመለከተ ሁሉ እኔም ሽልማቴን አሻግሬ ስመለከተው እጅግ የገዘፈ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።
ይህንን ሽልማት በቃላት ለመግለጽ ቀላል ቢመስልም ከባድና ውስብስብ ነው። በዚህ መስማት የተሳናቸውን በማስተማርና በመርዳት በጎ ስራ ላይ ኮቨናንት የትራንስፖርት ድርጅት አጋራችን በመሆኑ እጅግ ተባርከናል። ሌሎችን የሚባርኩ ይባረካሉ እንደሚል ቃሉ በድርጅቱ ስራ ውስጥ በየዕለቱ በማደርጋቸውን እንቅስቃሴ በጣም ደስተኛ ነኝ። ዛሬ ጠዋት በዘፀዓት ውስጥ ያለውን ታሪክ እያነበብኩ ነበር። በዚህ ታሪክ ውስጥ ትኩረቴን የሳበው እስራኤላውያን ወደ ተስፋይቱ ምድር ሲጓዙ ምን ያህል ጊዜ በመንገዳቸው ላይ እየሰፈሩ እንደተጓዙ ነበር። 42 ያህል ጊዜያት ድንኳናቸውን በመንገዳቸው ላይ ጥለዋል። ራዕይ 11፡2 እና 13፡5 ላይ ሁለቱም ቦታ ዲያብሎስ ለ42 ወራት ሀይል እንደሚሰጠው ይናገራል። ይህ ምናልባት የእስራኤል ልጆች ወደ ተስፋይቱ ምድር ሳይደርሱ በፊት ዲያብሎስ በላያቸው እንደሚሰለጥን ቀጥተኛ የሆነ አመለካች ይሆን? የሆነ ወደ ተፈለገ ዓላማ ለመድረስም በተከታታይ ሂደቶች ውስጥ ያለውንም የጊዜ ወሰኖችንም የሚያመለክት ይመስለኛል። ይህ እንግዲህ የእኔው ሃሳብ ነው። አሁን በዚሁ ላቁምና ወደ ዘኍልቁ 33 በመሄድ እንደገና እስራኤላዊያን ወደ ተስፋይቱ ምድር በሚያደርጉት ጉዞ ላይ ምን ያክል በመንገዳቸው ላይ እንደሰፈሩ የሚያሳየውን ክፍል ማንበቤን ልቀጥል። እወድሻለሁ
ኒል
ጥቅምት 11, 2001
ሃይ ኒል እንደምን አለህ
እኔ በቀኝ እጄ ላይ ጉዳት እንደደረሰብኝ አልሰማህም እንዴ? እጄ የተጎዳው በመውደቄ ነበር። አወዳደቄ ከባድ ጉዳት የሚያደርስ ነበር፤ ሰው እስኪረዳኝ ድረስ መነሳት አልቻልኩም ነበር። ከዚያም ሰው ደርሶልኝ ከወደኩበት ካነሱኝ በኋላ ወደ ሆስፒታል አደረሱኝ። ያዩኝ ዶክተርም የራጂ ምርመራ እንዳደርግ አዘዙልኝ። በራጂ የምርመራ ውጤት መሰረት እጄ መሰበሩን ከነገሩኝ በኋላ የቀዶ ጥገና ህክምና እንደማያስፈልገኝ አስረዱኝ። የጉዳት መጠኑ እጄን አያዘራጋኝም ነበር። በዚህ ሁኔታ አንድ ሳምንት አለፈ። ቀጥሎም አንድ የእኛ ጥበቃ አንድ የስፖርተኞች ወጌሻ እንዲያየኝ መከረኝ። ወጌሻውም እርዳታ ከማድረጉ በፊት የራጂ ውጤቱን እንዳሳየው ጠየቀኝ። ወዲያውም የተመረመርኩበት የራጅ ውጤት ሳሳየው እጄ አለመሰበሩን ከነገረኝ በኋላ የተጎደውን እጄን በማሸት እገዛ አደረግልኝ። በዚህ ዓይነት ለአንድ ሳምንት ያህል የማሸት አገልግሎት ካደረግልኝ በኋላ እጄን ማንቀሳቀስ ቻልኩ። በተጨማሪም ወደ ፍል ውሃ እየሄድኩኝ እዚያም እንዲያሹኝ አድርጌያለሁ፤ ዛሬም ወደዚያው ለመሄድ እየተነሳሁኝ ነው። እናም በነዚህ ሂዳቶች ውስጥ እየተሻለኝ መጥቷል። የህመም ስሜት የሚሰማኝ በተለይም የምልክት ቋንቋ አብዝቼ በማደርግበት ጊዜ ነው። በአሁኑ ጊዜ መስማት ለተሳናቸው ወገኖች በሁለተኛ ደረጃ ትምህረት 9ኛ ክፍልና እና 10 ክፍል ማስተማር የሚያስችለንን ፈቃድ አግኝተናል። ነገር ግን በዚህን ሰዓት የገጠመን ሌላ ፈተና ደግሞ በፕሮግራማችን ተጠቃሚ የሚሆኑት ተማሪዎች ወደ እኛ ለመምጣት ፈቃደኞች ሊሆኑ አልቻሉም። ፈቃድ እንዳናገኝ ይገዳደሩን የነበሩት ጠላቶቻችን አሁን እነዚህ ተማሪዎች ወደ እኛ እንደይመጡ ጫና እያደረጉባቸው ነው። ለማንኛውም እግዚአብሔርን በመተማመን ለ9ኛ እና 10 ክፍሎች የማስጠናቱን ፕሮግራም አቁመን በየቦታው እየዞርን 9ኛ እና 10 ክፍል ውስጥ ሊማሩ የምችሉትን በማፈላለግ ላይ ነን። ነገሮች በምን ፍጥነትና ሁኔታ እየተቀያየሩ እንሆነ ስመለከት እጅግ ያስደንቀኛል። አንዱ አለፈ ሲባል ሌለው ይተካል።
አንዱን የጠላት ፈተና ስንሻገረው መልኩን ቀይሮ ሌላ ይተካል። ነገር ግን ምንም እንኳን ጠላቶቻችን ሊያፈርሱን ዘዴያቸውን እየቀያየሩ ጥቃታቸውን ቢያፈራርቁብንም ተማሪዎቻችን በእውቀት ዳብረው ህይወታቸውን በሚቀይር ሁኔታ ተምረው ጠላቶቻችን ሲያሳፍሩ ይታየኛል። በ1970ዎቹ ውስጥም ተመሳሳይ ሁኔታ ገጥሞን ነበር። የዚያን ጊዜ ሁኔታ ከዚህኛው ልዩ የሚያደርገው ግን በዚያን ጊዜ ተነስተውብን የነበሩት መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች ራሳቸው ነበር። እኛ በዚህ ስናጎርሳቸው እነርሱ ደግሞ ያንኑ ያገረሳቸውን እጆቻችንን ይነክሱን ነበር። ይህ ክስተት ሌላም የሚያስተውሰኝ የእስራኤላዊያንን ሁኔታ ነበር። እስራኤላዊያን ከግብጽ ምድር ወደ ተስፋይቱ ምድር እግዚአብሔር ሲመራቸው እነርሱ ግን ያለማቋረጥ በእርሱ ላይ በአመጽ ይነሳሱ ነበር:: በዚህም ምክንየት ለ40 በበረሃ ውስጥ ይመላለሱ ነበር። እዚህ ያሉት መስማት የተሳናቸውም ተመሳሳይ ናቸው። ብዙ እንዲያገኙ ሁኔታዎች ተመቻችቶላቸው ሳለ እርሱ ግን በቀረበላቸው በረከት ላይ በአመጽ ይነሳሳሉ። በጣም ያሳዝናል። እዚህ ከመጣሁ ጊዜ ጀምሮ ያሳለፍናቸው ውጣ ውረዶችና የጠላት ውጊያዎች መንፈሳዊ ህይወቴ ከምንጊዜውም በላይ እንዲጠነክር አድርጎታል። መንፈሳዊ እድገቴ እስኪታወቀኝ ድርስ ነው ከፍ ያለው። አዎ እግዚአብሔር በእያንዳንዳችን ህይወታችን ውስጥ እጁን የሚያስገበው በተለየ ሁኔታ ነው። በመንግስቱ ውስጥ እያንዳንዳችን የየድርሻችን ስንወጣ በዚህ ዓለም ሳይሆን በመንግስቱ ይሸልመናል። እኔም እንዳንተው ሽልማቴን የማያው በዚህ ዓለም ካለው ሽልማት ባሻገር ነው። እውነት ነው በዚህ ዓለም መልካም ውጊያ ካልሆነ በስተቀር ልታቀርብልን የምትችለው ነገር የለም። እናም ዋናው ነገር መልካሙን ውጊያ ታግሎ ማሸነፍና ለሚበልጠው ሽልማት መዘጋጀት ነው። በዚህ ዓለም የምናደርገው ውጊያ ለሌሎች ነፍሳት ጥቅም ሲባል ብቻ ነው። ይህም ጥቅም የእግዚአብሔርን ማንነት በሚገባ ሲያውቁ ነው። እወድሃለሁ ኒል:: እግዚአብሄር በቶሎ ወደ እኔ እንድትመጣ ይርዳህ
ቤኪ
ጥቅምት 18, 2001
ቤኪ
ትላንተና ቻርሊን አነጋግሬ ነበር። የታክስ ማሳያ 990 ሞድል እንደሚፈልግ ነግሮኛል። ይህንን የታክስ ነገር ደግሞ ለማንኛውም ጊዜ አዘጋጅተን መያዝ አለብን። ምናልባት የሆነ ሰው ስለዚህ ጉዳይ ለሚመለከተው አካል ቅሬታ የሚያቀርብና በተጠየቅንበት ሰዓት የማናሳይ ከሆነ ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደምንገባ ነግሮኛል። ለማንኛውም ከኮቨናንት የትራንስፖርት ድርጅት ጋር በምናደርገው የገንዘብ እንቅስቃሴ መያዝ የሚገባንን ሰነዶች በስርዓቱ ያልያዝን ከሆነ መልካም እድሎችን የምናጣ ይመስለኛል። ቻርሊ በጥቂት ቀናት ውስጥ ስለ እኛ ት/ቤት የሚያውቀውን ሁሉ በቻታኑጋ ለድርጅቱ ሰራተኞች ሁሉ ሪፖርት እንደሚያደርግ ይጠበቃል። እንደምገምተው ከሆነ ይህ ሪፖርት ለሾፌሮችም ሁሉ ክፍት የሚሆን ይመስለኛል:: በመረጃ መረብ የምትረዳሽ ዴኒስ የምትባለው ሴት ስለዚህ ጉዳይ ነግራኛለች። እኔ ግን ካለብን እዳዎች ነፃ እስክንሆን ድረስ ምንም እረፍት የለኝም። አንቺ የነገርሽኝ የተማሪዎች ጉዳይ የሚገርም ነው። እንዲህ እየተደረገላቸው ያለውን ነገር እንኳን ማድነቅ ነበረባቸው። ሁኔታቸው ልክ ለአሜሪካን ምርጫ እንደሚሮጥ ፖለቲከኛ ነው የሚመስለው። ይህ ሁኔታቸው በፊታቸው በረከት ተቀምጦ እንደሆነ የሚረዱ አይመስልም። ስለዚህ ትእግስቴ እጅግ የሳሳ ነው።
አንቺም ሁኔታዎችን በዚሁ መነጽር መመልከት አለብሽ። በዚህ ወር ከ25 እስከ 30 ድረስ ዊንዲ ቤት ነው የምቆየው። እንደውም በእነዚህ ጊዜያት ከእኔ ጋር ብትሆኝ እመኝ ነበር። በአጠቃላይ መረጃን በተመለከተ በጥንቃቄ መያዝ አለብሽ። በተቻለሽ መጠን ድርጅቱንና ቻርሊን በሚያሳምንና በሚያስደስት መልኩ መያዝና ማቅረብ አለብሽ። እያደረጉልን ያሉት ነገር የተለየ ችሮታ ነው። ይህ ከእግዚአብሔር የሆነ በረከት ነው:: በእነዚህ ቅርብ ቀናት በተለይም እስከ ጥቅምት 8 ድረስ ስራዬ በዝግታ ይሆናል። ከዚያም ረዳቴ ይመለሳል። ቀጥሎም ለአንድ ሳምንት ያለማቋረጥ ከሰራን በኋላ ለምስጋና በዓል እረፍት እወጣለሁ። ትላንትና ከቀደመው ረዳቴ የስልክ ጥሪ ተቀብዬ ነበር። እርሱ እንደሚለው ከሆነ እንደገና ከእኔ ጋር ለመስራት ይፈልጋል። በአሁኑ ሰዓት አትላንታ ውስጥ በሰዓት 30 ዶላር እየተከፈለው ይሰራል። ነገር ግን እንደዚያ አይነት ስራ ከመልቀቁ በፊት ደጋግሞ እንዲያስብ መክሬዋለሁ። ምክንያቱም በየቀኑ ቤቱ እያደረ ነው የሚሰራው። ከዚህም ሌላ የትረፍ ጊዜ ክፍያ አለው። በአየር ንብረት ችግር ምክንያት ስራ መስራት እንኳን ባይችል ክፍያው አይቋረጥበትም። አሁን ያለሁት በኦሃዮ ያንግስታዎን ከተማ ውስጥ ነው። እና የ34 ሰዓት ስራ ለመጀመር ሙከራ እያደረግሁ ነው። ወደዚህ ለመድረስ 8.75 ሰዓት ይቀረኛል። እወድሻለሁ
ኒል
ጥቅምት 19, 2001
ኒል
ስለ ፃፍክልኝ በጣም ደስ ብሎኛል። ፎርም 990ን በተመለከተ ለጠበቃችን ነግሬዋለሁ። እርሱ ያዘጋጅልናል። ቻርሊ በጣም የሚረዳንና ቀና ሰው ስለሆነ በቦርዳችን ላይ ቢገኝ መልካም ነው። ስለዚህ እርሱ ቻታኑጋ ሲመጣ በቦርድ ስብሰባ ላይ ጋብዙት። ኡግኔ እንዴት ነው? ለመሆኑ አነጋግረኸው ታውቃለህ? የቀድሞ መስማት የተሳናቸው መምህራኖቻችን ከሰውኝ ለ6ቀናት ሊያሳስሩኝ ነበር። ይህንን ለማድረግም በተወሰነ ደረጃ ዳኛውን አሳምነው ነበር። ስለሆነም ፖሊስ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ወስዶኝ ነበር። እንዳጋጣሚ ሆኖ ግን ህግ አማካሪያችን አብሮን ስለ ነበረ ትክክለኛ ታሪክ አስረድቶልኝ ከመታሰር ድኛለሁ። ያበሳጨኝ እነዚያ መስማት የተሳናቸው የቀድሞ ሰራተኞቻችንን ለመጉዳት እስከማሰብ ድረስ እኔ መጥላታቸው ነው። ሀሳባቸው በብዙ ሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ ለማግኘትና እኔን ከሀገር ውስጥ ለማባረር ነበር። ለማንኛውም በክርክሩ ተሸናፊ ሆነዋል። ይሁንና በሰዓቱ ተግዳሮቱ እጅግ አስጨናቂ ነበር። ሁል ጊዜ ከእኔ ጋር ያለው አምላኬ በዚያ ሁኔታ ውስጥም ይረዳኝ ስለነበረ አስቸጋሪውን ሁኔታ አሻግሮኛል። እንድታስታውስ የምፈልገው ውጊያችን ከደምና ከስጋ ጋር ሳይሆን በጭለማው ዓለም ውስጥ ካለው ስልጣናትና ሀይላት ጋር መሆኑን ነው። ስለዚህ ትግዕስትህ ሳስቶ በቅርብ ርቀት ላይ ያለውን መዳረሻችንን ማየት ካልቻልክ እግዚአብሔር ለዚህ ተልዕኮ እንዴት እየተጠቀመብህ እንደሆነ መገንዘብ ችግር ይሆናል። ሽልማታችን በዚህ እንደ ትንፋሽ ሽው ብሎ በሚያልፋው በዚህ ዓለም አይደለም። ነገር ግን ዘለዓለማዊ በሆነውና በማያልፈው ዓለም ነው። ይህንን ሽልማት በትዕግስት መጠባበቅ አለብን። ስራችን መስማት ስለተሳናቸው ወገኖች ብቻ አይደለም። ነገር ግን በሙስና የተጨማለቀውን መንግስት ደካማ ጎኑን ማሳየት ጭምር እንጂ።
እናም ከምናሳድርበት ጫና ተነሳ ምናልበት በእኛ ላይ ያለውን የተሳሳተ ፖሊሲ ይቀይራል የሚል እምነት አለኝ። ስራችን የሚመራው በእግዚአብሔር በመሆኑ በመንግስት ቢሮዎች ውስጥ ያሉ አንዳንድ ቁልፍ ቦታ ላይ ያሉ ሰዎች በምንሰራው ስራ ላይ መልካም ግምት መያዝ ጀምረዋል። የምንሰራው የእግዚአብሔር ስራ እና የሚከናወነውም በእርሱ መንገድ ስለሆነ የሰዎችን ቀልብ ቢስብ የሚደንቅ አይሆንም። ከሳምንት በፊት የእኛ ስራ በቴሌቪዥን መተላለፉን ነግሬህ ይሆን? በሀገሪቷ ቴሌቪዥን ጣቢያ በሁለት ክፍለ ጊዜ እያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ 40 ደቂቃ የሸፈነ ፕሮግረም ተላልፏል። ወደ ት/ቤታችን መጥተው ፕሮግራሙን የሰሩት ጋዜጠኞች የመስማት የተሳናቸውን ወገኖች ጉዳይ ለህዝብ ይፋ በማድረግ ረገድ የተቻላቸውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል። እግዚአብሔር እነዚህን ሰዎች በእኛ ስራ በኩል ተጠቅሞ ስራውን በመስራት ላይ እንደሆነ አምናለሁ። ይህንን ማመን ያዳግታል። ከመጋባታችን በፊት እግዚአብሔር እኛን የማጣመሩ ጉዳይ እንቆቅልሽ እንደሆነብህና ታላላቅ ነገሮችንም በእኛ በኩል እንደሚሰራ እምነትህ እንደሆነ ነግረኸኝ ነበር። ይህን ነገር ታስታውሳለህ? ምንም እንኳ መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች የተሰጣቸውን በረከት መረዳት ባይችሉም እየሰራን ያለነው ስራ ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ መተንተን ይከብደኛል። በዚህ በመጨረሻው ዘመን ከችሎታችን በላይ በሆነ ደረጃ በሌሎች ግለሰቦችና ዜጎች ህይወት ውስጥ እየሰራን ነው። ይህም የእግዚአብሔር ታላቅ እጅ ነው በእኛ በኩል የሰዎችን ህይወት እየዳሰሰ ያለው። ስለሆነም ሁለታችንም በአስፈላጊ ጉዞ ላይ ከመሆናችን ውጭ በሌላ መልኩ በፍጹም እንዳታስብ እለምንሃለሁ። ይህም እጅግ ጠቃሚ የሆነ መንፈሳዊ ጉዞ በችሎታችን ልንሰራበት ከማንችልበት ስፍራ የሆነና ለእግዚአብሔር ዓላማ ብቻ የሚከወን ነው። ይህንን መንፈሳዊ ስራ በስጋዊ ችሎታችን የምንሞክረው አይደለም።
በአሜሪካ ውስጥ በበጎ መልኩ የሰዎችን ህይወት እየነካን ነው፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነውና። ጫናም እያሳደርን ነው። በኢትዮጵያ ውስጥም በሚገርም ሁኔታ የሰዎችን ህይወት እየነካን ነው። እናም ኒል እባከህ ከእንግዲህ በኋላ ከመንፈሳዊ እይታ ውጭ ነገሮችን እንዳታስብ እለምንሃለሁ። ምክንያቱም ዓላማችን ከምናስበው ፍጥነት በላይ እየተለወጠች፣ ለእግዚአብሔር መስራት የሚገባን ጊዜም እያጠረ ነው። ከዚህ አንፃር ገንዘባችንም ምንም ነው። ምናልባት ለእግዚአብሔር ጉዳይ እየዋለ ይሆናል። የቀረንም ጊዜ ምናልባት በሙሉ ሀይላችንና ትኩረታችን ለተጠራንበት ለራሱ ስራ ማዋል ብቻ ነው። ከዚያም በዘለዓለማዊ መንግስቱ ውስጥ መልካም ሰርታችኋል! የሚለውን የእርሱን ድምጽ ለመስማት መዘጋጀት ነው። ኒል በጋራ እንድንሆን አብዝቼ እፈልጋለሁ። እባክህ ይህ ይሳካልን ዘንድ ዓይንህን በእግዚአብሄር ላይ አድርግ። የምንጠይቀውን ጉዳይ ለመፈጸም እግዚአብሄር የተለየ እቅድ አለው። ስለዚህ ትዕግስትህ ሊሳሳና ሊፈተን አይገባም፤ አንተም ይህንን አትፍቀድ። ምክንያቱም እርሱ ብቻ ነው የፈቀደውን ስራ በፈቀደበት ሰዓትና ቦታ የሚያከናውነው። ሊባርከን የሚችለውም የእርሱን ስራ በፈቃዱ መሰረት ስናከናውን ብቻ ነው። ለእርሱ ስንሰራ ደግሞ ስጋዊ እቅዳችንና ዓላማችንን መካድ አለብን። ዓላማችንና መንገዳችን ከእርሱ ፍፁም ሊገጥም አይችልም። በአጠቃላይ በዚህን ሰዓት እጅግ ታስፈልገኛለህና ተስፋ አትቁረጥ፤ ጠንክር። ከልቤ እወድሃለሁ!
ቤኪ
ምን ማለት እንዳለብኝ አላውቅም። ሁሉ ጊዜ የባሰውን አታምጣ እላለሁ። ስለተሰጠን ፈቃድ ብዙም አያስጨንቀኝም። ነገር ግን አሁን ክፍያ እየፈጸምሽበት ያለሽው ሁለት ግቢ ነው። ጭንቅላቴን! ወገቤን! የሚያስብል ነገር ነው። እንዲያው አንቺና እኔ ለሌሎች የምንሰጠው ደስታ በአንድ ጭብጥ የሚገለጽ ነው። አንዳንዱማ የስራ እድል ከማስገኘት የሚዘል አይደለም። ይህ የሚያስፈልገን አይደለም። ለእኛ እንዲሰሩልን የምንፈልገው ለሌሎች መልካም የሚፈልጉ እንጂ ለራሳቸው ብቻ የቆሙ መሆን የለባቸውም። ምናልባት እግዚአብሄር የሆነ መልካም ሰው ሊያገናኝሽ አቅዶ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ወደዚያ ሰው ሊያመራሽ ይሆናል። ኢትዮጵዊያን ለምንሰራላቸው በጎ ነገር ምላሻቸው ይህ ከሆነ እዚያ ያለንን ተግባራችንን የምናቆምበት ወቅቱ አሁን መሆን አለበት። ውድ የሆነን ነገር ለአሳማ ማቅረብ ስህተት ነው። አያያዛቸው እንደነገርሽኝ ከሆነ በኢትዮጵያዊያን መስማት ከተሳናቸው ፈንታ ለሌሎች ማድረግ ያለብን ብዙ ነገር አለ። አየሰለቸኝ ነው። ለመሆኑ በከፍተኛ ድካም የማገኘውን ገንዘብ የምልከው ለራሴ የረባ ቁርስ እንኳን ሳልበላ እንደሆነ ያውቃሉ? ለዚያውም የበቆሎ ገንፎ ከህፃናት ምግብ ጋር እየቀላቀልኩ ነው ቁርሴን የምበለው።
ለመሆኑ መቀየሪያ እንኳ የሚሆነኝ ጫማ አንደ ሌለኝ ያውቃሉ? ለጡረታ በሚሆነን ገንዘባችን ስጋ እንደምናበላቸውስ ያውቃሉ? በድካም የተገኘውን ገንዘብ የምልከው ጥቂቱ በትክክለኛ ቦታ፤ የሚበልጠውን ግን በሚቀልዱብኝ ሰዎች ጉዳይ የማባክን ይመስለኛል። በጎበጠ ወገቤ ለፍቼ የማገኘው ገንዘብ እንዲህ የሚባክን ከሆነ ወደ ሀገሬ የሚያድረስሽን ገንዘብ አንዴ ልኬልሽ መገላገሉን እመርጣለሁ። የፈረምሽው ስምምነት እስኪያልቅ ድረስ እንግዲህ ክፉዎች ለሚፈልጉት ጉዳይ መላክ የግድ ነው። ከዚያ በኋላ የተሻለ ኑሮ ይኖረናል። ነገር ግን አብዝተው የሚወዱንን እንርሳቸው ማለቴ አይደለም። እየኖርንበት ያለነው ነገር እየሰለቸኝ ነው። አብረን ስንሰራ የነበረውን ጊዜ አስታውሺ። እንዳ አንቺ የሚረዳኝ ረዳት እስከ ዛሬ አላገኘሁም። ሁሉም ረዳቶቼ በሁሉም ስራዎች በእኔ ላይ ተጠግተው የሚኖሩ ናቸው፤ በጠዋት ተነስተው ተግባራቸውን ለመፈጸም፣ ጭነቶችን በወቅቱ ማራጋፍ፣ ማራገፊያ ቦታ መፈለግ፣ አድራሻ መቀበል ይህን ሁሉ በአግባቡ የሚሰራ ረዳት አላጋጠመኝም። ህይወቴ ከአንቺ ጋር የተሰናሰለ ነው። በዚህም ምክንያት ሁሉን አጥቻለሁ፤ የቀረኝ የለም። ይህ በዚህ ሁኔታ መቀጠል የለበትም።
ኒል
ጥቅምት 2, 2001
ኒል
አንደኛውን ግቢ ለመዝጋት ወስነናል። ይህ ደግሞ ለወቅታዊ ችግራችን ጥሩ መፍትሄ ነው። ሁለተኛውን ግቢ ስንይዝ ዕውቅና ለማግኘት መንግስት ላይ ጫና ለማሳደር ነበር። መንግስትም ቢሆን ተጨማሪ ክፍሎች እንደ መስፈርት ይፈልግብን ነበርና በወቅቱ ትክክለኛ ውሳኔ ነበር። ለፈለግነውም ዓላማ በእጅጉ ረድቶናል። አሁን ግን መልቀቃችን ተገቢ ነው። ጠንካራ የት/ቤት ማህበረሰብም አለን። ለገንዘብ ብቻ ብሎ ከእኛ ጋር ያለ አንድም የለም፤ ነገር ግን መስማት የተሳናቸውን ተማሪዎችን ለመርዳት ጭምር ነው እንጂ። ሁሉም ለዚህ ዓላማ የተሰለፍን በመሆናችን ታላቅ ሰላም አለን። የመንግስት መስፈርትና የሀገሪቱን ደንብ ለማሟላት ተጨማሪ ሰራተኛ መቅጠር ያስፈልግ ነበር። የሁሉንም ቅጥር የፈፀምነው በየ9 ወሩ በሚታደስ በኮንትራት ነው። ምናልባት በገና ወቅት ካልሆነ ኮንትራት ከማለቁ በፊት ሰራተኞችን ማሳናበቱ አስቸጋሪ ነው። ሁሉም መስማት የተሳናቸው ሰራተኞች የሚደገፉት በእኔ ብቻ ነው። ተማሪዎቹ ልነግርህ ከምችለው በላይ ነው ከፕሮግራማችን የሚጠቀሙት። ነገር ግን ከጀርባ ከሚሸረበው ደባ የተነሳ መደበኛ የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች እስከ አሁን ድረስ አላገኘንም። የሆነ ሆኖ በመጨረሻ ይመጣሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ከተለያየ አቅጣጫ የሚመጣ መንፈሳዊ ውጊያ በየቀኑ ያጋጥመኛል። አብዛኛው የዚህ ውጊያ ምንጭ አንተ በመስዋዕትነት ከምትልከውና ያ የተላከው ገንዘብ በከንቱ ቦታ አለመዋሉን እዚህ ሆኜ መመልከት ከመቻሌ ነው።
ስለዚህ ፕሮግራማችንን አንድ እርምጃ ወደ ፊት ለማስኬድ በምጥርበት ጊዜ የሚገጥመኝ ተቃውሞ እጅግ ከባድ ነው። እዚህ ሀገርና መንግስት ውስጥ ያለውን አስተሳሰብና እሴት በሚገባ ተገንዝቤያለሁ። የድህነታቸው ምክንያት እነርሱ ራሳቸው ናቸው። ምናልባት የምታሰር ቢሆን የእስራቴም ምክንያት ሊሆን የሚችለው በግልጽ ይሄው ድህነታቸው ነው። ወንድወሰን የብርታቴ ዋና ምሰሶ ነው። የሚገርም መንፈሳዊ ጥበብ አለው። ዘወትር እያነጋገረኝ ገንቢ የሆኑ ሀሳቦችን ይሰጠኛል፣ ያበረታታኛል፣ ገንቢ የሆኑ መልዕክቶችን ይልክልኛል። በዚህ ረገድ በእውነት እግዚአብሔር እየተጠቀመበት ነው። እርዳታህን ለማቆም በመፈለግህ አልወቅስህም። ነገር ግን ተጨማሪ ሳምንታትን ወስደን እስኪ እንፀልይበት፤ እግዚአብሔር መልስ ይሰጠን ይሆናልና። ለሁሉም ነገር እግዚአብሔር ምክንያት አለው። እኔም ቢሆን የምትልክልኝን ገንዘብ ማባከን አልፈልግም። ነገር ግን ይህ ውጊያ የእኔና የአንተ አይደለም የእግዚአብሔር ነው። እግዚአብሔር በብዙ ተራራዎች ላይ ብዙ ዋጋ አለው። እናም ምን እንደሚለን እስኪ በፀሎት ውስጥ በመቆየት እንጠይቀው። በዚህ ሁሉ ውስጥ እዚ ባሉት አባሎቻችን ዘንድ የተከበርክና የተወደድክ መሆንህን ልነግርህ እፈልጋለሁ። ሁላችንም በጋራ ሆነን እንፀልይልሃለን። ምንም መውጫ የሌለ በሚመስልበት ሁኔታ ውስጥ እግዚአብሔር መንገድ አለው። እናም ትንሽ እንታገስና ስራውን እንመልከት። በጣም እወድሃለሁ!!
ቤኪ
ሕዳር 3, 2001
ቤኪ
ከትላንት ወዲያ ረዳቴ ለጥቂት ነበር ከመኪና ግጭት የተረፈው። በተዓምሩ ነበር አምላክ ያተረፈው። ዛሬ ከአንድ ሰዓት በፊትም ሌላ ተመሳሳይ ሁኔታ ገጥሞት ነበር። እናም በጣም ፍርሃት ስለ ተሰማው በረዶ ወደ ሌለበት አካባቢ እንድንሸሽ ጠየቀኝ። ከሁለት ወይም ሶስት ቀናት በፊት በፍጥነት መንገድ ላይ የመኪና አደጋ ተከስቶ ነበር። በዚህ ምክንያት የምእራቡን የትራፊክ ፍሰት በግምት ከ5- 6 ማይል ይሆናል ወደ አደጋ አቅጣጫ ቀይረውታል። የጭነታችን ክብደትም 19,000 ፓውንድ ያህል ነው። በእርግጥ ይህ አነስተኛ ክብደት ነው። የንፋሱ አቅጣጫ ከሰሜን በኩል ነው። እናም ተሰቢያችን ከጊዜ ወደ ጊዜ ከ3-5 ጫማ ያህል ወደ ቀኝ ይንሸራተታል። ወደ እስር ቤት እንደምትወሰጂ በሰማሁና ይህንን ነገር ባስታወስኩ ቁጥር የወገቤ ህመም ይበረታብኛል። ለጥቂት ጊዜ ይደነዝዘኝና ቀጥሎ እንቅልፍ የሚባል ነገር ይርቀኛል። በአንቺ ላይ የሆነ ችግር መኖሩን በሰማሁ ጊዜ ሁሉ ሰውነቴ በአመፅ ይሞላል። ትናንትና ጭነታችንን ያራገፍነው ሚድል ታዎን ፔንሰልቬኒያ አጠገብ ነው። በኋላም ሰዓት ስለነበረን ዘወትር አብረን ወደምንሄድበት ከሀዲዱ ማዶ ወደሚገኘው ሱፐርማርኬት ጎራ ብዬ ነበር። ያኔ እንደምናውቀው ሁሉም ነገር ርካሽ ነው። ወድሻለሁ!!
ኒል
ታህሳስ 4, 2001
ኒል
ወደ እስር ቤት እንደሚወስዱኝ በማሰብ ለጥቂት ቀናት እጨነቅ ነበር። በሚገርም ሁኔታ ተሾመ፣ አለምነሽና ወላንሳ (ጥበቃችን፣ ወጥ ቤት ሰራተኛችንና የፅዳት ሰራተኛችን) ሁኔታውን ለማስቀረት 1100.00 ብር ወደ አካዎንታችን ለማስገባት ቢያመጡም የህግ አማካሪያችን እንዳያደርጉ ከለከላቸው። ምክንያቱም በህጋዊ መንገድ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ጠይቆ ስለነበር ነው። ይሁንና ምናልባትም በጉቦ ሊሆን ይችላል ይግባኛችን ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል። እናም ትንሽ ችግር የሚሆነው የዚህ የይግባኝ መከልከል ጉዳይ ነው። ለማንኛውም ጭንቀትህን አቁም። ምክንያቱም ሁሉም በእግዚአብሔር እቅድ መሰረት ይከናወናልና። ማስታወስ ያለብህ አንዳንዴ ሳይነጋ በፊት ክፉኛ ጭለማ ይሆናልና። ምናልባት ይህ ችግር ሊጠናቀቅ የመጨረሻ መጀመሪያ ሊሆን ይችላልና። ነገር ግን መልካሙን መጨረሻ ከማየታችን በፊት የክፉውን መጀመሪያ እናይ ሆናል። ለማንኛውም በፊት ስጽፍልህ እንደነበረው ጊዜ እየተጨነቅሁ አይደለሁም። በእውነት እግዚአብሔር መረጋጋትንና ሰላሙን ሰጥቶኛል። ስለዚህ በመንገዳችን ሁሉ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የመሆኑን ነገር አስታውሰህ ጭንቀትህን እንድታቆም እለምነሃለሁ። የወገብህ ህመም እንዲባባስ አልፈልግም፤ ጉዞዎችህ ሁሉ ከአደጋ ፀድተው የተሳካ መንገድ እንዲሆንልህ እፈልጋለሁ። በዚህ ጊዜ የዓመቱ የበረዶ ጊዜ እንደሆነ አውቃለሁ። እናም እግዚአብሔር እንዲጠብቅህ እፀልያለሁ። እወድሃለሁ!
ቤኪ
ታህሳስ 12, 2001
ለውድ ፍቅሬ
መጥፎ ቀኖች ነበሩኝ፤ መልካም ቀኖችም እንዲሁ። አሁን ያለሁት በፔጅላንድ ውስጥ ነው። ዛሬ በጠዋት ጭነቴን አራግፌ ማለፊያ እንቅልፍ ተኝቻለሁ። ይገርምሻል በጥሩ ሁኔታ ነበር የተኛሁት። ከዚያም ምናልበት ያኔ አንቺ እየተኛሽ ይሆናል ተነስቼ ደጋግሜ አንድ ፊልም አየሁ። ፊልሙ በዓመት ውስጥ በዚህን ወቅት ስለሚሆን ነገር የሚተርክ መሆኑን ተረዳሁ። ደጋግሜ ያየሁበት ምክንያት በፊልሙ ውስጥ ያለው ገፀ-ባህርይ አንድ ብቸኛ ሰው ከሌላ ብቸኛ ሰው ጋር ሲገናኝ የሚያሳይ ነው። ምን ማለት እችላለሁ? ስንገናኝ መናገር ከምችለው በላይ ይሆናል። የእኔና ያንቺ ታሪክ የገዘፈ ነው። የእኔና የአንቺ ታሪክ የተሻለ ታሪክ ነው። የእኔና የአንቺ ታሪክ ረጂም ታሪክ ነው። የእኔና ያንቺ ታሪክ የጠለቀ ታሪክ ነው። የእኔና ያንቺ ታሪክ ጠንካራ ታሪክ ነው። የእኔና ያንቺ ታሪክ ታሪክም ብቻ ሳይሆን ከዚያም በላይ የሆነ እውነተኛ ክስተት ነው። አመንሽም አላመንሽም ታላቅና መልካም ታሪክ አለን፤ ታላላቅ ሰዎች እንደ ፖል ሀርቬ ወይም ሪፕሌይ ከሚተርኩት ታሪክ እኩል የሚሆን። ለመሆኑ ማድረግ ያለብሽን ነገር አቁሜሽ ታውቂያለሽ? የምፈልገውን ማግኘት እንዳለብኝ ማሰብ አቁሜሽ ታውቂያለሽ? ስለምትፈልጊው ነገር ስታስቢ እርግጠኛ ሆነሽ ታውቂያለሽ? ነገር ግን ምን እንደምፈልግ አሁንም እርግጠኛ መሆን አትችዪም። ቀጥሎም ይህ ሁሉ ይረሳና በሌላ ሀሳብ መያዝ፤ ስለ ምግብ፣ ስለ መታጠብ፣ በእግር ስለመጓዝ ወዘተ። ሁሉ ነገር አለኝ፤ የምፈልገው ምግብ ሁሉ በመኪናዬ ውስጥ ይዣለሁ። የጎደለኝ ነገር ቢኖር አንቺ ብቻ ነሽ። ሁል ጊዜ ሀሳቤ በዚህ ዙሪያ ብቻ የሚያጠነጥን ነው:: አንዳንድ ጊዜ በጣም ገራሚ ይሆናል፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ በጣም አሳዛኝ። ቶናስኬት ሳለን ሻውኒ ያመጣልንና ደጋግሜ ስላየሁት ፊልም ለረዳቴ አወራለት ነበር። እርሱም እንደዚያ ባሉት ታሪኮች እንደሚያምን ይነግረኛል። እርሱም ብዙ የሚያስቁት ነገሮችን ይነግረኝ ነበር። በተለይም ሰዎችን ወደ ጌታ ሲያመጣ በመንፈስ ሲሆኑ፤ በልሳን ሲናገሩ ሲለወጡ አስገራሚ የሆነ ለውጥ ሲያይባቸው እንደሚያስቀው ይነግረኝ ነበር።
እነዚህ ነገሮች መንፈሳዊ ሰው መሆኑንና መንፈስ ቅዱስ እንዳለው እንደሚያረጋግጡለት ይተርክልኛል። እርሱ እንደ እውነት የሚያምናቸው ነገሮች የሚያስደንቁ ናቸው። እርሱ የሚያምነው እውነት አሁንም የሚያስደንቅ ነው። አሁን በዕድሜ እየገፋሁ ስሄድ ሌሎችም እውነት እንዳላቸው እያመንኩ መጥቻለሁ። ነገር ግን እውነታቸው ሁሉ-አቀፍ የሆነ የእውነት መሰረት ያለው አይደለም። ነገር ግን ውስን በሆነ እውነታ ላይ የተመረኮዘ ነው። እውነታነቱ የሚረጋገጠው በራሱ ነው። አብዛኛዎቻችን እምነትን የምንከተል አማኞች ነን። ነገር ግን ሌሎችን ከሚከተሉ ሌሎች የተሻልን አይደለንም።እናም ከቤተክርስቲያኑ ዶግማ ጋር የማይጣጣም የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል ሳመጣለት የሚለኝ ነገር ቢኖር “ስለዚህ ነገር መወያየት አልፈልግም” ይለኛል። ሌሎችም በማይስማማቸው የቅዱስ ቃል ክፍሎችን የሚደመድሙት በዚሁ በተመሳሳይ መልኩ ነው። ስለምወድሽ ይህንን ከክፋት እንደማትወስጂ ተስፋ አደርጋለሁ። አማኞች የተለያዩ ዶግማዎች የመከተላቸው ጉዳይ በጣም ይደንቀኛል። ለምሳሌ 10 ሰዎችን ብንወስድ ወደ 10 የተለያዩ ዶግማዎች በመከፋፈል ወደ አስር አብያተ ክርስትያናት ይሄዳሉ። እያንዳንዱ ቤተክርስትያንም እኔ ትክክል ነኝ ብሎ ያምናል፤ ቢያንስ ቢያንስ በተሻለ ሁኔታ ከሌሎች እበልጣለሁ ይላል። እያንዳንዱ ቤተ ክርስትያን ሰዎችን በራሱ መንገድ ለመቅረጽ ይጥራል። እያንዳንዱ ቤተ ክርስትያን ስለ ጥሩ ዶግማውና በዚያ መንገድም ስለመራኸኝ በማለት እግዚአብሄርን ያመሰግናል። ሌሎች ደግሞ የእነርሱን ዶግማ የማይከተሉት ሰይጣን ስለሰወራቸው ነው ይላሉ። እንግዲህ ከ10ሩ አንዱ 9ኙን የሚስለው እውነታውን ማየት ተስኖታል በማለት ነው። ስለሆንም የእግዚአብሔር መንፈስ በአብዛኛዎቹ ቤተ ክርስትያን ውስጥ አለ ብዬ አላምንም። ነገር ግን ትክክለኛ ሰዎች በሁሉም ቤተ ክርስትያናት ውስጥ አሉ ብዬ አምናለሁ። የእግዚአብሔር መንፈስ ቅድስና ከሌላቸው ቤተ ክርስትያነት ውስጥ የራሱን ሰዎች ይጠራል ብዬ አምናለሁ።
እግዚአብሄር ከሁሉም አብያተ ክርስትያናት ውስጥ የራሱን ሰዎች ይጠራል ብዬ አምናለሁ፤ ይህ ያደግሁበትን ቤተ ክርስትያን ይጨምራል። በዚህ ንግግሬ ጋር እንደምትስማሚ ተስፋ አለኝ። በአንድ ሀሳብ እንድንሆን የምፈልገው ሁላችን በዚህ አይነት አባጣ ጎርባጣ በሆነ ሁኔታ ውስጥ የመሆናችን እውነታ ነው። ስለዚህም እግዚአብሔር ምህረት እንዲሰጠን ነው። ካልሆነ በእግዚአብሔር ላይ እየቀለድን ስለመሆናችን እና ከመንግስቱ ጋር የምንተላለፍ መሆናችንን እንዲሁም በየዕለቱ የማይመራን መሆኑን መረዳት አለብን። በዚህ ሰዓት ሰውነቴ ከእንቅልፍ ልምምዱ የወጣ ይመስለኛል። በቀን ውስጥ በየትኛው ሰዓት የእንቅልፍ ፍላጎቴ እንደሚመጣ አላውቅም። ዛሬ ታህሳስ 10 የሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ነው። ሰዓቱም 01:30 ነው። ምናልባት የሚያስፈልገኝ ከሆነ መመገብ የሚገባኝን ምግብ እስኪ ልወስን። ነገር ግን አሁን የመሸ ስለሆነ ምንም ማድረግ አልችልም:: ውጭው የመሸ ይሁን እንጂ እንደ ወትሮ አይበርድም። የእለቱ የሙቀት መጠን 61 ዲግሪ ነው። ነገር ገን ዘወትርት በዚህን ወቅት የሙቀት መጠኑ ከ25 – 40 ዲግሪ መሆን ነበረበት። ባለፈው ወር ደግሞ የሙቀት መጠኑ ያው ድሮ እንደተለመደው ነበር:: ረዳቴ ለተሃድሶ ስብሰባ ወደ ቤቱ ሄዷል። በስብሳው ላይ ከሚናገሩትና ከሚሰብኩት አንዱ ነው። ተመልሶ ሲመጣ ምን እንደተከናወነ መጠየቅ ስለ መድፈሬ እርግጠኛ አይደለሁም። እወድሻለሁ!
ጣፋጭ ለሆንከው ለውድ ኒል
ስለፃፍክልኝ ያለህበትን ስላሰማኸኝ አመሰግናለሁ። ዕምነቶቹን የማትወድለት ሰው ረዳት አድርገህ በአንድ መኪና ውስጥ በመስራታችሁ በጣም ተገርሜያለሁ። ወደ ጂቡቲ ጉዞ ለማድረግ ተዘጋጅቻለሁ። እዚያ የምቆያው ለአራት ቀናት ነው። ወደዚያ የምሄደው ቪዛዬን ለማደስ ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ ህጋዊ ሆኜ ለመንቀሳቀስ ቪዛዬን ማደስ የግድ ነው። ይህንን ጉዞዬን ከወንድወሰንና ከህግ አማካሪዬ ውጭ የሚያውቅ ማንም የለም። ጂቡቲ የማላውቀው አገር ስለሆነ በዚህ ጉዞ ደስተኛ አይደለሁም። ነገር ግን የግድ ስለሆነ መሄድ አለብኝ። የነ ሞላን ጉደይ በተመለከተ እግዚአብሔር ተዓምር ሰርቷል። እነርሱ እኔ እስር ቤት አስገብተው ብዙ ገንዘብ ለማግኘት ብዙ ጥረዋል። በእርግጥ ቼኩ ላይ የመፈረማችን ጉዳይ ስህተት ነበር። የፈረሙትም ወንደወሰንና ደመቀ ናቸው። ይህ የሆነው ዳኛው ስላስገደደን ነበር። ነገር ግን በቼኩ ጀርባ ላይ ማህተማችን አርፎ ስለ ነበር ባንክ ቤት ሊቀበላቸው ፈቃደኛ አልሆነም። ይህም የተሳሳተ ቼክ በመጻፍ ወንጀል ከመከሰስ ያዳነኝ ተዓምር ነው። ይህንን ያደረገልኝ እግዚአብሄር ነው። ለማንኛውም አሁንም ቢሆን ሁሉም ነገር ያለቀ አይደለም። ሞላ ሊያሳስረኝ አንደንዴ ፖሊስ ይዞ ይመጣል፤ እናም እደበቀዋለሁ። ይህ ሁሉ ምናልባት ተማሪዎቻችን ወደ እኛ እንዳይመጡ ስለሚያደርግ ስጋት አለኝ። ኢትዮጵያውያን በመንገዴ ላይ በሚያስቀምጡት መሰናክልና ደባ መሰላቸት ጀምሬያለሁ። በትልቁ ያበሳጨኝ ደግሞ ህዳር ውስጥ ላለመምጣት የመወሰንህ ጉዳይ ነው። ላይህ እጅግ ናፍቄያለሁ። ለማንኛው ትልቅ ታሪክ ነውና አንድ ቀን ስንገናኝ የምንጫወተው ይሆናል። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር እንደሆነና በጉዳያችን ጣልቃ እንዴት እንደገባ እንጫወታለን። ከልቤ እውድሃለሁ!
ቤኪ
ሃሎ ውድ ኒል
እንደምን አለህ። አሁን ፀሎትህ በጣም ያስፈልገኛል። ያለሁት ጂቡቲ ውስጥ ነኝ። በወጥመድ ውስጥ ያለሁ ይመስለኛል። እግዚአብሔር እንዴት እንደሚያወጣኝ አላውቅም። እዚህ የመጣሁት ቪዛ ለማግኘት ነበር። ነገር ግን ወደ ኢምባሲ ገብቼ ጥያቄዬን ሳቀርብ አዲስ አበባ ያለው ኢምባሲያችን እንዳልተቀበለኝ ሁሉ እነዚህም ሊያስተናግዱኝ ፈቃዳኞች አልሆኑም። ጂቡቲ ያለው ኢምባሲያችን የአዲስ አበባ ኢምባሲያችን ጥያቄዬን ለመቀበል ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ሰምቷል። የሆነ ሰው ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳልሰራ እየተከታተለኝ እንደሆነ ግልጽ ነው። ይህ ሰው ስራችንን ከእኛ ለመንጠቅ ዝግጅት ላይ ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለኝም። እናም በእርግጥ በችግር ውስጥ ነው ያለሁት። አዲስ አበባ ስመለስ በአየር መንግድ ውስጥ ምን ሊገጥመኝ እንደሚችል አላውቅም። ከዚህም ሌላ ለተሰናባቹ ዳይሬክተራችን ይከፈል ብሎ ዳኛ ባዘዘው ገንዘብ ጉዳይም ችግር አለብኝ። በዚህም ምክንያት ሊከሰትብኝ የሚችል ጉዳይ ምን ሊሆን እንደሚችል አላውቅም። ምናልባት ከሀገር ሊያባርሩኝ ወይም እስር ቤት ሊያስገቡኝ ይሞክሩ ይሆናል። ነገር ግን እውነተኛ እና ታማኝ ስለሆንኩኝ ዋሾዎችንም ስለምጠላ ሁል ጊዜ እነዚህ ሰዎች በእሳት ላይ ይጥዱኛል፤ ችግር ውስጥም ይከቱኛል።
የዚህ ምክንያት እኔ በግሌ ከእግዚአብሔር ጋር ባለኝ ግንኙነት የተነሳ እና እርሱም በህይወቴ ውስጥ እየሰራ ባለው ጉዳይ ነው። እግዚአብሔር ሁሉ ነገሮቼን እየተቆጣጠረ እንደሆነ እርግጠኛ ነኝ። ነገር ግን በህይወቴ ውስጥ ሲሰራ በምን አቅጣጫ እንደምሄድ አላውቅም። እንደማስበው ከሆነ ሁሉ ነገር በተቃራኒ መንገድ እየመጡብኝ ነው። ሁሉ ተቃራኒ በሆነበት በዚህ ጊዜ ጥንካሬ ይሰጠኝ ዘንድ ከእኔ ጋር ያለው ጌታ ብቻ ነው። በአደጋ በተከበብኩበት ጊዜያት ሁሉ በተዓምሩ ከእኔ ጋር የነበረውን ጌታ ሳስብ በዚህም ጭለማ በሆነበት ጊዜ ከእኔ ጋር እንደምሆን አልጠራጠርም። አሁን በጉጉት ከጌታዬ እምጠብቀው አሁን ከገጠመኝ ፈተና እንዴት እንደሚያስመልጠኝ ማየት ነው። እናም በዚህ በየቀኑ በብቸኝነት ውስጥ በተዘፈኩበት ጊዜ ከእኔ ጋር ብትሆን እመኝ ነበር። በየቀኑ ብትመጣ እና ባይህ እመኛለሁ:: ወንድወሰንም ከጂቡቲ እንዴት መመለስ ባለብኝ ጉዳይ ላይ በጣም እየተጨነቀ ነው። ወደዚህ ወደ ጂቡቲ ባልመጣ ይሻል ነበር። በሆነ ምክንያት ወደ አዲስ አበባ የማልመለስ ከሆነ መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች ከፍተኛ ችግር ላይ የሚወድቁ ይመስለኛል። በእርግጥ በአሁኑ ጊዜ ሙሉ በሙሉ በእኔ የሚደገፉ ናቸው። እባክህ በርትተህ ፀልይልኝ። አብዝቼ እወድሃለሁ።
ቤኪ
ህዳር 25, 2001
ኒል
እንደምን አለህ? በጣም ናፍቀሀኛል። በአሁኑ ጊዜ በርካታ መንፈሳዊ ውጊያዎች በዙሪያዬ እየተካሄዱ ናቸው። ይህ ውጊያ ከፍ እያለ መጥቷል። ነገር ግን እግዚአብሔር በሚሆነው ነገር ውስጥ ከኔ ጋር ስለሆነ ዲያብሎስ ስራችንን ከእኛ ሊነጥቀን አይችልም። አንተና እኔ በእግዚአብሔር አገልግሎት ውስጥ በሰፊው እየተሳተፍን ነው። በተለይም ክብሩ ለእግዚአብሔር በሆነ መልኩ መስማት ለተሳናቸው ኢትዮጵያዊያን አገልግሎት እየሰጠን ነው። ለእነዚህ ወገኖች እየሰጠን ያለነውን ስራ ልታምን በማትችልበት ሁኔታ እያከናወንን እንገኛለን። በመሃከሉ ያን ያህል ሊያሳስበን የማይገባ ነገር ግን አፍራሽ ሀሳብ የያዘ የኢሜይል መልእክት ከኪዳኔ ደረሰኝ። በኢሜይሉ ውስጥ የተጠቀሰው ያቺን መኪና በተመለከተ ዳግመኛ ዛቻ አዘል መልዕክት ነው። እናም በዚህ ጉዳይ ሊያጠቃኝ ይፈልጋል። ነገር ግን ሁሉንም በአግባቡ ሊመልስ የሚችል ጠንካራ ጠበቃ አለኝ። ችግር ሊፈጥሩብኝ የሚመጡትን ሁሉ እንደ አመጣጣቸው ሊመልሳቸው ይችላል። እግዚአብሔር እዚህ ከሚደርስብኝ የጠላት ጥቃት ሊጠብቀኝ ስለሚፈልግ ነው ይህንን ሰው የሰጠኝ። ከዚህም በላይ አንተ እና እኔ መስማት የተሳናቸው ኢትዮጵያዊያን ላይ መንፈሳዊ እና የመዋዕለ-ንዋይ ፍሰታችንን ለመጠበቅ ጭምር ነው ይህንን ሰው የሰጠን። የሚገርም ነገር ነው!!! እዚህ በምናደርገው ስራ ውስጥ መልካም ተጋድሎ በማድረግ ረገድ ጠንካራ እንደ ሆንክ አውቃለሁ።
በዚህ ሰዓት በጋራ ካልሆንና አንተ ከምትልከው ገንዘብ ውጭ የሚሆን ነገር የለም። እግዚአብሔር እኔን እንደጠራኝ ሁሉ አንተንም እንደጠራ አውቃለሁ። ብርታታችንም በእርሱ ብቻ ነው። ከጌታ ውጭ ዞር የምንልበት አንድም ቦታ እንደሌለ ሁለታችንም እናውቃለን። በእርግጥ በዚህ ስፍራ መሆን አስደናቂም ከባድም ነው። ምክንያቱም እግዚአብሄር በስራ እድልና በተለያዩ መንገዶች አብዝቶ በረከቱን መስማት ለተሳናቸው ሲያፈስ ጠላታችን የሆነው ዲያብሎስም በዚያው መጠን ፈተናውንም ያበዛብናል። ነገር ግን እግዚአብሄር ከፈተናዎቹና ቆሻሻ ከሆኑት ከሰይጣን ስራዎች ሁሉ በላይ ነውና፤ ይበልጥልናል:: ስራዎቻችን ይጠፋ ዘንድ አይፈቅድለትም። ስለሆነም ሀይልንም በሚሰጠን በክርስቶስ ኢየሱስ ከአሸናፊዎች በላይ ነን። ስራዎችህን በሚገባ እንደምትሰራ እየተደነቅሁ ስለ አንተ ደግሞ በጣም እጨነቃለሁ። ምክንያቱም በእነዚህ ቅርብ ቀናት ከአንተ የደረሰኝ ምንም መልዕክት የለም። በስልክ ላገኝህ ብሞክርም ላገኝህ አልቻልኩም። አንተ በህይወቴ ታላቅ የሆንክ ፍቅሬ እና ረዳቴ ነህ። እባክህ ቶሎ ጻፍልኝ:: ራስህን ጠብቅ እናም እወድሃለሁ!
ቤኪ
ታህሳስ 27, 2001
ቤኪ
እባክሽ ለኪዳኔ ሀብቴ ኢሜይል በማድረግ የእህቱን አድራሻ እንዲሰጥሽ አድርጊ። የከድርንም የስልክ ቁጥር ላኪለት። የከድር ቁጥር 703 560 7272 ነው። ሶስቱንም በማገናኘት ተወያይተው የመኪናውን ሰነድ እንዲሰጡ አድርጊ። ለከድር መልካም ሁኚለት ሶስተኛ ልጁን ሊወልድ ተቃርቧል። ህጻኑ ገና ሳይወለድ የልብ ችግር እንዳለበት ሰምቻለሁ። ምናልባት በህይወት ላይኖር ይችላል፤ ወይንም ተወልዶ ብዙ ላይቆይ ይችላል። “ለእቃዎቼ በቂ ቦታ እንዲኖረኝ ቅራቅንቦህን ከመንገዴ ላይ አስወግድ” የሚባለውን አባባል ምናልባት ሰምተሽ ይሆናል። በተመሳሳይ መልኩ እግዚአብሔርም ክብሬንና ሀይሌን አሳይ ዘንድ ቅራቅንቦአችሁን ከፊቴ አስወግዱ እያለ ይሆናል። የደረሰብን ታላቁ ኪሳራ እና ስብራት ታላቁን የእግዚአብሄር በረከት እንዲሁም በእኔና በአንቺ ሊሰራ ያቀደውን ታላቁን ስራ እንድንገናዘብ ምክንየት ሊሆን ይቻላል። ዛሬ ጠዋት በመንገድ ሳለሁ ምን ልጽፍልሽ እንደሚገባኝ አስቤ ነበር። በልቤ ሙሉ እና ስለ ፍቅር እግዚአብሔር ባስገነዘበኝ መጠን ሁሉ እወድሻለሁ። ምንም እንኳ ዲያብሎስ በሙሉ ሀይሉ ስራችንን ለማፍረስ ያለ እረፈት የሚሰራ ቢሆንም እኔም ስራችንን ለማስቀጠልና የጠላታችንን ተቃውሞ ለመቋቋምና ለመሻገር የማደርገው ውሳኔ ከመቼውም በላይ የጠነከረ እየሆነ መጥቷል።
በዚህን ሰዓት ታላቅ ወደሆነ መዳረሻ የተቃረብን መሆን አለበት። አንቺና እኔ ይህንን መዳረሻችን እናያለን፤ እንመለከታለን። አፍራሽ ሀይሎችና መሪያቸው ሰይጣን ደግሞ መጨረሻችንን ለማደናቀፍ በስሌት ተጠምዷል። ከገጠመኝ መጠነኛ እክል እያገገምኩ ነው። በሶስት ሳምንተት ውስጥ በጉልበቴ ውስጥ ይሰማኝ ከነበረው ህመም አገግሜ ከህመም ነጻ ሆኛለሁ። በእነዚህ ሶስት ሳምንታት ውስጥ ከትላንትና ጀምሮ ምንም ህመምና እብጠት አልተሰማኝም፤ አላየሁም። በእነዚህ ሳምንታት ውስጥ ያለምንም ችግር መሮጥ የቻልኩትም ትላንትና ነው። በጣም ተሽሎኛል። ሰይጣን ከእኛ መውሰድ የሚያደርገውን ሙከራ ሁሉ አንፈልግም። ምናልባት ሊወስድብን ከሚሞክረው ገንዘባችን ሙሉ በሙሉ ወይም ጥቂቱን ማትረፍ ብንችል መልካም ነው። ብዙ ጊዜ ከብዙ በረከት ቀድሞ ብዙ ፈተናዎች ይከሰታሉ። እግዚአብሔር በደረቅ መሬት ላይ እንድንሻጋር እንደሚያዘጋጀን ተስፋ አደርጋለሁ። በሕይወቴ ውስጥ እኔ ከምፈልገው በላይ አብዝቶ እንዲባርከኝ እፈልጋለሁ። ሌሎች ሰዎችም ይህንን በረከት ተመልክተው ይህ የእግዚአብሔር እጅ እንጂ ሌላ ምንም ሊሆን አይችልም ለማለት እንዲበቁ እፈልጋለሁ። መልካሙን ተጋድሎሽን አጠንክረሽ ያዢ። ለአፍታም እንኳ ወደኋላ እንዳትዪ:: መንገደኛ ሾፌርሽንም አሁንም ውደጂ::
ውድ እናቴ
ባለሽበት ሀገር እየሆኑ ባሉት መልካም ያልሆኑ አንዳንድ ጉዳዮች ዙሪያ ወሬዎችን ሰምተናል። እናም ያለሽበትን ሁኔታ ማወቅ በእጅጉ እንሻለን። ሰላም መሆንሽን ማወቅ እፈልጋለሁ። ስለዚህ ይህ ኢሜይል እንደ ደረሰሽ ለእኔ ወይም ለዊንዲ መልሰሽ ቶሎ ጻፊልን። በስልክም ላነጋግርሽ ስለምፈልግ ቁጥርሽን ላኪልኝ። (ለፒተር ተጽፎ ለኒል ግልባጭ የተደረገ)
ልጅሽ ፒተር ማክዶናልድ
ታህሳስ 12, 2001
ሃይ ፒተር!
ስለ ፃፍክልኝ በጣም ደስ ብሎኛል። እንዴት ነህ? ካሮላይንስ ደህና ነች? ያለሁት የጦርነት ያህል በሆነ ትግል ውስጥ ነው። በእርግጥ አብዛኛዎቹ አልፈዋል። አምና ያባረርናቸው ተስፋ የቆረጡ ሰራተኞቻችን ከሰውኝ ሊያሳስሩኝ ሞክረው ነበር። የተከሰስኩት በሁለት ጉዳዮች ነበር። አንደኛውን አሸንፈናል። ነገር ግን ማሸነፋችን ከእስር ስጋት ነጻ የሚያደርገኝ አልነበረም። ምክንያቱም መንግስተ- ስርዓቱ ሙሰኛ ስለሆነ ዳኞቹ በጉቦ የተያዙ ራስ ወዳዶች፣ መልካምነት የሌለባቸው ናቸውና በፍርዳቸው መተማመን አይቻልም። ይህ ባሕርያቸው ራስን ቀና እንዳላደርግ አድርጎኛል። ለማንኛውም መሰረቴ አምላኬ ነውና ከክፉ ሁሉ ይጠብቀኛል። ለምሳሌ በሁለተኛው ክስ ላይ ዳኛው ባልተገባ ሁኔታ ከሳሼ ለነበረው ሞላ የተሳሳተ ቼክ እንድጽፍለት አዘዘኝ። ይህንን ካላደረግኩ እንደምታሰር አሳወቀኝ። የኔ ጠበቃም ይህንን ጉዳይ ማድረግ እንዳለብኝ መከረኝ። ለምክሩም ምክንያት ብሎ የነገረኝ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ብለን ስለ ነበር ስለ ሁሉም ፍትህ ከዚያ ስለምናገኝ ይህንን ቼክ መጻፍ ጠቃሚ ነው አለኝ። ነገር ግን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስንደርስ እኔ በማላውቀው ምክንያት ክሶቻችን ተዘግቶ ጠበቀን። ሰኞ ዕለት ለሞላ የፃፍኩለት የተሳሳተ ቼክ ከባንክ ለማውጣት በሚሞክርበት ቀን የተሳሳተ ቼክ በመፃፌ ምክንያት ወደ እስር ቤት ሊልኩኝ ነበር። ይህ እንግዲህ በጉቦ የተሰራ ስራ ነው። ነገር ግን የተከሰተው አስደናቂ ነገር ነው:: እኔ ሳላውቅ በቼኩ ጀርባ ላይ ማህተማችንን አድርጌ ስለ ነበር ሞላ ገንዘቡን ለማውጣት በሚሞክርበት ጊዜ ባንኩ በስህተት የተመታውን ማህተም በመመልከት ገንዘቡን ለመክፈል እምቢተኛ ይሆናል:: ይህን የተረዱት ሞላና ጠበቃው እሳት ጎርሰው እሳት ለብሰው ሌላ የተሳሳተ ቼክ እንድፅፍላችው ወደ ግቢያችን ይመጣሉ:: በዚህን ወቅት ጉዳዩን ለአሜሪካን ኤምባሲ ለማመልከት ሄጄ ነበር:: ስመለስም እነሞላን በግቢያችን ውስጥ አገኘኋቸው፤ ሌላ ቼክ እንደማልሰጣቸው ነግሬያቸው ተለያየን::
ሰጥቼያቸው ቢሆን ኖሮ ለእስር እዳረግ ነበር:: በዚህ በስህተት ከመታሳር ያወጣኝ እግዚአብሔር ነው:: እነዚህ ሰዎች ቀጥሎም ምን ሊያደርጉ እንዳሰቡ እርግጠኛ ስላልነበርኩ መደበቅ አስፈላጊ ነበር። ለዚሁ ጉዳይ ወደ ጂቡቲ መጓዝም ነበረብኝ:: ይህም በራሱ እጅግ አስፈሪ ተግባር ነው፤ ምናልበት ስመለስ አዲስ አበባ አየር መንገድ ተይዤ ከሀገር ልባረርም እችል ይሆናል:: የሆነ ሆኖ ግን ይህም አልተፈፀመብኝም:: ወደ አዲስ አበባ በተመለስኩ በማግስቱ የሞላ ጠበቃ ወደ ቢሮዬ በመምጣት ሌላ ቼክ የማልፅፍ ከሆነ እንደምታሰር በመንገር አስፈራራኝ:: እንግዲህ በማስፈራራት እየጠየቀኝ ያለው የተሳሳተ ቼክ እንድፅፍለት ነው:: እንዲህ ማሰቡ በራሱ አላዋቂነቱ ምን ያክል የጎላ መሆኑን የሚያሳይ ነው:: እንዳጋጣሚ ሆኖ ኢትዮጵያ ውስጥ ላሉት መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች ኒል ከፍተኛ መስዋዕት እየከፈለ እንደሆነ የሚያሳይ መፅሄት አሳይቸየው ነበር:: እናም በማስፈራራት የምጠይቁኝን ገንዘብ እንደለሌኝ ነግሬው ሞላ ፍርድ ቤቱ የሚወስንለትን ክፍያ ቢጠባበቅ እንደሚሻለው ከዚህ ውጭ ምንም ሊያገኝ እንደማይችል ስነግረው በመሸማቀቅ በፍረሃት ተውጦ ወጥቶ ሄደ:: እንግዲህ እግዚአብሔር ጣልቃ በመግባት እኔን በመከላከሉ ምክንያት ነው ይህ ሰው የዚህ አይነት ስሜት ሊሰማው የቻለው;; በዚህን ወቅት በማላውቀው ምክንያት ፋይሌ በመዘጋቱ ይህ ነገር እንዲጣራ የኔ ጠበቃም ወደ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቤቱታ አቅርቦ ነበር:: ኒል እስከ አሁን ድረስ ይህን ጉዳይ አያውቅም:: አሁን ልትነግረው ትችላለህ፤ ለዊንዲና ለኬንትም እንዲሁ ንገራቸው:: እዚህ ያሉ ሰዎች ምን ያክል ጨካኞች እና ራስ ወዳዶች ቢሆኑም እዚህ እየሰራን ያለነውን መልካም ስራ ለማከናውን ኒል ከፍተኛ ስፍራ አለው:: እግዚአብሔር በአግባቡ እየተጠቀመበት ነው:: ለእነዚህ ሰዎች የኒልን ከፍተኛ መስዋዕት የመመስከር ብዙ አጋጣሚዎች አግኝቻለሁ::
በተቃራኒው የእነርሱ ክፉ ስራ ምን ያክል እየተሰራ ያለውን መልካም ስራ በተለይም እየተረዱ ያሉትን መስማት የተሳናቸው ወገኖችን እየጎዳ ብሎም እያጠፋ እንዳለ በግልፅ እየነገርኳቸው ነው:: ይህንንም ሆን ብለው እያጠፉ መሆኑን እየነገርኳቸው ስለሆነ ምናልባትም ራሳቸውን ያስተካክላሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ:: የነዚህን ክፉ ሰዎች ህይወት በመቀየር ረገድ እግዚአብሔር ይህንን ምስክርነት እየተጠቀመበት መሆኑን ኒል ማወቅ አለበት:: ክፉ ሰዎች የእኛን ድርጅት በመጠቀም በተጭበረበረ መንገድ ብዙ ገንዘብ ማግኘት ይፈልጋሉ:: እዚህ ያሉ አብዛኛዎቹ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁ ያደርጋሉ። የድርጅቶቹ ሀላፊዎችም ሳይቀሩ ደሃን እንረዳለን እያሉ ለራሳቸው በተዋበ ቤት ውስጥ ይኖራሉ፤ ውድ መኪናዎችን ለራሳቸው ይገዛሉ። በደሃ ስም በተደላደለ ኑሮ ውስጥ እየኖሩ የሚያመጡትን ገንዘብ ለራሳቸው ጉዳይ ያባክናሉ:: እኛ ግን በኒል መስዋዕትነት ምክንያት ያለንን ሁሉ እንሰጣለን:: ስለዚህ እዚህ ካለው መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር ሲነፃፀር የእኛ የተለየ መልክ አለው:: ተልዕኳችን በሰዎች ኑሮ ላይ ዕውነተኛ ለውጥ ማምጣት ነው:: ይህም መስማት የተሳናቸውን ወገኖች ዛሬ የሚታየውን ለውጥ ብቻ ሳይሆን ከጀርባ የነበራቸውን ታሪካቸውን ጭምር የሚቀይር ይሆናል:: እግዚአብሔር ጠባቂዬ ከመሆኑም በላይ ነገሬ በእስር ቤት መጣል እንኳን ቢሆን ለተለየ ዓላማ እንደሚጠቀምብኝ አውቃለሁ:: በዚህ አገልግሎት ላይ ለረጅም ጊዜ ቆይቻለሁ፤ በስራዬም እታወቃለሁ:: በዚህ ሀገር ውስጥ ለአንድ ለተለየ ጉዳይ እግዚአብሔር እየተጠቀመብኝ ነው:: ለእግዚአብሔር ዓላማ የሚሰሩ ሰዎች በአብዛኛው ጥሩ ሁኔታ አይገጥማቸውም::
ለዚህም ይሆናል ዘመኔን በሙሉ መልካም እየሰራሁ አስቸጋሪ ፈተናዎች የሚፈራረቁብኝ:: ለነዚህ ፈተናዎች ተዘጋጅቻለሁ:: ካሳለፍኳቸው ተነስቼ ሳስብ ጭለማን ጥሶ እንደማለፍ ነው:: በዚህ ሀገር ብቻዬን ሆኜ በአስደናቂ ሁኔታ የተፈራረቁብኝ ፈተናዎች ብዙ ናቸው:: በዚህ አገር አብዛኛዎቹ ሰዎች መስማት የተሳናቸውን ወገኖች በመጠቀም ለራሳቸው ኑሮ ያመቻቻሉ:: በዚህም ምክንያት መስማት የተሳናቸው ወገኖችም በቀላሉ ሌሎችን ስለማያምኑ የሚደገፉት በእኔ ነው:: በሌላ መልኩ እኔ ነጭ አሜሪካዊት ስለሆንኩ ከመጠን በላይ ዶላር ያለኝ ይመስላቸዋል:: በተጨማሪም ብቻዬን የመሆኔ እውነታ ደግሞ ለመታለልና ለመከዳት የተጋለጥኩኝ አደርጎኛል:: የሆነ ሆኖ የማይታየው አምላኬ አስደናቂ በሆነ ሁኔታ ይጠብቀኛል፤ 100% እተማመናለሁ:: የስልክ ቁጥሬ 0913539363 ነው:: እንደምትደውልልኝ ተስፋ አደርጋለሁ:: እወድሃሁ!
እናትህ ነኝ
ታህሳስ 23, 2001
ኒል እንደምን አለህ
ምንም ያህል ሁሉም የመኪና መንገዶች እና የአየር ፀባይ በተመሳሳይ መልኩ ምቹ ባይሆኑም በጥሩ ሁኔታ እየሰረህ ነው ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ:: ብልሹ በሆኑ መንገዶች ላይ መንዳት አስቸጋሪ እንደሆነ አውቃለሁ:: ሁል ጊዜ እየፀለይንልህ ነው:: በእርግጥ አንተ የኛ ጀግና ነህ:: ሁሉም ያጀግኑሃል፤ ሁሉም አብዝቶ ያስቡልሃል:: ስለ አንተ በምንሰጠው ምስክርነት እግዚአብሔር ምን ያህል እንደሚጠቀምብህ ብነግርህ ይደንቀሃል:: በአሁኑ ወቅት ክስ ሂደቱ የደረሰበትን ደረጃ ከፒተር ትሰማለህ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ:: ይህንን በተመለከተ ኢሜይል ፅፌለት ነበር:: በአሁኑ ወቅት አንዳንድ ዋና ዋና ለውጦችን አድርገናል:: ምናልባት ይህ ለውጣችን በአንተና በፋይናንሳችን ላይ አሉታዊ ጎን የሚኖረው ይመስለኛል:: ባደረግነው ለውጥም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ለመጀመር ሁኔታዎች ተመቻችቷል:: በዚህ የተሳካልን ቢሆንም ከመንግስት ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎችን ማግኘት አልቻልንም:: ምክንያቱም ተማሪዎች ወደ እኛ እንዳይመጡ የክፋት ስራ ስለሰሩብን ዘንድሮ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማካሄድ አልቻልንም:: ነገር ግን በሚቀጥለው ዓመት ይህ እንዳይደገም በጥንቃቄና በተለየ ስትራቴጂ እንሄድበታለን:: በዚህ ምክንያት አዳዲስ ሰራተኞቻችን ያሰነበትን ሲሆን እነርሱም በደስታ ነው የተቀበሉት::
የሰራተኞቹ መሰናበትም 600.00 ዶላር አስቀርቶልናል:: ይህ መልካም ነገር ነው:: አዲስ የተከራየነው ግቢም ስለምንለቅ ሌላ የ1,000.00 ዶላር ወጭ ይቀርልናል:: ከዚህም ሌላ የክለሳ ጥናት የምናደርገውም በ7ኛ እና 8ኛ ክፍሎች ብቻ እንዲወሰን አድርገናል:: ባለፈው ወር ከ9ኛ እና 10ኛ ክፍሎች ጋር የምናደርገውን ጥናት እንዳቆምን ሁሉ አሁንም ከ5ኛ እና 6ኛ ክፍሎች ጋር ይህን ስራ እናቋርጣለን:: ይህም ወጭያችንን በተጨማሪ 400.00 ዶላር እንድንቀንስ ይረዳናል:: አሁን ከአጠቃላይ ሰራተኞቻችን ጋር የተስማማነውና በጉጉት የምንጠብቀው አንተ ካለህበት ድካም አረፍ ብለህ እዚህ መጥተህ ከእኛ ጋር እንድትሆን ነው:: ይህ ቀዳሚ ጉዳያችን ነው:: እዚህ ያሉት ሁሉም ሰራተኞች በጣም ይወዱሃል ያከብሩሃል:: ቀደም ብዬ እንደገለፅኩልህ አንዳንድ ስራዎችን በመቀነስ ከ2,000.00 ዶላር በላይ ስለቆጠብን ትንሽ ያሳርፍሃል እፎይታም ይሰጥሃል:: ከሁሉም በላይ ግን እዚህ ላሉት ሰራተኞቻችን እጅግ አስፈላጊ መሆንህን ልነግርህ እፈልጋለሁ:: በጣም እወድሃለሁ!
ቤኪ











