Skip to main contentSkip to footer

የ1999 የፍቅር ደብዳቤዎች

የ1999 የፍቅር ደብዳቤዎች

 

ነሐሴ 11, 1999

ትላንትና በአለንታወን ነበርኩ። በዚያም የ34 ሰዓታት ዕረፍት ነበረኝ። በዚያ ሳለሁም የእግር ጉዞ አደረጉ፣ የንባብ ጊዜ ነበረኝ፣ ግብይት እንዲሁ። ኦልድ ካንትሪ ቡፌት በሚባለው ሆቴልም የመመገብ አጋጣሚ ነበረኝ። እናም በዚህ ሆቴል ብዙ በላሁ። በእውነት ምን ያክል እንደራበኝም አላውቅም። 11.00 ዶላር ነው ያወጣሁት። ይህን ያህል ገንዘብ በማውጣቴ የጥፋተኝነት ስሜት ተሰምቶኛል። ገንዘብ በምትፈልጊበት በዚህን ጊዜ እኔ ይህን ያህል ለምግብ ሳወጣ አግባብ መስሎ አልተሰማኝም።በነዚህ ቅርብ ቀናት ኒውዮርክ፣ ኮኔክትከት እና ማሳቹሴትስ ነበርኩ። በመሆኑም ለመንገድ ክፍያ ብዙ አውጥቻለሁ። በመሆኑም ማግኘት የሚገባኝን ያህል አላገኘሁም። ቅዳሜ በ18 285.00 ነበረኝ። እኔ ግን እፈልግ የነበረው 200.00 ነው። ብዙ መስራት አለብን ብዬ አስባለሁ፤ ቆይቼ ደግሞ ለጥቃቅን ነገሮች አያስፈልግም እላለሁ፤ ትንሽም ነገር ነውና።  ለማንኛውም በምናደርገው ሁሉ የሚመራን እኔ ወይም አንቺ አይደለንም መሪያችን እግዚአብሔር ነው። ስለ ውጤቱም መጨነቅ የለብሽም ነገር ግን ትክክለኛውን ነገር በትክክለኛው ምክንያት አድርጊ እንጂ። በአንድ ጊዜ ዓለምን ልንቀይራት አንችልም። በእግዚአብሔር ሀይል ደግሞ ትክክል የሆነውን እስከሰራን ድረስ ልንቀይርም እንችላለን። ምናልበት ስራ በዝቶብሽ ወይም ከከተማ ውጭ ሄደሽ ወይም ጠቃሚ የሆኑ ሰዎችን በማነጋገር ጊዜ አጥተሽ ሊሆን ይችላል ከአንቺ ምንም መልዕክት አልደረሰኝም። እናም ይህ መልዕክቴ እንደደረሰሽ ቶሎ ጻፊልኝ።

 

ቤኪ ትላንትና ለማለት የፈለኩት እግዚአብሔር ትሰሪ ዘንድ ያመለከተሽን ነገር በማንኛውም መስዋዕት ደረጃ በምታከናውኚበት ጊዜ ያንን ሂደት ለስኬት ወይም ለውድቀት ስታደርጊው ውድቀቱ ለርግማን ስኬቱ ለጽድቅ ይቆጠራል ማለቴ ነበር። አሁን ለእኔ ከባዱ ነገር ያለኝን ገንዘብ መልቀቅ አለመቻል ነው። በእድገቴ ውስጥ ሁል ጊዜ የማስበው ክፍተቴን ለመሙላት ያለኝን ገንዘብ በእቅድ ብቻ በጥንቃቄ መጠቀም በማለት መወሰኔ ነው። አብዛኛው ሰው በትምህርት ይሳካላቸዋል። ነገር ግን ወጪያቸውን መቆጣጠር አይችሉም። ስለሆነም በጥቂት ገቢዬ ወደ ስኬት እየሄድኩኝ ነው። ምክንያቱም ወጪዎቼን በጥበብ ስለማወጣ ነው።አሁን አከናውን ዘንድ እግዚአብሔር ከፊቴ ያስቀመጠው ከባዱን ነገር ነው። ይህንንም በራሱ በእግዚአብሔር ፀጋ አደርገዋለሁ። በህይወቴ የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት ውሳኔ ትልቁ ፈተናዬ ነው። ይህን የማመሳስለው አንድ ሰው ውድ ዋጋ ያለውን እንቁ አግኝቶ ያንን የራሱ ለማድረግ ንብረቱን ሁሉ ከሸጠው ጋር ነው። እኔና አንቺ ለራሳችን ደስታ ስንል ማድረግ ስንችል ያላደረግናቸው ብዙ ነገሮች ነበሩ። ነገር ግን እግዚአብሔር እንድንተው አደረገን። በዚህም ምክንያት ያጣነው ምንም ነገር የለም። ይህ ነገር ትል በተለያዩ የዕድገት ዑደቶችዋ ውስጥ የምትቆይበትን ጊዜያት ጋር ሊመሳሰል ይችላል። ትል በአንድ የእድገት ዑደት ውስጥ የነበረውም መልክ በሌላ ዑደቱ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ቀይሮ ሌላ ይሆናል፤ ፍጹም ይቀየራል።

 

እግዚአብሔር ቀስ በቀስ ወደዚህ ለውጥ አምጥቶኛል። ምክንያቱም በእያንዳንዱ ደረጃዎቼ የነበሩኝ ሁኔታዎቼ ለየደረጃዎቹ ከበቂ በላይ ይመስሉኛል። ጉረኛ ለመሆንም ከበቂ በላይ ጊዜ ነበረኝ። ጉረኛነቴም ለራሴ አልነበረም ነገር ግን እግዚአብሔርን መመኪያ አድርጌ በእርሱ ከመመካት የተነሳ የሆነ ጉረኝነት ነው እንጂ ከስጋ ማንነቴ የተነሳ አልነበረም። እግዚአብሔር በተለያዩ ደረጃዎች ውስጥ ያሳልፋል። በአንድ ጊዜ አንድ እርምጃ ወደፊት ይወስደናል። በእርሱ ሀይል የምናልፍባቸውን ደረጃዎች በራሳችን ብቻ ልንረዳ አንችልም፤ በፍላጎታችንም በእነዚያ ደረጃዎች ውስጥ የማለፍ ብቃት አይኖረንም። እግዚአብሔር ለማይሰራባቸው ይህንን ተንትኖ መንገር አስቸጋሪ ነው። እንደዚህ ላሉት ሰዎች ልክ የምንረማመድበት ምድር ያክል ርካሽ ነው። ለእኔና ለአንቺ ግን ከሁሉ በላይ ውድ የሆነ የመሸጋገሪያ ሂደቶች ናቸው። በየሂደቶቹ ባሉት ግዜያት ቀንና ማታ የእግዚአብሔር ጥበቃ ልዩ ነው። ያለ ልክ እወድሻለሁ!

ኒልመስከረም 5, 2000

በማለዳ ተነስቼ ቀደም ብዬ ልጽፍልሽ እንደሚገባኝ አሰብኩ። ነገር ግን በድካም ውስጥ እንደ ነበርኩ አስታወስኩ። በአመጻ ውስጥም ነበርኩ። 38 ሰዓታት መፈፀም የሚገባኝን ጉዞ በ33 ሰዓታት ውስጥ አጠናቅቄ ስለ ነበር ከፍተኛ ድካም ውስጥ ነበርኩ፤ በዚህም ምክንያት የሚቀጥለውን ጭነት ለመቀበል ፈቃደኛ ልሆን አልቻልኩም። ከላይ የጠቀስኩት 38 ሰዓታት ደግሞ በእውነት 35 ሰዓታት ነበሩ። በመጀመሪያው ሳምንት የተጓዝኩት ጥቂት ማይሎችን ብቻ ነበር፤ በሚቀጥለው ሳምንት ደግሞ የቀደመውን ሳምንት ሶስት እጥፍ ነበር የተጓዝኩት። በመጨረሻው ሳምንት የነበረኝ ድካም ደግሞ የድካሞቼ ሁሉ ሁለት እጥፍ ያህል ነበር የደከመኝ።መነሻዬ ፎንታና ነው። በዚሁ ከተማ ውስጥ ከሪቨርሳይድ ካልፎርኒያ ጭኜ 2140 ማይሎች ርቃ ከአትላንታ በደቡባዊ ምዕራብ በኩል ወደ ምትገኘው ሞንሮይ ጆርጂያ ማክሰኞ ጠዋት በ2፡01 ላይ ደረስኩ። በቀን መቁጠሪያችን መሰረት አንቺ ከመኪና ላይ ከወረድሽ አራት ወራት ሆኖሻል። ምንም እንኳ ቀን መቁጠሪያዎችን አንቺ በየወሩ የምትቀጂ ቢሆንም እኔ በስርዓቱ አጣጥፌ አስቀምጣቸዋለሁ።የስራችንን ሁኔታ በተመለከተ በአንድ ወቅት በእግዚአብሔር ላይ አምጽ ነበር። ይህንን በተመለከተ በአንድ ወቅት ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም ነበርኩ። በነጋታው ደግሞ እቀየራለሁ፤ ልክ በበረት ውስጥ እንደሚበጠብጥ በሬ።

 

በብቸኝት በመንጋ ውስጥ ያለ በሬ ከሰውም ከከብቱም ጋር ሰላም የለውም።ዛሬ በህፃንነት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ የተዋበውን ልብስ ለብሼ ነው በከተማዋ ጎዳና ላይ የማሽከረክረው። የሚታየው ዓለም ተመሳሳይ እብደት ያለበት ነው። ከዚህ እብደት ርቄ መቆየትን እመርጣለሁ። ለእኔ ምርጥ የሆነው ጊዜዬ ከእረፍት ሰዓቴ ማለትም ከሌሊቱ 9 ወይም 10 ሰዓታት ቀደም ብሎ ባለው ከ3-4 ሰዓት የሚሆነው ጊዜ ነው። በነዚህ ሰዓታት ወደ እግዚአብሔር እፀልያለሁ። ይህ ሰዓት አንድ ቀን በስርዓቱ ተጠናቆ ለሌላ አዲስ ቀን መብቃቴን የምገነዘብበት ጊዜ ስለሆነ እውነተኛ ፀሎት አደርጋለሁ። ለማንኛውም ይህ ጊዜ እጅግ የተሻለ እና እጅግ መጥፎም የሆነ ጊዜ ነው። ይህ ጊዜ ከአባታችን ጋር የጉዲፈቻ ሰነዶቻችንን ያጠናቀቅንበት ወቅት ነበር። እነዚያን ሰነዶች ስንፈራረም ቀደም ሲል  የተጓዝንባቸው መንገዶችንም ያስታወስኩበት ጊዜ ነበር። እንኖርበት ዘንድ ግዜያቶችን ሁሉ ያዘጋጀ እግዚአብሔር ነው። እናም ምንም ይሁን ምን የተዘጋጀልንን ግዜያቶችን ልንናፍቅ ይገባል። በጌታ ቃልም “ይህንን ጽዋ ከእናንተ ጋር ልቀምስ፣ ይህንንም ዳቦ ከእናንተ ጋር ልቆርስ እመኝ ነበር” ብሏል። ከላይ እንደጠቀስኩት ያ ጊዜ ጥሩ ነው ያልኩበት ምክንያት ዛሬ ለምኖርበት ኑሮ የተዘጋጀሁበት ጊዜ ስለሆነ ነበር። እናም ይህንን ጽዋ አብረን እናንሳ። ከእምነታችን ማነስ የተነሳ የተሰጠንን ሁሉ መጠቀም በሚገባን ልክ እንዳልተጠቀምን አውቃለሁ። ስላልጠየቅንም ደግሞ እንዳልተሰጠን አውቃለሁ።

 

እናም ከእጃችን መጠቀም እንድንችል እና በውዱ ቦታ ያስቀመጠልንን ወርቅ እንዲያበዛልን ወደ አምላኬ ሁል ጊዜ እፀልያለሁ። ያለፈውን ሳምንት በህመም ነበር ያሳለፍኩት። በመሆኑም ታስታውሺ ከሆነ በአንቺ በኩል መኪና ውስጥ የነበሩትን አብዛኛዎቹን ፎጣዎች ተጠቅሜያለሁ። እግረ-መንገዴንም ስለማትወጃቸውና የተውሻቸውን ለውዝ አግኝቻለሁ፤ ተጠቅሜያለሁም። በዚህም ምክንያት ወለሉ ምን እንደመሰለ ባየሽ! ገላዬን ስታጠብ ልብሶቼንም በዚያው ስለማጥብ ብዙ ገንዘብ አጠራቅሜያለሁ። አሁን ይህንን መልዕክት ወደ መጨረሱ ስደርስ እየጨለመ ነው። ወደ መዳረሻዬም ወደ መድረሱ ነኝ፤ ከመኪናው ላይ እንደማየው 399 ማይሎች ብቻ ነው የቀረኝ። የአካባቢው የሙቀት መጠንም እየተሻሻለ ነው። ባለፈው ወር የነበረው ቃጠሎ ልነግርሽ አልችልም። በአሁኑ ጊዜ በተለይም ምሽት ላይ ያለው ጥሩ ቅዝቃዜ ነው ያለው። አሁን ደግሞ ሌላ ምሽት ለመጓዝ መዘጋጀት አለብኝ።  አሁንም በጣም እወድሻለሁ። ዝግ ብለሽ ተኳኩለሽ ነይልኝ። እናም እንዲህ እያልኩ እዘምራለሁ “ቤኪ አመፀኛ አምፀሽ አትቅሪ ተመልሰሽ ነይልኝ…..”

ኒል

 

 

መስከረም 18, 2000

ጣፋጭ ለሆንከው ለውዴ ኒል

መልእክትህ ሲደርሰኝ እጅግ ተደስቻለሁ። ድምጽህን ቶሎ ቶሎ መስማት እፈልጋለሁ እባክህ ቶሎ ቶሎ ፃፍልኝ፤  እንደዚህ አትቆይ። ድምጽህ ሲርቀኝ ተሰፋ እቆርጣለሁ። እንዲህ ተራርቀን በተለያዩ ቦታዎች ስንኖር ለሁለታችንም በጣም ከባድ ነው። በጣም እወድሃለሁኝ። እንግዲህ ይህን አስቸጋሪና የብቸኝነት ጊዜ በድል መጠናቀቅ እንችል ዘንድ አንተ ፈቃደኛ ከሆንክ ሁሉንም ለመታገስ እኔ ፈቃደኛ ነኝ። ለምን እንዲህ እንደሆነ እግዚአብሔር ያውቃል። ነገር ግን እግዚአብሔር በስራ ላይ ነውና ሁሉንም እንደ ፈቃዱ እንደሚያደርገው አምናለሁ። እኛ ለእርሱ ስንል መስዋዕት እንከፍላለን በምንልበት ጊዜ እርሱ ደግሞ ወዴት እንደሚመራንና ምን አይነት መስዋዕት እንድንከፍል እንደፈቀደ አናውቅም። እናም ለዚህ ለተጠራንበት ታላቅ ጥሪ ፈቃደኛ እና ያለህን ሀሉ ለመስጠት መወሰንህ እጅግ ያኮራኛል፤ ያስደስተኛል። በዚህን ሰዓት የምንሰራቸውን ስራዎች እና የምናከናውንበትን መንገድ ለምን እንደመረጥኩ ታውቃለህ፤ ትረዳለህ። ይህ መረዳትህ ደግሞ ሁል ጊዜ ልቤን ወደ አንተ የበለጠ እንዲጣበቅ አድርጓል። እኔ ለምሰራቸውን ነገሮች ሁሉ በአዎንታ መቀበልህ ለእኔ ምን አይነት ትርጉም እንደምትሰጠኝ ልነግርህ ቃላቶች ያጥሩኛል። ከሰው ልጆች ውስጥ አንተን የሚስተካከል ለመሆኑ ከወዴት ይገኛል? ከሁሉም በላይ ምንም ከባድ ቢሆንም ምንም ዋጋ ቢያስከፍልህም የምታደርጋቸውን እንደ ጌታ ፈቃድ ብቻ እንደምታከናውን አውቃለሁ።

 

በአሁኑ ሰዓት ትምህርት የመከፈቻ ወቅት እንደመሆኑ መጠን የሚከናወኑ ብዙ ነገሮች አሉ። እናም በብዙ ስራዎች ስለተያዝኩ ያለ ዕረፍት ነው የምሰራው። የምትልክልን ገንዘብ ሁሉንም ስለማይሸፍንልኝ ለማብቃቃትና ክፍተት እንዳይፈጠር በማለት እጅግ ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ነው የምጠቀመው። ይህም አንዳንድ ስራዎቻችን የቀድሞ መስማት የተሳናቸውን ሰዎች መመገብን ጨምሮ ሌሎች ተዛማጅ የሆኑ እቅዶቻችንን በመቀነስ ነው። ይህ ካልሆነ የሚቀጥሉትን ሁለት ወይም ሶስት ወራት መዝለቅ አስቸጋሪ ይሆናል።  በቁጠባ ሂሳባችን ውስጥ የሚገኘውን ገንዘብ ሁሉንም ወደ ሊመክዲ አስተላልፌያለሁ። በመሆኑም በሚቀጥለው ሰኞ ለመምህራን ደሞዝ ክፍያ የሚበቃ ገንዘብ አለን። ቶምና ሃያስ ለቤት ኪራይ የሚሆን ገንዘብ ልኮልናል። ይህ እርዳታቸው ይህን አስቸጋሪ ጊዜ ለማለፍ እጅግ ረድቶናል።  ከወንድወሰን ኢሜል አግኝተሃል? በጣም ይወድሃል። እባክህ ኢሜሉ ከደረሰህ በተቻለ መጠን በቶሎ መልስለት። ተስፋ አትቁረጥ ኒል! አንድ ቀን የምትልከው ገንዘብ ሁሉ ምን ላይ እንደዋለ በዓይንህ ስለምታይ በጣም ትደሰትበታለህ፤ ትባረክበታለህ። በጣም እወድሃለሁ።

ቤኪ

 

 

መስከረም 18, 2000

ቤኪ

ጥፍት ላልሽብኝ ፍቅሬ፣ ብቸኛ ለሆንሽልኝ ፍቅሬ፣ መተማመኛ ለሆንሽኝ ፍቅሬ፣ የፍልሚያ ጊዜ አስተማማኝ ጓዴ፤ ገንዘብ ቤቴ እና ብርሃኔ ለሆንሽው ቤኪ ስራ እጅግ ስለበዛብኝ በድካም ተሞልቻለሁ። የሆነ ሆኖ ስተኛም ስሄድም በተቻለኝ መጠን ሁሉ ግባችንን ለማሳካት እየጣርኩኝ ነው። እንደገና ጉዞዬን ለመጀመር ስድስት ሰዓታት ያክል አለኝ። ማጠናቀቅ ያለብኝ 70 ሰዓታት ለመጓዝ ገና ሶስት ቀናት ይቀሩኛል።አሁን ያለሁት ኢዳሆ ሲሆን የምሄደው ወደ ፖርትላንድ ኦሬገን ነው። ቀጥሎ የምሄደው ዋሽንግተን ያኪማ ሲሆን የመጨረሻ ጉዞዬን የማጠናቅቀው ደግሞ በአማሪሎ ቴክሳስ ነው። አሁን ደስተኛ ነኝ ቆይቼ ደግሞ ይከፋኛል ነገር ግን እግዚአብሔርን እወደዋለሁ ልጁንም እንዲሁ። ለእኛ ያለውንም እቅድ እወዳለሁ። ነገር ግን ብዙ ስራ ስለሚበዛብኝ ለእርሱ መስጠት የሚገባኝን ሰዓት ልሰጠው አልቻልኩም።በስተመጨረሻም ልታውቂልኝ የምፈልገው ከስራ ብዛት የተነሳ ተስፋ ቆርጬ እንጂ ጠፍቼ እንዳልሆነ ነው። እወድሻለሁ!

ኒል

 

 

መስከረም 23, 2000

ቤኪ

በሕልም ውስጥ ሆኜ ከ15 እስከ 30 የሚሆኑ ሰዎች ምግብ ለመመገብ ተሰብስበው አየሁ።  እኔ ባለሁበት ጠረጴዛ ዙሪያ እንዲሁ 4 ሰዎች ነበሩ። በዚያ ስፍራ የነበሩት ጠረጴዛዎች 4 ሰዎች ተዝናንተው ሊስተናገዱበት የሚችሉ ዓይነት ጠረጴዛዎች ናቸው። የሚቀርበውም ምግብ ደህና ምግብ ነበር። ከእኔ ጋር የነበሩ ሰዎች መልካም ሰዎች ነበሩ። እናም ሁላችን እየተጫወትን ነበር ምግባችንን በጥሩ ሁኔታ የተመገብነው።መልከ መልካም የሆነች ሴት ከእኔ ትይዩ ተቀምጣለች። ሁኔታዋ በእጅጉ ስለሳበኝ በትኩረት እመለከታት ነበር። ምን እንደሆነ በትክክል አልተገለጠልኝም እንጂ የሆነ ነገሯ ትኩረቴን ሁሉ ተቆጣጥሯል። ስለዚህ ጉዳይ በጥልቀት እያሰብኩ እያለሁ ወደኋላዬ ደገፍ እንዳልኩ የያዝኩትን ምግብ እና በእጄ የነበረው ሹካ ወደቀብኝ። በዚህን ግዜ አይኖቼን አፍጥጨ ስመለከት ያቺ ሴት አንቺ፣ ርብቃ፣ ውዷ ፍቅሬ ነበርሽ። ወዲያው በፍጥነት መጥተሽ ከወደቅኩበት ደግፈሸ አስነሳሽኝ። ወዲያውም እነዚያን ውብ እጆችሽን በአንገቴ ዙሪያ አድርገሽ አጽናናሽኝ። ከዚያም ምግባችንን እየበላን ወደ ማብቃቱ እየተቃረብን እያለን አንቺ ከጓደኝነትም በላይ መሆንሽን ተገነዘብኩ። እወድሻለሁ!

ኒልመስከረም 23, 2000

ቤኪ

ምናልባት ቀጥሎ ያለውን ጉዞዬን ካላዘገዩ በስተቀር  5524 ማይሎችን የማጠናቅቀው በሚቀጥለው መቆምያዬ ላይ ነው። ከዚህ የምትገነዘቢው ጠንከር ብዬ እየሰራሁ መሆኔንና ጭነቶችም ቶሎ ቶሎ እየተራገፉ መሆኑን ነው። በተለይም ጭነቶችን የሚያራግፉ አስጫኞች ብቻቸውን ለሚሰሩ ሾፌሮች ቅድሚያ ይሰጣሉ።  ባለፈው ሳምንት ቶሚ የመሰከረልኝም ይህንኑ እውነታ ነው። እርሱ እንደ ነገረኝ ከሆነ በተለየ ሁኔታ ስራዎቻችንን እያከናወንን የምንገኘው እኔና አንድ ሌላ ሾፌር መሆናችንን ነግሮኛል። ሌሎች በተለየ ሁኔታ የሚሰሩ ሰዎች ተቀጣሪ ሾፌሮች ሳይሆኑ የመኪናው ባለንብረት ለይቷል። እናም ቤኪ አንቺ ከሄድሽ ወዲህ ብዙ ነገሮች ተቀያይረዋል።

 ኒል

 

 

መስከረም 30, 2000

ለውድ ፍቅሬ

እኔ እንደማስበው ከሆነ እዚህ አሜሪካ ውስጥ ባሉት ጥቂት ሰዎች ሁኔታ የተደስትሽ አይመስለኝም። ለዚህም ይሆናል እዚያ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚወዱሽ ጓደኞችሽ ጋር መቆየትን የመረጥሽው። ልክ ነሽ። አልፈርድብሽም፤ እኔም ቢሆን ተመሳሳይ ስሜቶች ይኖረኝ ይሆናል። ዛሬ ጠዋት ከከባድ ድካሜ በግድ ነበር የተነሳሁት። ባለፈው በዎልማርት ጭነት ሳራግፍ አራት ሰዓታት ብቻ ነበር የተኛሁት። ከ26 ሰዓታት በኋላ የነበረብኝ ድካም ልነግርሽ አልችልም። ትላንትና ቻታኑጋ ነበርኩ፤ ከአራት ጊዜ የመቀስቀሻ ድምጽ በኋላ ነበር የተነሳሁት። ቶሚ እንደነገረኝ ከሆነ ረጅም ሰዓት የመንዳቴ ጉዳይ ስለገባቸው ቻታኑጋ በደረስኩ ከሶስት ሰዓታት በኋላ መኪናው ይጠገን በማለት እንዳርፍ ያደረጉት። ከዚያም ጥቂት ቆይተው ተፈራርሞ ያለቀ ሰነዶችን ስለሚሰጡኝ በተቻለኝ ፍጥነት መውጣት እችላለሁ ማለት ነው። መኪናው ተጠግኖ እንዳለቀ የሚኖረኝ ጭነት ወደ ኒውዮርክ የሚወሰድ ነው።  አሁን እዚህ ከ4-5 ሰዓታት ስለነበሩኝ ወደ መኝታ የሄድኩት ቀደም ብዬ ነበር። እናም ምንም እንኳ ብዙ ብተኛም ጥሩ ቀን አልነበረኝም፤ ድካምም አለቀቀኝም። አንቺም እኔ በምሰራው መልኩ በመስራት ልታግዥኝ ይገባል። ምክንያቱም እኔ የምሰራውንና ጠንክሬ መስራቴን አልቀየርኩምና። ለነገሩ አንቺ ምንም ብትሰሪ እኔ የምሰራውን ሊቀይረው አይችልም። የተወሰነ ገንዘብ እንድቆጥብ ልትፈቅጂልኝ ይገባል። ወይም ጠንክሬ እንድሰራ ልታግዢኝ ይገባል።

 

በዚህ ሰዓት በመሰጠት ነው እየሰራሁ ያለሁት። እንግዲህ ከእኔ ጋር መቆም ከፈለግሽ አንቺም እንዲሁ በመሰጠት መስራት አለብሽ። ዛሬ አብዛኛውን ቀኔን በእንቅልፍ ነው ያሳለፍኩት። የነገ ድካም ደግሞ የበዛ ይሆን ይሆናል ነገር ግን ከስራ ብዛት አይሆንም፤ ዛሬ ካለልክ ከመተኛት ከሚመጣ የአዕምሮ ወቀሳ ግን ይሆናል። እንደ ማንኛውም ክርስቲያን ሁሉ የወንድወሰን ባለቤት ብዙ ስራ እንዳለባት ንገሪያት። ታላቁን ተልዕኮ የሚፈጽም ማንኛውም ክርስቲያን ብዙ ስራዎች አለበት።ዎልማርት ብዙ ትምህርት ነው የሰጠኝ። ሰውነቴን ማስተማር ያለብኝ ይመስልሻል? ወይም ሰውነቴ ያስተማረኝ ነገር ያለው ይመስልሻል? ለማንኛውም ትምህርቱ ከየትኛውም ይምጣ ውጤቱን መቋቋም የምችል አይመስለኝም። ማድረግ ያለብኝን ሁሉ ግን አደርጋለሁ። ጭነቶቹ ባለፉት 2-3 ሳምንታት ተጠናቀዋል። ስለዚህ አብረን ብንሆን ኖሮ ልክ ሽርሽር የሄድን ያክል እንቆጥረውና ብዙ ገንዘብም እንቆጥብ ነበር። ሰ.ዓ.ት የሚሉትን ፊደላት በማነብበት ጊዜ ሁል ጊዜ አቋራጩን መንገድ ነበር የምፈልገው፤ ምክንያቱም ፈጥኜ አንድ እርምጃ ወደ ፊት መራመድ ስለምፈልግ። ልቤ ባለሽበት ሀገር ያለሽው ከመስማት የተሳናቸው ወገኖች ጋር ነው። አንቺም መስማት የተሳነሽ ነሽ፤ እኔም መስማት የተሳነኝ ነኝ። ይህ ደግሞ መልካም ነገር ነው። በር ለመክፈት በምንይዝበት ጊዜ በትክክል የማንይዝ ከሆነ በትክክል አይከፈትምም አይዘጋምም።

 

በትክክል የማይዘጋ ከሆነ ደግሞ ክረምት ሲመጣ ጉንዳኖችና አቧራ ይገባበታል። በክረምት ደግሞ በዚያው አቧራና ጉንዳን በገባበት በረዶ ይገባል። በተመሳሳይ መልኩ የልባችንንም በር በትክክል ካልያዝን እርኩስ መንፈስ ይገባበትና መላ ህይወታችንን ያጠፋልና ያወድማል። መጽሐፈ ኢያሱ 24፡15። ይህንን ሰባኪው እንደ ተናገረው ነው የነገርኩሽ። ነገር ግን እኔም እውነት እንደሆነ አምናለሁ፡፡ በቴሌቪዥን ከሚተላለፉት ሌሎች ነገሮች ይልቅ ይህንን ማዳመጥ እመርጣለሁ። በዚህ ጉዳይ ላይ ሰፋ አድርጌ ስላልፃፍኩልሽ ውስጤ ጥሩ አልተሰማኝም። በዚህ ምድራችን ውስጥ ብዙ ሰዎች አሉ ነገር ግን እንደ አንቺ በፍቅር የተሞላ ልብ ያላቸው በጣም ጥቂቶች ናቸው። አንቺን የሰጠኝን እግዚአብሔር እጅግ አድርጌ አመሰግነዋለሁ። ምንም ያህል በአካል ብንራራቅም በጣም ደግሞ የተቀራረብን ነን። ተስፋ የቆረጥን ብንሆንም የተጣልን ግን አይደለንም። ብዙ ልንሰራ የጠየቅን ቢሆንም በቂ የሆነውን የተሰጠነው ነን። ምክንያቱን ባላውቅም እግዚአብሔር በሚከፍታቸውና በሚዘጋቸው በሮች ውስጥ መመልከት አልቻልንም። ምናልበትም የእምነታችን ደረጃ ሊሆን ይችል። በዚህ ረገድ የሆነ ቀን አንድ እርምጃ ወደፊት እንራመዳለን።  ወደኋላችን ስንመለከት እግዚአብሔር እንዴት እንደመራን፣ በምን መልኩ እንዴት እንደመራን ወዴት እንዳደረሰን እንረዳለን። ወደፊታችን ስንመለከት ደግሞ እግዚአብሔር እንዴት እንደሚመራን ልንረዳ አንችልም። ነገር ግን በእግዚአብሔር መንፈስ እየተመራን በየቀኑ በትክክለኛ አቅጣጫ አንድ እርምጃ ወደፊት እንራመዳለን።

 

ስለዚህም እምነታችንን ለማጠንከር ወደኋላችን መመልከት ተገቢ ይሆናል። ያለ ስራና ስራ የፈታን ሲመስለን ማድረግ ያለብን ወደኋላችን መመልከትና እምነታችንን መፈተሽ ነው። ወደ ከፍታ የምናደርገውን ፍጥነት ለመጨመር ይህን ማድረግ አለብን። ሊከፈትልን የሚገባውንም በር ለማፋጠንም፤ መዘጋት የለበትንም በር በቶሎ ለመዝጋት ይህንን ማድረግ አለብን። ከዚህም በተጨማሪ ጌታ ኢየሱስ በገባልን ቃል መሰረት መጠቀም ያለብንንም ለመጠቀም ያሳለፍነውን መለስ ብለን መመልከት ጠቃሚ ነው። በእርግጥ ጌታ ሁሉንም ፈጽሞ አድርጎታል።  ነገር ግን በየቀኑ እንደቃሉ ለመኖርና ለመስራት በየዕለቱ መወሰን አለብኝ። በየዕለቱ በእምነት እርምጃ መውሰድ አለብን። ባለሽበት ሁኔታ እያደረግሽ ባለሽው ጉዳይ ላይ ትክክል ትሆኚ ይሆናል። የእኔን ከአንቺ ጋር ሳነፃጽርም ለመገንዘብ ቀላል ይሆናል። ነገር ግን ልረሳ የማልችለው ውድ ጊዜዬን ፈሰስ ያደጉበት ነው። ከዚህም በተጨማሪ በአካል ሳይሆን በእምነት ሆኜ የማፈቅራቸውን ነገሮች የማይበት ወቅት ነው። እወድሻለሁ!

ኒልጥቅምት 6, 2000

ቤኪ

በዚያ ስራ ቶሚ የራሱ ቡድን እንዳለውና ቡድኑንም እንደማይተው እንዲሁም ለእኛ የሚሰጥ ሌላ ጥሩ ስራም እንዳለ አጫውቶኛል። ስለዚህ እንደማስበው ከሆነ ቶሚ እኛን ስለሚወደንና ስለሚመካብን ጥሩ ነገር የሚሰራልን ይመስለኛል።  መነሳት ካለባቸው ጭነቶች ውስጥ ግማሽ ያህሉ ተነስቷል። ግማሽ ያህሉ ገና የሚቀር ስለሆነና ቶሚም እዚያው ስላለ መልካም ሁኔታዎች ይገጥሙናል።  በዚህ ተመሳሳይ ስራ ላይ ቶሚ ወደ ቻታኑጋ መምጣት ከፈለገ እና እየሰራን እያለን ሌላ ሀይል ሊጨምር እንደሚችል ነግሮኛል። በአሜሪካ የከባድ መኪናዎች ማቆሚያ የቀን መቁጠሪያ መሰረት አንቺ ከሄድሽ አሁን 5 ወር ሆኗል። እናም እንደ ልማድሸ አሮጌዎቹን እንድትቀጂያቸው እየጠበኩሽ ነው። ዛሬ ጠዋት አንድ 16 ሳንቲሞች የያዘ ከቆዳ የተሰራ መያዥያ አግኝቻለሁ።  አሁን ያለሁት ጆርጂያ ውስጥ ዳሎታ ከተማ ነው። እኔ የማስበው የሚቀጥለው ስራዬ ከታኔል ሂል ወደ ዴንቨር እንዲሆን ነው። ቀሪውን ታሪክ አንቺም ታውቂያለሽ። እወድሻለሁ!

ኒል

 

 

ጥቅምት 8, 2000

ኒል

አንተ ከማንም በላይ የምወደው ወንድ ነህ፤ እንደገና ላይህና ላቅፍህ የምናፍቅ ውዴ ነህ። ልገልጸው በማልችለው መልኩ ከልቤ በፍቅርህ ወድቄያለሁ። በቶሎ ላገኝህ ጓጉቻለሁ። ከአንተ መልዕክት ማግኘቴን ከኢንተርኔት ላይ አስሰህ መልስ የመስጠቱ ሀላፊነት ነው ብዬ ነበር። ነገር ግን አንተ ፃፍክልኝ አልፃፍክልኝ ሳልል ዝም ብዬ መፃፍ ነበረብኝና ባለመፃፌ ይቅርታ! ከአሁን ሰዓት ጀምሬ በሰላም እስክንገናኝ ድረስ ዘወትር እፅፍልሃለሁ። ነገር ግን የፃፍኳቸውን ኢሜሎች ሁሉንም ያገኘህ አልመሰለኝም። እዚህ እየሆነ ያለውን ሁሉንም እንድታውቅ በማሰብ ረጃጅም ኢሜሎችም ፅፌልሃለሁ። ይህም በዚህን ሰዓት ለምን እዚህ ኢትዮዽያ ውስጥ እንደሆንኩ በደንብ እንድትገነዘብ ያግዝሃል። እንዲሁም ግልባጩን ዳግም እልክልሃለሁ። ቶሎ ለመመለስ እንድችል ብዬ መስማት የተሳናቸውን እንዲፀልዩልኝ ነግሬያቸው ወዲያው ደግሞ የቶሚን መረጃ እንደ ነገርከኝ የፃፍኩልህ ኢሜል ደርሶሃል? በዚያ ኢሜል ውስጥ የኢትዮዽያ አየር መንገድ የሼባ ማይሎችን እንዳጠራቅም እንዳሳወቀኝ ፅፌልህ ነበር። ይህም በቀላሉ እንድመለስ የሚያግዘኝ ነው። ለማንኛውም ይህንን በተመለከተ እርግጠኛ አይደለሁም።

 

ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት ዳይሬክተራችን ሞላን በተመለከተ ተስፋ የሚያስቆርጥ ሁኔታ እየገጠመኝ ነው። ስለዚህም በገዛ ፍቃዱ ስራውን እንዲለቅ ለማድርግ እየጣርኩ ነው። የምናባርረው ከሆነ ያልሰራበትን የሁለት ወራት ደሞዝ ልንከፍለው ነው። ይህን ገንዘብ ደግሞ የለንም። እኔና ኩቢ ደግሞ በሁሉም ጉዳዮች ላይ የምንጨቃጨቅ ስለሆነ በስራ ላይ ባለን ግንኙነታችን ላይ እንቅፋቶች እየተፈጠረ ነው። በዚህ ሁሉ ሂደት ውስጥ ደግሞ በቂ ስልጠናና ለቦታው አስፈላጊ የሆነ መቅጠር የሚገባን ሰው እያገኘን ነው። ነገር ግን በቂ በጀት እስክናገኝ ድረስ ልቀጥረው አልችልም። ምናልባት ሞላ ከለቀቀ ልንቀጥረው እንችላለን። ይህ ደግሞ ወደ አንተ ለመመለስም ምቹ ሁኔታ ይፈጥርልኛል።  ስለዚህ ኒል ትንሸ ጊዜ ደግሞ ታገስ። እግዚአብሔር ሁሉን ነገር ጨርሶ ያውቃል። በጣም ከጥልቁ ልቤ እወድሃለሁ። እዚህ ማጠናቀቅ ያለብኝ የድርሻዬ የሆነ ስራ የማከናውንበት ጠቃሚ ጊዜ ነው። እወድሃለሁ!

ቤኪጥቅምት 9, 2000

ውድ የሆንክ ፍቅሬ ኒል

እንደምን አለህ? ከባለፈው ኢሜልህ ወዲህ ስለ አንተ እየተጨነቅሁ ነው። በጣም ተሰፋ እንደቆረጥክና እንደ ደካከመህ ተረድቻለሁ። እንዴት እንደማፅናናህ አላውቅም። በዚህን ሰዓት ምን ማድረግ እንዳለብኝም ማወቅ አልቻልኩም። በእውነት ጥሩ እየተሰማኝ አይደለም። ትላንትና እግዚአብሔር እያደረገ ያለውን ለመረዳት ከቦታ ቦታ በእግሬ በመንቀሳቀስ እያሰብኩ ነበር ያሳለፍኩት። ለመስማት የተሳናቸው ልጆች እዚህ መሆን የሚገባኝ ጠቃሚው ሰዓት አሁን ነው። እናም ቶሎ መሄድ ያለብኝ ሰዓት ላይ አይደለሁም፡፡ አለበለዚያ እዚህ በመሆኔ የምቆጣጠራቸው ጉዳዮች በአንዳፍታ ይበላሻሉ። እነዚህን ነገሮች በጥልቀት ብታውቅ ኖሮ ለማድረግ የምጥረውን ሁሉ ትረዳ ነበር። ጉዳዩ የምርጫ ጉዳይ አይደለም። የምወደው ቦታ ለመሆን መርጨ ከአሜሪካ የመራቅ ጉዳይ አይደለም። ጉዳዩ ከዚያም በላይ ጥልቀት ያለው ነው። ጉዳዩ ለትምህርት ቤታችን ስኬት ጥሩ አካባቢ እንዲፈጠር የማድረግ መንፈሳዊ ስራ ነው። ባለፈው ዓመት ከአንተ ጋር በነበርኩበት ጊዜ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ስራዎች ተዘንግተው ነበር። ያ ደግሞ የኩቢ ጥፋትም አይደለም። ሞላ እንዴት መምራት ስለማያውቅ እርሱ የፈጠረው ችግር ነበር። ከዚህ ጋር በተያያዘ ሰራተኞችም ስነ ምግባር ጎድሏቸዋል። ኩቢ ተጠምዶ የነበረው በሌሎች ጉዳዮች እንደ ፋይናንስ፣ በጀት ለማፈላለግ ሰነድ ማዘጋጀት፣ ሪፖርት መፃፍና ሌሎች መንግስትን የሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ነው።

 

እነዚህ ተዘነጉ ያልኩህ ውዝግብ ያለባቸው ጉዳዮች ስለነበሩ ሊነካቸው አልፈለገም። ወደዚህ ወደ ኢትዮጵያ እንደተመለስኩም እኔም ወደ እነዚህ ጉዳዮች አልተመለከትኩም ነበር፡፡ ምክንያቱም አብዛኛውን ጊዜዬን ወስዶ የነበረው በጀት የማፈላለጉ ጉዳይ ነበርና። ከስድስት ሳምንታት በፊት ኩቢ እነዚህን ነገሮች መፍታት እንዳለብኝ በማሰብ ሁኔታዎችን ነግሮኝ ስለ ነበረ ሰራተኞችን ዳግም ወደ ስራ ለመመለስ ሌላ 6 ሳምንታትን ነበር የወሰደብኝ። የችግሩ ዋና የነበረው ሰራተኞች በሙሉ ጊዜያቸው ወደ ስራ አይመጡም ነበር። እንደምክንያት የተወሰደውም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስላልተከፈተ ነበር። ከሁሉም በላይ ግን ስራን በተለየ ሁኔታ ሊያሰራ የሚያስችል የተለየ ፕሮግራም ስላልተፈጠረ ነው። መጥፎና ጠቃሚ የሆኑ ባሕሪያትም በሰራተኞች መካከል ተፈጥረው ስለነበር ለእነዚህም በትክክል ተጠያቂ የሚሆነውን አካል ተጠያቂ የሚያደርግ ስላልነበረም ጭምር ነው። በየቀኑ ሙሉ ቀን እዚህ የሚውል ሰው ቢኖር ኩቢ ብቻ ነው። እርሱ ደግሞ ስራውን በተገቢው ሁኔታ እየተወጣ ነበር። በእዚህ ጉዳዮች ጣልቃ ለመግባት ሞክሮ ቢሆን ኖሮ ለራሱም መስራት አይችልም ነበር። እናም ይህንን ሁሉ እንደተረዳሁ በጣም ነበር የተበሳጨሁት፡፡ በተለይም ለአንተ ስል። አንተ ተቸግረህ የምትልከውን ገንዘብ በትክክል ላልሰራ ሰው ሙሉ ክፍያ ስከፍለው ያበሳጫል። ይህ ደግሞ ገንዘባችንን ያለአግባብ ባልተገባ ቦታ መበተን ነው።

 

በዚህ ሰዓት እዚህ እንዲሆን እግዚአብሔር የመረጠው እነዚህን ነገሮች ለማስተካከል ነው ብዬ አምናለሁ። ሰራተኞች ሙሉ ቀን እንዲሰሩና መስማት የተሳናቸው ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተለያዩ ፕሮግራሞችን እየተገበርኩኝ ነው። ዳይሬክተሩ የፃፋቸውን እና በባህላቸው ምክንያት የተፈጠሩትን መጥፎ ልማድ ለማስተካከል ግዜ ወስዶብኛል። እንግዲህ ነገሮችን ለማስተካከልና ሞላን ደግሞ በእሳት ላይ መጣድ የእኔ ድርሻ ይሆናል። መጥፎ ልማዶች በአንዲት ጀምበር ሊጠፉ አይችሉም።  ስለዚህ ይህንን ፕሮግራም በቦታው መመለስና በደንብ መሬት ለማስያዝ ትንሽ ጊዜ በቅርበት መከታተል ያስፈልጋል። አለበለዚያ እስከ አሁን የደከምኩበት ሁሉ ከንቱ ይሆናል። ምንም እንኳ ለሌላ ችግር የሚሰጠን ቢሆንም ሞላን ማሰናበት ያለብን ይመስለኛል።  ሞላ ምንም ጥፋት የለብኝም ይላል ነገር ግን እኔና ኩቢ እርሱ በሚናገራቸው ልናምን አልቻልንም። ከመምህራን ጋር ደግሞ ብዙ አስቸጋሪ ነገሮች ከፊት ለፊታችን እንዳሉ በግልጽ ይታያሉ። ይህንን የፈጠረው ይህ ሰው ነውና ማስተካከል ይገባል።ስለዚህ ከአሜሪካ ይልቅ እዚህ እንድሆን እግዚአብሔር የመረጠው ለአላማ ነው ያልኩት ለዚህ ነው። በዚህ ሰዓት እዚህ መሆን የሚያስፈልገኝ ሌሎች ምክንያቶችም አሉ። ከእነዚህም አንዱ በገንዘብ ሊረዱን የሚችሉ አቅም ያለቸው መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ቀደም ሲል ማነጋገር ጀምሬ ነበር። እነዚህንም በቅርበት በመከታተል ሁኔታዎችን ከዳር ማድረስ ያስፈልጋል።

 

በእነዚህ ቅርብ ቀናት እነዚህን ድርጅቶች ማነጋገር አስፈላጊ እንደሆነ ተነግሮኛል፤ ኩቢ በራሱ የሰራቸው ብዙ ነገሮች አሉ ነገር ግን አሁን በአንዳንድ ነገሮች ባግዘው ሁኔታዎች በፍጥነት እንዲከናወኑ ይረዳል። ስለዚህ የትምህርት ቤቱንና የበጀት ማፈላለጉን ስራዎች ሁለቱንም እየሰራሁኝ እገኛለሁ። ካስታወስክ ወደዚህ ለመመለስ ያሰብኩት ባለፈው ወር ነበር። ነገር ግን ወደዚህ የመመለሻ ትኬት መግዣ ገንዘብ አልበረኝም። የኔን ደግሞ እግዚአብሔር እዚህ እንድቆይ እኔን ያደረገበት መንገድ ነው ብዬ ወስጃለሁ። እንዲያውም በዚህ ሰዓት እዚህ ብትሆን መልካም ነበር ብዬ አስባለሁ። ለት/ቤት የሚሆነንን በረከት እግዚአብሔር ለምን እንደሚያዘገይብን አልገባኝም። የከባድ መኪና ልምዴን መድገም አልፈልግም ምናልባት ከእግዚአብሔር ካልሆነ በስተቀር። በሌላ መልኩ ደግሞ ት/ቤታችን እያደገ የስራ ማስኬጃ በጀት እጥረት ደግሞ የማያቋርጥ ተደጋጋሚ በሽታ ሆኗል። እኛ ደግሞ በኢትዮዽያ ውስጥ መስማት ለተሳናቸው የተሻለ ትምህርት ለመስጠት የተሻልን ሰዎች ሆነናል። መለያ ስማችን የሆነው ሊመክዲ የጥራት ምልክት በመሆን እየታወቅን ነው። እናም ለእግዚአብሔር ክብር የጀመርነውን ስራ እግዚአብሔር በሚፈቅደው መንገድ መጨረስ አለብን።  እንደደከመህና ተስፋ እንደ ቆረጥክ ይገባኛል ኒል። እዚህ ያለውን ስራ አጠቃላይ ጫናው በአንተ ላይ እንዳለ ግልጽ ነው። እኔ ከአንተ ጋር በስራ ላይ ስለሌለሁ ሁሉንም ብቻህን እንዴት እንደ ቻልክ ማንም ሊረዳው አይችልም።

 

ይህ ሁሉ ብቸኝነት እንዲሰማህና ተስፋ እንዴት እንደሚያስቆርጥ እረዳለሁ። እባክህ እግዚአብሔርን በመታመን በያዝከው መንገድ ጠንክረህ ቀጥል! ሽልማታችን በሰማይ መሆኑንም አትርሳ። ዘለዓለማዊውንም ሀገር አትርሳ! እኔንም ደግሞ እመነኝ። እዚህ ያለሁት ስለሚሻለኝ እና ለራሴ ምቾት ሳይሆን የጀመርኩትን ለመጨረስ ስለምፈልግ ብቻ ነው። ይህ ችግር ደግሞ በአግባቡ ካልተቋጨ ለወደፊቱ ለከባድ ችግር ይዳርገናል። እወድሃለሁ ኒል። ከሁሉም በላይ ደግሞ በጋራ መሆናችንን እፈልገዋለሁ። ቀን ቀን በት/ቤቱ ውስጥ ከሰራተኞች ጋር እሆናለሁ ሁሉም ስራቸውን ጨርሰው ወደ ቤታቸው ሲሄዱ ግን በብቸኝነት ተውጬ አንተኑ በናፍቆት ወደ ማሰላሰሉ እገባለሁ። ከንጋት በፊት ያለውን ጭለማውን የንጋትን ክፍል አስታውስ።  እኛ መያዝ ከምንችለው በላይ አይሰጠንም። በችግራችን ግን መውጫውን በቃል ኪዳኑ ሰጥቶናል። ይህንን ማመን አለብህ ኒል። ይህንን ጊዜህን የበለጠ ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ ተጠቀምበት። ይህንን ለማድረግ መልካም አጋጣሚዎች አሉ። እስኪ ሁሉ ነገርህ እንዲሆን አድርግ። ከዚህ ጭንቅ ከሆነ ጊዜ ሊያወጣህ ይችላል። እዚህ ያለን ሁላችን ስለ አንተ እንፀልይልሃለን። ሁሉም ስለአንተ ያስባል እኔም በቶሎ ወደ አንተ እንድመለስ እና እንዳይህ ይፈልጋሉ። በዚህ ውስጥ ሁሉ የጌታ ፈቃድ ለመፈፀም እየሞከርኩኝ ነው። እባክህ ኒል ተስፋ አትቁረጥ አንተን በተመለከተ እዚህም እዚያም ሁኔታዎች አልተለወጡም እያልክ ነው። ነገር ግን እግዚአብሔርን በመተማመን ትንሽ ጊዜ ታገስ ይለወጣሉ። እግዚአብሔርም ያደርገዋል። በጣም እወድሃለሁ!

ቤኪ

 

 

ጥቅምት 9, 2000

ቤኪ

ወደ መኪናዬ በተመለስኩ ቁጥር የመጀመሪያ ስራዬ ማስታወሻ እንደላክሽልኝ ማረጋገጥ ነው። መልዕክቶችሽ ለእኔ ጣፋጭ ናቸው። አንዳንድ ጊዜ ቦታ ሳልመርጥ መልዕክቶሽን ካነበብኩ በኋላ እጮሃለሁ። መልዕክቶችሽ ምን? መቼ? የሚሉትን ሀሳቦች የሚነግሩኝ ናቸው። እናም መልዕክቶችሽ በየዕለቱ የሚያበረቱኝ የብርታት ምንጮቼ ናቸው። ለዕለቱ የሚሆኑኝ ምንም መልዕክት፣ ደህና መሆንሽን የሚነግሩኝ መልዕክት ካላገኘሁ ደግሞ  በዚያን ቀን ጥሩ ሀሳብና አመለካከት ሳይኖረኝ እውላለሁ። እንዲህ ከሆነ በአንቺ ዘንድ ቦታ እንደሌለኝ ወይም ለእኔ ከመፃፍና እና ለእኔ ቦታ ከመስጠት የበለጠ ጉዳይ እንዳለሽ ስቆጥር እውላለሁ። መለስ ብዬ ደግሞ የማስበው እኔ ስላልፃፍኩላት ነው፤ መውደዴን ስላልፀፍኩላት፣ በየቀኑ ያለ እረፍት እንደምወዳት ስላልነገርኳት ነው በማለት ወደ ራሴ እመለሳለሁ። ከማንኛውም ነገር በላይ በአብዛኛው ቀኑን ሙሉ የማስበው አንቺን ነው። በየሌሊቱም ስራዬ ብዬ ስለአንቺ ብቻ ለማሰብ እነቃለሁ። ስለ አንቺ አስባለሁ ቀጥሎም ከሀሳቤ ሳርፍ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ ምክንያቱም ስለ ጠብቀኝ። ይህ በየሌሊቱ መደበኛ ስራዬ ነው። ሲነጋ ደግሞ የአንተው ነኝ፣ ላይህ እናፍቃለሁ የሚለውን ሀሳብሽን አገኝ እንደሆነ እመለከታለሁ። ይህ ደግሞ የዕለቱ ስንቅ ሆኖ ይውላል ይመሻል። መልዕክቶሽን የምፈልገው ለዚህ ነው፡ የተወደድኩ መሆኔን የአንቺ ብቸኛ ሰው መሆኔን እንደነገርሽኝ ለማየት። ከአድናቆት ጋር እወድሻሁ!

ኒል

 

 

ጥቅምት 20, 2000

ቤኪ

ታሪኩ ይህ ነው። ከዳልተን ወደ ዋሽንግተን ኬንት ከተማ ረጂም ጉዞ ላይ መድበውኛል። ጭነቱን ለመጫንም በቂ ጊዜ ሰጥተውኛል። አርብ ማታ ደግሞ የትራፊክ ፍሰቱ የተጨናነቀ ይሆናል። ስለዚህ ለ15 ደቂቃ ያክል ጉዞዬ እንደሚዘገይ አውቃለሁ። ነገር ግን አቅጣጫው በጣም ጥሩ አይደለም፤ የመውጫ መንገዶችም የሌሉ በመሆናቸው 1 ሰዓት ያክል መዘግየቴ የማይቀር ነው። ትንሽ ቆይቶ አስጫኙ ድርጅት ይህ ጭነት መዳረሻው ኬንት አይደለም አለ። ከአንድ ሰዓት ተኩል በኋላ ኮቨናንት የጭነት ማመላለሻ ድርጅት በበኩሉ ደግሞ ጭነቱ ሚደርሰው በ26 ደቂቃዎች ርቀት ላይ ነው ብሏል።  ከዚህ ሁሉ እስጥ አገባ በኋላ 4 ሰዓት ዘግይቼ ጭነቱን ለመጫን በቃሁ። አስጫኚው ድርጅት በወቅቱ ማድረስ እስከ ቻልኩ ድረስ ለመጫን መዘግየቱ ችግር የሌለው መሆኑን ነግሮኛል።  ከዚያም ጭነቱን ይዤ ከ19 ሰዓታት በኋላ  ይኸው ካልፎርኒያ ውስጥ ትሬሲ ከተማ ውስጥ ለማስረከብ ተዘጋጅቻለሁ። በእርግጥ የማስርከቢያ ሰዓቱ ረፍዷል። ይህን መኪና በምረክብበት ጊዜ የጭቃ መከላከያ አልነበረውም። ነገር ግን ከመኪና ማቆሚያ ውስጥ ያገኘሁትን አንድ ገጥሜለታለሁ። ምናልባት የሆነ ሰው የጣለው ይመስለኛል። ትላንትና አንድ ሌላ እየፈለኩኝ ነበር። ዛሬ ደግሞ አንድ በማግኘቴ ደስ ብሎኛል። በጣም እንደናፈቅሽኝ ስትነግሪኝ እንዲያው እፎይ አልኩ ምክንያቱም ማወቅ የማልችለውን ህይወት ይኖርሽ ይሆናል። ያለሽን ህይወት ይዘሽ ደግሞ ያለሽው እጅግ ሩቅ በሆነ ሀገር ውስጥ ነው። ነገር ግን እንደ እኔው ሁሉ ባዶ እግርሽን ሆነሽ ሀሳብ አርግዘሽ ነው ያለሽው። ምናልባት በቂ ገንዘብ ሲኖርሽ ትመጭያለሽ፤ በዛን ጊዜ ብዙ ጥያቄዎች ይኖሩኛል ምናልባትም በጥያቄዎቼ እፈትንሽ ይሆናል። አንቺ የምትሰሪውን ስራ መደገፍ ደስም ይላል፤ ጉዳትም አለው።

 

ለማንኛውም ሁል ጊዜ ብፈለግ ደስ ይለኛል። ባለፈው ወር ውስጥ መኪናዬ ጋራጅ ውስጥ የቆመው 4 ጊዜ ነበር። በመጨረሻም ችግሩ የተገኘው ቴክሳስ ውስጥ በአማሪሎ ነበር። ችግሩ በ5ኛ ኢንጄክተር ላይ ነበር። ተመሳሳይ ችግር በቀደሙ መኪና ላይም ተከስቶ ነበር። ሁለት ቦታ ላይ በርካሽ ስለ አገኘሁት ብዙ ድንች በልቻለሁ። አንደኛው ማቀዝቀዣ አሁን ድርስ ግማሽ ያህል የያዘው ይህንኑ ድንች ነው። ብዙ ፍሪቶስ እና ዶሪቶ ሳንዱች አሉኝ። አንድ ቀን በኮሎራዶ ውስጥ ስነዳ አልፎ አልፎ ዷ ዷ ዷ የሚል ድምጽ ሰማሁ። ቀስ ብዬ ሳዳምጥ በኮሎራዶ ከፍታ ቦታ ምክንያት የታሸጉ ከረጢቶች ሲፈነዱ መሆኑን ተገነዘብኩ። ትንሹ ውሻ ትልቁን አጋዘን ሲያባርር አይተሽ የነገርሽኝ ታሪክ አስታወሰኝ። እነዚያ ሁሉ ድምፆች ከዬት እንደሚመጡ ቶሎ መለየት ባለመቻሌ ደካማነቴን አሳይቶኛል። በጣም አወድሻለሁ። ከነበርኩበት የበለጠ በስራ ተይዣለሁ።  ሌላው ቀርቶ እሁድና ቅዳሜ እንኳ የማርፍ አይመስለኝም። እያንዳንዱ ቀን በስራ የተያዘ ተከታይ ቀን አለው። እሁድ ይሁን ቅዳሜ የትኛው ቀን እደሆነም ማወቅ አልቻልኩም። ለነገሩ በጣም ሲደክመኝ ነው ተወጥሬ መስራቴን የማስተውለው። ያለኝን ሁሉ ለሌሎች ባዋልኩ ቁጥር በአባቴ ቤት በሚኖረኝ ዘለዓለማዊ እረፍት እደሰታለሁ። በዛ ላይ ለነገ መጨነቅ የለም። በዘለዓለማዊው ዓለም ውስጥ ሆኜ ስለ መፈለጌ፣ ስለመወደዴ ሁሉ የሚታሰብበት ቦታ አይደለም። የምትከተይውን አቅጣጫ ሁሉ ጊዜ ውደጂ

ኒልጥቅምት 20, 2000

ሃይ ኒል

አንተ ስለማታውቀው ህይወት እንዳለኝ እያሰብክ እባክህ አትጨነቅ። እዚህ ባለሁበት በተለያዩ ጉዳዮች ተወጥሬ እንደቃሉ ጌታን ለመከተል እየሞከርኩ ነው። በእርግጥ አንተም እዚያ እንደምትቸገርበት እዚህም ፈተናዎች የሉም ማለት አልችልም። መኪና ተበላሽቶብህ ትኩረትህን የሚይዙ ፈተናዎች እንደሚገጥሙህ ሁሉ እኔ ዘንድም ፈተና ቢኖርም መደምደሚያው ጌታ በሚሰጠኝ ሀይልና ፀጋ ፈቃዱ መከተል ብቻ ይሆናል። ስለነዚህ ጉዳዮች ብዙ ጊዜ እንደተወያየነው በዚህ ሀገር የምናደርጋችው ሁኔታዎች በጥንቃቄ ካልተያዙ ሁሉንም ነገር እንደሚያበላሽ ተስማምተንበት ነበር። ብዙ ፈተናዎች ከፊቴ ተጋርጠው እንደነበሩ ማመን አለብኝ። ነገር ግን እግዚአብሔር ጠብቆኝ ሁሉንም ፈተናዎች በአሸናፊነት እንድወጣ ረድቶኛል። ምናልባት ስለነዚህ ጉዳዮች ስንገናኝ እንደገና ትሰማ ይሆናል። ፈተናዎችን እንዴት እይዝ እንደነበረ ልታስታውስ ይገባል። በዚህ ረገድ የእኔ ፖሊሲ አካላዊ መነካካትን ማስወገድ እንደሆነ ታስታውሳለህ። ትግላችን ከደምና ከስጋ ጋር እንዳልሆነ አትርሳ ምክንያቱም ውጊያው በሰማያት ካሉት መናፍስት ጋር ስለሆነ ነው። እነዚህ መናፍስት የሚታዩ ሳይሆኑ እኛን በማሳሳት ከመንገድ ሊያስወጡን በተለያዩ ሁኔታዎች መልክ የሚገለጡ ናቸው። ዝንጉ ሆኜ የምኖር ሳልሆን  የሰይጣንን መሣሪያዎች በንቃት እየጠበኩኝ ስለሆነ እባክህ አእምሮህን ከዚህ አይነቱ አስተሳሰብ አሳርፍ።

 

አብረን ባሳለፍናቸው ዘመናት ውስጥ ከአንተ የማገኛቸውን ፍፁም የሆኑ እርካታዎችን እያሰብኩ በደስታ እሞላለሁ እናም ዳግም በእቅፍህ የምሆንበትን ጊዜ በናፍቆት እጠባበቃለሁ። አንተስ ኒል??? ይህን በተመለከተ እንዴት ይዞሃል? እንደነዚህ ያሉ ፈተናዎች በጥንካሬ አልፈሃቸዋል ወይ? በፀሎቴ ጊዜ ሁሉ በሀሳቤ ውስጥ ነህ። በጣም እወድሃለሁ፤ እግዚአብሔር እንደሚጠብቅህም እያደነቅሁ እቀጥላለሁ። በጥርጣሬህ ምክንያት እዚህ ያለውን ሁኔታ መመልከት ባለመቻልህ መጨረሻ ሊሆን ስለሚችለው ውጤት በፍርሃት ተሞልተሃል። ኒል በዚህኛው የሰማይ በኩል አንተ ማየት በማትችለው ሁኔታ የምትወደድና የምትደነቅ ነህ። ምክንያቱም በሰማይ ያሉቱ ትጉሃን ሀይሎች በዚህን ሰዓት ስለ አንተ በጌታ ስም እያሞገሱህ ናቸው። ለአንተ የምመኘው በዚህ ምድር በማንኛውም ሁኔታ ትልቁን ሽልማት እንድትቀዳጅ እና ይህም ለእግዚአብሔር ደስታ እንዲሆን ነው። በዚህ መንገድም በእዚህ በኢትዮዽያ ውስጥ ሁሉም የሚመኙልህን ፍቅርና ትኩረት አብዝቶ እንዲሰጠን ነው። እዚህ ባሉት ወገኖች እንዴት እንደምትወደድ ልታስብ አትችልም። እጅግ ይወዱሃል፤ ይናፍቁሃል። የተሰጠንን ጥሪ በትክክል ተቀብለን በመለኮታዊ ሀይል መልካም ኑሮ እየኖርን መስማት ከተሳናቸው ወገኖች በሰላም እንድኖር እንጂ በነቀፋ የተሞላ ኑሮ እንዲታይብን አልፈልግም። በተሰጠን ጥሪ ውስጥ ሁለታችንም ለጌታ ታዛዦች ሆነን እንድንገኝ አፈልጋለሁ። እወድሃለሁ። እኔ የአንተው ነኝና እባክህ አእምሮህን በሰላም ሙላ።

ቤኪ

 

 

ጥቅምት 23, 2000

ቤኪ

በጣም እወድሻለሁ፣ በጣም እወድሻለሁ፣ በጣም እወድሻለሁ። ከማውቃቸው ሴቶች ውስጥ በጣም ተፈላጊና ጠቃሚ ሴት በማግባቴ እጅግ ያስደንቀኛል። እወድሻለሁ፣ እ.ወ.ድ.ሻ.ለ.ሁ። እግዚአብሔር ለእኔ የሰጠው ፈቃድ አንቺን ማስደሰት ነው።እወድሻለሁ። ያለፈው ታሪካችን ምንም ቢሆንም ዛሬ ይህን ታላቅ እና ትክክለኛ ውሳኔ መወሰኔ በጣም ተገቢ ነው። ይህ ማለት ትክክለኛ የሆነውን ነገር ብቻ ለአንቺና ለአንቺ የማድረግ ውሳኔ ነው። አንቺን መውደድና ለአንቺ እውነተኛ ለመሆን መወሰን ቀላል ውሳኔ ቢሆንም ይህንን ማድረግ ግን የግድ ነው። መሆንም አለበት። ምንም እንኳን ለችግር ቀን ገንዘብ የማጠራቅም ቢሆንም ከሚኖረኝ ገንዘብ ደስታ ላገኝ አልችልም ነገር ግን አንቺ የህይወቴ የደስታ ምንጭ ነሽ። ሊኖረኝ የማይችለውን ነገር የምፈልግ መስሎሽ ለአፍታ እንኳን እንዳታስቢ። ያለኝን ነገር በትክክል አውቃለሁ። ከዓለም በወዲያኛው በኩል አንቺን አለኝ። እኔ ብዙዎችን እንደምባርክ እግዚአብሔርም እንዲሁ ይባርከኛል። አንቺ ያለሽ ነገር ሀብታም ሊያደርግሽ አይችልም ነገር ግን ሌሎች ብዙዎች ያላቸው ነገር ሀብታም ሊያደርግሽ ይችላል። በሕይወታችን ውስጥ ትልቁ ሀብት ፍቅር ማሳየት፣ ርህራሄ ማሳየትና ከእንደነዚህ ነገሮች ጋር እና ከጌታ መንገድ ጋር ራስን መለየት ነው።

 

የእኔ ፍቅር ራስሽን ለሌሎች በሰጠሽ ቁጥር እኔ ደግሞ ራሴን ከአንቺ ጋር የበለጠ አጣብቃለሁ። ሊያገባት ያሰባትን ሴት ለማየት የሚሄደውን ሰው ታሪክ ማንበብ ደስ ይለኛል። ለመገናኘት ያሰቡት በአየር መንገድ ውስጥ ነው። ይህ ሰው ሀገሩን በጦርነት ወቅት ያገለገለ ሰው ነው። እና ይህ ሰው ይህች ሊያገባት ያሰባት ሴት ከእርሱ የምትጥለው ነገር ካለ መልኩንም ጨምሮ ማለት ነው ሊያገኛት አይፈልግም። ይህችን ሴት ለማየት በሚመጣበት ቀን አንድ የጦር ሜዳ ጡረተኛ አብሮት እንዲመጣ አድርጎ ነበር። ይሕ ጡረተኛ እጅ እና እግር አልነበረውም። በዚህን ቀን ይህን የጦር ሜዳ ጡረተኛ አስቀደሞ ለራሱ ተደብቆ ይመለከት ነበር። ይህች ሴት ግን ገና ከሩቁ እንዳየችው ይህን በተሽከርካሪ ወንበር ላይ የተቀመጠውን ሰው ተቀበለችው። ሰውዬውም ራሱን ማስተዋወቅ ጀመረ። እንግዲህ እኔ በተሽከርካሪ ወንበር ውስጥ ያለው ጡረተኛ አይነት ስሜት ይሰማኛል። ምንም እንኳ ብዙ የሚጎድሉኝ ነገሮች ቢኖሩም አንቺ ግን ተቀብለሽኛል።ለአንቺ ያለኝ ፍቅር አንቺ ከምታውቂው በላይ የገዘፈ ነው። ሁል ጊዜ እወድሻለሁ!

  ኒል

 

 

ህዳር 01, 2000

ቤኪ

ቅርብ ጊዜ የላክሽልኝን ኢሜል ካነበብኩ በኋላ አሜን! ነበር ያልኩት። ሁለታችንም ተራርቀን ስንኖር በመካከላችን ያለው እግዚአብሔር ነው። ከካሊፎርኒፍሬንች ካምፕ ፖማና ካሊፎርኒያ የደረስኩት ገና አሁን ነው። አሁን የዓመቱ የበረዶ ወቅት ነው። ከጉዞ በፊት ሁለት ካቦዎችን ይዤ ነው የተነሳሁት። የማርቲን ሉተርን ታሪክ ታውቂያለሽ አይደለም? ንሰሃ ሊገባ ወደ ገዳም እየወጣ በነበረበት ጊዜ ቀደም ሲል ያነበበው ቃል  ወደ እርሱ መጣ። ይህ ቃል “ፃድቅ በእምነት ይኖራል” የሚል ነበር።በባለፈው ጉዞዬ ከአይዋ ወደ ካሊፎርኒያ በምመጣበት ጊዜ ገና ከእንቅልፌ ስነሳ “ፈቃድህን ለእግዚአብሔር ስጥ” የሚል ቃል ወደ ሀሳቤ መጣ። ማድረግ ያለብኝ ይህ ብቻ ነው።  የእኔና የአንቺ የቀረው የዘመናችን ጉዳይ በእነዚሁ ቃላት ውስጥ የሚጠቃለል ይሆናል። ሀዘኖቻችንን ሁሉ ወደ ደስታ መቀየር ይችላል። እስኪ ሳይነጋ በፊት ትንሽ ልተኛ! በፍቅርሽ የተያዝኩ ነኝ::

ኒል

 

 

ታህሳስ 5, 2000

ፍቅሬ

አንቺን ቸል ለማለት እየጣርኩ አይደለም። ከአጋሮቼ ጋር ሆነን በሀይለኛ ስራ ተይዘናል። መጀመሪያ  አብረን መንዳት የጀመርን ጊዜ በጣም ትንሽ እንቅልፍ እንደ ተኛሁ ታስታውሽ ይሆናል። ከቻታኑጋ ወደ ኒውዮርክ እየሄድን ነው። ቀጥሎም ኬንተኪ እናልፋለን። አሁን ወደ ሰንፍራነሲስኮ እየተቃረብን ነው። በመጨረሻም ወደ ሪቨርሳይድ ካሊፍፎርኒያ ሄደን ኦፔሊካ አላባማ ውስጥ ጭነቱን እናራግፋለን።ሁለታችንም ከባድ ነገር መኪና ላይ መጫን የተፈቀደልንን መድሃኒቶች ይዘናል። ምናልባት አትላንታ ጆርጂያ ላይ እነዚህን መድሃኒቶችን እንጠቀም ይሆናል። ይህንን ሁሉ ልነግርሽ የፈለኩበት ምክንያት በርትቶ ወደፊት መግፋት መጨረሻው መልካም መሆኑን ላስገነዝብሽ ፈልጌ ነው። ለረዳቴ ከሁለት ሳምንት በፊት ያየሁትን ህልም እየነገርኩት ነበር።ከህልሙም በኋላ ድካሜ ሁሉ መና አልቀረም ነበር። በየሳምንቱ የምጠቀምባቸው ገንዘብም በከንቱ አልወጣም። እግዚአብሔር ለራሱ ጉዳይ እንድጠቀምበት እየረዳኝ ነው። ህልሜን ባላስታውስም ከህልሙ በኋላ ግን ይህንን እንዳስብ ነበር እግዚአብሔር ያደረገኝ።

 

ነገሩ ስለ አንቺና እኔ ነበር። ስለ ደስታዬ፣ ሀዘኔ፣ ብቸኝነቴ፣ በትምህርት ቤት ነገሮች አንቺን ስለመርዳቴ፣ እነዚህ ነገሮች መጨረሻቸው መቼ ስለመሆናቸው፣ በእነዚህ ነገሮች እግዚአብሔር ምን ያህል እንደሚባርከኝ እንዲሁም ፈቃዱን ለመፈፀም እንደሚያጠነክረኝ ስለነዚህ ሁሉ ነበር ህልሜ። ያ ህልሜ ከጆፓ የሆነ ሰው ስለ ነበረው ህልም ነበር ያስታወሰኝ። ይህ ሰው እግዚአብሔር ወደ በሆነ ከተማ ውስጥ ቀጥታ ወደ ተባለ መንገድ እንዲሄድ ነግሮት ነበር። በዚያም ፒተር የሚባለውን ሰው እንደሚያገኝ እና ይህም ሰው ምን ማድረግ እንደሚገባው እንደሚነግረው ነበር እግዚአብሔር ያሳሰበው። ከዚህም ሌላ እግዚአብሔር ይህንን ከጆባ የሆነን ፀሎትህና ምጽዋት ወደ እኔ ዘንድ ደርሷል ብሎት ነበር። ይህ ትንሽ ነገር ይመስላል ነገር ግን አይደለም። ይህ ታሪክ ሰላም የሚሰጥሽ ይመስለኛል፤እያደረግን ስላለነው ጉዳዮችን በተመለከተ እረፍት ሰጥቶኛልና። ያን ህልም ባስታውሰው እመኝ ነበር ነገር ግን አልቻልኩም። ማስታወስ የቻልኩት የህልሙን መደምደሚያ ብቻ ነው። መደምደሚያው ሰላም ነው የምንሰራውም ስራ መጨረሻው ምን እንደሚሆን የሚያሳይ ነው። እወድሻሁ!

ኒል

 

 

 

Leave a Reply

Discover more from LeaMcD Deaf Ethiopia

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading