Skip to main contentSkip to footer

የተገለለች

የተገለለች

የክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ቤኪ ሊች ማክዶናልድን ከአባልነት አግልላታለች

ምዕራፍ 1 የቤኪ የልጅነት ሕይወት

ኤል ሰጉንዶ የክርስቶስ ቤተ ክርስትያን የባህር ማዶ ተልዕኮ  የኢትዮጲያ ተልዕኮ ሪፖርት መጋቢት 18, 1963

 

“እኔ ግን እነሆ በእጃችሁ ነኝ”

“እኔ ግን እነሆ በእጃችሁ ነኝ፤ በዓይናችሁ መልካምና ቅን የመሰለውን አድርጉብኝ።” (ኤርሚያስ 26፡14) በቅርብ ወደ ኢትዮጲያ ለሚሄደው የላይሌ ሊች ቤተሰብ ከዚህ የሚሻል ገላጭ የሆነ ነገር የለም። ይህ ቤተሰብ በአሁኑ ጊዜ በኦሬገን ኒውበርግ ከተማ ውስጥ ይኖራሉ። በዚህ ከተማ ውስጥ በግንባር ቀደምትነት የተሰማሩበት የቤተ ክርስትያን አገልግሎት ነው። ወንድም ሊች በግሉ በንግድ ስራ ላይ የተሰማራና ጊዜ የሌለው ቢሆንም በኦሬገን ውስጥ ብዙ አብያተ ክርስቲያናት እንዲከፈቱ የረዳ ወንድም ነው። ወንድም ሊች ለብዙ ዓመታት በቤት ለቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ላይ በንቃት የሚሳተፍ ወንድም ነው። በማእከላዊ ስቶክተን የምትገኛው የክርስቶስ ቤተ ክርስትያን መሪዎች (ሽማግሌዎች) ወንድም ጆን ኤድን የሚተካ ሰው በሚያፈላልጉበት ጊዜ ከታሰቡት ሰዎች ውስጥ አንዱ ወንድም ሊች ነበር። እነዚህ የቤተ ክርስትያን ሽማግሌዎች ወንድም ሊችን ያሰቡበት ምክንያት ቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ለብዙ ዓመታት ሲያከናውን የነበራውን ታላቅ አገልግሎት መሰረት በማድረግ ነበር። አሁን ደግሞ ኢትዮጲያ ውስጥ ለሚካሄደው ለሌላ ታላቅ የተልዕኮ ስራ አጭተነዋል። ሊች ስቶክተን የምትገኘውን ቤተ ክርስትያን በጎበኘበት ጊዜ ኢትዮጲያ ውስጥ የሚካሄደውን የስራ ሪፖርት በማይንቀሳቀስ ምስል አይቶ ነበር።

 

በዚህ በኢትዮጲያ ታልእኮ ላይ ብዙ ሰዓት የፈጀ ውይይቶችን አድርጓል፤ በፀሎትም ቆይቷል። ቤተሰቡም በዚህ ተልዕኮ ውስጥ ለመሳተፍ ወደ ኢትዮጲያ መሄድ እንዳለበት በሙሉ ድምፅ ወስኗል። ቤተሰቡ እንዳለው ጌታ ለአገልግሎት እንዲለየንና እንዲመራን ለብዙ ጊዜያት ስንፀልይ ነበር። ይህን ጥያቄ ለጌታ ስናቀርብ እስከ አሁን ምንም አልሰራንም ብለን ሳይሆን  ለጌታ እንደሚገባው  አላገለገልንም ብለን በማሰባችን ነው ብለዋል። ወንድም ሊች ለዚህ ስራ የተመረጠበት ምክንያት ቤተ ክርስትያን በደከመችበት ቦታ ሁሉ ድርሻ የነበረው፣ እምነት ያለው እና የበሰለ ውሳኔ ሊሰጥ የሚችል ሰው በሚያስፈልግበት ቦታ ላይ የተሻለ ለውጥ በማምጣቱ ነበር። ከዚህም ሌላ የግንባታ ስራዎችንና የመካኒክነት ስራዎችን የመስራት ችሎታ  ስላለው ለመመረጡ ተጨማሪ ምክንያት ሆኗል። በዚህ ዓይነት መመረጡ እንግዲህ በእውነት ታላቅ መባረክ ነው። እህት ሊችም ለባለቤቷ ታላቅ አጋር ስለምትሆን ኢትዮጲያ ውስጥ ላለው ስራ እጅግ ጠቃሚ ናት። ከዚህም ሌላ  ለእህቶች ታላቅ የወንጌል አስተማሪ መሆንዋ በወንድሞች ዘንድ ይታወቃል። ስለዚህ ይህ ቤተሰብ እንደ አንድ ቡድን ሆኖ ነው ወደ ኢትዮጲያ የምሄደው። በኢትዮጲያ ውስጥ ታላቅ ለውጥ እየመጣ ስለሆነ በሊች በኩል የኢትዮጲያን ተልዕኮ እግዚአብሔር የበለጠ ይባርካል የሚል እምነት አለን።

 

ከካርል ጋር የመገናኘት አጋጣሚ 1963, ክረምት

ከካርል ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ የመገናኘቴ ነገር የእጣ ፈንታዬ አመላካች ክስተት ነበር። ቦታው ኦሬገን ሲሆን ቀኑ እሁድ ነበር። የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችም ከእሁድ አምልኮ በኋላ ባለው የምሽት ፕሮግራም ላይ ለመታደም እየተሰበሰቡ ናቸው። ካርል የሰላም የክርስትያን ወጣቶች ህብረት በጎ ፈቃደኞች አባል በመሆኑ አገልግሎት ሊሰጠን መጥቶ ነበር። ቀደም ሲል የቤተ ክርስትያናችን ወጣቶች ጠንካራዎች መሆናቸውን ሰምቶ ነበር። እናም የኮሌጅ ተማሪዎችን በመምራት ሊያገለግለን ወደ ተሰበሰብንበት አዳራሽ መጥቷል። አዳራሹ በሰው ተሞልቷል። ወደ አደራሹ የደረስኩት ዘግይቼ ነበር። የምቀመጥበት ቦታ በዓይኔ ማፈላለግ ያዝኩ። አንድ ወንበር አገኘሁ። ይህ ቦታ የቤተ ክርስትያናችን ወንጌላዊ ሊዮናርዶ እና ካርል መካከል ነበር። በዚህ ቦታ ቁጭ ከማለቴ ከካርል ጋር ተዋወቅን። መጀመሪያ ሳየው ኩራተኛ መስሎ ስለ ታየኝ ከእርሱ ጋር የጀመርኩትን ንግግር አቁሜ ወደ ወንጌላዊ ሊዮናርዶ ፊቴን አዞርኩ። ከዚያም ይህ ወንጌላዊ ንግግር ለመጀመር ያህል

 

“በሳምንቱ መጨረሻ ቤተሰቦችሽ ወዴት ነበር ይሄዳሉ ያልሽኝ?” ብሎ ጠየቀኝ።

“አዎ ኦሬገን  ስቶክተን ናቸው። ከቤተ ክርስትያን ሽማግሌዎች ጋር ስለ አገልግሎታቸው እየተነጋገሩ ናቸው” አልኩት።

“የት ሀገር ነበር በሚስዮናዊነት ለማገልገል እንዲሄዱ የተጠየቁት?” ብሎ እንደገና ጠየቀኝ።

ከካርል ጋር የጀመርኩትን የንግግር አቅጣጫ ለመለወጥ የተጠቀመውን ሀሳብ እያደነቁት “ኢትዮጲያ” አልኩት።

በዚህን ጊዜ ካርል ንግግሬን በጥሞና እያዳመጠ መሆኑን ተገነዘብኩ። በትኩረት ነበር ያዳምጠኝ። ኩራተኛ ነው ያልኩትን ሀሳቤንም ወዲያው ቀየርኩ። በፍፁም ኩራተኛ ሊሆን አይችልም ብዬ አሰብኩ።

ካርል ወደ እኔ እየተመለከተ “አንቺ ወደ ኢትዮጲያ ትሄጂያለሽ?” ብሎ ጠየቀኝ።

“አዎን” አልኩት።

“ስለዚህ እኔም እሄዳለኋ!” አለኝ።

 

በመገረምና ግራ በተጋባ ስሜት ትኩር ብዬ አየሁት። እንዲህ አይነት ግራ የሚያጋባ አስተያየት እንዴት ሊሰጥ ቻለ? ለምንስ ሰጠ? ንግግሩን በመቀጠል መስማት  በተሳናቸው የትምህርት ክፍል የኮሌጅ ትምህርቴን እየተማርኩ እገኛለሁ። ዘንድሮ እመረቃለሁ። ከምርቃቴ በኋላ ወደ ኢትዮጲያ ሄጄ እነዚህን ወገኖች ለመርዳት አቅጃለሁ። ካርል ኢትዮጲያን በትክክል አያውቃትም። ሌላ ቀርቶ ስለ ኢትዮጲያ ከማን ጋር እየተነጋገረ እንደሆነም በትክክል አያውቅም። እኔና ካርል ስለ ኢትዮጲያ በምንነጋገርበት ጊዜ ቤተሰቦቼም እንዲሁ ከስቶክተን የቤተ ክርስትያን ሽማግሌዎች ጋር በኢትዮጲያ ያለውን የጌታ የአገልግሎት ተልዕኮ በዳይሬክተርነት ስለመምራት እየተነጋገሩ ናቸው። እንግዲህ ካርል ወደ ኢትዮጲያ የሚሄድ ከሆነ ዕቅዱን የሚያሳካው በአባቴ በኩል ነው። በዚያን ቀን ምሽት ወደ ቤቴ ስሄድ ካርልን እንደማገባ ውስጤ አውቆት ነበር። እንግዲህ ካርል ማክዶናልድን ላገባ ነው።

ምዕራፍ 2 ካርል ማክዶናልድ

መስማት ለተሳናቸው ልዩ ትምህርት መምህር ኤል ሰጉንዶ የክርስቶስ ቤተ ክርስትያን የባህር ማዶ ተልዕኮ የኢትዮጲያ ተልዕኮ ሪፖርት ቅጽ 12 ቁጥር 3

“እነሆ እኔን ላከኝ”

 

ዊሊያም ለስራው በጎ ፈቃደኛ አድርጎ ያቀረበው ስራውን ለማግኘት ያለው ምስጢራዊ ፊላጎቱ ነው ብዬ እገምታለሁ። ነገር ግን ጌታን ለማገልገል ሲወሰን ሁል ጊዜም ችግሮችን መጋፈጥ አይቀሬ ነው። በተለይም ከሀገር ውጭ ወደ ማያውቁት ባህልና ቋንቋ ለአገልግሎት ስኬድ መስዋዕት ያስከፍላል። እስኪ ኢትዮጲያ ውስጥ ጌታን ለማገልገል ስለ ወሰነው ወጣቱ ወንድም ካርል ማክዶናልድ ትንሽ ልንገርዎ። ካርል 24 ዓመቱ ሲሆን ያደገው ካልፎርኒያ ውስጥ ነው። ይህ ወጣት ገና አላገባም። የክርስትና እድገቱ ደግሞ ቤተሰቡ በሚያመልኩበት በካምቤል የክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ውስጥ ነው። ወደ ኢትዮጲያ ለመሄድ የመወሰኑ መሰረትም የዚሁ የቤተ ክርስትያን እድገቱ ነው። የኮሌጅ ትምህርቱ በሚጨርስበት ዓመት በቤተ ክርስትያኑ በሚሰጠው የምልክት ቋንቋ ትምህርት እየተከታተለ ሲሆን መስማት ለተሳናቸው ወገኖች አገልግሎት መስጠት የጀመረው በቤተ ክርስትያኑ ውስጥ ነበር። የኮሌጅ ትምህርቱን የተከታተለው በፔፐርዳይን ኮሌጅ፤ ዌስት ቫሊ ኮሌጅ እና በሶስዮሎጂ የመጀመሪያ ድግሪውን ባገኘበት በጆሲ ስቴት ነበር። የማስተርስ ድግሪውን በስነ-ትምህርት የትምህርት ክፍል መስማት በተሳናቸው የማስተማር ዘዴ ከኦሬገን ኮሌጅ አግኝቷል። በዘመናችን እንዳሉት ወጣቶች ሁሉ ካርልም ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ ቤተሰብ ከመመስረቱ በፊት አነስተኛ ኑሮና በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ለሚገኙት ወገኖች የሆነ ነገር ለማድረግ ወይም ለማገልገል ወስኖ ነበር። በኢትዮጲያ ውስጥ ያለውን ስራችንን ያውቅ ነበርና ይህንን ስራ ለመቀላቀል ተነሳሳ።

 

የሁለታችንም የእኔና የካርል ቤተሰብ የሚኖሩት በኦሬገን ነው። ካርል በሳሌም ያሉትን የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ወንጌል በማስተማር ረገድ ንቁ ተሳትፎ ያደርጋል። ካርል የሳሌምን ወጣቶች ይዞ ኒውበርግ በተዘጋጀው የወጣቶች ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ የመጣው የሊች ቤተሰብ ወደ ኢትዮጲያ ሄደው ለማገልገል ከወሰኑ ከጥቂት ጊዜ በኋለ ነበር። በስብሰባው ቦታ ካርል፣ ወንጌላዊውና እኔ ስለ ራሴ የኢትዮጲያ እቅድ እንወያይ ስለ ነበር ይህ ውይይት ካርልን ውሳኔውን ወደ ኢትዮጲያ እንዲያድርግና ፈጠን ያለ ውሳኔ እንዲያደርግ አስችሎታል። እግዚአብሔር በካርል ሕይወት ውስጥ እየሰራ በመሆኑ በእጭር ጊዜና በአጋጣሚ ከእኔ ጋር በማገናኘት ወደዚህ ውሳኔ ደረሰ። በኢትዮጲያ ውስጥ ላለው ስራ ካርል ታላቅ እሴት ነው። ከትምህርት መሰረቱ ውጭም ከቤተ ክርስትያኑ ሽማግሌዎችና ወንጌላዊያን መልካም ምስክርነት አለው። ወጣት በመሆኑም መስማት የተሳናቸውን ወጣቶች ለመርዳት የወሰነው ውሳኔ ታዓማኒነት ያለው ነበር። ከካርል ጋር ባደረግነው የመጀመሪያ ስብሰባችን አስፈላጊ ከሆነ ወደ ኢትዮጲያ ለሚደረገው ጉዞ መኪናውን እንደሚሸጥና ለጉዞ ትኬት እንደሚጠቀምበት ነግሮኛል። በኤል ሰጉንዶ ያለው የቤተ ክርስትያኑ ሽማግሌዎችና አባላት ያን ያህል ዋጋ መክፈል እንደማያስፈልግ ነግረውታል።

 

ሚያዝያ 1964 ካርል ወደ ኢትዮጲያ ተጉዟል

ካርል ማክዶናልድ ወደ ኢትዮጲያ ለመሄድ አቅዷል። ነገር ግን ከምርቃቱ ጥቂት ቀደም ብሎ የካምቤል ክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ከተማሪነት ወደ ሚሲዮናዊነት ለመቀየር የማጣራት ስራ በሚሰሩበት ጊዜ የአሜሪካን መከላከያ የማጣራቱን ስራ ወደ 1 ኤ በመቀየር ለውትድርና አገልግሎት እንዲመለመል አደረገ። በመጨረሻም ከአንድ ዓመት ጥረት በኋላ የወቅቱ በኢትዮጲያ የአሜሪካን አምባሳደር እገዛም ተጨምሮበት ሚያዝያ/1972 ወደ ኢትዮጲያ እንዲሄድ ተደረገ። የጉዞ ወጪውን የሸፈነችው በካልፎርኒያ የምትገኘው ኤል ሰጉንዶ የክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ነች። ካርል መካኒሳ መስማት የተሳናቸው ት/ቤት ስራ ከላይሌ በመረከቡ ምክንያት ላይሌ ሙሉ ጊዜውን የጌታን ቃል ወደ ማገልገል ገብቷል። ካርል ወደዚህ ሀላፊነት በሚመጣበት ጊዜ ቤኪ በትምህርት ቤቱ የ1ኛ ክፍል መምህርት ነበረች። ካርልና ቤኪ ወደ ኢትዮጲያ ከመምጣታቸው በፊት በኦሬገን ውስጥ ለአንዳፍታ ተገናኝተው ነበር። በት/ቤቱ በጋራ መስራታቸው የላቀ ትስስር በመፍጠሩ አንዱ ለሌላው የተፈጠረ/ች መሆኑን ተገንዝበው በጋብቻ ከተሳሰሩ በኋላ ቀሪ ጊዜያቸውን በጋራ ሆነው በአገልግሎት መበርታት ቀጠሉ። ካርልና ቤኪ ለሁለት ዓመታት መካኒሳ መስማት የተሳናቸው ት/ቤት ውስጥ ካገለገሉ በኋላ ለሶስት ወራት ያህል በፈቃድ ወደ አሜሪካ ተመልሰው ቆይታ አድረገዋል። እግረ መንገዱንም የማስተርስ ድግሪውን ለመጨረስ ዕድል አግኝቷል። ከአሜሪካ ከተመለሰ በኋላ ትምህርት ቤቱን በተሻላ ሁኔታ ለማደራጀት የማሻሻል ስራዎችን ሰርቷል።

 

ትምህርት ቤቱን ለማሻሻል ከተሰሩት ስራዎች አንዱ በት/ቤቱ ውስጥ የመምህራን ስልጠና ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስ ነበር። ካርል ትምህርት ቤቱን በሀላፊነት ከመምራቱም በተጨማሪ ክፍል ገብቶ በማስተማር ረገድም ከፍተኛ ድርሻ አበርክቷል።አንድ አዲስ ፕሮጀክተር እና ለስልጠና አገልግሎት የሚውሉ ስድስት የጆሮ መመርመሪያ መሳሪያዎች ለትምህርት ቤቱ እንዲገዛ አድርጋል። 250 የአሜሪካን ዶላር በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ በኩል በማስላክ ስድስት ተጨማሪ የማዳመጫ መሳሪያዎች እንዲገዙ አድርጓል። እነዚህ የማዳመጫ መሳሪያዎች ተማሪዎች ወደ መንግስት ትምህርት ቤት ገብተው እንዲማሩ ከማድረጉም ባሻገር መስማት የተሳናቸው ልጆች ወደ ትምህርት ቤት እንዲሄዱ ማበረታቻ ስልት ሆኖ ነበር። በተጨማሪም የሙያ ትምህርቶችን በትምህርት ቤቱ ውስጥ ለማስተዋወቅ የልብስ ስፌት ትምህርት እንዲሰጥ አድርጓል። ይህንን ትምህርት የሚያስተምሩት ፒርል የሚባሉ መምህር ናቸው። እኚህ መምህር የአልጋ ልብስ ስራ ያስተማሩ እና በትምህርት ቤቱ ውስጥ የሚሰራው የአልጋ ልብስም መስማት ለተሳናቸው ቤተሰቦች በነፃ እንዲሰጥ አድርጓል። ይህም ሴት ተማሪዎች ይህን ጥበብ ከመማራቸውም በላይ ትምህርት ቤቱን በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛ ድርሻ ነበረው። በዚህ በልብስ ስፌት ትምህርት አማካይነት መስማት የተሳናቸው ሴት ተማሪዎች የቤት አያያዝ እና የቤተሰብ ኑሮ ዘዴ እንዲማሩ አስችሏቸዋል። ፒርል መሰረታዊ የልብስ ስፌት ጥበብ ሲያስተምሩ እግረ መንገዳቸውን የአልጋ ልብስ፣ የሕፃናት የብርድ ልብስ፣ ክራቫት፣ ሽርጥ፣ መሃረብ እና ቀሚስ የመስፋት ጥበብ አስጨብጠዋቸዋል። ተማሪዎች የተማሩትን አዳዲስ ጥበቦች ስራ ላይ ማዋላቸውን ሲያዩም እጅግ ተደስተዋል።

ምዕራፍ 3 ከጆን ኤድ የተላከ ደብዳቤ ሐምሌ 8, 1967

ቤተሰቦቼን በሕይወት ሳሉ ለመጨረሻ ጊዜ ከማየቱ ከአንድ ሳምንት በፊት

 

ለውድ ካርል እና ቤኪ

በደብዳቤ ከተገናኘን ረዝም ጊዜ ሆኖናል። ባለፈው የፃፈችሁልኝ ደብዳቤ እንደ ደረሰኝ ስለ ፃፋችሁልኝም አድንቄያችሁ መልስ እንደ ፃፍኩላችሁ ታስታውሳላችሁ። በዚያ ሀገር ብጥብጥና ሁከት በሆነበት በዚህን ጊዜ ስለ እናንተ እጅግ እያሰብን ነው። የዚህ ዓይነቱ ሁኔታ ተስፋ ሊያስቆርጥ እንደሚችል አውቃለሁ። እኔም በዚህ ዓይነቱ ሁኔታ ውስጥ አልፌ ነበርና። በተቻለኝ መጠን በኢትዮጲያ እየሆነ ያለውና በእናንተ ላይ ሊደርስ የሚችለውን ሁሉ ለቤተ ክርስትያናችን ሽማግሌዎች እያስረደኋቸው ነው። ነገር ግን በፍፁም ሊረዱኝ አልቻሉም። የምቀልድባቸው ይመስላቸዋል፤ ጊዜ ሰጥተው አያዳምጡኝም። እንዲያውም ወቀሳው ይበዛል። አንዳንዴ መልካም ሰርተን ምላሹ ወቀሳ ሲሆን ለማመን የሚከብድ ነው። ወቀሳው የሚሲዮኑ ስለሆነ እናንተም ድርሻ አላችሁ። በተለይ የረዳሃቸውና ያገዝካቸው ተመልሰው ሲወቅሱ እንግዳ ነገር ነው። ለማለት የፈለኩት መስማት የተሳናቸው ራሳቸው ያደርሱብን የነበረው ፈተና ቀላል አይደለም። ምናልባት እናንተም ሁለታችሁ ከማንኛችን በላይ በዚህ ጉዳይ ተስፋ ቆርጣችኋል ብዬ አስባለሁ። የሆነ ሆኖ የመልካም ስራችሁ ውጤት ወቀሳ ቢሆንም ከኢትዮጲያ ውጡ እያልኩ አይደለም። ጥሩ ነገር እንዳልሰራችሁ እንዲሰማችሁም አልፈልግም። ምናልበት በአሁኑ ሰዓት ምን ያህል ታላቅ ተግባር እንደፈፀማችሁ የተገነዘባችሁም አይመስለኝም። ካርል ወደ ኢትዮጲያ በሄድክበት ወቅት መስማት የተሳናቸው የትምህርት ፕሮግራም ምን ያህል ደካማ እንደነበረ ታስተውሳለህ።

 

በትምህርት ቤቱ የነበሩ መምህራኖች ችሎታቸው በጣም ዝቅተኛ እንደነበር ታስታውሳለህ። አንተ ግን ያንን ሁሉ ችግሮች በእርግጥ ቀይረሃቸዋል። መንግስት ስራችን ገምግሞ ጥሩ ውጤት እንዳገኘን አይተናል። መልካም መስራታችንን ለመጀመሪያ ጊዜ የተገነዘቡልን ያኔ ነበር። ይህ ሁሉ መልካም ነገር የሆነው በአንተ ታላቅ ስራ ነው። ከአንተ መምጣት በፊት ይህን የትምህርት ቤቱን ስራ ገምግመን ቢሆን ኖሮ ገና ድሮ በተዘጋ ነበር። ካርል ታስታውስ ከሆነ ወደ ኢትዮጲያ ከመሄድህ በፊት መስማት ከተሳናቸው ወገኖች የሚመጣብንን ችግሮች ነግሬህ ነበር። ከእነርሱ ጋር ምንም ነገር በቋሚነት ማከናወን አንችልም ነበር። ምናልባት ትምህርቱን አቋርጦ የሄደ መስማት የተሳነው በማግስቱ ትልቅ ችግር ይዞብን ይመጣ ነበር። በእኔና በቤኪ መካከል ያለው ልዩነት እኔ እንደ ቤኪ በስሜት ተሞልቼ ከሕፃናት ጋር ስለማልጋጭ አያጠቁኝም። ቤኪ ግን ከእኔ ተቃራኒ ነች። በመሆኑም ከእያንዳንዱ ህፃን ጋር የሚኖረኝ የግንኙነት ጊዜ ሁሉ ለእኔ ትምህርትና ልምድ ይሆነኝ ነበር። ነገር ግን ለብዙ ችግሮች ከሰጡኝ ወንጌላዊያን ጋር ሰፊ ግንኙነት ስለነበረኝ ምን ያህል እንደጎዳኝ እኔ አውቃለሁ። ቁጭ ብለን ሁሉንም የሚሲዮኑን ፕሮግራሞች በአንድ ቦታ ስናመጣው ተስፋ ሰጪ የሆነ ውጤት ያሳያል። ነገር ግን የአንድ ወይም የሁለት ወንጌላዊ ስራና የሚፈፅሙብን ነገር ለብቻው አውጥተን ስናየው ጥረታችን ሁሉ በአፈ-ጢሙ የተደፋ ይመስላል።

 

በዚያው ልክ መልካም ስራ የሚሰሩ ሰዎችም አሉ። በዚያ በነበርኩበት ጊዜ ከፍተኛ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ የምገባው  ከቢሊ ካርል ጋር ችግር ሲኖረኝ ነው። ከፍተኛ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ የምገባው ከእርሱ ጋር ስንጋጭ ነው። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ስሆንና መያዣ እና መጨበጫ ሳጣ ወንጌላዊያን ደግሞ ትክክለኛ ስራ ውስጥ ይሆናሉ፤ አብያተ ክርስቲትናትም እድገት ማሳየት ይጀምራሉ። በዚህን ጊዜ ጥቂቶች ብቻ ይጠፋሉ። አሁንም ነገሮች በዚህ ሁኔታ  ይቀጥላሉ። እናንተም 20 ወይም 30 መስማት የተሳናቸውን ተማሪዎች ከቤተ ክርስትያን ውስጥ እንደሚጠፉባችሁ ነው። ነገር ግን ቤተ ክርስትያን እድገቷን ትቀጥላለች። ሪታ ደግሞ የነበራት ችግር ከእኔ የበለጠ ነበር። ምክንያቱም አብዛኛውን ጊዜዋን የምታሳልፈው ከተማ ውስጥ ስለ ሆነ ነው። ከተማ ውስጥ ሆና ቤተ ክርስትያንን የምትለካው በቤተ ክርስትያኑ ውስጥ ባለው አነስተኛ የሰው ቁጥር ነው። ከዚህም ሌላ መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች የሚሰጡንን ችግሮችንም ትመለከታለች። እነዚህ ሁለቱ ነገሮች እጅግ ያበሳጩአታል። ሁል ጊዜ እዚያው አዲስ አበባ ውስጥ ስለምትሆን ገጠር ውስጥ የሚካሄደውን ታላቅና ተስፋ ሰጪ ስራዎችን የማየት እድል የላትም። የሆነ ሆኖ አዲስ አበባ ውስጥ የምናከናውነው ስራ በማንኛውም ቦታ ለሚሰራው ስራ እጅግ ጠቃሚ ስራ ነው። አዲስ አበባ ውስጥ የቤተ ክርስትያን ስራ እና መስማት የተሳናቸው የማስተማር ስራ ባይኖር ኖሮ የገጠር ውስጥ ስኬት ባልኖረ ነበር።

 

ምንም እንኳ እንደ ላይሌ፣ በኃይሉ፣ እኔ እና ሌሎች እናንተ በቤተ ክርስትያን ስራ ውስጥ ባትሳተፉም ለቤተ ክርስትያን እድገት የማይተካ ሚና አላቹህ። ካርል እና ቤኪ አዲስ አበባ ውስጥ ሆናችሁ እዚያ የሚደርስባችሁን ሁሉ ተቋቁማችሁ ባትመሩን ኖሮ ስራችን ሁሉ ከንቱ ይሆን ነበር። ደጋግሜ ለቤተ ክርስትያን ሽማግሌዎች የነገርኳቸው በዚያ በአስቸጋሪ የመንግስት ለውጥ ወቅት እኛን ያዳነን ካርል እንደሆነ ነው። መንግስት ራሱ መካኒሳ መስማት የተሳናቸው በአስተማማኝ ሰዎች እጅ መሆኑንና በአስተማማኝ ሰው እየተመራ መሆኑን ይገነዘባል። እኔን በተመለከተ በኢትዮጲያ ውስጥ ባለው ተልዕኮ ተስፋ እንድቆርጥ ያደረጉኝ ሁለት ምክንያቶች አሉኝ። አንደኛው በነገሮች ሁሉ ስለታከተኝ ነበር። ምናልባት ከሁለት ዓመት በኋላ ለእረፍት ወደ አገር ቤት መጥቼ ቢሆን ኖሮ ነገሮች ከዚህ የተለየ ሊሆኑ ይችሉ ነበር። በትግል ውስጥ መኖር ታከተኝ። በማንኛውም አገልግሎት ውስጥ ከባድ ውጣ ውረድ ነበርና። እናም ከዚያ ውስጥ መውጣት እፈልግ ነበር። ሁለተኛው ምክንያቴ መስራት የምችለውን ሁሉ አከናውኜ ያጠናቀቅኩ ይመስለኝ ነበር። እናም ሌላ አዲስ ሃይል በአዲስ ሀሳብ እንዲተካ እፈልግ ነበር። ይህ ሁለተኛው ምክንያቴ ከመጀመሪያው ጋር ሳነፃፅር የተሻለ የጀግና ውሳኔ ይመስላል። እነዚህን ነገሮች አሁን ሳስባቸው በፍፁም የተሳሳትኩ መሆኔን ተገንዝቤያለሁ።

 

ምክንያቱም በሌላ መልኩ ማሰብ ነበረብኝ፤ የተጀመረው አገልግሎት እንዳይቋረጥ ማድረግ በሚያስችል መልኩ መታሰብ ነበረበት፤ ይኸው በእናንተ ምክንያት ታላላቅ ስራዎች በዚህን ወቅት እየተከናወኑ ናቸውና። ብዙ እንደ ተሳሳትኩ ተገንዝቤያለሁ። እነዚህን ስህተቶቼን በማንም ሰው ፊት ማመን አልፈልግም ነበር። ካርል እና ቤኪ አሁን እየተናገርኩ ያለሁት በኢትዮጲያ ውስጥ እጅግ ታላላቅ ነገሮች ሰርታችኋል። በዚህ ሀገር ላለው አገልግሎት ከሕይወታችሁ ቀንሳችሁ ለሰጣችሁት ጊዜ ሁላችን ባለ እዳዎች ነን። እንዲህ ብዬ ስነግራችሁ ከልቤ ነው። በግሌ ምናልባት ኢትዮጲያን ብትለቁ ይፀፅታችኋል ብዬ አምናለሁ። ነገር ግን በዚህ ውጥቅ ጥቅ በሞላበት ወቅት ብትለቁ በፍፁም አልፈርድባችሁም። በኢትዮጲያ ያለው የቤተ ክርስትያን ስራ እናንተ በዚያ መስማት በተሳናቸው ት/ቤት በምትሰሩት ስራ ላይ ብቻ የተመሰረተ ነው። ይህንን እውነታ ማንም ሊክደው የማይችል ነውና እናንተም ልትረዱት ይገባል። በመጨረሻም በነገር ሁሉ እግዚአብሔር ያበርታችሁ እያልኩኝ እዚህ ያሉ ወንድሞች ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።

ከልቤ እወዳችኋለሁ

ጆን ኤድ

ምዕራፍ 4 ሐምሌ 15, 1967

የላይሌ እና ፔሪል ሊች አሳዛኝ የመኪና አደጋ ሞት  ከስቶክተን የተገኛ መረጃ ስቶክተን ከሊፎርኒያ

 

በመኪና አደጋ ሶስት ሰዎች ተገደሉ፡- አንድ ልጅ እና  ባልና ሚስት ሚሲዮናዊያን

በመኖሪያ ሰፈር ውስጥ ከፍጥነት በላይ በሚሽከረከር መኪና የዘጠኝ ዓመት ሕፃንና ሁለት ባልና ሚስት ሚሲዮናዊያን ተገደሉ። ከእነዚህም ሟቾች አንደኛው ቶሚ ሱሳ የሚባል ሕፃን ሲሆን በቤቱ አቅራቢያ  መንገድ ዳር ባለው የእግረኞች መንገድ ላይ ሲሄድ ነበር በዚህ መኪና ተገጭቶ የሞተው። ሌሎቹ ሟቾች ላይሌ ሊች እድሜው 58 እና ባለቤቱ ፒርል እድሜዋ 58 የሆኑ በተመሳሳይ አደጋ ሕይወታቸው አልፏል። ይህ ቤተሰብ በኢትዮጲያ ውስጥ በሚሲዮናዊነት  የሚሰሩና ለዕረፍት ወደዚህ የተመለሱ ነበሩ። ከካልፎርኒያ የመንገድ ቁጥጥር ባለስልጣንና ከስቶክተን ፖሊስ በተገኘው መረጃ መሰረት ለአደጋው ተጠያቂ የሆነው  ሰው ኤወርት አራይ ቡኞ የሚባል የጀስማይን ነዋሪ የሆነ ሰው ነው። ይህ ሰው ሎዲ ውስጥ በሚገኝ ኤም እና አር በሚባል ኩባኒያ ውስጥ ተቀጥሮ የሚሰራ ነው። መኪናው በግልፅ ሕፃኑን ገጭቶ 25 ሜትር ከወረወረ በኋላ መንገድ ዳር ያለውን የቁም የመንገድ ዳር ምልክት በመግጨት ሁለቱ ሚሲዮናዊያን በሚያሽከረክሩት መኪና ላይ በመውጣት ይህንን ከባድ አደጋ አድርሷል። ፖሊስ የዓይን እማኞችን ጠቅሶ እንደተናገረው አሽከርካሪው በሕፃኑ ላይ አደጋ ካደረሰ በኋላ ከመኪናው ውስጥ ወጥቶ በደም የተጨማለቀውን ህፃን አይቶ እንደገና ፍጥነቱን በመጨመር በተወሰነ ርቀት ላይ የ54 እድሜ ያለውን ሰው ለጥቂት በመሳት የሚሲዮናዊያኑን መኪና በመግጨትና አደጋ በማድረስ ሊያዝ ችሏል።

 

ሚሲዮናዊያኑ ኮምፓክት በሚባለው መኪናቸው ውስጥ ሆነው የተገጩት ላ ጆላ 1880 በሚባል ስያሜ በሚታወቅ መንገድ ላይ መሆኑን ፖሊስ አሳውቋል። በካልፎርኒያው የመንገድ ባለስልጣን ሰራተኛ ሮበርት ኩርትዝ መሰረት አደጋ አድራሹ ሕፃኑን ከገደለ በኋላ በከፍተኛ ፍጥነት በማሽከርከር ከእነ ሊች መኪና ጋር ከተጋጨ በኋላ ነበር የተያዘው። በዚያን ወቅት ሮበርት ኩርት በሰዓት 70 ማይል እያሽከረከረ አደጋ አድራሹን ይከተለው እንደነበር ተናግሯል። ቡኞ ተጠያቂ የተደረገው በሶስት የመኪና አደጋዎች፣ በነፍስ ግድያ፣ ጠጥቶ በማሽከርከር፣ ከፍጥነት በላይ በማሽከርከር፣ ገጭቶ ለማምለጥ በመሞከር፣ የመንገድ ህግ ባለማክበር እና የለ መንጃ ፈቃድ በማሽከርከሩ ነው። ይህ ሰው የእነ ሊችን መኪና ከገጨ በኋላ በሁለት ሰዎች አማካኝነት ተይዞ ለፖሊስ ተላልፎ እንዲሰጥ ተደርጓል። ቡኞ ፊቱ ላይ በደረሰበት መጠነኛ አደጋ በሳን ጆኪን ጠቅላላ ሆስፒታል እርደታ ተደርጎለታል። ሊች እና ባለቤታቸው በመኪናቸው ውስጥ ተጣብቀው ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን ከአደጋው ቦታ የተነሱትም በእሳት አደጋ ሰራተኞች ነው። እነዚህ ሚሲዮናዊያን በክርስቶስ ቤተ ክርስትያን በኩል ለበርካታ አመታት በኢትዮጲያ ውስጥ ሲያገለግሉ የነበረ ሲሆን አሁንም በዌስት ኮስት ላሉት አባላት ንግግር ካደረጉ በኋላ ነሀሴ 1/1975 ወደ ኢትዮጲያ እንደሚመለሱ እቅድ ነበራቸው። ከአደጋው በፊት እነዚህ ጥንዶች በስቶክተን ውስጥ ከጓደኞቻቸው ጋር ለጥቂት ቀናት ቆይታ አድረገው ነበር። የቶሚ ቤተሰብ እንደተናገሩት ቶሚ የታለር ት/ቤት ተማሪ፣ በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን የ3ኛ ክፍል ተማሪ የሚሆን ሲሆን የካብ ስካውት ክለብ አባል ነበር። ቶሚ አንድ የ11 ዓመት ወንድም አለው። ሁለቱም ልጆች ከአደጋው ጥቂት ቀደም ብለው መክሰሳቸውን ከበሉ በኋላ ለጫወታ ነበር የወጡት።

 

 

ሐምሌ 20, 1967 በካምፕቤል ያለችው የእግዚአብሔር ቤተሰብ ክርስቶስ ቤተ ክርስትያን

ላይሌ እና ፔርል ሊች ተገድለዋል፡ የኢትዮጲያ ተልዕኮ እጣ ፈንታም የማይታወቅ ሆኗል

 

ባለፈው ሳምንት የላይሌ እና ሊች የሞት ዜና በመስማታችን ከፍተኛ ድንጋጤ ወድቆብን ነበር። የቤኪ አባት የሆኑት ላይሌ ከጥቂት ሳምንታት በፊት  በኢትዮጲያ ውስጥ ያለችው የእግዚአብሄር ቤተሰብ የክርስቶስ ቤተ ክርስትያን የተደቀነባትን ፈተና በተመለከተ ለመወያያት ወደ ቤተ ክርስትያናችን መጥቶ ነበር። ይህች በኢትዮጲያ ያለችው ቤተ ክርስትያን በመንፈሳዊው እና አካላዊ አመፅ እና ድቀት ውስጥ የምትገኝ ቤተ ክርስትያን ነች። ባለፈው ሳምንት ከካርል እና ቤኪ ማክዶናልድ አንድ ደብዳቤ ደርሶን ነበር። በደብዳቤያቸውም ውስጥ እንደጠቀሱት በአመቱ መጀመሪያ አከባቢ በኢትዮጲያ ውስጥ ያለውን የተልዕኮ ስራቸውን አቁመው ወደ አመሪካ ተመልሰዋል። የነዚህ ጥንዶች ወደዚህ የመመለስ ጉዳይ  ደግሞ ላይሌ እና ፔርል በዚያ አገር ይሰጡ በነበረው እና አሁን አደጋ ላይ ያለው አገልግሎት የቤተ ክርስትያናችን ዋና ጉዳይ እንዲሆን አድርጎታል። ካርል እና ቤኪ የቤተሰባቸውን ሞት እንደ ሰሙ በቀብር ስነ ስርዓት ላይ ለመገኘት ወስነው አሜርካ የደረሱት ሀሙስ እለት ነበር።

 

በዚህ እያሉም በኢትዮጲያ ስላለው የጌታ አገልግሎት የወደ ፊት ዕጣ ፈንታ በተመለከተ ከቤተ ክርስትያናችን ሽማግሌዎች እና ስቶክተን ካለችው የቤተ ክርስትያን ሽማግሌዎች ጋር ይወያያሉ። ካርል እና ቤኪ በቋሚነት ወደ ሀገራቸው ለመመለስ እቅድ እንዳላቸው የሚያመላክቱ ፍንጮችም አሉ። ላይሌ እና ፔርል በኢትዮጲያ ውስጥ እያከናወኑ የነበረውን ስራ ተረክበው የማስቀጠል አማራጭ እንዲይዙ ግፊቶችም እየተደረጉ ናቸው። የላይሌ እና የፔርልን ህይወት የቀጠፈው የመኪና አደጋ በቀጠናው ሰፊ ዜና ሆኖ ስለ ከረመ ዝርዝር ሁኔታውን ሰምታችኋል የሚል እምነት አለን። ምናልባት ካልሰማችሁም እነዚህ ባል እና ሚስት በመኪና አደጋ የተገደሉት በስቶክተን ካሊፎርኒያ ሲሆን አደጋ አድራሹ ሌላ አደጋ ካደረሰ በኋላ ለማምለጥ ሲያደርግ በነበረው ሁኔታ ውሰጥ ነበር የእነዚህን አገልጋዮች ነፍስ የነጠቀው። ፖሊስ እንዳመለከተው ይህ አደጋ አድራሽ ላይሌ እና ፔርል ያሽከረክሩ የነበረውን መኪና በሚገጭበት ጊዜ ይጓዝበት የነበረው ፍጥነት በሰዓት 75 ማይሎች ነበር። ከዚህ ግጭት ጥቂት ደቂቃዎች ቀደም ብሎ ይህ አደጋ አድራሽ የ9 ዓመት ልጅ ገድሎ ነበር።

 

ምዕራፍ 5 ሰላምን መሻት እና ጌታን መፈለግ  1968 የመኸር ወቅት

አብሊን ቴክሳስ

 

በአስራ ሰባት ዓመቴ ለዚያውም በዚያ በአፍላ እድሜ ላይ እያለሁ በውጭ ሀገር የአገልግሎት ልምድ ለማግኘት እና ለማገልገል ከወላጆቼ ጋር ወደ ኢትዮጵያ ሄድኩ። በዚያ አገልግሎት አራት ዓመታት ውስጥ ብዙ ሁኔታዎች ተለዋውጠዋል። ጥሩ የወጣትነት የፍቅር ጊዜ አሳልፌያለሁ፤ ትዳር መስርቻለሁ፤ የመጀመሪያ ልጄን ወልጃለሁ። ይሁንና አንድ የስልክ ጥሪ የሕይወቴን አቅጣጫ እንዲቀየር አድርጋለች። ያቺ የስልክ ጥሪ ልትለወጥ በማይችል መልኩ አስደንጋጭ እና አሳዛኝ ሊታመን የማይችል መልዕክት አድርሳኛለች። እናትሽና አባትሽ በመኪና አደጋ ሞተዋል የሚል መልእክት። እኔና ባለቤቴ ካርል ሊታመን የማይችል የሚመስለውን እውነታ ሰማን፤ ግራ ተጋባን። ከዚህ አሳዛኝ መልእክት በፊት ግን ቤተሰቦቼ ወደ ኢትዮጵያ የሚመለሱበት ቀን፤ በናፍቆት እንጠባበቅ ነበር። ሶስት ወራት ያክል ከቤተሰቦቻችን ርቀን መቆየት ማለት እጅግ ረጂም ጊዜ ነው። በሕይወታችንና በክርስቶስ ስራ ውስጥ ከነበራቸው የተከበረ ሚና በተጨማሪ እናቴና አባቴ የስራ ባልደረቦቻችንና ጓደኞቻችን ነበሩ። እናም አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ አጣናቸው። የሞታቸውን አሳዛኝ ዜና የሰማነው ተመልሰው ኢትዮጵያ ይደርሳሉ ተብሎ በሚጠበቅበት ቀን ነበር። ከአደጋው ቀደም ብሎ በካሊፎርኒያ ባረፉበት ጓደኛቸው ቤት ብዙ ወዳጆች፣ ዘመድ አዝማድና ጓደኞች ይጎበኙአቸው ነበር። በሚቀጥለው ቀን በፍጥነት መንገድ ላይ በስካር ያሽከረክር የነበረው ሰው ሕይወታቸውን ቀጠፈ፤ ላይመለሱ እንዲያሸልቡ ምክንያት ሆነ። ከአደጋው በኋላ ሕይወታቸው ያለፈው ወዲያው ነበር ። ከተጨፈላለቀው መኪና ውስጥ ሞተው የተገኙት ተቃቅፈው ነበር።

 

በዚህ አሳዛኝ እና እንደ መቅሰፍት በሆነ አደጋ ደንዝዘን ህልም በሚመስል ሁኔታ ነበር እኔና ባለቤቴ ካርል የመጀመሪያ ሴት ልጃችንን ይዘን ወደ አሜሪካ የተመለስነው። በቤተሰቦቼ ሞት ምክንያት ወደ አሜሪካ ተመልሼ ብዙም ሳልቆይ ነበር ሊቆርጥልኝ በማይችል ሀዘን ውስጥ የገባሁት። ይህ ሀዘን ደግሞ ለብዙ ዘመን ከነበርኩበት ኢትዮጵያ በመራቄ ነበር። በእነዚያ ውብና ውድ ህዝቦች የተያዝኩት በፍቅር ብቻ ሳይሆን ከእናትና አባቴ ጋር ሆኜ የተለየ ህይወት ቁርኝትም ነበረኝ። እናም ሁል ጊዜ እራባቸዋለሁ። በዚህን ወቅት እነዚያ ከልቤ የማፈቅራቸው የኢትዮጵያ ሕዝቦች በሚያሳዝን መልኩ የሕይወቴ አካል የመሆናቸው ነገር ያበቃ ይመስላል። ከቤተሰቦቼ አሳዛኝ ሞት አንድ ዓመት በኋላ በ1976 ከመያቋርጥ ሀዘንና ተስፋ መቁረጥ እላቀቅ ዘንድ ወደ አምላኬና ፈጣሪዬ መንበርከክ መረጥኩ። በሀዘን ብዛት ውስጤ የሞለውን ባዶነትና ራቁትነቴን ሊሞላልኝ ለሚቻለው ጌታዬን አብዝቼ ለመንኩት። ግንዛቤ ስላልነበረኝም በዚህ የተነሳ ይህ በሕይወቴ ውስጥ የመጀመሪያ እርምጃ መሆኑን አላወቅኩም ነበር። ይህ ጌታን ለመልበስ የመጀመሪያው ቅድመ-ሁኔታ ነው። እያደግሁ ስሄድ ትክክለኛ ወደ ሆነው ቤተ ክርስትያን በመሄድ ለሀጢዓት ስርዬት በመጠመቅ ክርስትያን መሆን እንደሚቻል ተምሬ ነበር። በዚያ ትምህርት ላይ በመመርኮዝ ክርስቲያን የሆንኩ ይመስለኝ ነበር። በእርግጥ መንፈስ ቅዱስ ያለሁበትን ትክክለኛ ገፅታና ደረጃ ያውቅ ነበር። ጌታን የማገኝበት ትክክለኛ ጊዜ አሁን መሆኑን ተረድቼ ነበር። ጌታ በሚያስደንቅና በሚያስገርም በሚያስፈልገኝ መልኩ ልቤን በሰላሙ ሞላው። ጌታ ከእኔ ጋር እንዳለ እኔም በሚገኝበት እንደሚሆን ገለፀልኝ።

 

 

ምዕራፍ 6 ጌታን በመውደዴ ተገለልኩ የማግለያ ደብዳቤ ህዳር 5, 1973

ለቤኪና ካርል

 

ይህን ደብዳቤ ስጽፍላችሁ እጅግ ደስ እያለኝ ነው። ፖረትላንድን ከለቀቅንበት ጊዜ ጀምሮ ስለ እናንተ እያሰብኩና ለአምላኬም እየፀለይኩ ነበር። ስለ እናንተ በተለየ ሁኔታ እንደምናስብና እንደሚያሳስበን ልንገልፅላችሁ እንፈልጋለን። ይህንን ደብዳቤ ለመፃፍ ያስገደደንም ይኸው ነው። ህዳር 4 እና 5/1980 እምነትሽንና አዲስ ልምምድሽን በተመለከተ ተነጋግረን ነበር፡፡ ለውይይታችን ምክንያት የሆነኝ ከኢትዮጵያ እንደመምጣትሽ የተለየ እምነት መያዝ የለብሽም ለማለት ነበር፡፡ እግዚአብሔር ወደ ትክክለኛ ቃሉ እንዲያመለክትሽ ለቃሉ ተገዢ እንድትሆኚ እፀልያለሁ፡፡ አንቺ የእግዚአብሔር ልጅ እና መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን የምትናገሪ ሰው ነበርሽ፡፡ አንቺ ክርስትያንና የክርስቶስ አካል ነበርሽ፡፡ የተማርሽውም ትምህርት ያው የጌታን ቃል ነበር፡፡ ነገር ግን ካደረግነው ረጂም ውይይታችን ከቤተ ክርስትያናችን ውጪ መሆንሽንና ሰው ሰራሽ የሆነውን የሀይማኖት ድርጅት አባል መሆንሽን ስረዳ በጣም ነው ያዘንኩት፡፡ በሕይወታችን ውስጥ የእምነታችን መመሪያ ማድረግ ያለብን የእግዚአብሔርን ቃል ብቻ ነው፡፡ በዚህን ሰዓት የምትጠይቂውን ጥያቄ በመጠየቅ እግዚአብሔርን ማስደሰት አትችዪም፡፡ ጥያቄውም እግዚአብሔርን የሚያስደስት አይደለም፡፡ እኔ የተረዳሁት የጴንጤ ቆስጤ አስተምህሮ ውስጥ እንዳለሽና ይህንንም እያስተማርሽ ነው፡፡

 

የእነርሱ ዶክትሪን እንደ እግዚአብሔር ቃል ለመሆኑ እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ በውይይታችን ወቅት ስለ ጥምቀት፣ በልሳን ስለ መናገር፣ ስለ ተዓምራት እና የመሳሳሉት እግዚአብሔርን ቃል የሚቃራኑ ናቸው፡፡ ሁሉን አይተሽ እና ተገንዝበሽ የእግዚአብሔርን ቃል ወደ መቀበል እንድትመለሽ እፀልያለሁ፡፡ በሰማይ ያለው አባታችን ዛሬ የሚናገረው በልጁ በኩል ነው። ይህን በዕብ 1፡1­ እና 2 ላይ እናገኛለን፡፡የእምነት ጉዳይ በስሜት አይደለም፡፡ ቤኪ በግልፅ ልነግርሽ እፈልጋለሁ ከአንቺ የተገነዘብነው የስሜት ጉዳይ ነበር፡፡ ፖርተላንድ በነበርንበት ጊዜ ሁሌ ታለቅሽ ነበር፣ እግዚአብሔር ልዩ በሆነ ሁኔታ ተገልጦልኝ አናግሮኛል ብለሽም ነበር፡፡ ክርስትያን ለመሆን ደግሞ ሁል ጊዜ ማልቀስ አያስፈልግም፡፡ ክርስትያኖች ደስተኞች ናቸው፡፡ ክርስትያኖች በስሜት የሚነዱ ህዝቦች አይደሉም፡፡ እነዚህ ህዝቦች የዳኑ ህዝቦች ናቸው፡፡ በውይይታችን ጊዜ ግልጽ ሆኜ ነበር የቀረብኩሽ፡፡ በመሆኑም በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆነሽ እኔ ከአንቺ ጋር ምንም ህብረት አይኖረኝም፡፡ ንሰሃ ገብተሽ መመለስ አለብሽ፡፡ የተማርሽውንና ተቀብለሽ የነበረውን ትተሽ በመሄድሽ በንሰሃ ካልተመለስሽ ከህብረታችን አግድሻለሁ። ሮሜ 16፡16 እና 17 አንብቢ፡፡ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰሽ አብረን በህብረት የምንዘልቅ ነበር የመሰለኝ ነገር ግን  የጴንጤ ቆስጤን ዶክትሪን እስከ ተከተልሽ ድረስ በፍጹም አንፈልግሽም፡፡

በሀይሉ እና አለም

ምዕራፍ 7 እርቅ ጥር 1973

ለኒውበርግ ላለችው የቤተ ክርስትያን ሽማግሌዎች

 

ይህን ደብዳቤ ለመፃፍ ያነሳሳን ያደረግናቸውን አንዳንድ ለውጦች ልናሳውቃችሁ ወደን ነው፡፡ በህዳር 26/1968 ከኢትዮጵያ ከተመለስን በኋላ መኖሪያችን በአብሊን ቴክሳስ ውስጥ አድርገናል። ለዚህም ምክንያቱ በቅርቡ በቤኪ እናትና አባት ላይ በደረሰው የሞት አደጋ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ በተከሰተው አመፅ እና ከብዙ ቆይታና ከቤተሰባችን የሞት አደጋ ጋር ተያይዞ እዚህ ባጋጠመን ማሕበራዊ ቀውስ የተነሳ ነው። ከዚህም ሌላ በአጋጠመን በእነዚህ ሁሉ ቀውሶች ውስጥ በምንገኝበት በአሁኑ ጊዜ ከቤተ ክርስትያን የሚደረግልን አንድነት አብሮነት እንደሚገባን ሆኖ አላገኘነውም። ምንም እንኳን በቤተ ክርስትያን ጉዳዮች ውስጥ መሳተፍ ብንፍለግም ከደረሰብን ውስብስብ ችግሮች የተነሳ በጥልቀት የምንፈልገውን የአንድነትና መንፈሳዊ እርዳታ ከቤተ ክርስትያኗ ልናገኝ አልቻልንም። በዚህ ከምን ጊዜውም የበለጠ መንፈሳዊ እርዳታ በምንፈልግበት ጊዜ ተገፍተን ከቤተ ክርስትያኗ ወደ ዓለም ጫፍ የተጣልን ስለሆነ የምንፈልገውን መንፈሳዊ እርካታ ፍለጋ ስንል ወደ እዚህ ወደ አብሊን ልንዛዋር ችለናል። ሌላ ምንም ምክንያት የለንም። ወዲያውም እግዚአብሔር የነገሮቻችን ምንጭ እና ምንም እንደማያሳጣን የተረዳን ቢሆንም በተቃራኒው አሉን ያልናቸው ሁሉ በአደጋ ውስጥ እና በሀዘን ውስጥ ጥሎን ሄዷል። ይህንንም በአይናችን አይተን አረጋግጠናል። በእነዚህ ሁሉ እውነታ ተገፍተን የክርስቶስ ቤተ ክርስትያንን በመተው ወደ ሌላ ቤተ ክርስትያን ሄደናል።

 

እዚህም በመንፈሳዊ ሕይወታችን እያደግን ጌታችንም ከውስጥ ልባችን በመፈለጋችን ምክንያት ስብራታችን ሊጠገን ችሏል። ወደ ኒውበርግ የመጣነው በጥር ወር 1971 ሲሆን የቤኪ እናትና አባት ያመልኩበት ለነበረው የክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ውስጣዊ ቀረቤታ ያለን መስሎን ሰለተሰማን በዚህ በአስቸጋሪ ወቅት መንፈሳዊ እርዳታ እናገኛለን ብለን ነበር። ነገር ግን በአብሊን ውስጥ ከቤተ ክርስትያኗ ባጋጠመን የማግለል አደጋ እና በዚህም ምክንያት በደረሰብን መንፈሳዊ ስብራት የክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ምቹ የእምነት ቦታ ሆኖ አላገኘነውም። በመሆኑም ከ1972 መጀመሪያ ጀምሮ የቤተ ክርስትያን አንዳንድ ዶክተሪን በመመርመር ከተሳሳተው ሀሳብ መመለስ ጀመርን። ባለፈው ወር ወንድሞቻችንን ለመጎብኘት ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰን ነበር። በዚያ ስንደርስ የጠበቀን ግን  ከክርስትያኖች የማይጠበቅና እጅግ አሳዛኝ የሆነ ክስተት ነበር። ይኸውም ያፅናኑናል፤ ይቀበሉናል ያልናቸው የምንወዳቸው ወንድሞች በኃይሉ እና ደመረ ከማህበራችን አስወግደውን ጀርባቸውን አዙረውብን ጠበቁን። ከዚህ በላይ ስብራት ምን አለ? ቀጥለንም ወንድሞች ከሆኑት ከወንድም በኃይሉ እና ደመረ ጋር ስንወያይ የተረዳነው ቤታችን በክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ውስጥ እንደ ነበረ ነው። እናም በትህትና የምንጠይቀው ከማህበር የመገለላችን ጉዳይ እንደገና እንዲታይልን ዳግም ወደ ማህበሩ እንድትመልሱን ነው።

በጌታ ስም

ካርል እና ቤኪ ማክዶናልድ

 

ከበኃይሉ የተላከ ደብዳቤ የካቲት 17, 1973

ውድ ለሆናችሁ ለካርል፣ ቤኪ እንዲሁም ቤተሰባችሁ

 

የእናንተን መልዕክት በማግኘቴ በጣም ደስ ብሎኛል። ጊዜያችሁን ወስዳችሁ ይህንን ደብዳቤ በመፃፋችሁና ለልጄ ለርብቃም የተቻላችሁን እገዛ በማድረጋችሁ በጣም አመሰግናለሁ። እሷም የላካችሁላትን ነገር ለመቀበል በጉጉት እየጠበቀች ትገኛለች። ጤንነቷም መልካም ነው። እግዚአብሔር ይመስገን። በእውነት እግዚአብሔር ልጆቹን ይጠብቃል። ካርል እና ቤኪ  በኢትዮጵያ ባደረጋችሁት ጉብኝት እጅግ ረክቻለሁ። እንደገና በቤታችሁ ሆናችሁ ስላገኘኋችሁም ተደስቻለሁ። ከሁሉ በላይ እንደገና ወደ ጌታ ቤት በመመለሳችሁ እጅግ ደስ ብሎናል። ካርል እና ቤኪ ትክክለኛ ውሳኔ ወስናችሁ ከጌታ ጋር በመታረቃችሁ በእናንተ እጅግ ኮርቻለሁ። እንዲህ አይነት ውሳኔ ለመወሰን ትልቅ ጀግንነትና ለጌታም ታላቅ ፍቅር እንዲኖረን ያስፈልጋል። ጌታን ለማገልገል ያላችሁንም ታላቅ ውሳኔያችሁን  ስመለከት በጣም ደስ ብሎኛል። ማን እንሁን፤ የትም እንኑር፤ የትኛውንም ቋንቋ እንናገር ለክርስትያኖቸ የሚያስፈልገውን እንዲህ ዓይነቱ ውሳኔና ፍላጎት ነው። በአገልግሎቱ ውስጥ በፀናንበት ነገር ሁሉ ጌታ ይባርከናል። በአሁኑ ጊዜ በከተማችን ውስጥ ከአንድ ቤተሰብ ጋር መፅሐፍ ቅዱስ እያጠናሁኝ ነው። የቤተሰቡ አባወራ ታደለ ይባላል። ታስታውሱ ከሆነ  እናንተ እዚህ እያላችሁ ነጯን ፔጆ የሚነዳ ሰው ነው። ስድስት ልጆችና ቆንጆ ሚስት አለችው። ባለፈው ሳምንት ወንጌልን ታዞ በቤተ ክርስትያን ላይ ተጨምሯል። ይህንን ወንድም በቤተ ክርስትያን ውስጥ በማየቴ ክብር አለኝ።  በጣም ሀብታምና ተፅኖ ፈጣሪ የሆና ሰው ነው። ሁለት ትልልቅ ቤቶችም አሉት።

 

ከንብረቱም በላይ ጌታን ይወዳል። ሚስቱና የመጀመሪያ ሴት ልጁ ነገ ይጠመቃሉ። በዚህ ሳምንት ሌሎች ሁለት ወጣቶችንም አጥምቀናል።  ለዚህ ታላቅ ስራው እግዚአብሔርን እናመሰግናለን። ታደለ አንድ መስማት የተሳናት ልጅ እዚህ እኛ ዘንድ አለው። ስሟም ገነት ይባላል። ደመረም እርሷን መፅሐፍ ቅዱስ ሊያስጠናት ነው። መስማት የተሳናቸው ት/ቤታችንም የሁለተኛ መንፈቀ ዓመት ትምህርቱን ጀምሯል። ተማሪዎችም ዳግም ወደ ት/ቤት በመመለሳቸው በጣም ደስተኞች ናቸው። በትምህርት ቤት በኩል ሁሉም ነገር መልካም ነው። ጆኔድ እንደተገናኛችሁ ፅፎልኛል። በመገናኘታችሁ ደስ እንዳለውም ነግሮኛል እርሱ ይወዳችኋል። ስለ እናንተም ብዙ መልካም ነገሮች አሉት። የላካችሁልንን ቼክ ተቀብያለሁ። ይህን ገንዘብ ስለላካችሁልን አመሰግናለሁ። በከምባታ ውስጥ ለ6 ቀናት የቆየ ሰሚናር ነበረን። በዚያ ቆይታችን ወቅት በጋራ ሆነን ፀልየናል፣ ዘምረናል እንዲሁም ተማምረናል። በዚህ ቆይታችን ሁላችንም ተባርከናል፤ ተፅናንተናል። ለዚህ ሁሉ እግዚአብሔርን እናመሰግናለን። አልማዝም ደውላ የተላከላትን ቀሚስ እና ሌሎችንም ነገሮች መቀበሏን ነግራኛለች። ዳዊትና ቤተሰቡም የድርሻውን መቀበላቸውን እንዲሁ ነግሮኛል። ጊዜያችሁንና ገንዘባችሁን ሰውታችሁ ይህን ሁሉ ስላደረጋችሁ እግዚአብሔርን ይባርካችሁ። በጌታ ወንድማችሁ እና እህታችሁ የሆንን

በኃይሉ እና ዓለም

ከደመረ የተላከ ደብዳቤ

 

 

መጋቢት 7, 1976

ውድ ለሆናችሁ ካርል፣ ቤኪ፣ ዊንዲ እና ታላቅ ለሆንከው ለፒተር

 

ይህን ደብዳቤ የምጀምረው ይቅርታ በመጠየቅ ነው። ምክንያቱም ደብዳቤ መፃፍ የነበረብኝ ይህንን ያህል  በመዘግየት አልነበረብኝምና ነው። ቶሎ ልጽፍላችሁም ይገባኝ ቢሆንም የስራ ጫና ስለነበረብኝ እና ነገሮች ባለመመቻቸታቸው ይህን ያህል  ቆይቻለሁ። እዚህ ያለብኝን የስራ ብዛት በዚህ ደብዳቤ በሙሉ ዘርዝሬ ልነግርሽ አልችልም። ሌላ ቀርቶ ቀደም ሲል እናደርግ እንደነበረው ወደ ሲዳማ እና ከምባታ በመሄድ እዚያ ያለውን የስራ ሁኔታ መጎብኘት አልቻልንም። አዲስ አበባ ያለው የትምህርት እና የቤተ ክርስትያን ስራ በጣም ጥሩ ነው። የቤተ ክርስትያን ስራን በተመለከተ እሁድና ረቡዕ ለአምልኮ እና ትምህርት የሚመጡ ሰዎች ብዙ ናቸው። የማስተማሩንና የመስበኩን ጉዳይ እኔና በኃይሉ ጠንክረን እየሰራን ነው። መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በሚገርም ሁኔታ እየጨመሩ ናቸው። በዚህን ዓመት 123 ተማሪዎችን በትምህርት ላይ ናቸው። ብዙዎች ደግሞ ለሚቀጥለው ዓመት ተራቸውን የሚጠብቁ አሉ። በመሆኑም 17 ተማሪዎች በጀማሪ ሀ ውስጥ እንዲሁም 16ቱን ደግሞ በጀማሪ ለ ውስጥ ለመመደብ ተገድጃለሁ። በተመሳሳይ መልኩ የአንደኛ ክፍል ተማሪዎችም በዚሁ መልክ ነው የደለደልኳቸው። በሲዳማ ሴንተሪያ ማስማት የተሳናቸው ትምህርት ቤት ውስጥ 26 ተማሪዎች አሉ። በከምባታ ማዞሪያ ደግሞ 20 ተማሪዎች ያሉ ሲሆን በእነዚህ በያንዳንዱ ቦታ 3 መምህራኖች አሉ። ይህ እንግዲህ ደያሞንና ወልዴን የሚጨምር ነው። ደያሞን በተመለከተ በሚቀጥለው መስከረም ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ወደ አሜሪካ እንዲመጣ ታስቧል።

 

ችግሩ ግን ይህንን ሰው የሚተካልን ሰው አላዘጋጀንም። ወልዴ ደግሞ የሚኖርበትን ቦታ በተመለከተ ደስተኛ አይደለም። በክፍያም ቢሆን በዚያ አካባቢ እና ከእኛ እኩል ተከፋይ ስላልሆነ በእጅጉ ደስተኛ አይደለም። ጆን ኤድ እና ባለቤቱ እዚህ በነበሩ ጊዜ ምክር ብጤ ነገር ለግሰውት የነበረ ቢሆንም በአግባቡ የሰማቸው አልነበረም። እናም እነርሱ ከሄዱ በኋላ ተቀውሞውን ማሰማት ጀምሯል። እንግዲህ እንደምትመለከችው ብዙ ችግር እጅግ ብዙ ስራ እንዲሁም በእጅጉ ብዙ መፍትሄ ማፈላለግ የሚያስፈልግ ነበር። ነገር ግን የሁሉ ጌታ የሆነ የጥበብ እና የእውቀት ሁሉ ባለቤት የሆነው አምላክ እንዲረዳን እና በውሳኔያችን ጊዜ ሁሉ እንዲመራን በየቀኑ እንማፀነዋለን። በእርግጥ እዚህ ብትሆኑ ኖሮ በመልካሙም በመጥፎውም ሁሉ ትካፈሉ ነበር። ለላካችሁልኝ ቴፕ እና ጥንድ ጫማ እጅግ አመሰግናለሁ። ነገር ግን ቴፑ የፔፐርዳይን ሲሆን በውስጡ ምንም የለም፤ ባዶ ነው። ምናልባት ወይ ቀድሞውኑ አልተቀረጸበትም ወይም እዚህ ፖስታ ቤት ተሰርዞ ይሆናል። ስለዚህ ከዚህ በኋላ ቴፖችን አትላኪ ምክንያቱም ስለማይደርሰኝ። ወደ ኬንያ በምትሄጂበት ጊዜ እግረ መንገድሽን ወደ ኢትዮጲያ ጎራ እንድትይ የትምህርት ሚኒስቴር ሰዎችን አነጋግሬያለሁ። እነርሱም ምን ችግር እንደሌለው እና መምጣት እንደምትችይ ነግረውኛል። ይህንን ጉዳይ በሚቀጥለው ደብዳቤዬ እነግርሻለሁ። እግዚአብሄር ሁላችሁንም ይባርካችሁ።

ከልቤ እወዳችኋለሁ

ደመረ ቸርነት

እባክሽ ለኒው በሪ ክርስቶስ ቤተ ክርስትያን የከበረ ሰላምታዬን አቅርቡልኝ።

 

 

ምዕራፍ 8 የካርል መሞት ህዳር 26, 1981

የካርል ማክዶናልድ እረፍቱ ዜና

 

የሮበርት እና ባርባራ ማክዶናልድ ልጅ የሆነው ካርል ኢ ማክዶናልድ የተወለደው መጋቢት 23/1939 በሰን ፍራሲስኮ ካሊፎርኒያ ነበር። ያደገውና የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን የተከታተለው በቤይ አከባቢ ሲሆን  የዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን ደግሞ ሳን ጆስ ክልላዊ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ተከታትሏል። የሁለተኛ ድግሪውን ደግሞ የሰራው ማነማውዝ በተባለው የኦሬገን የስነ ትምህርት ኮሌጅ ውስጥ ነው። ከቤኪ ሊች ጋር የተጋባው ጥቅምት 28/1972 በኢትዮጲያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ውስጥ በሚሲዮናዊ ተልዕኮ ስራ ላይ እያለ ነበር። በዚህ የሚሲዮናዊ ተልዕኮ ለሶስት ዓመት ተኩል ከሰራ በኋላ በ1968 ወደ አብሊን ቴክሳስ ተመልሷል። ከ1971 ጀምሮ ደግሞ መኖሪያቸውን ዱዴ በማድረግ ኑሯቸውን ይገፉ ነበር። ይህ ወንድም በሰላም አውራጃ ውስጥ መስማት የተሳናቸውን ተማሪዎች ያስተምር የነበረ ሲሆን ይህንን ስራ ያቆመው ህመሙ ፀንቶበት አልጋ ላይ በዋለበት ጊዜ ነበር። ካርል ኢ ማክዶናልድ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ሰኞ ህዳር 1981 በዚያው በመኖሪያ አገሩ በዱዴ ሲሆን በዚህ ጊዜ ዕድሜው 41 ዓመት ከ8 ወራት እና ከአራት ቀናት ነበር። ሕይወቱን በክብር የሚያስታውሱ በዚሁ ዱዴ የሚኖሩ ቤተሰቡ፡ ባለቤቱ ቤኪ ማክዶናልድ፣ በሳን ጆሴ ካሊፎርኒያ የሚኖሩ እናቱ ባርባራ ማክዶናልድ፣ ሰባት ልጆቹ፡ እድሪስ ማክዶናልድ፣ የሚኖረው ሳን ጆሴ ካሊፎርኒያ፣ ራህዋ ማክዶናልድ፣ ዊንዲ ማክዶናልድ፤ በያን ማክዶናልድ፣ ከዲር ማክዶናልድ፣ ጄይላን ማክዶናልድ ሁሉም የሚኖሩት በዱድ፤ ሁለት እህቶቹ ኤልዛቤት ክላርክ መኖሪያዋ በካሊፎርኒያ ክሬሳንት ከተማ፣ ክርስታል ማክዶናልድ የምትኖራው ካሊፎርኒያ ውስጥ ሰን ጆሴ ከተማ እንዲሁም የሚያውቁት ሁሉ ናቸው። የቀብር ስነ ስርዓቱ የተፈጸመው ሐሙስ ታህሳስ 8 ከሰዓት በኋላ በኒው በርግ ቻፔል ዱዴ ከሚገኘው ክሮስ ሮድ ቤተ ክርስትያን አማካይነት ነበር። የስንብት ስነ ስርዓት የተደረገውም በሜሞሪያል ፓርክ እና በመዕከላዊ የክርስቶስ ቤተ ክርስትያን በኩል በኢትዮጲያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ መካኒሳ መስማት በተሳናቸው ትምህርት ቤት ጭምር ነበር።

 

 

ከበሀይሉ የተላከ የሀዘን መግለጫ ደብዳቤ መጋቢት 6, 1981

ውድ ቤኪ እና ቤተሰብ

 

የካርልን የሞት ዜና ስንሰማ በሁላችንም ላይ ከባድ የሆነ ሀዘን ነበር የወደቀብን። ሰምተን የነበረው እንደ ታመመ ነበር እንጂ እስከ ዛሬ ድረስ መሞቱን አልሰማንም ነበር። በእውነት በሞቱ በጣም አዝነናል። ስለ ደወልሽልን እና ስለ ፃፍሽልን በጣም እናመሰግንሻለን። ይህ የሚያሳየን እስከ አሁን ድረስ ምን ያህል እንደምትወጂን ነው። ምንም እንኳ በእምነት ብንለያይም እጅግ እንወድሻለን እጅግም ናፍቀሽናል። ሁል ጊዜ ስለ አንቺ እና ቤተሰብሽ  እናስባለን። ከሁለት ሳምንታት በፊት እናንተ ያላችሁበትን ጥቂት ስላይዶችን አይተን በእጅጉ አልቅሰን ነበር። ስለ ሁላችሁ እና አብረን ስላሳለፍነው መልካም ጊዜ ሁሉ አምላካችንን እጅግ አከብራለሁ፤ አመሰግንማለሁ። የእግዚአብሄርን መንገድ እንድትከተሉ እና ቃሉን ብቻ እንድትሰሙ አበረታታችኋለሁ። በሁለት ወራት ውስጥ ለመምጣት እቅድ ስላለኝ እንደደረስኩ እደውልልሻለሁ። የእግዚአብሔር መንፈስ ሁል ጊዜ በተለይም በዚህ በሀዘን ጊዜ እንዲመራሽ እፀልያለሁ።

በጣም እንወድሻለን

በሀይሉ ዓለም እና ቤተሰብ

 

ምዕራፍ 9 ለጆን ኤድ ጥር 24, 1992

ከታመቀ ስሜት የመላቀቅ እና እፎይታ የማግኘት ሄደት

 

ውድ ጆን ኤድ

ከአንተ ጋር ግንኙነት ካቆምኩ ብዙ ዓመታት አልፏል። ይህንን ግን እኔ ፈልጌ ሳይሆን በስልጣንህ በሕይወቴ ውስጥ እጅግ ጠቃሚ ከሆኑት ሕዝቦች እንዳልገናኝ በማድረግህ ነው። ዝም ብዬ ሳስብ አንተ ጠቃሚ ከሆኑት ሰዎች አንዱ ነህ። በነገራችን ላይ ነገሮች ሊያያዙ የሚችሉት ባለን ግንኙነት ላይ የተመረኮዘ ይሆናል። እኔ የማስባቸው ነገሮች በአንተ ደረጃ መልስ የሚያገኙ ናቸው፤ አንተ ግን ቆም ብለህ ለማየትም ሆነ ትኩረት ልትሰጣቸው አልወደድክም። ለማንኛውም እውነታው በአንተ እና በእግዚአብሔር መካከል የታወቀ ነው። ለማንኛውም ማለት ያለብኝን ልበል። በመጀመሪያ በጋራ ነበር ተልዕኳችንን ስንፈፅም የነበረው። ከአሜሪካ በኩል አንተ ዋና ደጋፊያችንም ነበርክ። በኢትዮጵያ ውስጥ የገጠመንን ማንኛውንም ውጣ ውረድ ጠንቅቀህ ታውቃለህ። እኔና ካርል የነበሩን ሰዎች እናቴ፣ አባቴ፣ በኃይሉ፣ ደመረ እና አንተ ብቻ ነበራችሁ፤ ሌላ ማንም አልነበረንም። እናም ከእኛ ጋር በመሆናችሁ እድለኞች ነበርን። በአስቸጋሪ ጊዜያችን ሁሉ ትረዱንና ታበረታቱን ነበርና በደስታ ጊዜያችንም ከእኛ ጋር ትደሰት ነበርክ። እናቴ እና አባቴ የተገደሉት ከአንተ ቤት ከወጡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ነበር። ከመሞታቸው በፊት ለመጨረሻ ጊዜ ያዩትና የተነጋገሩት ከአንተ ጋር ብቻ ነበር። በዚህ ዓይነት አደጋ መሞታቸው ደግሞ ለአንተም ጉዳት ነው። ወላጆቼን በዚህ አይነት አሰቃቂ አደጋ ባጣንበት ጊዜ አንተ ከእኔና ከካርል ጋር በመሆን የሀዘናችን ተካፋይ በመሆንህ እድለኞች ነበርን።

 

በዚያን ፈታኝ በሆነ ጊዜ ከወንድሞቼ እና እህቶቼም በላይ  በቅርበት ከእኛ ጋር የነበራችሁ አንተ፣ ደመረና በኃይሉ ብቻ ነበራችሁ። ነገር ግን ወደ አሜሪካ ከተመለስን ወዲህ እኔና ካርል ባደረግነው ነገር የተነሳ በእጅጉ እንደተቀየርክ ይሰማኛል። በዚህ በ25 ዓመታት ውስጥ ድርጊትህ ሕይወቴን ምን ያህል እንደጎዳ በድፍረት ልነግርህ እፈልጋለሁ። ዛሬ ለበኃይሉ ኢሜይል ስፅፍ ስለ አንተ በእጅጉ አስብ ነበር። ከአንተ ጋር ስለነበረን የቀደሞው ዘመናችንን ሳስብ እጅግ እናደዳለሁ። እናም ስለ አንተ እያሰብኩ ለበኃይሉ  ኢሜይል ከመፃፍ ውጭ ምንም አማራጭ አልነበረኝም። በእውነት በኢትዮጵያ ውስጥ የነበረህን ሚና ተጠቅመህ እጅግ ከምወዳቸውና ከማፈቅራቸው ኢትዮጵያዊያን ለይተኸኛል። በእውነት በዓለም ዙሪያ እኔና ካርል ያለንን እምነት የያዙ የክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ሚሲዮናዊያን የሉም? ይህንን አላስብክም ነበር ከምንወዳቸው ኢትዮጵያዊያን ስትለየን? እኛ ግን እምነታችንን ደብቀን ምንም ልናደርግ አልወደድንም፤ ከአንተም የደበቅነው አንዳች ነገር የለም። ራሳችንን ደብቀን ወደ የሚሲዮን ሜዳ መሄድ እንችል ነበር። ያንን ግን አልፈለግንም። ነገር ግን 85% የክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ሚሲዮናዊያን እንደዚህ ናቸው። እኛ ግን አይደለንም። በሕይወቴ ውስጥ ለአንተ እና ለክርስቶስ ቤተ ክርስትያን እውነተኛ የመሆኔን ፍሬ ማየት ትወዳለህ? ከዚያ በፊት ግን 25 ዓመታትን ወደኋላ ሄደህ የእናቴንና የአባቴን አሟሟት ለማስታወስ ፈቃደኛ ነህ?

 

እንደተገደሉ የነበረህን ስሜት አስታውስ። ምን ይመስል ነበር ስሜትህ? በሕይወትህ ውስጥ በዚያ አሳዛኝ ሁኔታ ያጠኸው ሰው ይኖር ይሆን? ከሆነ ግንኙነት ነበራችሁ? ካልሆነ ምን ዓይነት ሀዘን እንደሚጠብቀኝ መገመት ትችላለህ? ስለ ሀዘን የሚያማክሩ ባለሙያዎች ብትጠይቃቸው እናትና አባቱን በአንድ ጊዜ ስላጡ ሰዎች ምን የሚነግሩህ ይመስለሃል? በዚህ ብቻም አታቁም ልክ እነርሱ እንደሞቱ እኔ ወደዚህ መጠሁ፤ ይህም ሌላ ኪሳራ አስከተለብኝ። ይኸውም ከእናትና አባቴ ጋር የነበርኩበትን ሀገር ማጣት፤ ለዚያውም እዚያ ያሉትን የድጋፍ መስመሬ የሆኑት ሁሉ አጠሁ። ጆን ኤድ ማጣትን በተመለከተ በተለያዩ ጊዜያት ተሰቃይቼበታለሁ። ካጣሁትና ከተጎዳሁበት ሰው አንዱ አንተ ነህ። ለማንኛውም እኔን የማስታመም ጉዳይ ላይ አቅም አለህ። እስኪ አንድ ታሪክ ልንገርህ። ካርል ከመሞቱ በፊት ከኤርትራ በማደጎ የወሰድናቸው ልጆች ጉዳይ እንደምታውቅ እርግጠኛ ነኝ። ካርል ከሞተ በኋላ የሰባት ልጆች እናት መበለት ነበርኩ። በእርግጥ በኋላ ትዳር መስርቻለሁ። እነዚህን ልጆች ያሳደኩት ከልጅነታቸው ጀምሮ ነው። ይህም በጣም ከባድ ስራ ነው። እነዚህን ልጆች ሳሳድግ የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች እንደሚያደርሱት ችግር ተመሳሳይ የሆነ ችግር አይቻለሁ፤ ጥላቻን ጨምሮ። ነገር ግን የወደፊት ዕጣ ፋንታቸው መልካም እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ። ከቤት ከመልቀቃቸው በፊት የስነ ልቦና ጫናን ጨምሮ ለተለያዩ ችግሮች ዳረገውኛል።

 

አብዛኛዎቹ ያደጉና ራሳቸውን የቻሉ ቢሆንም ለብዙ ወራቶች ላያቸው አልሻም ነበር። ሁል ጊዜ ለፈተና ያጋልጡኝ ነበር። እኔም ከእነርሱ የሚመጣውን ፈተና ማስተናገድ አልቻልኩም ነበር። እያደጉ በነበሩበት ጊዜ በጉዳያቸው ታላቁን ድርሻ እይዝ ነበር። እነርሱ በሚያነሱት ችግር ምክንያት ምንም የተዘረጋልኝ የእገዛ ስርዓት አልነበረኝም። በሄዱበት ቦታ ሁሉ ጠላቶችን ያፈሩብኝ ነበር። ይህንን ጉዳይ በሚገባ ታስታውሳለህ። በኢትዮጵያ ውስጥ በነበርንበት ጊዜ መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች ያጎረስንበትን እጆቻችንን እንዴት ይነክሱን እንደነበረ። የማደጎ ልጆቼም ተመሳሳዩን ነበር ያደርጉብኝ። ከልጆቼ ጋር አብሮ መልካም ስራዬንና የልጆቼ መልካም አስተዳደግ ያፈርሱ ነበር። ስለዚህ ከልጆቼ ጀርባ ሰዎች ነበሩ። ልጆቼም ከእኔ ይልቅ ሌሎችን ይቀበሉ ነበር። አሁን ነገሮች በትክክለኛ መንገዱ እየሄዱ ስለመሆናቸው የተረዳሁት በጣም ዘግይቼ ነው፤ ሁነቶች ሁሉ እኔን የሚጎዱ አለመሆናቸውን ማለቴ ነው። በኢትየጵያ ውስጥ ካለው ስራችን ጋር በተያያዘ ማስታወስ ያለብኝ ወገኖች የአንተ ልጆች አንተ፣ ደመረ፣ በኃይሉ፣ የወንጌዊያን ማሰልጠኛ ት/ቤት እና አንተ ለእነርሱ ግድ ባይኖርህም መስማት የተሳናቸው ት/ቤት ናቸው።  በእርግጥ በዚያ ያለውን ስራ ከውስጥ እና ከውጭ ጥቃቶች ትከላክከል ነበር። እዚያ ያለውን ሀላፊነታችንን ለመወጣትና የተጣለብንን ሀላፊነት ለመሸከም ድርብ ስራ ነበረብህ።

 

እንደ በሀይሉ፣ ደመረ፣ አባቴ፣ እናቴ ካርል እና እኔ ሁሉ በዚያ ያለውን ተግዳሮት ለመቋቋም ግንባር ቀደም ሚና ነበረህ። ከአንተ ጋር ለመሆን የፈለኩት ግንኙነት ለመፍጠር የፈለኩት ለዚህ ነው። በሌላ መልኩ ደግሞ አንተ በአብዛኛው የክርስቶስ ቤተ ክርስትያንን ዶክትሪን በመከላከል ላይ ብቻ ታተኩራለህ። የክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ክፍተት ያለበትን ቦታ ለመሙላት ጥረት በማደርግበት ጊዜ እኔን ለማጥፋት ትነሳለህ። ይህንን ስታደርግ ያለሁበትን አስቸጋሪ ገፅታ እንኳን ለመመዘን ጥረት አታደርግም። አስኪ ልጠይቅህ ወላጅ አልባ ህፃናት ናቸው ወይስ ዶክትሪን መጠበቅ ነው የበለጠ ግድ የሚልህ? በጉዳት ምክንያት የማለቅሰውን እኔን በፍቅር ሸፍነህ ማፅናናት ነው ወይስ ዳር ዳር እያልክ አስፈላጊ ባልሆነ መንገድ በህይወቴ ውስጥ አስፈላጊ ከሆኑት ሰዎች ታቆራርጠኛለህ? ጆን ኤድ ከፍተኛውን ከበሬታ ነበር አቀርብልህ የነበረው። ለባሀይሉና ለደመረም እንዲሁ። ነገረር ግን የፈፀምከው ነገር ስህተት ነው። ካለማወቅና ከመሰልቸት የተነሳ ይሆናል ብዬ አምናለሁ። በእኛ ላይ የፈፀምከውን በገዛ እህትህ ላይ ትፈፅማለህ? ከቤተሰቤ አንፃር ያለኸን አንተ ብቻ ነበርክ። ይህንን ጥላቻ በእኔ ላይ ለማድረስ ምን አስቻለህ? በእነዚህ ጉዳዮች ከአንተ መስማት እፈልጋለሁ።

እወደሃለሁ

ቤኪ

 

ጥር 24, 1992

 ለውድ በኃይሉ

 

ታሪኬ ጠቃሚ የሆኑ ሰዎችን በማጣት የተሞላ ስለሆነ ምናልባት አንተንም እንዳላጣ ለጊዜው ማንነቴን ባልገልፅልህ ይሻላል። ነገር ግን እግዚአብሔር በሁሉ ነገሮቼ ውስጥ ከእኔ ጋር ስለ ነበረ እዚህ አድርሶኛል። አንተ እና ደመረ ሁል ጊዜም ቢሆን ተናፋቂዎቼ ናችሁ። የሆነ ሆኖ ከአንተም ጋር ግንኙነት ካቆምኩ ብዙ ዓመታት አልፏል። ይህንን ግን እኔ ፈልጌ ሳይሆን በስልጣንህ በሕይወቴ ውስጥ እጅግ ጠቃሚ ከሆኑት ሕዝቦች እንዳልገናኝ በማድረግህ ነው። ዝም ብዬ ሳስብ አንተ ጠቃሚ ከሆኑት ሰዎች አንዱ ነህ። ነገሮች ሊያያዙ የሚችሉት ባለን ግንኙነት ላይ የተመረኮዘ ይሆናል። እኔ የማስባቸው ነገሮች በአንተ ደረጃ መልስ የሚያገኙ ናቸው፤ አንተ ግን ቆም ብለህ ለማየትም ሆነ ትኩረት ልትሰጣቸው አልወደድክም። ለማንኛውም እውነታው በአንተ እና በእግዚአብሔር መካከል ይታወቃል ሆኖም ማለት ያለብኝን ልበል። በመጀመሪያ በጋራ ነበር ተልዕኳችንን ስንፈፅም የነበረው። በኢትዮጵያ ውስጥ የገጠመንን ማንኛውንም ውጣ ውረድ ጠንቅቀህ ታውቃለህ። እኔና ካርል የነበሩን ሰዎች እናቴ፣ አባቴ፣ ደመረ እና አንተ ብቻ ነበራችሁ፤ ሌላ ማንንም አልነበረንም። እናም ከእኛ ጋር በመሆናችሁ እድለኞች ነበርን። በአስቸጋሪ ጊዜያችን ሁሉ ትረዱንና ታበረታቱን ነበርና፤ በደስታ ጊዜያችንም ከእኛ ጋር ትደሰት ነበር። ወላጆቼ በአደጋ በሞቱበት በዚያን ፈታኝ በሆነ ጊዜ ከወንድሞቼ እና እህቶቼም በላይ በቅርበት ከእኛ ጋር የነበራችሁ አንተ፣ ደመረና ጆኔድ ብቻ ነበራችሁ።

 

ነገር ግን ወደ አሜሪካ ከተመለስን ወዲህ እኔና ካርል ባደረግነው ነገር የተነሳ በእጅጉ እንደተቀየርክ ይሰማኛል። በዚህ በ25 ዓመታት ውስጥ ድርጊትህ ሕይወቴን ምን ያህል እንደጎዳኝ በድፍረት ልነግርህ እፈልጋለሁ። በእውነት በኢትዮጵያ ውስጥ የነበረህን ሚና ተጠቅመህ እጅግ ከምወዳቸውና ከማፈቅራቸው ኢትዮጵያውያን ለይተኸኛል። በእውነት በዓለም ዙሪያ እኔና ካርል ያለንን እምነት የያዙ የክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ሚሲዮናዊያን የሉም? ይህንን አላስብክም ነበር ከምንወዳቸው ኢትዮጵያዊያን ስታገለን? እኛ ግን እምነታችንን ደብቀን ምንም ልናደርግ አልወደድንም፤ ከአንተም የደበቅነው አንዳች ነገር የለም። ራሳችንን ደብቀን ወደ ሚሲዮን ሜዳ መሄድ እንችል ነበር። ያንን ግን አልፈለግንም። ነገር ግን 85% የክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ሚሲዮናዊያን እንደዚህ ናቸው። እኛ ግን አይደለንም። በሕይወቴ ውስጥ ለአንተ እና ለክርስቶስ ቤተ ክርስትያን  እውነተኛ የመሆኔን ፍሬ ማየት ትወዳለህ? ከዚያ በፊት ግን 25 ዓመታትን ወደኋላ ሄደህ የእናቴንና የአባቴን አሟሟት ለማስታወስ ፈቃደኛ ነህ? እንደተገደሉ የነበረሕን ስሜት አስታውስ። ምን ይመስል ነበር ስሜትህ? በሕይወትህ ውስጥ በዚያ አሳዛኝ ሁኔታ ያጠኸው ሰው ይኖር ይሆን? ከሆነ ግንኙነት ነበራችሁ? ካልሆና ምን ዓይነት ሀዘን እንደሚጠብቀኝ መገመት ትችላለህ? ስለ ሀዘን የሚያማክሩ ባለሙያዎች በዚህ ላይ ብትጠይቃቸው እናትና አባቱን በአንድ ጊዜ ስላጡ ሰዎች ምን የሚነግሩህ ይመስለሃል? እዚያ ብቻም አታቁም።

 

ልክ እነርሱ እንደሞቱ እኔ ወደዚህ መጣሁ፤ ይህም ሌላ ኪሳራ አስከተለብኝ። ይኸውም ከእናትና አባቴ ጋር የነበርኩበትን ሀገር ማጣት፤ ለዚያውም እዚያ ያሉትን የድጋፍ መስመሬ የሆኑት ሁሉ አጠሁ። በሀይሉ ማጣትን በተመለከተ በተለያዩ ጊዜያት ተሰቃይቼበታለሁ። ካጣሁትና ከተጎዳሁበት ሰው አንዱ አንተ ነህ። ለማንኛውም እኔን የማስታመም ጉዳይ ላይ አቅም አለህ። እስኪ አንድ ታሪክ ልንገርህ። ካርል ከመሞቱ በፊት ከኤርትራ በማደጎ የወሰድናቸው ልጆች ጉዳይ እንደምታውቅ እርግጠኛ ነኝ። ካርል ከሞተ በኋላ የሰባት ልጆች እናት መበለት ነበርኩ። በእርግጥ በኋላ ትዳር መስርቻለሁ። እነዚህን ልጆች ያሳደኩት ከልጅነታቸው ጀምሮ ነው። ይህም በጣም ከባድ ስራ ነው። እነዚህን ልጆች ሳሳድግ የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች እንደሚያደርሱት ችግር ተመሳሳይ የሆነ ችግር አይቻለሁ፤ ጥላቻን ጨምሮ። ነገር ግን የወደፊት ዕጣ ፋንታቸው መልካም እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ። ከቤት ከመልቀቃቸው በፊት የስነልቦና ጫናን ጨምሮ ለተለያዩ ችግሮች አጋልጠውኛል። አብዛኛዎቹ ያደጉና ራሳቸውን የቻሉ ቢሆንም ለብዙ ወራቶች ላያቸው አልሻም ነበር። ሁል ጊዜ ለፈተና ያጋልጡኝ ነበር። እኔም ከእነርሱ የሚመጣውን ፈተና ማስተናገድ አልቻልኩም ነበር። እያደጉ በነበሩበት ጊዜ በጉዳያቸው ታላቁን ድርሻ እይዝ ነበር። እነርሱ በሚያነሱት ችግር ምክንያት ምንም የተዘረጋልኝ የእገዛ ስርዓት አልነበረኝም። በሄዱበት ቦታ ሁሉ ጠላቶችን ያፈሩብኝ ነበር።

 

ይህንን ጉዳይ በሚገባ ታስታውሳለህ። በኢትዮጵያ ውስጥ በነበርንበት ጊዜ መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች ያጎረስንበትን እጆቻችንን እንዴት ይነክሱን እንደነበረ ታስታውሳለህ። የማደጎ ልጆቼም ተመሳሳዩን ነበር ያደርጉብኝ የነበረው። ከልጆቼ ጋር አብሮ መልካም ስራዬንና የልጆቼ መልካም አስተዳደግ ያፈርሱ ነበር። ስለዚህ ከልጆቼ ጀርባ ሰዎች ነበሩ። ልጆቼም ከእኔ ይልቅ ሌሎችን ይቀበሉ ነበር። አሁን ነገሮች በትክክለኛ መንገድ እየሄዱ ስለመሆናቸው የተረዳሁት በጣም ዘግይቼ ነው፤ ክስተቶች ሁሉ እኔን የሚጎዱ አለመሆናቸውን ማለቴ ነው። በኢትየጵያ ውስጥ ካለው ስራችን ጋር በተያያዘ ማስታወስ ያለብኝ ወገኖች የአንተ ልጆች አንተ፣ ደመረ፣ ጆኔድ፣ የወንጌዊያን ማሰልጠኛ ት/ቤት እና አንተ ግድ ባይኖርህም መስማት የተሳናቸው ት/ቤት ናቸው። በእርግጥ በዚያ ያለውን ስራ ከውስጥ እና ከውጭ ጥቃቶች ትከላከል ነበር። እዚያ ያለውን ሀላፊነታችንን ለመወጣትና የተጣለብንን ሀላፊነት ለመሸከም ድርብ ስራ ነበረብህ። እንደ ጆኔድ፣ ደመረ፣ አባቴ፣ እናቴ ካርል እና እኔ ሁሉ በዚያ ያለውን ተግዳሮት ለመቋቋም ግንባር ቀደም ሚና ነበረህ። ከአንተ ጋር ለመሆን የፈለኩት ግንኙነት ለመፍጠር የፈለኩት ለዚህ ነው።

 

በሌላ መልኩ ደግሞ አንተ በአብዛኛው የክርስቶስ ቤተ ክርስትያንን ዶክትሪን በመከላከል ላይ ብቻ ታተኩራለህ። የክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ክፍተት ያለበትን  ቦታ ለመሙላት ጥረት በማደርግበት ጊዜ እኔን ለማጥፋት ትነሳለህ። ይህንን ስታደርግ ያለሁበትን አስቸጋሪ ገፅታ እንኳ ለመመዘን ጥረት አታደርግም። እስኪ ልጠይቅህ ወላጅ አልባ ህፃናት ናቸው ወይስ ዶክተሪን መጠበቅ ነው የበለጠ ግድ የሚልህ? በጉዳት ምክንያት የማለቅሰውን እኔን በፍቅር ሸፍነህ ማፅናናት ነው ወይስ ዳር ዳር እያልክ አስፈላጊ ባልሆነ መንገድ በህይወቴ ውስጥ አስፈላጊ ከሆኑት ሰዎች ማቆራረጥ? በሀይሉ ከፍተኛውን ከበሬታ ነበር አቀርብልህ የነበረው። ለጆኔድና ለደመረም እንዲሁ። ነገር ግን የፈፀምከው ነገር ስህተት ነው። ካለማወቅና ከመሰልቸት የተነሳ ይሆናል ብዬ አምናለሁ። በእኛ ላይ የፈፀምከውን በገዛ እህትህ ላይ ትፈፅማለህ? ከቤተሰቤ አንፃር ያለሀኝ አንተ ብቻ ነበርክ። ይህንን ጥላቻ በእኔ ላይ ለማድረስ ምን አስቻለህ? በእነዚህ ጉዳዮች ከአንተ መስማት እፈልጋለሁ። ለዓለምና ልጆችህ አብዝቼ እንደምወዳቸው ንገርልኝ።

እወደሃለሁ

ቤኪ

 

ምዕራፍ 10 ከ20 ዓመት የኋሊት ጉዞ ማገገም የካቲት 14, 1992

ውድ የሆናችሁ በሀይሉ እና ዓለም

 

ከ20 ዓመታት የኋሊት ጉዞ ማገገም መተረክ ከመጀመሬ በፊት ከአንተ ጋር ትክክለኛ ተግባቦት አለመጀመራችንና ኢሜይል ለመፃፍ እንኳ ሳስብ እንደምሸማቀቅ እና ከብዙ ጸሎት በኋላ ኢሜሌን መፃፍ እንደምጀምር እንድታውቅልኝ እፈልጋለሁ። በዚህ 20 ዓመታት ውስጥ የተማርኩት ታላቅ ነገር ቢኖር እጅግ ከምወዳቸው ሰዎች ተገልዬ መኖር እንደምቻል ነው። በሆነ መልኩ ግን ይህ መገለሌ በራሱ ጓደኛ ሆኖኛል። ምክንያቱም ባዶ አድርጎኝ በትህትና እግዚአብሔር ፊት እንድቆይ አድርጎኛል። ነገር ግን የእኔ ትልቁ ስጋት ኢሜይል በፃፍኩልህ ቁጥር በሚገባ ተረድተኸኝ ከአንተ እና ኒው በርግ ካለችው ቤተ ክርስትያን ያጣሁትን ሁሉ  አገኛለሁ የሚለው ነው። በዚህም ምክንያት ባልተገባ ሁኔታ በኩራት እና ትዕቢት ተወጥሬ ከአምላኬ ጋር ያለኝን ቅርበት ካጣሁ ነው። ይህ ደግሞ እኔን በማግለላችሁ ምክንያት አሁን ከሚደርስብኝ እና ከሚሆንብኝ ሁሉ በላይ የከፋ ኪሳራ ይሆናል። እኔ እንደተለማመድኩት እናንተም እግዚአብሔር ባልቴትና ወላጅ የሞተባቸውን ምን ያህል እንደሚወዳቸው ብትገነዘቡ እና ብትረዱ እንዴት ያለ መልካም ነገር ነው? ጌታ ልባቸው ለተሰበረው ቅርብ ነኝ ብሏል እና እኔም ይህንን በሚገባ አይቻለሁ። በእርግጥ እግዚአብሔር በዙሪያዬ ሆኖ በቅርበት ከእኔ ነው። ከዚህ በተቃራኒም ደግሞ እግዚአብሄር ዝም ያለበትንና ከእኔ የራቀበትንም ጊዜ እንዲሁ ነበር።

 

ይህ የአምላኬ ዝምታ በሕይወቴ ውስጥ ነብሴን እጅግ ያስጨነቀበት እንዲሁም የተሰቃየሁበት ጊዜ ነው። ሰው እግዚአብሔር ርቆት በዚህ ምክንያት የሚመጣበት ስቃይ እንዴት ሊቋቋም ይችላል? በ80ዎቹ ገደማ ልንጎበኛችሁ በመጣንበት ጊዜ እጅግ ከልቤ ተፀፅቼ ነበር፤ አልቅሼ ነበር። እናም ከበፊቱ በተሻለና በተለየ ሁኔታ ነገሮችን ለማከናወን ቃል ገብቼ ነበር። አንተንና እዚያ ያሉትን ሰዎች የምወደው ማሰብ ከምችለው በላይ ነው። መጀመሪያ ወደ ኢትዮጲያ መጥቼ በምኖርበት ጊዜ ከኢትዮጲያዊያን የተሻልኩኝ ነኝ ብዬ አስብ ነበር። እናም እዚያ መሆኔ ከደረጃዬ በታች ያደገኝ እና ዝቅ ያልኩ ያህል ይሰማኝ ነበር። ነገር ግን አሁን አዲስ የሆነውን የእግዚአብሔርን ፍቅር ስለማመድ በእርግጥ ወደ ኢትዮጲያ ተመልሼ ነገሮችን ማስተካከል እንዳለብኝ በጌታ ሆኜ ከማንም ያልተሻልኩ ይልቁንም አገልጋይ መሆን እንደሚገባኝ ተገነዘብኩ። እናም ከእኔ ያንሳሉ ብዬ አስብ ከነበረው ኢትዮጲያዊያን ጋር ለመኖር ከእነርሱ እንደ አንዱ ለመሆን እነርሱ ጋር አንድ መሆኔን  እና ህዝቤ መሆናቸውን ወሰንኩ። አብሬያቸው ኖሬ የጌታን ፍቅር ለእነርሱ ማካፈል ደግሞ የተለየ ትርጉም ይሰጠኛል። ከአሜሪካን ሳልነሳ በፊት የምኖረውም የምሞተውም እዚያው ኢትዮጲያ መሆን አለበት ብዬ ልጆቼን ፒተርንና ዊንዲን ዳግም የማላያቸው መስሎኝ ከልቤ ተሰናብቼያቸው ነበር። እናቴ አንተንና የኢትዮጲያን ሰዎች ምን ያህል እንደምትወዳችሁ ታስታውሳለህ?

 

አሁንም እግዚአብሔር የዚያን ዓይነት ፍቅር የሰጠኝ ይመስለኛል። ከክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ውጭ ሆኜ የማደርገው አንድም ነገር አልነበረኝም። በእግዚአብሔር ፍቅር ደግሞ ሁሉንም ማድረግ እችላለሁ። በክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ውስጥ ስላልሆንን ብቻ ይህንን ማድረግ እንደምንችል እንደማታስብ አውቃለሁ። ይህንን ልታውቅ የምትችለው ምናልባት አብረን ትንሽ ከቆየን በኋላ ይሆናል። እግዚአብሔር በፈለገው ዓይነት ይከብር ዘንድ፤ ይህንንም በግልፅ ለማሳየት ጥልቅ በሆነ ሁኔታ አንተን በጌታ ፍቅር ለመውደድ ከመወሰን ውጭ የለወጥኩት አንዳች ነገር የለም። ይህ ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር የመረጠው እንደገና ወደ ክርስቶስ ቤተ ክርስትያን እኛን መመለስ ነው። እዚያ ስንደርስ አብሮነትህን ካሳይሀን ወደ ክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ለመመለስ የሚያስችለንን ፍቅር ሰጥተኸናልና አብረን ለማምለክ መስማማታችን የሚያሳይ ነው ማለት ነው። ወደ አሜሪካ ስንመለስ ዳግም አብረን ማምለክ እንድንችል እንዲቀበሉን ኒው በርግ ያለችውን ቤተ ክርስትያን ጠይቀን ነበር። እነርሱም በሙሉ ፈቃደኛነት በፍቅር ነበር የተቀበሉን። ከእነርሱ ጋር መሆናችን በእውነት ትልቅ ደስታ ሰጥቶናል። በእውነት ካስደሰተን ነገር ውስጥ ከእነርሱ ጋር ስንቀላቀል እምነታችሁን ቀይሩ አላሉንም። ኢትዮጲያዊያን አሁንም ከልባችን ውስጥ ናችሁ እና ወደዚያ የመመለሱን ነገር እንቀጥላለን። ስቶክተን ውጥ የምትኖረው ኬይዝ ኢቫንስ ወደ ኢትዮጲያ እንድንመለስ ፈቅዳለች።

 

በዚሁ መሰረት ወደ ኢትዮጲያ ለመሄድ የሚያስችለንን ዝግጅት ማድረግ ጀምረን ቪዛችንን ለመውሰድ አመልክተን ሳለን ነበር ካርል በድንገት የሞተው። አጋጣሚ ይመስል በዚህን ጊዜ ጆን ኤድ የኢትዮጲያን ተልዕኮ በበላይነት ለመስራት ሀላፊነት ወሰደ። እርሱ ደግሞ የማይጨበጥ ሰው በመሆኑ ከእርሱ ጋር ለመነጋገርም አልቻልኩም ነበር። እንደመሰለኝ ከሆነ ጆን ኤድ ምንም እንኳ በዚያን ጊዜ በክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ውስጥ ያለን ቢሆንም በእምነታችን ሰግቷል። በመሆኑም እኔና ባለቤቴ ካርል ወደ ኢትዮጲያ የምንመለስበትን ሌላ መንገድ መፈለግ ጀመርን። እናም በሌላ ድርጅት ወደ ኬኒያ የመሄድ እድል አገኘን። ከኒው በርግ ከመልቀቃችን በፊት የቤተ ክርስትያን ሽማግሌ የሆነው ፍሬድ የአምልኮ ሁኔታዬን እንድቀይር አጥብቆ ጠይቆኝ ነበር። በወቅቱ የውይይታችን ትኩረት የነበረው የማጥመቅ ጉዳይ ሳይሆን ክርስቲያን የሆነ የምንለው ማን ነው ያልሆነውስ ማን ነው የሚለው ነበር። በውይይታችን መጨረሻ የነገርኩት ነገር የአምልኮ ስርዓቴን እንደማልቀይር እና ክርስትና በክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ውስጥ ብቻ ከሆነ እና በክርስትና ላይ ያላቸው በጣም ጠባብ አመለካከታቸው ወደ ክርስቶስ የሚያቀርብ ነው በሚሉት የሚፀኑ ከሆነ ክርስትና አስፈላጊ እንዳልሆነ ጭምር ነግሬዋለሁ። ቀደም ሲል የክርስቶስ ቤተ ክርስትያን የአምልኮ ሁኔታ ስለማውቅ በዚያ እምነት ውስጥ ምንም ህይወት እንደሌለ ነው።

 

ይህ ሕይወት አልባ ጉዞ ደግሞ ወደ ትክክለኛ ክርስትና አይወስድም። ለማንኛውም በዚያን ቀን ወደ አፍሪካ እንደምንሄድ ማስታወሻ ተወስዶ ተለያየን። እቅዳችን የነበረው በመጀመሪያ ወደ ሳን ጆሲ ተጉዘን የካርልን ቤተሰቦች ተሰናብተን ቀጥሎም ወደ አፍሪካ ጉዞ ለማድረግ ነበር። ነገር ግን ሳን ጆሲ እንደ ደረስን ካርል በጤንነቱ ላይ አንዳንድ ምልክቶችን መመልከት ጀመረ። እነዚህ ምልክቶች ቸል የማንለው ጉዳይ ሆኖ አገኘን። በኋላም የአንጀት ካንሰር እንዳለበት በህክምና በመረጋገጡ ወዲያው የቀዶ ጥገና ህክምና እንደሚያስፈልገው ተነግሮን ቀጠሮ ተያዘ። ሳን ጆሴ ደግሞ የትውልድ አገሩ እና ያደገበት እንዲሁም የተማረበት በመሆኑና የካምቤል የክርስቶስ ቤተ ክርስትያንም በሚገባ ስለሚያውቁት የካምቤል የክርስትያን ትምህርት ቤት የኢንሹራን ሽፋን ሰጥተውት ከብዙ ሺ ዶላር ወጪ አዳኑን። በዚህን ጊዜ ካርልም ከቀዶ ጥገናው እያገገመ ስለነበር እኛም በቤተ ክርስትያን ውስጥ በንቃት እንሳተፍ ነበር። በቤታችንም በአነስተኛ ቁጥር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ፕሮግራም ነበር። ካርል በክርስትያን ትምህርት ቤቱ ውስጥ ለዓመት ያስተማረ ቢሆንም ልባችን ግን ያለው እዚያው ኢትዮጲያ ውስጥ ነው። እናም ወደዚያ የሚደረገውን ጉዞ ለመጀመር ሙከራ ማድረግ ጀመርን። በዚህን ጊዜም ቢሆን የተረዳነው ነገር ቢኖር ጆን ኤድ ጥሩ ነገር እንደማያስብልን ነው። ነገር ግን በሳን ጆሴ ውስጥ አንድ ድርጅት ወደ ኬኒያ በመሄድ መስማት ለተሳናቸው ትምህርት ቤት የሚከፍትላቸው ሰው ይፈልጉ ነበር።

 

 

በዚህን ጊዜ እግዚአብሄር ለእኛ የራሱ እቅድ እንዳለው ተረድተን በዚህ ድርጅት በኩል ወደ ኬኒያ ሄድን። በዚህ መሰረት ወደ ኬኒያ ሂደን በዚያ ለሶስት ወራት ቆየን። በቆይታችን የተማርነው ነገር ቢኖር ወደዚያ የመሄዳችን ነገር ከፍተኛ ስህተት መሆኑን ተገነዘብን። የድርጅቱ መሪዎችም በብዙ መጥፎ ድርጊቶች ውስጥ እንዳሉ ግንዛቤ ወሰድን። በሶስተኛ ወራችን መጨረሻ ላይ ቪዛችን ያበቃ በመሆኑ ውርደት ሊባል በሚችል ደረጃ ወደ ሀገር ቤት ተመለስን። ድርጅቱ አዋረደን ተስፋ አስቆረጠን ከእግዚአብሄር ጋር የተለያየን ያህል ተሰምቶን ወደ ሀገራችን ተመለስን። እናም ቤታችን ወዳለበት ወደ ኒው በርግ ተመልሰን በዚያ ባለችው የክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ማምለክ ጀመርን። እነዚያ ቀኖች ለእኔ እጅግ አስቸጋሪ እና ጭለማ የሆኑ ቀኖች ነበሩ። የሆነ ሆኖ በጭለማው ውስጥ እንዳልዋጥ እየታገልኩኝ እግዚአብሔር ፈቃዱን እንዲያሳየኝ በፀሎት እተጋ ነበር። ኒው በርግ እንደተመለስን ብዙም ሳንቆይ ወደ አፍሪካ ሳንሄድ በፊት በእምነቴ ጉዳይ አጥብቆ በሀይለ ቃል አናግሮኝ የነበረው የቤተ ክርስትያን ሽማግሌ ቤቴ ድረስ መጥቶ ነበር። እናም እንዲህ አለኝ “ቀደም ሲል ባርከሽኝ ነበር አሁን ደግሞ እኔ ልባርክሽ።” ቀጥሎም ወደ አፍሪካ ለመሄድ ብለን ከተለየነው አንድ ዓመት ከሶስት ወራት ጀምሮ ተመልሰን እንድናገኘው ይፀልይ እንደነበረ ነገረኝ። በንግግሩ ውስጥ በዚያን ጊዜ የነገርኩትን ጉዳዮች እግዚአብሄር እንደነገረው ተረከልኝ።

 

የመጽሐፉን ቃል በአዲስ ብርሃን እንዳየ እና ቃሉም እንደተገለጠለት እኔ የተናገርኩትም እውነት እንደሆነ መረዳቱን ነገረኝ። እናም እግዚአብሔር ወደ ኒው በርግ የመለሳችሁ ስለ መንፈስ ቅዱስ እንድታስተምሩኝ እና በክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ውስጥ ላሉትም የእግዚአብሄርን እውነት እንድታስተምሩ ነው አለኝ። አሁን እንግዲህ ይህ የቤተ ክርስትያን ሽማግሌ ንግግር ምን ያህል እንደሚባርከኝ መገመት ትችላለህ። በድንገት ነገሮችን ይበልጥ መረዳት ጀመርኩ እግዚአብሄር የሚሰጠኝንም አቅጣጫ እና ዓላማ አየሁ። ስለሆነም መንፈሳዊ ስራ ላይ ማተኮር ስላለብን አነስተኛ በሆነ ቁጥር በሳምንት አንዴ ወይም ሁለቴ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በቤታችን ማካሄድ ጀመርን። በዚህም ፕሮግራም ላይ የተለያዩ የቤተ ክርስትያን ሽማግሌዎች፣ ሰባኪዎች እና እውነት ፈላጊዎች ይሳተፉ ነበር። የሰዎች ሕይወትም መቀየር ተጀምሮ ነበር። በሰዎች ላይ ይህንን ለውጥ ማየት ስንጀምር እኔና ካርል ከልክ በላይ የሆነ ደስታ ተሰምቶናል። ነገር ግን ወደ ኢትዮጲያ ለመሄድ ያለን ፍላጎት አሁንም በውስጣችን ይቀጣጠል ነበር። አንድ ክረምት እኔና ካርል መስማት በተሳናቸው ጉዳይ ላይ የተዘጋጀውን ዎርክሾፕ ለመከታታል ኦክልሆማ ሄድን። ይህ ዎርክሾፕ የተዘጋጀው በክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ነበር። በዚህን ጊዜ የሆነ ሰው ወደ ኢትዮጲያ ወይም ወደ ኬኒያ ያለንን ጥሪ እውን ያደርግ ይሆናል ብለን ሀሰብ በእርግጠኛነት ይዘን ነበር።

 

ይህ አጋጣሚ በእጅጉ የኢትዮጲያ ጉዞአችንን የተሳካ የሚያደርግ ይሆናል። ይህ ጉዳይ ግን ሳይሳካ ቀረ። እናም በጣም ተስፋ ቆረጥን። እግዚብሔር ፈቃዱ ቢሆንና ለዚህ ጥሪ አጭቶን ቢሆን በዚህ ጊዜ ኢትዮጲያ ውስጥ እንሆን ነበር። በመጨረሻም ወደ ኢትዮጲያ ያለን ፍላጎት እንደማይሆን አምነን ሀሳባችንን ገታ አደረን። ኒው በርግ ውስጥ እያለን ጓደኞቻችንን ለመጎብኘት ወደ አብሊን ቴክሳስ ሄድን። ከዶ/ር ጆን አሽቢን እና ባለቤቱ ጋር ጥሩ ጓደኛሞች ስለነበርን እነርሱንም ጭምር ጎብኝተናቸው ነበር። ከብዙ ዓመታት በፊት አብሊን  በምንኖርበት ጊዜ እነዚህ ሰዎች ብርቅ የሆኑ  ጓደኞቻችን ነበሩ። ዶ/ር አሽቢ መስማት ለተሳናቸው ትምህርትን በተመለከተ ተጨማሪ ሌላ የትምህርት ክፍል መከፈቱንና ሌሎች ተጨመሪ መረጃዎችን ሰጠን። በመሆኑ ካርል ለአንድ ዓመት ያህል ወደ ትምህርት ቤት የሚመለስ ከሆነ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ለማስተማር ብቁ እንደሚሆንና የዶክትሬት ዲግሪ ትምህርቱንም መከታተል እንደሚችል አረጋገጠልን። ስለሆን ካርል በአብሊን ክርስትያን ዩኒቨርሲቲ ውስጥ እንዲያስተምር በዶ/ር አሽቢ ግብ ቀርቦለት ካርልም አጋጣሚውን በደስታ ተቀበለ። የአብሊን ቆይታችንን ጨርሰን ወደ ኦሬገን ስንመለስ እኛ የነበረን ግንዛቤ ካርል የዶክትሬት ዲግሪውን እየሰራ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የተወሰኑ ዓመታትን ያሳልፋል የሚል ነበር።

 

በዚህ ምክንያት ይህ ሌላ አዲስ ራዕይ ነውና ወደ ኢትዮጲያ ለመሄድ ከውስጣችን ይፈላ የነበረውን ፊላጎት ለተወሰነ ጊዜ ያህል አስታግሶልናል። ይህንን ጉዳይ በዚሁ ላይ ላቁምና ወደ ሌላ ሀሳብ ልሻገር። የክረምት የእረፍት ጊዜያችን ጨርሰን ወደ ኒው በርግ ስንመለስ በህይወታችን ውስጥ አዲስ ምዕራፍ ተከፈተ። አሁን እንግዲህ ስለ እኔ ምን እንደሚሰማህ ማወቅ አልችልም። ምክንያቱም በውስጤ የጠለቀ ፍቅርና ቅን የሆነ ሀሰብ እያለኝ ሰዎች በተሳሳተ መንገድ እንደተረዱኝ ብዙ ስለ ተማርኩኝ ነው። የፃፍኩልህን ሁሉ በቅንነት እንድትረዳ እፀልያለሁ። እኔ ለአንተ ያለኝ ጥልቅ የሆነ ክርስትያናዊ ፍቅርና መልካም አስተሳሰብ ነው በከባድ ሀዘን ታጂቦ ነው። ደመረም ምን ያህል እንደምንወደው እንዲያውቅ እንፈልጋለን። ካርልና እኔ ከእርሱ ጋር ሆነን ልናግዘው ልንደግፈው እንፈልጋለን። ስለ ደመረ ስናስብ ሁል ጊዜ ሀዘን ይሰማናል። ምክንያቱም አንተ ጆን ኤድ አለህ። ደመረ ደግሞ ያለው እኛውኑ ቢሆንም በአጠገቡ ሆነን ልንረዳው አልቻልንም። ከዚህም ሌላ ከተወሰኑ ዓመታት በፊት የልብ በሽታ አጋጥሞት እንደ ነበርም በፊት ዋልተር ፋኔል ነግሮናል። ይህንን ስንሰማ ደግሞ ልንቋቋመው የማንችል ህመም ነበር በልባችን ውስጥ የተሰማን። ይህንን ጉዳይ ባሰብኩ ቁጥር እጅግ አለቅሳለሁ። እባክህ በሀይሉ ዝምታህን ስበር። ይህ ዝምታህ ከአሁን በኋላ ይብቃ። ተነጋግረን ችግራችንን ሳንጨርስ የምንሞት ከሆነ ይቅርታ የሚኖረን አይመስለኝም።

እወድሃለሁ

ቤኪ

 

የካቲት 14,1992

ውድ ቤኪ

 

እንደምን አለሽ። ይህንን መልዕክት የምልክልሽ ወንድም በሀይሉን ወክዬ ነው። ወንድም በሀይሉ በአሁኑ ጊዜ ያለው አሜሪካ ውስጥ ነው። ላለፉት ሁለት ወራት ተኩል እዚያ ነበው። ዳግም ወደ ኢትዮጲያ ይመለሳል ብለን የምንጠብቀው የካቲት 16, 1992 ነው። የላክሻቸው ኢሜሎች ሁሉ እኔ ዘንድ ናቸው፤ እርሱም እንደደረሰ እልክለታለሁ። እስከዚያው ሰላም ሁኚ

የአንቺው

ዓለማየሁ ደሳለኝ

 

 

የካቲት 14, 1992

ውድ ዓለማየሁ

 

የአንተ ኢሜይል ሲደርሰኝ ምን ዓይነት መባረክ እንደ ሆነ ማሰብ አልቻልኩም። ስለአበረታታሀኝ በጣም አመሰግንሃለሁ። ተዋውቀን እንደ ሆነ አላስታውስም። እንተዋወቃለን? ለደመረም ኢሜይል ለመፃፍ በእጅጉ እፈልጋለሁ። ነገር ግን እኔ ከሰዎች ጋር ያለኝን ቅርበት በተመለከተ በሀይሉ ምን እደሚሰማው አላውቅም። ከሰዎች ጋር ግንኙነት ማድረግ እችል ዘንድ ይፈቀድልኝ እንደሆነም አላውቅም። እባክህ ደመረ ኢሜይል እንዲጽፍልኝ ንገርልኝ። ስለ እሱ በጣም እጨነቃለሁ። እባክህ ለበሀይሉ የፀፍኳቸውንም ኢሜይሎች ለደመረም አስተላልፍልኝ። ስለምታደርግልኝ እገዛ በጣም አመሰግንሃለሁ። እባክህ ስለማንነትህም ንገረኝ፤ አውቅህ እንደሆነ ለማወቅ ፈልጌ ነው። ምንም እንኳ ግማሽ ልቤ እዚያው አዲስ አበባ ቢሆንም እዚያ ካሉት ሰዎች ጋር የተነጋገርኩት ከብዙ ዓመታት በፊት ነው። አሁን የአንተ ኢሜይል ሲደርሰኝ ምን ያክል ሸክሜን እንዳቃለልክልኝ ልነግርህ አልችልም።

እግዚአብሄር ይባርክህ

ቤኪ

 

 

የካቲት 14, 1992

ውድ ቤኪ

 

ሰላምታዬ ይድረስሽ

የእኔን ኢሜይል በማግኘትሽ መባረክሽን ስትነግሪኝ በጣም ደስ ብሎኛል አንቺ እንዳልሽው እኔም አላውቅሽም። የሆነ ሆኖ የላክሻቸውን ኢሜይሎች ለወንድም በሀይሉ ለማስተላለፍ ልረዳሽ ስወስን ደስ እያለኝ ነው። እኔ በዚህ መካኒሳ ባለው የክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ከሚያገለግሉ የጌታ ባሪያዎች አንዱ ነኝ። እናም በዚህ በመካኒሳ ከበሀይሉ እና ደመረ ጋር እያገለገልኩ እገኛለሁ። ከኢትዮጲያዊያን ወገኖቼ ጋር ለመስራት ከኬኒያ የመጣሁት በቅርቡ ነው። በሀይሉ ወደ አሜሪካ ከሄደ ወዲህ ወደ ቢሯችን የሚመጡትን ኢሜሎች እየመለስኩ ያለሁት እኔ ነኝ። የአንቺ ኢሜል የደረሰኝም በዚሁ ምክንያት ነው። ላረጋግጥልሽ የምፈልገው ለበሀይሉ እና ደመረ የፃፍሽላቸው ኢሜይሎች ሁሉ ያለ ምንም ችግር በትክክል እንደሚደርሷቸው ነው። እግዚአብሔር አምላካችን ሁል ጊዜ ከአንቺ ጋር ይሁን!

እወድሻለሁ

አለማየሁ ደሳለኝ

 

 

የካቲት 15, 1992

ውድ በሀይሉ፣ ደመረ እና ቤተሰብ

 

ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጲያ ስትመለስ ኢሜሎቼን አለማየሁ እንደሚሰጥህ ሲነግረኝ ልቤ እጅግ አረፈ። አሜሪካ ውስጥ እንደሆንክ አውቄያለሁ። ምክንያቱም ዋልተር ፋኔል ሲያትል ያሉትን ልጆችህን እየጎበኘህ እንደሆነ ነግሮኛል። በእርግጥ ልጆችህ ሲያትል መኖራቸውን አላውቅም ነበር። ወደ ኢትዮጲያ ከመመለስህ በፊት ወደዚህ ወደ ኦሃይዮ መጥተህ ልትገበኘን ያለውን አጋጣሚ ሳስብ እጅግ ደስታ ይሰማኛል። ወደ እኛ መምጣት እንደምትችል ዋልተር ነግሮኛል። አጋጣሚ ሆኖ ከዋልተር ጋር የተነጋገርነው ለአንተ እና ጆን ኤድ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢሜይል ከፃፍኩላችሁ በኋላ ነው። እርሱም የእናንተን የደብዳቤ ግልባጭ እንዲደርሰው እፈልጋለሁ። ስለ እርሱን በቅርበት ባላውቅም በኮርዶፋ የክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ሽማግሌ መሆኑን ግን አውቃለሁ። ኮርዶፋ ቤተ ክርስትያን ደግሞ አንተንና አለምን በገንዘብ ትረዳቹህ አለች። ዋልተር ለአንተ እና ደመረ የጻፍኩላችሁን ኢሜይል መቀበሉን ቢነግረኝም ነገር ግን መልሶ አልደወለልኝም። አንተና ጆኔ ኤድም በፍፁም አልፃፈችሁልኝም። በጣም ሀዘን የሚሰማኝም ለዚህ ነው። ጥሩ አይሰማኝም። ምናልባት አሁንም በድጋሜ አገለሉኝ እንዴ? ብዬ አሰባለሁ። ምክንያቱ ይህ እንዳይሆን እፀልያለሁ። የሆነ ሆኖ ምክንያታችሁን በእርግጥ ለማወቅ አልቻልኩም። ቀደም ብዬ የጀመርኩላችሁን የ20 ዓመታት ታሪኬን ልቀጥልላችሁ።

 

ከክረምት ጎዟችንና ከወርክሾፑ ወደ ኒው በርግ እንደተመለስን ሀሳባችን ያደረግነው ካርል በአብሊን ዩኒቨርስቲ ውስጥ ለማስተማር ብቁ የሚያደርገውን ትምህርት እንዲቀጥል  በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ነበር። ይህንን ለማሳካት ካለንበት ኒውበርግ ቅርብ ወደ ሆነው ከተማ ሳሌም ለመዛወር አሰብን። ምክንያቱም ይህ ከተማ ትምህርቱን ወደ ሚከታተልበት ቦታ ይቀርባል። ነገር ግን ይህ ሊሳካ አልቻለም። ከጉዟችን ተመልሰን ለአምልኮ ወደ ቤተ ክርስትያን በሄድንበት የመጀመሪያ ቀን አንዲት ሴት በችኮላ ወደ እኛ መጣች። የሴትየዋ ጉዳይ ደግሞ ስለ 5 ኢትዮጲያዊያን ልጆች ጉዳይ ነበር። እነዚህ ልጆች የአንድ ቤተሰብ ልጆች ሲሆኑ ቤተሰቦቻቸው ስለ ሞቱባቸው ወላጅ አልባ ሆነዋል። ይኖሩ የነበረውም በፖርትላንድ ነው። እነዚህን ልጆች የማደጎ አገልግሎት እንዲያገኙ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ለሁለት ሳምንታት ስትሰራ ነበር። የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ትሰራ የነበረው አምስቱንም ልጆች ለአንድ ቤተሰብ ለመስጠት ነበር። ይህም እነዚህ ልጆች እንዳይበታተኑ ነው። ወዲያው ልቤ ወደ እነዚያ  ሆነ። እነዚህን ልጆች የመደገፉ ነገር ደግሞ የእኛ ጥሪ ነበር።  እነዚህን 5 ልጆች ወደ ቤታችን ስናመጣ ያጣናቸውን ኢትዮጲያዊያን ያገኘን መሰለኝ። እናም ልጆቹን ወደ ቤቴ ለማምጣት የማሰቢያ ጊዜ አልነበረኝም። የእነዚህን ልጆች ዜና እንደሰማሁ ወዲያው የራሴ ልጆች፤ የቤተሰባችን አባላት የሆኑ ያህል ቆጠርኩኝ።

 

በሌላ በኩል ደግሞ ካርል በዚህ ጉዳይ ላይ ዝምተኛ ነበር። ምንም አስተያየት አልሰጠም። እናም አብዝቼ ለመንኩት፣ ወተወትኩት፤ አለቀስኩበት። በመጨረሻም ተሸነፈልኝና እሺ አለኝ። እርሱን ለማሳመን ያደረጉት ልመናዬ እና ውትወታ የኋላ ኋላ ዋጋ አስከፍሎኛል። ከአመታት በኋላ እነዚህን ልጆች ለማምጣት በካርል ላይ ያደረኩት ጫና “ይቅርታ!” አስብሎኛል። በዚህ ዓይነት ነበር ቤተሰባችን ከ 4 ወደ 9 ያሳደግነው። ይህም በጣም አስደስቶኛል፤ አስፈንድቆኛልም። እነዚህን ልጆች እናሳድግ ዘንድ እግዚአብሔር ራሱ አደራ የሰጠኝ ያህል ተሰምቶኛል። ስለሆነም የተመረጡ እና በመልካምነታቸው የታወቁ ናቸው ብዬ የማስባቸውን ቤተሰብ ፈለግ በመከተል እግዚአብሔርን እንዲያውቁ ላስተምራቸው፣ የእርሱን ፍቅር ያውቁና ይተገብሩ ዘንድ ላሰለጥናቸው፣ እግዚአብሄር የሰጣቸው የምድር ላይ ዓላማ እንዲያሳኩ እና ከራሳቸው አስበልጠው ሌሎችን እንዲወዱ እና ቅድሚያ በመስጠት አምላክን እንዲያሳዩ ለማሰልጠን ቆርጬ ተነሳሁ። ምንም እንኳ ቀላል ባይሆንም ዓላማ እና ግቤ ይህ ነበር።

 

ነገር ግን እነዚህ ልጆች እቤታችን ከረገጡበት ቅጽበት ጀምሮ የዲያብሎስ ጥቃት ተጀመረ፤ እውነተኛ ጦርነት ተከሰተ። የሆነውን ሁሉ ነው ብዬ ያመንኩት እና የገለጽኩት ከመንፈሳዊ ውጊያ አንፃር ነበር። መንፈሳዊ ውጊያ ደግሞ እግዚአብሔር በመረጣቸው አገልጋዮች በኩል የሚከሰት እግዚአብሔርም የፈለገውን የሚያሳካበት መንገድ ነው። የዚህ ዓይነት መንፈሳዊ ውጊያ የቆመው ባለፈው ዓመት ከአምስቱ ልጆች የመጨረሻው ልጅ ራሱን ችሎ ከቤታችን ከወጣ በኋላ ነው። እነዚያ ልጆች ወደ ቤታችን ከመጡ ከ17 ዓመት ተኩል ገደማ ድረስ እና ይህ የመጨረሻው ልጅ ራሱን ችሎ እስከ ወጣበት ጊዜ ድረስ ወደ ኢትዮጲያ የመመለስ ሀሳብና ፍላጎት አልነበረኝም። የመጨረሻው ልጅ ከወጣበት ቅጽበት በኋላ ጀምሮ ኢትዮጲያ፣ አንተ እና ደመረ እና ሁሉም የኢትዮጲአ ነገር ወደ ልቤ መጣችሁ፤ የዘወትር ፀሎቴም መሆን ጀመራችሁ። የታሪኬ አቅጣጫ እንግዲህ አሁን ይቀየራል። ይህንን ታሪክ የምነግራችሁ ከልቤ ነው። ጥቂት ቆይቼ እመለሳለሁ።

እወድሃለሁ

ቤኪ

 

የካቲት 15, 1992

 ውድ ደመረ

 

ኢሜሎቼ እንተ ጋ እንደሚደርሱ አለማየሁ ስላረጋገጠልኝ በጣም ተደስቻለሁ። ቀደም ሲል ኢሜሎቼ ማይደርሱህ መስሎኝ እንዴት አድርጌ ኢሜል እንደማደርስህ ወይም እንዴት እንደምደውልልህ መንገድ እያፈላለግሁ ነበር። በሀይሉም ለአንዱም ኢሜሌ መልስ ስላልመለሰልኝ የደረሰው አልመሰለኝም። እናም ግራ ተጋብቼ ነበር። ነገር ግን ስለ ሁኔታዎች ከአለማየሁ ከሰማሁ ወዲህ ግን አምላኬን እጅግ አመሰገንኩ። ከአሁን በኋላ እንግዲህ ከልቤ ያለውን ሁሉ ወደ አንተም ማጉረፍ ብቻ ነው። ከጥቂት ዓመታት በፊት ጆርጂያ በነበርክበት ጊዜ በጣም መታመምህን ሰምቼ በጣም አዘንኩ። ዋልት ፋንለ ይህን ጉዳይ ሲነግረኝ እጅግ አዘንኩ እጅግም አለቀስኩ። ዛሬም ቢሆን ያን ጉዳይ ባሰብኩ ቁጥር አለቅሳለሁ። እግዚአብሔር ረጅም እድሜ ይሰጥህ ዘንድ እጸልያለሁ። ቀደም ሲል የብዙ ዓመታት አብሮነት ስለነበረን አሁንም እንደገና የአብሮነት ጊዜ ይኖረናል ብዬ ተስፍ አደርጋለሁ። እኔና ካርል እንደረሳንህ አድርገህ እንደምታስበው ሁሉ እኔም እንደዚያ አስባለሁ። ዳግም ተመልሰን እንደምንመጣ ቃል የገባንልህ ቢሆንም ነገር ግን ይህ ቃላችን እውን ሊሆን አልቻለም። ለዚህ በጣም አዝናለሁ። ነገር ግን ይህ እንዲሆን በእውነት ምርጫችን አልነበረም፤ እመነኝ። ታሪካችንን በኢሜል ለአንተ እና በሀይሉ ማካፈል ጀምሬያለሁ። ይህንን ታሪኬን የማንበብ እድል አግኝተህ እንደሆን አላውቅም። ምናልባት በሀይሉ ከአሜሪካ እስከሚመለስ ማግኘት የምትችል አይመስለኝም። የሆነ ሆኖ የምጽፍላችሁ ታሪክ ከተለያየንበት ጊዜ ወዲህ 20 ዓመት ገደማ የሸፈነ ታሪክ ነው። ለመሆኑ እንዴት ነህ? ቤተሰብህስ? ስለ ሁሉም እስኪ ነገረኝ።

 

መስማት የተሳናቸው ትምህርት ቤትስ እንዴት ነው። የቀድሞ ተማሪዎችን ታገኛለህ? ባፈና፣ ጎሳዬ፣ እልፍነሽ እና የምወዳቸው ሁሉ እንዴት ናቸው? ለመሆኑ ስለ አበራሽ ሰምተሃል? እባክህ ትምህርት ቤቱ ምን እንደሚመስል ንገረኝ። ትምህርት ቤቱን ሊጎዱ የሚሞክሩ ተማሪዎችና ሰዎች አሁንም ለችግር እየዳረጉህ ነው? ካርል እና እኔ ከአንተ ጋር በሆን እና በረዳንህ! የምታቀርባቸውና ሀሳብህን የምታከፍላቸው ሰዎች ምን ያህል እንደሚረዱ አላውቅም። ተማሪዎችን ልትረዳቸው ስትል ሙሉ ልብህንና ህይወትህን ስትሰጣቸው በተቃራኒው ምን ያህል እንደሚያስቸግሩህ እና እንደሚጎዱህ አውቃለሁ። አንዳንዴ የልጆቹን ሁኔታ በመመልከት ጥሩ ሰዎች አይሆኑም ብለህ በመገመት ተስፋ እንደምትቆርጥና ድካሜ ከንቱ ሆነ ብለህ እንደምታስብ አውቃለሁ። ይህን ጉዳይ አሳምሬ አውቃለሁ። ለዚህ ልምድ የሆነኝ በመካኒሳ መስማት የተሳናቸው ትምህርት ቤት ውስጥ በማስተማሬ ብቻ ሳይሆን እዚህ ሀገር አምስት ኢትዮጲያዊያ ልጆችን በማሳደጌ ነው። እንዴት  በትክክል መኖር እንዳለባቸው ለማስተማር በእጅጉ ጥሬ ነበር። በዚህ ውስጥ ሰይጣን ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ እኔና ቤተሰቤን ያጠቃ ነበር። በእርግጥ ሁሉ ጊዜ እግዚአብሔር ከነገሮች በላይ ስለሆነ አሸናፊ እንደ ሆነ እናውቃለን። ደመረ ይህን ሁሉ ዓመት ከአንተ ጋር ባልሆንም ከስራ ጋር በተያያዘ የሚደርስብህን የልብ ስብራት የማልረዳ እና የማላውቅ እንዳይመስልህ። መምህራኖቹስ እንዴት ናቸው? ሁሉም ጠንካራ ክርስትያኖች ናቸውን? አንድ የምነግርህ ነገር ነበረኝ፤ ጨርሼ አልነገርኩህም። በደንብ ከሰማኸኝ እግዚአብሔር እርሱ ብቻ ሀያል መሆኑን እንደገና ትመለከታለህ። ኢሜልህን በጉጉት እጠብቃለሁ። ቶሎ ፃፍልኝ!

እወድሃለሁ

ቤኪ

 

የካቲት 16, 1992 የ 20 ዓመት ታሪኬ ቀጣይ ክፍል…

ውድ በሀይሉ፣ ደመረ እና ሌሎች ወዳጆቼ

 

ከሁለት ሳምንታት በፊት ሁለታችሁ በ1973 መጀመሪያ አከባቢ ለካርልና ለእኔ የፃፋችሁልን ደብዳቤ አግኝቼ ነበር። ለመጨረሻ ጊዜ ከእናንተ የደረሰኝ ደግሞ ደመረ መጋቢት 1976 የፃፈልኝ ደብዳቤ ነበር። እነዚህን የድሮ ደብዳቤዎችን ሳነብ በጣም ነበር ደስ ያለኝ። ምክንያቱም እንደ እኔ ሁሉ እናንተም ለቤተሰቤ ያለችሁን መልካም ፍቅር ስላስታወሰኝ ነው። ጆን ኤድ ሀምሌ 15/1975 የፃፈልኝ ደብዳቤም እንዲሁ አግኝቼ ነበር። እንደምታስታውሱት አባቴ እና እናቴ የሞቱት ከሀምሌ 15/1967 ትንሽ ቀደም ብሎ ነበር። እናም ከላይ ከጠቀስኩት ሌላ ከቀብር ከመመለሳችን በፊት ከጆን ኤድ የደረሰን ደብዳቤ እንዳልደረሰን እርግጠኛ ነኝ። እነዚያን ደብዳቤዎች ካነበብኩ በኋላ ያስታወስኩት ነገር ቢኖር ከእናንተ ጋር ቁጭ ብለን የተነጋገርነውን ነገር ነበር። ካስታወሳችሁ ወደዚህ ከመመለሳችን በፊት ቁጭ ብለን ወደ ኢትዮጲያ ተመልሰን እዚህ ባለው ስራ እንደምንረዳችሁ ቃል ገብተናል። ታስታውሳላችሁ? የጆን ኤድ ደብዳቤም ቆንጆ ደብዳቤ ነበር። የእርሱን ደብዳቤ እንደገና ካነበብኩ በኋላ አሁንም ለእኛ ያለውን መልካም ፍቅር ተገንዝቤያለሁ። ይህ ግንዛቤዬ ደግሞ በዚህ ረጂም ጊዜ ዝምታ ውስጥ ሆኜ በተለይም ከጆን ኤድ ምንም መልስ ባላገኘሁበት ጊዜ መጽናናትን የሚሰጠኝ ነው። ያንን ደብዳቤ እናንተም ያነበባችሁ ይመስለኛል። እናትና አባቴ ከመሞታቸው በፊት እኔና ካርል ኢትዮጲያ ለመልቀቅ እቅድ እንደነበረን ታስታውሳላችሁ?

 

ነገር ግን ያንን እቅዳችንን ያስለወጠን የጆን ኤድ ደብዳቤ ነበር። በሀይሉ ደግሞ ኢትዮጲያን እንድንለቅ ትገፋፋን ነበር። በሀይሉ የተናገርከውን ላስታውስህ “አሁን በኢትዮጲያ ውስጥ ባለው ብጥብጥ እና በትምህርት ቤትም ውስጥ ባለው መጥፎ ነገር ምክንያት ወደ ሀገራችሁ ብትሄዱ ይሻላችኋል” ብለሀናል። እኛም ምክርህን ተቀብለን። አሁን በቅርብ እያለቀስኩ በፃፍኩልህ ኢሜይል ውስጥ ለምን ከኢትዮጲያ እንድንወጣ ገፋፋኸን ብዬ የጠየኩህ ሁኔታውን ሳስታውስ ግራ ስለገባኝ ነው። ለማለት የፈለኩት እዚያው ከእናንተ ጋር ሆነን ያለውን ችግር በጋራ ብንጋፈጥ መልካም አልነበረምን? ከዚያ ጊዜ ጀምሮ እዚያው ብንሆንና እናንተ ሁለታችሁን ደመረ እና በሀይሉ እንዲሁም ሌሎቻችሁን ባናጣ መልካም ነበር። እዚህ ወደ አሜሪካ ከተመለስን ወዲህ በሌላችሁበት እና ካለናንተ እርዳታ በእጅጉ እየተቸገርን ነው ያለነው። ከዚህ ሁሉ እናንተን አትርፈን በኢትዮጲያ የሚገጥመንን ችግር እየተቀበልን እዚያ ባለው ስራ ብንረዳችሁ መልካም ነበር። አሁንም ቢሆን በተሳሳተ መንገድ እንዳትረዱኝ፤ እየከሰስኳችሁ አይደለሁም። እየሞከርኩኝ ያለሁት ባለሁበት ውዥንብር ውስጥ ሆኜ የሚሰማኝንን ስሜት እንድትረዱኝ ነው። ከዋለት ፋኔል ጋር በተነጋገርኩበት ጊዜ በእናቴ እና አባቴ ሞት እንዲሁም በኢትዮጲያ ጉዳይ ላይ ውዥንብር መግባቴ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሆነ ጠይቆኝ ነበር። ለነገሩ ከእርሱም ጋር የተነጋገርነው አንድ ጊዜ ብቻ ነበር። የዚህ ዓይነት ሁኔታ ከዚህ በፊት ተከስቶብኝ አያውቅም።

 

ነገር ግን በዚህ ቅርብ ዘመን የተከሰተብኝ ነገር ውዥንብር ነው። በአሁኑ ጊዜ ያንን ክስተት በማስታውስበት ጊዜ ልክ አሁን የሆነብኝ ያህል ከባድ ህመም ነው የሚሰማኝ። ካለማወቅ የተነሳ ያን ሁሉ ዘመን እጅግ ከባድ የሆነ የአእምሮ ህመምና ሀዘን ብቻዬን በዝምታ ተሸክሜ ነበር። የ20 ዓመት ታሪኬን እየሰማችሁ ስለ ሆነ  ይህ እንዴት ተከሰተብኝ ምናልባት ልትረዱ ትችላላችሁ። እኔ ግን በደንብ መገንዘብ አልችልም ዳሩ ግን አብዝቼ ብፅፍላችሁ የበለጠ ትረዳላችሁ ብዬ አስባለሁ። ለእናንተ ብዬ በምፅፈው ውስጥ እኔም ግንዛቤ አገኛለሁ። ስለሆነም ለመፃፌ ምክንያት ስለሆናችሁ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ። ነገር ግን ልታገሉኝ ትችላላችሁ ብዬ አሁንም ስጋት አለኝ። ለዚህ ምክንያቴ እስከ አሁን ድረስ ምንም ከእናንተ ወገን የሰማሁት ነገር ስለሌለ ነው። በዚህ ረጂም ዓመታት ውስጥ የተለየ ሌላ ክስተት ያልገጠመኝ አሁን ብቻ ነው። ምናልባት በዚህን ሰዓት ስለ እናንተ እና ኢትዮጲያ በተደጋጋሚ አረፍት የሚነሳኝ ከተለያዩ ችግሮች እና ክስተቶች አረፍ ስላልኩኝ ይሆናል ብዬ አስባለሁ። በ20 ዓመታት ውስጥ ከውጣ ውረዶች ያረፍኩት ለመጀመሪያ ጊዜ አሁን ነው። አሁን ከባለቤቴ ኒል ጋር እየኖርኩ ያለሁት ቻይቸነቲ ኦሃይዮ ውስጥ ነው።

 

እዚህ መኖር ከጀመርን ሁለት ዓመታችን ነው። ቤታችን ለእህቴ ካራን ቅርብ ሲሆን ትንሹ ልጄ ጄይላንም የሚኖረው እዚህ ነው። ከዋሽንግተን ክልል ወደዚህ የተዛወርነው ለእህቴ ካረንና ቤተሰቧ ለመቅረብ ብለን ነው። ከዚህም ሌላ ለልጆቼ ቀረብረብ ለማለት ፈልጌ ነው። አብዛኛዎቹ ልጆቼ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ሲጨርሱ ለኮሌጅ ፣ አየር ሀይል ወዘተ ለመቀላቀል የመጡት ወደዚህ አገር ነው። ከዚህ ሌላ አንድ በስፖካኝ የሚኖር ልጅ አለኝ። በሳን ጆሲም የሚኖር ሌላ ልጅ አለኝ። በቻንቺናይት የሚኖሩ ግሩም የሆኑ የኢትዮጲያ ማህበረሰብ አሉ። ከብዙዎች ጋር ተገናኝቼ የተነጋገርኩ ሲሆን በሌሎች ደግሞ በቤታቸው በሚያዘጋጁት ዝግጅት ላይ ተገኝቻለሁ። በሰዎች ጉዳይ ውስጥ ብዙ አለመሳተፍ እና ዝግ ብዬ መኖርን እመርጣለሁ። ሌላ ባል ማግባት ልጆቼን ማሳደግ እነዚህ ነገሮች ሁሉ ሌላ ሰው አድርጎኛል። እግዚአብሄርም የጥገናና የማገግምበት ጊዜ የሰጠኝ ይመስለኛል። ነገር ግን በእርግጥ የምነግራችሁ ከታሪኬ በመነሳት በሚቀጥሉት 20 ዓመታት ውስጥ ያሳለፍኩት ሁሉ በመገንዘብ በትክክል እንደምትረዱኝ ነው። ታሪኩን እንቀጥላለን።

እወዳችኋለሁ

ቤኪ

 

መጋቢት 1, 1992  ከ20 ዓመት የኋሊት ጉዞ ማገገም…

ውድ ወዳጆቼ

 

አምስቱ ኢትዮጲያዊያን ከእናታቸው ጋር በፖርትላንድ ይኖሩ የነበር። ወደዚህ አገር የመጡት በካቶሊካዊያን በኩል ሲሆን አመጣጣቸውም በሱዳን በኩል በስደተኛ መልክ ነበር። ከካቶሊክ ጋር የተገናኙትም እናታቸው የካቶሊክ እምነት አማኝ ስለሆነች እንደመብለት እና አባት የሌላቸው ልጆች የማሳደጓ ጉዳይ ከግምት ገብቶ ነበር ወደዚህ ወደ አሜሪካ የገቡት። አባታቸው ሙስሊም ሲሆን በስደት እያሉ ነበር ትቷቸው ወደ ሳውዲ አረቢያ የሄደው። ይህ ሰው ሌላ ሚስት አግብቶ ሌላ ሕይወት የመሰረተው እነዚህን ልጆች ለማሳደግ ከመውሰዳችን በፊት ነበር። በካቶሊክ ህግ መሰረት ልጆቹን በጉዲፈቻ ከመስጠታቸው በፊት ለአንድ ዓመት አባታቸውን ፈልጎ ማስፈቀድ አለባቸው። እናም የካቶሊክ የማደጎ አገልግሎት እንደ ነገሩን አባታቸውን እንዳገኙ እና የቃል ፈቃድ እንዳገኙ ነበር። በዚህ መሰረት እኛም የጉዲፈቻ ሂደቱን ቀጠልንበት። ነገር ግን የእነዚህ ልጆች አባት የጉዲፈቻ ሂደቱ እየተካሄደ ባለበት ጊዜ ከታላቁ ልጄ እድሪስ ጋር በምስጢር ይገናኙ ነበር። እድሪስ ይህንን ምስጢር ከእኔ፣ ከካርል እና ከካቶሊክ ደብቆ ለሌሎች ልጆችም አካፍሎ ነበር። የጉዲፈቻ ሰነዱን ለመፈረም በምንሄድበት ቀን ጠበቃው አንድ አስፈሪ የሆነ ዜና ነገረን። ልጆቹ ከእኛ ጋር ለመኖር ከእኛ ጋር በሚቀላቀሉበት ሲቀላቀሉ የአሜሪካ ቆይታቸው 18 ወራት ብቻ ነው የሚሆነው። እናታቸውም ስትሞት የአሜሪካ ቆይታዋ ይህን ያህል ብቻ ነበር አለን።

 

ለነገሩ እንግሊዝኛ ቋንቋ በደንብ አይናገሩም እንጂ ተምረዋል። ከዚህም ሌላ ከፖርትላንድ የጎዳና ኑሮ ብዙ ጸያፍ የሆኑ ቃላቶች እና ልማዶችን የተለማመዱ በመሆኑ ገና ከጅምሩ በችግር ያጋለጡን ነበር። ልጆቹ ከእኛ ጋር ሲቀላቀሉ እድሪስ የ14 ዓመት ልጅ ነበር። ከሌሎች እህት እና ወንድሞቹ በእድሜ በጣም ይርቅ ነበር። እናም የእርሱን ፍላጎት በተለየ መነጽር ነበር የምናየው። ሁሉንም ልጆች ወደ ቤተ ክርስትያን ትምህርት ቤት የወሰድን ቢሆንም ተቀባይነት ያገኙት እድሪስ እና ጄይላን ነበሩ። ጄይላን እድሜው ለትምህርት ቤት ያልደረሰ በመሆኑ የክርስትያን ትምህርት ቤቱ ለእርሱ የሚሆን ፕሮግራም አልነበረውም። ስለሆነም በእስፖርት የምንደግፈው ከሆነ በህዝብ ትምህርት ቤት ውስጥ መሳተፍ እንደሚችል አሰብን። ማህበር ውስጥ ከዚያም በሌላ የወጣት የክርስትያኖች ህብረት ውስጥ እንዲገባ አደረግን። ይህ የወጣቶች ህብረት ግን በክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ውስጥ አልነበረም። አሁን የገባበት የክርስትያን የወጣቶች ህብረት መጋቢ እንክብካቤው በተለይም በመንፈሳዊ ትኩረቱ እጅግ የተለየ ነበር። እድሪስ ስለ ክርስቶስ ተረድቷል። ምናልባት በጣም ሳይወደውም አይቀርም። በመጨረሻም አድሪስ የሚማርበት ቤተ ክርስትያን ዋና መጋቢያቸው በመልቀቁ የወጣቶች ህብረት መጋቢ ትቷቸው ሄዷል። በዚህ ምክንያት እድሪስ ቀደም ሲል የነበረውን ትኩረት ያጣ በመሆኑ አላስፈላጊ ሁኔታዎች መግባት ጀመረ።

 

በመልካም ስነ ምግባር እንዲያድግ የተለያዩ እድሎችን ብንሞክርለትም ሁሉም ውጤታማ አልሆኑም። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሳለን እነዚህን ልጆች በጉዲፋቻ እንድንወስዳቸው ያስተዋወቀችን የክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ሴት እነዚህን ልጆች መውሰዳችን በማወቋ በጣም ተደነቀች። እናም እሷም እነዚህን ልጆች በማሳደግ ውስጥ ለመሳተፍ ፍላጎቷን አሳየችን። እንዳጋጣሚ ሆኖ ግን ይህች ሴት የእግዚአብሄር መንፈስ የሌለባት ሰው ሆና ተገኘች። በመሆኑም በልጆቹ ላይ መጥፎ ተጽዕኖ ታመጣ ይሆን ብዬ እጅግ ፈራሁ። ይህች ሴት በጣም መርዛማ በመሆኗ ከልጆቹ ጋር እንዳትገናኝ አደረኳት። በዚህ ምክንያት በቤተ ክርስትያን ውስጥ ህይወቴን አመሰቃቀለችው። ሴትየዋ ሌሎች እንደ እርሷ የከፉትን ሁለት ሴቶች ጋር አብራ ለቤተ ክርስትያን ሽማግሌዎች ደብዳቤ ፃፉ። የደብዳቤ ይዘታቸው እድሪስን ከክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ውጭ አድርጋለች፤ በሌላ ቤተ ክርስትያን ውስጥ እንዲሳተፍ አድርጋለች የሚል ነበር። ሌላ ሴት ቀደም ሲል ከእኔ ጋር መልካም ግንኙነት ያልነበራት አጋጣሚውን ተጠቅማ ስለ እምነቴ በሽማግሌዎቹ ላይ ክስ አቀረበችብኝ። ይህም ማለት በክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ዶክትሪን አታምንም በማለት ነበር ሽማግሌዎቹ ላይ ክስ ያቀረበችው። ይህች ሶስተኛ ሴት ከቀድሞቹ ሴቶች ጋር የተቀላቀለችበትን ምክንያት መለየት አልቻልኩም። እኔ እንደሚመስለኝ ክሱን እውነት ለማድረግ ሶስት ምስክሮች ለማግኘት የጣሩ ይመስለኛል።

 

እንግዲህ አንዷ ከሳሽ የተቀሩት ሌሎች ሶስት ምስክር ሆኑ ማለት ነው። በዚህ ዓይነት ነበር ከክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ጋር የነበረው ችግር የተጀመረው። ሽማግሌዎቹ ግን በእነዚህ ሴቶች እና በሰሩት ስህተት የተናደዱ በመሆኑ ለእኔ ሀፍረት እንዲሰማቸው የሚያደርግ ደብዳቤ ሰጧቸው። የዚያን ደብዳቤ ቅጂ ለእኔም ሰጥተውኛል። በመጨረሻም እነዚያ ሴቶች በማህበሩ ፊት ቀርበው በዚህ ጉዳይ ላይ ንሰሃ ገብተዋል። ጉዳዩ ግን ቀድሞ በማህበሩ ውስጥ በትነው ስለ ነበር ከጊዜ ወደ ጊዜ ማህበሩን ያምስ ነበር።በዚህን ጊዜ የቤተ ክርስትያን ሽማግሌዎች የሆነ እርምጃ ለመውሰድ አስበው ነበር። ነገር ግን እኔ በዚህ ቦታ ሆኜ የችግሩ አካል ላለመሆን ወደ ሌላ ቦታ ለመሄድ ተዘጋጅቼ ነበር። በምንም ዓይነት ግጭት ውስጥ መሳተፍ አልፈለኩም። ልጆቼንም በስነ ምግባር ለማሳደግ ወሰንኩ። ሽማግሌዎቹ አሁንም ለእኔ ጥሩ አመለካከት አላቸው። የእኔን መንፈስ እና ጽናት አድንቀው እዚያው ቆይቼ ነገሮች እንዲስተካከሉ ይፈልጉ ነበር። ካርልም በሀሳባቸው ተስማምቶ ነበር። ከካርል እና ከሽማግሌዎቹ በሆነው እገዛ እና በረከት እኔ በሀሳቡ በመስማማት ወሳኔያቸውን ተቀበልኩ። ችግሮቹም ሳይቆዩ ይወጋደሉ ብዬ አምኜ ነበር። ነገር ግን ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሀሳቤ በካርል ህመም፣ ልጆቼን በማሳደግ እና ይህን ግጭት ለማስተካከል ተከፋፍሎ ረጂም ዘመን ተሻገርኩ። የኒው በርግ ቤተ ክርስትያንንም እንደ ቤተሰቦቼ እየወደድኳቸው መጠሁ።

 

 

በመሆኑም የትኛውንም ዋጋ ቢያስከፍለኝም ከእነርሱ ጋር ለመቆየት በቤተ ክርስትያኑ ውስጥ ሕይወቴንና ኑሮዬን ለማድረግ ወሰንኩ። ከዚህም ሌላ ቀደም ብዬ የነገርኳችሁ ሽማግሌ፤ እግዚአብሄር ከአፍሪካ እናንተን የመለሰው ለእኔ ሲል ነው ላለን ሽማግሌ የተለየ ፍቅር አለኝ። ለሽማግሌዎቹ ያለኝ ፍቅር በማደጉ ትክክለኛ እረኞች መሆናቸውንና እንደ አባቴ የሚመለከቱኝ ስለመሆናቸው ተገነዘብኩ። በመጨረሻ ግን በፍፁም እንደማይፈልጉኝ ተማርኩ። የጉዲፈቻ ስምምነት ለመፈረም ስንሄድ የካቶሊኩን ጠበቃ የለመንኩት እድሪስን ብቻ ለማሳደግ ነው። ሁሉንም በጉዲፈቻ መቀበል መልካም አለመሆኑን ብንረዳም ነገር ግን እድሪስን ለመቀበል ወስነናል። ነገር ግን ጠበቃው ይህ እንደማይቻል የነገረን እንደ ምክንያት አድርጎ ያቀረበልን እድሪስ ከሙስሊም አባቱ ጋር በመመሳጠር የጉዲፈቻ ሂደቱን ያመሰቃቅላል በማለት ነበር። ሌለው ጠበቃው ያሳየን የልጆቹ አባት ልጆቹ በጉዲፈቻ እንዲሰጡ የቃል ፈቃድ ያልሰጠሁ ስለሆነ ልጆቹ ወደ ሳውዲ አረቢያ በፍጥነት ይላኩልኝ በማለት የፈረመበትን ወረቀት ከመሳቢያ ውስጥ አውጥቶ ነበር። የሆነ ሆኖ ጠበቃው ይህ እንደማይሆንና ሁሉም በልጆቹ ፈቃድ ላይ ተመስርቶ የሚወሰን በመሆኑ ስምምነቱን ፈርመን ልጆቹን መውሰድ እንደምንችል ማረጋገጫ ሰጥቶናል። በመሆኑም ስምምነቱን ፈርመን ልጆቹም በህጋዊነት የእኛ እንዲሆኑ ተደረገ። ይህም ያለመግባባቱን ወደ መቋጫ ያደረሰ ሳይሆን እንዲያውም ጉዳዩ ዓለም አቀፈዊ ይዘት እንዲኖረው አደረገ።

 

ሙስሊሞች በጉዲፈቻ አያምኑም። ከዚህም በላይ ካቶሊኮች ልጆቹን በክርስትያን ቤት ማድረጋቸውን የበለጠ አናደዳቸው። በዚህን ወቅት እነዚህ የኢትዮጲያ ልጆች ከእኛ ጋር ለሶስት ዓመታት ከኖሩ በኋላ ትምህርታቸውን በቤት እንዲከታተሉ እንደሚያስፈልግ አሰብኩ። እድሪስ ቀደም ብዬ በጠቀስኩት ምክንያት ችግር ስለገጠመው የቅርብ ክትትል ይፈልጋል። በዚህን ወቅት ይህ ልጅ አሰፈሪና አስጊ ሆኗል። ሁል ጊዜ ይዋሸናል። እኔና ካርል ልናምነው አልቻልንም። በያንም ተመሳሳይ አቋም ላይ በመሆኑ እንደ እድሪስ ይሆናል ብለን ፈርተናል። እናም ሲዋሹ እጅ ከፈንጂ ለመያዝና የዚያ ውጤት እንዲያገኙ እና ውሸት ለማቆም እንዲማሩ አሰብኩ። በዚህ መሰረት ከትምህርት ቤት አስወጥተናቸው በቤት እንዲማሩ አደረግን። እድሪስ በዚህ ደስተኛ ባለመሆኑና በመናደዱ ምክንያት ከቤት ሸሽቶ ወጣ። በዚያን ወቅት እድሜው 17 ዓመት ሁኖ ነበር። ከቤት ወጥቶ በቀጥታ የሄደው ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሲሆን እጅግ ክፉ ቤተሰብ መሆናችንና ሌላ ቤተሰብ እንዲያፈላልጉለት ጠየቃቸው። ከእኛ ጋር መሆኑ መልካም መሆኑን በእውነት አላወቀም። እናም በዚያን ወቅት የጉዲፈቻ ሂደቱ ያልተጠናቀቀ በመሆኑ ፖሊሶቹ ስለ እርሱ መወሰን ጀመሩ። ከዚያም በምግብ ዝግጅት ትንሽ ስልጠና ወሰዶ ከእኛ ተለየ። ካርል ከሞተ ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ ወደ ቤት እንዲመለስ ጋበዝኩት። ምክንያቴም ትምህርቱን እንዲጨርስ ለማገዝ ነበር።

 

በዚህን ጊዜም በልጆቹ ውስጥ መጥፎ ምሳሌ በመሆን ቤቴን ያምስ ጀመረ። በዚህ ምክንያት እንደገና ከቤት እንዲለቅ አደረኩት። በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለን ሙስሊም የሆነች የሴት ጓደኛ እስከ ያዘበት ጊዜ ድረስ ጥሩ ግንኙነት ነበረን። ከዚህ በኋላ ተመልሶ የእስልምና ሀይማኖት ተከታይ ሆነ። እንዲህ መሆኑን ሰምቼ ለመጨረሻ ጊዜ ስደውልለት ተራግሞ ተለያየን። ለእርግማኑ እንደ ምክንያት ያነሳ የነበረው ልጅ በነበረበት ወቅት በተገቢው አልረዳሽኝም እያለ ነበር። አሁን ትምህርት ስለ ሌለው በችግር ውስጥ ነው። ለአሁኑ መጥፎ የሆነ ኑሮው ምክንያት የሆነው ትቶኝ በመሄዱ ነው። እንደዚህ በማድረጉ እና መራር የሆነ ኑሮ ውስጥ በመግባቱ እጅግ የሚያሳዝን ነው። ቢሰማኝ ኖሮ፤ ቢቀበለኝ ኖሮ መልካም ነበር። እግዚአብሄር አሁንም ከእርሱ ጋር እንደሚሰራ አውቃለሁ። ስለሆነም በእርሱ ተስፋ መቁረጥ አልችልም። ካርል ከልጆቹ ጋር መልካም ግንኙነት ነበረው። እርሱ ከልጆች ጋር ሁሌ ጥሩ ግንኙነት ያለው ቢሆንም እነዚህን ልጆች ካገኘን ወዲህ አንድ የሆነ ለውጥ ተከስቶበታል። ይህንን ለውጥ ሳስብ በምን አካባቢ እንደተለወጠ አንዳንዶቹ መገመት እችላለሁ። በዚያን ጊዜ ቀኑን ሙሉ ይሰራ የነበረው ከልጆች ጋር ሲሆን ማታም የሚመለሰው ወደ ልጆች ነው።

 

ተስፋ ያደርግ የነበረው ልጆችን ከማስተማር ተላቆ ወደ ኮሌጅ ለመግባት ነበር። ነገር ግን የኢትዮጲያ ልጆች ከእኛ ጋር ከተቀላቀሉ በኋላ ክፍያውን ስለማንችል ስለእርሱ ወደ አብሊን ሄዶ መማር ጉዳይ ትተናል። እድሪስም ታማኝ ስለ ነበር ፈተና ይሆንበት ነበር። የምታስታውስ ከሆነ ካርል ዝግያለ ባህሪይ ያለው በመሆኑ ግጭት ውስጥ መግባት አይወድም። ምንም በይፋ ባያሳይም ይህ ጫና ያሳደረበት ይመስለኛል። ለእኔም እንኳ ሳይቀር ተለውጦ ነበር። በእኔም ላይ የተናደደ ይመስላል። እኔም ሁኔታዎችን ስገመግም የሆነ ነገር እንደሚያስጨንቀው አወኩ። ይህ ጉዳይ እንደገና ካንሰሩ አነሳስቶበት እንደሆነ ወይም ካንሰሩ የባህሪ ለውጥ አምጥቶበት እንደሆነ አላውቅም። እንግዲህ በዚህን ወቅት የአንጀት ካንሰር እንዳለበት አውቀናል። ነገር ግን ዶክተሮቹ ሁሉንም የካንሰር ሴሎች አውጥናል የሚል ሀሳብ ስለ ሰጡን እፎይታ አግኝተን ነበር። በሀይሉ እና ደመረ ስለ ምን እየፃፍኩ እንደሆነ የተረዳቹህ ይመስለኛል። የተለያዩ ችግሮች ነገር ግን በአንድ ጊዜ የተከሰቱብኝ ስለሆነ በጣም ከባድ ስለ መሆናቸው እየነገርኳችሁ ነው። እየነገርኳችሁ ያለሁት የችግሮች መጠን እየቀነሱ ሳይሆን እየናሩ ነበር የሄዱት። እናም ተስፋ የማደርገው ሂደቶቹ እየተከተላችሁ የደረሰብኝን ለመረዳት አብራችሁን ትጓዛላችሁ ብዬ ነው። ታሪኩ ይቀጥላል….

እወዳችኋለሁ

ቤኪ

ቀጣዩ የ20 ዓመት ታሪኬ…

በዚያን ዘመን በቤት የሚሰጥ ትምህርት በስፋት የሚታወቅ ባለመሆኑና ልጆቹን ከመደበኛ ትምህርት ቤት አስወጥቼ በቤቴ እንዲማሩ በማድረጌ ብዙ ወቀሳዎች ደርሰውብኛል። አብዛኛዎቹ ሰዎች በአግባቡ ስላልተረዱኝ እና በመረጥኩት መንገድ ለመቀጠል እና ከጊዜ ወደ ጊዜ ከሚደርስብኝ ፈተና መሸሸጊያ ይሆነኛል ብዬ ያሰብኩትና ድፍረት የሚሰጠኝ ጌታን መፈለግና ወደ እርሱ አብዝቶ መፀለይ ብቻ ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ የጥናት ጊዜም ነበረን። እንደ አስፈላጊነቱ ለሰዎችም ቃል እንሰብካለን። ነገር ግን ልጆቹ አብዛኛውን ጊዜያችንን የያዙ በመሆኑ ይህ አገልግሎታችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መጥቷል። አንዳንድ የቤተ ክርስትያን ሰዎች በተለይም በሁለት መልኩ ይናገር የነበረው የቤተ ክርስትያን መጋቢ ስጋት እንደሆንኩት ይናገራል። ስለዚህ እንደዚህ መናገሬን አልወድም፤ በእውነት ስለምወደው። ነገር ግን ይህ ሰው በመካከል ሆኖ ሁሉንም ለማስደሰት የሚሻ ሰው ነው። በመካከል ሆኖ ወዲህ እና ወዲያ የሚጫወት ስለሆነ እውነትን ይቀብራታል እንጂ አያሳያትም። በኒውበርግ ክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ውስጥ እግዚአብሔር እየሰራ ያለውን እውነትና መልካም ነገር ለይቶ ለማሳየት አልቻለም። ቀስ በቀስም ሌሎች ሽማግሌዎችም እርሱኑ መከተል ጀመሩ። ለዚህ ሁሉ ስህተቱ የእርሱ ነው አልልም። ነገር ግን በእርሱ የሚሰራው ዲያብሎስ ነው እንጂ። ሰይጣን በዚህ ዓይነት ስራው ይታወቃል። እናም እነዚህን የቤተ ክርስትያን ሰዎችን ተጠቅሞ ውዥንብር በመንዛት በእኔ እና በሰዎች መካከል ልዩነት እንዲፈጠር አደረገ።

 

ጊዜውን በትክክል ባላስታውስም በ1985 እና 1988 መካከል የነበሩት ጊዜያት ለእኔ ትክክለኛ የፈተና ጊዜዎች ነበሩ። ቤተ ክርስትያኗ እኔና መላ ቤተሰቦቼን በይፋ ከአባልነት አገለለችን። የካርልን በረከት ይዤ ለአምልኮ በየሳምንቱ ወደ ቤተ ክርስትያን የምሄደው እኔ ብቻ ነኝ። ይህ ያልተለመደ ልምምድ ነው ካርል ህመሙ እየጠና ሲመጣ በቤተ ክርስትያን በኩል የሚደርስብን ጥቃትም እንዲሁ ከባድ ህመም እየሆነብን መጣ። ወደ ክርስቶስ ቤተ ክርስትያን መመላለሴን የቀጠልኩበት ምክንያት ከእምነታችን ጋር ባይስማሙም ምናልባት ሀሳባቸውን ሰውተው እኔንና ቤተሰቤን ወደ አባልነት ይልመሱናል ብዬ ነበር። ሁለተኛ ቀድሞውኑ ከእነርሱ ላለመለየት ቃል ገብቼ ስለነበር መቀልበስ አልፈለኩም።የእነርሱ የአምልኮ ስርዓት ትክክል እንዳልሆነና በእግዚአብሄር ቃል መሰረት አለመሆኑን አውቃለሁ። ለእነርሱ ያለኝ ልብ መልካም በመሆኑ ይህንን ስህተታቸውን እንዲረዱ ለማገዝም ጭምር ነበር ከእነርሱ ጋር እየቆየሁ ያለሁት። አጠቃላይ የቤተ ክርስትያኑ አባላት አግልለውኛል፤ የሚያናግረኝ አንድም ሰው የለም። በዚህ ሁኔታ ውስጥ በፅናት ለማለፍ ወሰንኩ። ይህ ደግሞ እያመጽኩ ሳይሆን ስለምወዳቸው ነው። በጠሉኝ እና በራቁኝ ቁጥር እውነቱን እንዲያውቁ የበለጠ እየወደድኳቸው መጣሁ። ትክክለኛ ነገር ሰርቼ ከሆነ በዚህ ዓይነት ለብዙ ዓመታት ተመላለስኩ። መጽሐፍ ቅዱስ “ባይሰሙአችሁ የእግራችሁን ትቢያ አራግፋችሁ ሂዱ” ይላል። ነገር ግን እየወደድኳቸው ይህንን እንዴት ልፈጽም? ይህ በጣም የሚያም ነው።

 

የትክክለኛ አማኝ ዶክትሪን የሚረጋገጠው በፍቅራቸው ነው። የእግአብሔር ፍቅር በውስጣቸው ሰርፆ ከሆነ አማኞች ፍቅር ያሳያሉ እንጂ አያገሉም። ክርስትያን መሆናችንን በፍቅራችን ይለዩናል ያለው መጽሐፍ ቅዱስ አይደለም? ሊረዳቸው ሲል ግማሽ መንገድ ያህል ብመጣም እነርሱ ግን ፈቃደኞች አልሆኑም። በእርግጥ የካርል በጠና መታመም እና በከፍተኛ ጫና ውስጥ የመሆናችን ነገር ልባቸውን ይመልሳል ብዬ አስቤ ነበር። ነገር ግን ልባቸው እንደ ደነደነ ነው። ካርል ከሞተም በኋላ በፍቅር ወደ እኛ ተመልሰው ያጽናኑናል ብዬ ነበር። ነገር ግን በፍጹም መለወጥ አልታየባቸውም። እዚህ ላይ በግልጽ ማስቀመጥ የምፈልገው ግን ካርል ሊሞት ወደ መጨረሻዎቹ ቀናቶች ገደማ ከእነርሱ ውስጥ አንድ የቤተ ክርስትያን ሽማግሌ ከባለቤቱ ጋር ሆኖ ወደ እኛ ቤት በመምጣት አጽናንቶናል። የካርል አስከሬን በሚሸኝበት ጊዜም አጃቢ የነበረው ይህ የቤተ ክርስትያኑ ሽማግሌ ነበር። በዚህ በአስቸጋሪ ወቅት ከአምስቱ የቤተ ክርስትያን ሽማግሌዎች ፍቅር ያሳየን ይህ ሽማግሌ ብቻ ነበር። ከ300 የማህበሩ አባላት ውስጥም በቀብር ስነ ስርዓት ላይ የተገኙት 6ቱ ብቻ ናቸው። እንግዲህ ያደጉበት ማህበረሰብ፣ አብሬ ያመለኩት እና አውቃቸዋለሁ፤ እቀርባቸዋለሁ ያልኳቸው ሰዎች እነዚህ ናቸው። ካርል እስከሞተበት ቀን ድረስ አመልክ ነበረው በዚያው በኒውበርግ ክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ነው። እንግዲህ መበለት የሆንኩ የሰባት ልጆች እናት ምን ዓይነት ስጋት ልሆናቸው እችላለሁ?

 

በዚህ ጭለማ በሆነበት ጊዜ ቤተሰባችንን መውደድ ቢችሉ ሁሉም ነገር ትክክል ይሆናል። በኒው በርግ ከተማ ውስጥ ብዙ ጓደኞች አሉኝ። ነገር ግን እኔ ያመንኳቸውና የእኔ ናቸው ያልኩት የኒውበርግ ክርስቶስ ቤተ ክርስትያን የማህበሩ አባላት ናቸው። ካርል በሞተበት ጊዜ በሁለት ሀዘኖች ውስጥ ነበርኩ አንደኛው ባሌን ማጣቴ እና ሁለተኛው ከማፈቅራቸው የቤተ ክርስትያን አባላት ፍቅር ማጣቴ ናቸው። አሁን ወደ እነርሱ መመለስ እንደማልችል አውቃለሁ። እኔን በማግለል በማጽናናታቸው ወደ እነርሱ ብመለስ ሁኔታቸውን እንደማልቋቋም አውቃለሁ። ካርል በህመም ላይ በነበረበት ወቅት የአረብ ሊግ ልጆቹን ወደ አባታቸው ወደ ሳውዲ አረቢያ ሊመልሱ እየሞከሩ እንደሆነ ነግረናቸው ነበር። ይህ መረጃ ሲደርሰኝ ትኩረቴ ሁሉ በካርል ላይ ነበር። ምክንያቱም ካርል ህመሙ ፀንቶበት ስለ ነበር ነው። እናም የአረብ ሊጉን ጥያቄ ለማስተናገድ ጊዜ አልነበረኝም። ካርል የአልጋ ቁረኛ ሆኗል፤ በቅርበት የማስታምመው ደግሞ እኔ ብቻ ነኝ። ከዚህም ሌላ በቤት ውስጥ የሚካሄደውን የልጆቼን ትምህርት የምከታተለው እኔ ነኝ። ነገር ግን ቀስ በቀስ የአረብ ሊጉ ጉዳይ እየተጠናከረ ሄዶ ጉዳዩ በኦሬገን መታየት ጀመረ። ካርል ከመሞቱ ስድስት ወራት በፊት አንድ ቀን አክስቴ ስልክ ደውላ ኦሬገን በሚታተመው ጋዜጣ ላይ ይህ ጉዳይ መታተሙን እንዳነበበች ነገረችኝ። እኔም ወዲያው ነበር ጋዜጣውን ገዝቼ ያነበብኩት።

 

 

ከዛ በፊት እየሆነ ስላለው ነገር ምንም ሀሳብ አልበነረኝም። በጋዜጣው ላይ ያነበብኩትን ጉዳይ ማመን አልቻልኩም። አረብ ሊግ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያንን ከሷል። የክሳቸው ጭብጥም ልጆቹን ባልተገባ መንገድ ወስደው ክርስቲያን ቤት አስገብተዋል የሚል ነው። ዳኝነቱ የሚታየው በኒዮርክ ከተማ ነው። ነገር ግን ዳኛው ይህንን ጥያቄያቸውን ውድቅ በማድረግ የፍርድ ሂደቱ በኦሬገን እንዲካሄድ አደረገ። በዚህ መሰረት የፖርትላንድ ነዋሪ የሆነ አንድ የካቶሊክ እምነት ተከታይ የሆነ ሰው የአረብ ሊግ ጠበቃ ፖርትላንድ የሚደርሰው ጥቅምት 18/ 1988 መሆኑን ነገረኝ። በዚህ ቀን እኔንም ወደ ፍርድ ቤት ይወስዱኛል ብዬ አስቤ ነበር። ካርል በሞት አፋፍ ላይ በመሆኑ ልጆቹን ከእኔ ጋር ለማቆየት ያለኝ እድል የመነመነ መሆኑንም ነገሩኝ። ጠበቃው በዚህ በተባለው ጥቅምት 18 ባለመምጣቱ ደስተኛ ነበርኩ። ከጥቂት ቀናት በኋለ ታህሳስ 5 ካርል አረፈ። ከእርሱ እረፍት በኋለ በቀጥታ ትኩረቴን በቀጣይ ህይወቴ ላይ አደረኩ። የሞቱንም ጉዳይ ፈጠን ብዬ የኋላ ጉዳይ እንዲሁም የክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ጉዳይም ወደ ኋላ በማድረግ በቀጣይ ሁኔታዎቼ ላይ አተኮርኩ። ምክንያቱም ብቻዬን ሰባት ልጆች የማሳድግ በመሆኑ ከአሁን በኋለ ተጨማሪ ስቃይ ሊያገኘኝ እንደማይገባ አመንኩ። ከዚህን ጊዜ በኋለ ምንም እንኳ እግዚአብሄርን የምወድ ብሆንም የእርሱን ነገር ቀዳሚ ጉዳይ ማድረግ አቆምኩ። በጣም ሞኝ ሴት ሆንኩ ማለት ነው። ከመገለልና ሀዘን ጋር የሚደረገው ጦርነትም በጣም አደከመኝ። ጥሩ ጊዜ ዳግም እንዲኖረኝ ፈለኩ።

 

ይህ እኔ የፈለኩት የእግዚአብሔር ፈቃድ ስላልሆነ ካርል ከሞተ ከሁለት ዓመታት በኋላ የስህተታችንን ፍሬ ማጨድ ጀመርን። ወደ አረብ ሊግ ጉዳይ ልመለስ። ካርል ከሞተ ከጥቂት ሳምንታት በኋለ የአረብ ሊግ ክስ ጠንካራ ሊሆን ስለሚችል ካቶሊኮች ጠበቃ አቆሙልኝ። ይህ ጠበቃ መረጃ የማግኘት ነፃነትን በመጠቀም ከኒዮርክ ፍርድ ቤት የክስ ግልባጭ በማውጣት እንዲደርሰኝ  አድርጓል። በኒውበርግ ገጠራማ አከባቢ የሚኖሩ ሰዎች ስለ አረብ አሽባሪዎች ናቸው ከማለት ውጭ ሌላ የሚያውቁት ነገር የለም። በዚሁ ምክንያት ፖሊሶች ቤታችንን ይጠብቁ ነበር። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በጣም አስፈሪ የሆነ ነገርም ተከስቶ ነበር ነገር ግን ይህ ክስተት ከአረቦች ጋር የተያያዘ አልነበረም። ይህ ክስተት የዝርፊያ ሙከራ እና የነጮች የበላይነት የሚያቀነቅኑ የዘረኞች ሙከራ ነበር። ረጃጅም ኢሜሎችን ስልክላችሁ እንደማትሰላቹ ተስፋ አደርጋለሁ። እባካችሁ በትዕግስት ተከታተሉኝ። ታሪኬ ከድጡ ወደ ማጡ እየሆነ ይቀጥላል። ይህ ከጀርባዬ ያለውን ታሪክ በትዕግስት ካነበባችሁ እና ከተረዳችሁኝ ሁሉንም ነገር እንደ አዲስ መጀመር እንችላለን ብዬ አምናለሁ። ፀሎቴ በዚህ ዓይነት እንድትረዱኝ ነው። እባካችሁ አታግልሉኝ። እንደማታገሉኝ እና ነገሮችን ቀለል አድርጋችሁ ለአዲስ ጅማሮ እንደምትዘጋጁ ተስፋ አደርጋሉ። እባካችሁ ቶሎ ፃፉልኝ።

አብዝቼ እወዳችኋለሁ

ቤኪ

 

 

ከበሀይሉ የተላከ ደብዳቤ የካቲት 25, 1992

ውድ ቤኪ

 

ጌታ እና ንጉስ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰላምታዬን አቀርብልሻለሁ። ይህ ኢሜይል ይደርስሻል ብዬ ተስፋ አደርጋሁ። እኛ ደህና ነን። ልጆቻችንም በዋሽንግተን ሲያትል ውስጥ እየኖሩ ናቸው። ልጆቼ አሁን ራሳቸውን የቻሉ ሆነዋል። እኔና ዓለም የምንኖረው ብቻችንን ነው። ኢሜይልሽ ሲደረሰኝ በጣም ነው ደስ አለኝ። ነገር ግን ኢሜይልሽን ሳነበው በእውነት ነው ያስለቀሰኝ። በዚህ ከ20 ዓመት በላይ ጊዜ ውስጥ የደረሰብሽ ነገር በእውነት አሳዛኝ ክስተት ነው። ይህንን ኢሜይል ሳነብ የኋሊት ተጉዤ ብዙ መልካም ትውስታዎችን እንዳስታውስ አድርጎኛል። መልካም ቀኖችን አሳልፈናል። ቤተሰቦችሽን ሳላስታውስ ያሳለፉኩት ቀኖች የሉኝም። የእግዚአብሄርን ቃል ለማስተማር በየገጠሩ በምዞርበት ጊዜ ሁሉ እናትና አባትሽን አስታውሳለሁ፤ አስባቸዋለሁ። እነርሱ ያሉት በእግዚአብሄር መገኛ እንደ ሆነ አውቃለሁ። እኔም ከእነርሱ ጋር ለመሆን እመኛለሁ። ምን ያህል እንደምንቀራረብ ታውቂያለሽ አይደለም? አብረን ለጌታ የምናገለግል ብቻ ሳንሆን እውነተኛ ቤተሰብ ነበርን። ከአንቺ ጋር ከተለያየን ከ20 ዓመት በላይ ሆኗል፤ በሚግርም ሁኔታ ነው ጊዜው የሚበረው። ይህን ያህል የሆነ አይመስለኝም። እዚያ አሜሪካ በነበርኩበት ጊዜ ስለ አንቺ የነገረኝ ማንም የለም። በእርግጥ ወንድም ብሌይር እና ቦቢን ስላንቺ ጠይቄያቸው ነበር፤ ሁለቱም ዬት እንዳለሽ እንደማያውቁ ነበር የነገሩኝ። ከአንቺ ምንም እንዳልሰሙ ጭምር ነበር የነገሩኝ። ለማንኛውም ዛሬ ይህን ያህል መስማቴ እጅግ መልካም ነገር ነው። እስኪ እዚህ ስላለው ስራዎች ላሳውቅሽ

 

ቤተ ክርስትያንን በተመለከተ

በኢትዮጲያ ውስጥ ከ670 በላይ አብያተ ክርስትያናት አሉን። በእነዚህ አብያተ ክርስትያናት ውስጥ የሚያገለግሉ ከ600 በላይ አገልጋዮችን በወንጌል ማሰልጠኛ ጣቢያዎቻችን አሰልጥነናል። እነዚህ ማሰልጠኛ መዕከላት የሳን ሴት ዓለም አቀፍ የወንጌል ተቋም አካል ናቸው። አባትሽ ያሰለጠናቸው ሰዎች በአሁኑ ጊዜ በየጣቢያዎቹ የሚያሰልጥኑ አሰልጣኞች ሆነዋል። የማህበራት አባላትም ቁጥር 70,000 በላይ ናቸው።

 

መስማት የተሳናቸው ትምህርት ቤት

በአሁኑ ጊዜ ያሉን መስማት የተሳናቸው ትምህርት ቤቶች ቁጥር 3 ናቸው። እነርሱም መካኒሳ በአዲስ አበባ፣ ማዞሪያ እና ሴንታሪያ ናቸው። በእነዚህ ትምህርት ቤቶች በአጠቃላይ ከ800 ተማሪዎች በላይ አሉን። ተማሪዎቻችን መስማት የተሳናቸው ብቻ ሳይሆኑ የሚሰሙም ተማሪዎች አሉ። በእነዚህ ትምህርት ቤቶች ያሉን አጠቃላይ የመምህራን ቁጥር 25 ነው። ደመረ እስከ አሁን የአዲስ አበባውን ት/ቤታችን ዳይሬክተር ነው። ከጥቂቶች በስተቀር ሁሉም መስማት የተሳናቸው መምህራን በስራ ላይ ናቸው። ወርቅዬ፣ በብርሃ፣ ወልደጊዮርጊስ እና ፀጋዬ አሁንም እዚሁ ናቸው። ከትምህርት ቤታችን ጨርሰው የሄዱ ተማሪዎች ት/ቤቱን አሁንም ይወዳሉ። አብዛኛው ከት/ቤታችን የጨረሱ ተማሪዎች ጥሩ ስራ ያላቸው ስለሆነ ራሳቸውን የቻሉ ናቸው። ባፈና የምትኖረው እዚሁ ግቢ ውስጥ ሲሆን በት/ቤት ውስጥም ስራ አላት። ባፈና ሁል ጊዜ ደስተኛ ናት። አራት ልጆችም አሏት። ባለቤቷ ጎሳዬ የመጠጥ ሱሰኛ በመሆኑ ትዳራቸው ፈርሷል። አልፎ አልፎ ጎሳዬን መካኒሳ ውስጥ አየዋለሁ። ቤኪ እባክሽ ያለፈውን ሁሉ ረስተሽ አዲስ ሕይወት ለመጀመር ሞክሪ። እንደዚህ ብዬ ሀሳብ ሳቀርብ ቀላል ይመስላል። ለማንናውም አዲስ ሕይወት እንድትጀምሪ እፀልይልሻለሁ። ለሰው የማይቻለዉ ለእግዚአብሄር አይሳነውም። እግዚአብሔር በመንገዱ ሁሉ እንዲመራሽ እፀልያለሁ። ለአእምሮሽ ሰለሙን ይስጥሽ። ኤፌሶን 3:20–21 አንቢቢ። እግዚአብሄር ሁል ጊዜ እንደሚጨነቅልሽ እወቂ። ከአሁን በኋለ በቅርበት ግንኙነት እናደርጋለን ቶሎ ቶሎ ብዬም እፅፍልሻለሁ። ነገ ለሳምንት ያህል ወደ ገጠር እወጣለሁ። እግዚአብሄር ካለ እንደተመለስኩ እጽፍልሻለሁ። ዓለም ሰላምታ እያቀረበችልሽ ነው። በጣም ናፍቀሽናል በጣም እንወድሻለን።

እግዚአብሔር ይክበር

በሀይሉ አበበ

የካቲት 26, 1992

ውድ ለሆንከው በሀይሉ

 

ስለፃፍክልን መልካም ኢሜይል እግዚአብሔር ይባርክህ። ከአንተ ይህን ያክል በመስማቴ እና በመካከላችን መጥፎ ነገር አለመኖሩን በማወቄ በጣም ደስ ብሎኛል። አዎን ያለፈውን መርሳት እችላለሁ። በተለይም አንተ ከእኔ ጋር መሆንህን እንደዚህ ከተረዳሁኝ ያለፈውን መርሳት ይቻለኛል። በሀይሉ በመጀመሪያ ኢሜይሌ ውስጥ የነገርኩህ ነገር በድንገት ነበር የተከሰተብኝ። ላብራራልህ እንደሞከርኩት ሀዘን በተገቢው መንገድ ካልተያዘ ብዙ እንግዳ ነገሮችን ይዞ ይመጣል። በተከሰተብኝ ነገር ውስጥ ሳትናደድብኝ እንደወደድከኝ ስለቆየህ እግዝአብሔርን አመሰግናለሁ። አንተንም በድጋሚ አመሰግንሃለሁ። አሁንም ከ2 አመት በፊት በኒውበርግ በተፈጠረውና ሀዘን ውስጥ ከቶኝ ስሜቴን በጎዳው ጉዳይ ላይ እየሰራሁኝ ነው። የዚያ ሀዘን ምንጭ የሆነው እኔና ባለቤቴ ኒል እንዲሁም ታናሹ ልጄ ጄይላን ከቤታችን ትንሽ ርቃ በምትገኘው ክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ለማምለክ በምንሄድበት ጊዜ ነው። ነገሮች ሀዘንን አስከትለው የመጡት እንደ ጎርፍ በአንዴ ነበር። ውጤቱም ልክ በኢትዮጲያ ጉዳይ ላይ ስሜቴ በተጎዳው ዓይነትና መጠን ነበር። ያ ጉዳይ አሁንም አልተፈታም። ነገር ግን ቶሎ እንደሚፈታ እምነት አለኝ። ይህንን በተመለከተ ጽፌልሃለሁ። የፃፍክልኝ ደብዳቤ በእውነት ከልቤ ነው ያዘመረኝ። እናም በትክክለኛ መንገድ ወደፊት ለመቀጠል ተዘጋጅቻለሁ። በዚህ 20 ዓመት ውስጥ ስለ ነበረው ጉዳይ ላይ ሙሉ መረጃ ከአንተ አላገኘሁም። ይህንን ለበኋላ ላዘግይ።

 

በጥሩ ሁኔታ ላይ ስለምገኝ ስለ እኔ አትጨነቅ። እግዚአብሄር ድንቅ በሆነ ሁኔታ በአእምሮዬ እና ስሜቴ ውስጥ እየሰራ ነው። አምላክ ታላቅ የሆነ አምላክ እና ፈዋሽ የሆነ ነው። እናም አብዝቼ እወደዋለሁ። ይህንን ታላቅ ስራውን ገና ከአንተ ባልሰማም እንኳ እግዚአብሔር አስቀድሞ የእርሱን ፍለጋ አስተምሮኛል። ይህንን የእርሱን ፍለጋ ከምንም ምቾት ከሚሰጥ ነገር እንዳላነፃፅር ምቾት ደግሞ ከምንም እንዲሁም ከማንም እንዳልሻ አስተምሮኛል። ከአንተ ጋር ግንኙነት መጀመሬ በደስታ እንድፈነድቅ እና እንድዘል አድርጎኛል። በደስታ ላይ ደስታ ጨምሮልኛል። ዓለም በእንግሊዝኛ መፃፍ ትችላለች? ብትችል የእርሷንም መልዕክት ማንበብ ብችል ደስ ባለኝ። ስለ ልጆች እስኪ አብራርተህ ፃፍልኝ። በፊት በዋሽንግተን ክልል ውስጥ እንኖር ነበር። አሁንም ከዚያው ክልል በካናዳ ድንበር በኩል ቤት አለን። እናም ልጆችህን መጎብኘት እንችል ነበር። ላያቸውም እፈልጋለሁ። ስለ መስማት የተሳናቸውና ወንጌላዊያን ማሰልጠኛ ጣቢያ የነገርከኝ መልካም ይመስላል። ቀደም ሲል የነበሩ ሰዎች አሁንም በስራ ላይ የመሆናቸው ነገር በጣም ያስደስታል። የቀድሞ ተማሪዎች መልካም ኑሮ የመኖራቸው ነገር ደግሞ በጣም አስደሳች ነገር ነው። ስለ ባፈና ያሰማሀኝ ዜናም በጣም አስደስቶኛል። እባክህ እዚያ ላሉት እና ለማውቃቸው ሁሉ የከበረ ሰላምታ አቅርብልኝ። በተለይም ለደመረ፣ አልማዝ እና ቤተሰቧ። ሁሉም ለእግዚአብሔር ይሁን

እወድሃለሁ

ቤኪ

ምዕራፍ 11 የፔፐርዳይን ትምህርታዊ ኮንፈራንስ ዳግም ማግለል ሚያዝያ 23-26, 1993

ዳግም ማግለል

 

በሀይሉ በ1992 ከፃፈልኝ ኢሜይል ወዲህ ምንም መልእክት ጽፎልኝ አያውቅም። በድርጊቱ ልቤ ተሰብሮ ስለነበር እኔም እስከ አሁን ድረስ አልፃፍኩለትም። ሚያዝያ 1993 ውስጥ ሳንታ ሮዛ ካሊፎርኒያ ውስጥ ከሚኖር የቆየ ጓደኛ እና ቤተሰብ ከሆነ ሰው አንድ የስልክ ጥሪ ደረሰኝ። እንዳጋጣሚ ሆኖ በዚህን ጊዜ በሀይሉ ስለ እኔ መረጃ ያፈላልግ ነበር። ቭርጂል ዊር ከበሀይሉ እና ደመረ ጋር የጠበቀ ግንኙነትና ወዳጅነት ያውቅ ስለ ነበር አንዳች አስደሳች ዜና ሊያሰማኝ ይሻ ነበር።  በዚህን ጊዜ በፔፐርዳይም ትምህርታዊ መግለጫ ተጀምሮ ስለነበር በሀይሉ እና ደመረ ያንን ትምህርታዊ መግለጫ ይከታተሉ ነበር። በዚያ ታላቅ በሆነ ዩኒቨርሲቲ በሚሰጠው ትምህርት ላይ ተገኝቼ እነዚህ የቀድሞ ወዳጆቼን የማግኘት አጋጣሚ ይኖረኝ ይሆን? የቆየ ወዳጄ እንደመሆኑ መጠን የቭርጂልን እኔን ለማግኘት ጉጉት እንዳለው ስሰማ የተባረክሁ ያህል ተሰማኝ። እናም በዋሽንግተን ክልል ውስጥ እንኖር ስለነበር ከባለቤቴ ኒል ጋር ሆነን ቭርጂል ለምን እንደፈለገኝ ለማወቅ 1200 ማይሎችን የሚሸፍነውን ርቀት እየነዳሁ ዳግም ከዚህ ወዳጄ ጋር ለመገናኘት ጉዞ ጀመርን። ይህ ጉዞ አንድ ቀን ተኩል ያህል ነበር የወሰደብን። ነገር ግን ፍርሃት ይሰማኝ ነበር ምክንያቱም በሀይሉ እግዚአብሄር እንደፈቀደ ቶሎ ቶሎ እፅፍልሻለሁ ብሎኝ የነበረ ቢሆንም በዓመት ውስጥ የፃፈልኝ አንዴ ብቻ ነበር። የደመረ ሁኔታ ደግሞ ሰምቼም አላውቅም። እንዲያውም እርሱ ኢሜሌን ያነባል የሚል እምነት የለኝም።

 

ምናልባት ደመረ ስለ እኔ መረጃ እንዳያገኝ ያደረገው በሀይሉ ይሆን? እኔ ሁለቱንም በእኩል ደረጃ የምወዳቸው ሲሆን የዚህ ጥርጣሬዬ ምንጭ ካለፈው ልምዴ ምን እንደሆነ በሚገባ አውቃለሁ። ደመረ ከእኔ ጋር ካለው ቅርበት የተነሳ ምናልባት በሀይሉ በኢትዮጲያ ውስጥ ያለኝን እንቅስቃሴ ትገዳደረኛለች ብሎ ፈርቶ ይሆናል። ከዚህ ውጭ ያለ ምንም ጥርጥር ከደመረ ጋር መልካም ግንኙነት ሊኖረኝ እንደሚችል አውቅ ነበር። እኔና ደመረ ሁል ጊዜ ግልጽ ተግባቦት ነበረን። ነገር ግን ከበሀይሉ ጋር ታሪኩ የተለየ ነው። በመንገዴ ላይ ሳለሁ ወደ ፔፐርዳይን በቀረብኩ ቁጥር ሀዘኔ እየጨመረ ነበር። በምን ዓይነት ሁኔታ እንደሚቀበሉኝ እርግጠኛ መሆን አልቻልኩም። ምናልባት በሀይሉ አግሎኝ ከደመረ ጋር ያለኝን ግንኙነት አደጋ ላይ ይጥል ይሆን? እናም በጉዞዬ በሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ በፀሎትና የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን ከካሴት እያዳመጥኩኝ ነበር የተጓዝኩት። ይህን ያደረኩትም ምናልባት እግዚአብሔር ለግራ መጋባቴ መልስ ይሰጠኝ እንደሆነ በማሰብ ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር ዝምታ የመረጠ ይመስላል። እዚያ ከመድረሴ በፊት የሆነ ስልት መቀየስ እንደሚገባኝ ታሰበኝ። እናም እዚያ ስደርስ በሀይሉን ከማግኘቴ በፊት ደመረን  ማግኘትና ኢሜሌ ደርሶት እንደሆነ መጠየቅ እንዳለብኝ እንደ ስልት ቀየስኩ። መልእክቶቼን ካላገኘ በሀይሉ በሁለታችን መሀል እንደገባ እና የኢሜል ግንኙነት እንዳይኖረን ለማድረጉ ማረጋገጫ ይሆነኛል።

 

ይህ ከሆነ ከደመረ ጋር የሚኖረኝን አብሮነት መቀነስ ብሎም በስውር ማድረግ አለብኝ ማለት ነው። ፔፐርዳይን በሚገኘው ማሊቡ ካምፓስ እንደደረስኩ ብዙ ሰዎች በሚራወጡበት አደባባይ ከህዝቡ ጋር ተቀላቅዬ ተቀመጥኩ። ሰዎች አንዱን ክፍለ ትምህርት ከሌላው በማማረጥ ለመከታል ይቸኩላሉ። በዚያን ቀን ከሰዓት በኋላ አደባባዩ በተለየ ትርኢት ማለትም የሰዎች ከክፍለ ጊዜ ክፍለ ጊዜ ሲቻኮሉ በማስተናገድ አለፈ። ምናልባት ደመረ እና በሀይሉ ከእነዚያ ሰዎች መካከል ይሆናሉ ብዬ ተስፋ በማድረግ በዓይኔ መፈለግ ያዝኩኝ። ያየኋቸው ከረጂም ጊዜ በፊት በመሆኑ ላላስታውሳቸውና መልካቸውን ላላይ እችል ይሆናል። የሰው ብዛት እጅግ በመሆኑ ከጭድ ውሰጥ መርፌ እንደመፈለግ ነው። ነገር ግን እኔን ትኩረት የሰጠኝ ምንም አልነበረም። እናም በሀይሉ አስቀድሞ እንዳያየኝ መጠንቀቁ ይቅርና በጭርሽ ደብዛቸውም ባለ መኖሩ ተስፋ ቆረጥኩ። በዚያ አደባባይ እነርሱን በዚህ ዓይነት በዓይን ፈልጎ የማግኘቱ ነገር እጅግ የመነመነ ሆኗል። ምሽት ከመሆኑ ሁለት ሰዓት አስቀድሞ መኪና ተከራይቼ ወደ አንድ ታላቅ አደባባይ ሄድኩኝ። ይህ አደባባይ በእስፖርት ሜዳ ዓይነት መቀመጫ የተዘጋጀለት በመሆኑ የተቻለኝ ያህል ወደ ሁለቱ የመጀመሪያ መግቢያ ተጠግቼ ቦታ ያዝኩ። ይህ አደባባይ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ አማኞች ለማታ የአምልኮ እና ትምህርት የሚሰባሰቡበት ነው። አቀማመጤ ምቹ ስለ ነበር እይታዬን ያስተካከልኩት በመግቢያው በኩል በሚገቡት በያንዳንዱ ሰው ላይ ነበር።

 

በአንድ ደቂቃ ውስጥ በበሩ የሚገባ የሰው ቁጥር ብዙ ቢሆንም ትኩረቴ እንዳይሰረቅ በመጠንቀቅ በዓይኔ ፍለጋዬን ቀጠልኩ። ከደቂቃዎች ቆይታ በኋለ ደመረ እና በሀይሉ ወደ ውስጥ ሲገቡ አየኋቸው። ነገር ግን ወደ ሚሔዱበት በዓይኔ ስከተል ከሰው ቁጥር የተነሳ በህዝብ ውስጥ ገብተው ከዓይኔ ተሰወሩ። ተስፋ ቆረጥኩ። የሆነ ሆኖ የአምልኮ ሰዓት የተጀመረ በመሆኑ ባለሁበት ቦታ ተመቻችቼ ተቀመጥኩ። የተወሰኑ መዝሙሮች ከተሰሙ በኋላ ከአትሮኖሱ አከባቢ አንድ ማስታወቂያ ተሰማ። “በዛሬው ምሽት በዚህ በፔፐርዳይን የትምህርት መዕከል ሁለት ኢትዮጲያዊያን በሀይሉ አበበ እና ደመረ ቸርነት በኢትዮጲያ ውስጥ ለሰጡት የላቀ አገልግሎት ክብር እና እውቅና እንሰጣለን” በማለት ጎላ ባለ ድምጽ መልዕክቱ ተስተጋባ። ልቤ በደስታ ተሞላ፤ ምቱም ጨመረ። በመጨረሻም ከ18 ዓመታት በኋለ ላነጋግራቸው ብዬ ወዳሉበት ቦታ ሄድኩ። ቆይቶም እነርሱ ዘንድ ከመድረሴ በፊት የተሰጣቸውን እውቅና ለመቀበል ወደ መድረኩ እየወጡ በመመልከቴ ሀዘኔ ወደ ፍንደቃ በቅጽበት ተለወጠ። ይህ አጋጣሚ እነዚህ የድሮ ወዳጆቼ የት እንደተቀመጡ በትክክል መለየት ቻልኩ። በአደባባዩ ውስጥ የተቀመጡበትን ቦታ እንዳየሁ ግንኙነቴን በጥንቃቄ እና በሚስጢር አደርጋለሁ ብዬ የወሰንኩት ውሳኔዬ ከመቅጽበት በኖ ጠፋ። እናም በፍጥነት ወዳሉበት መራመድ ጀመርኩ። በውስጤ ይናኝ የነበረው ደስታ እና ለእነርሱ ያለኝን የጋለ ወንድማዊ ፍቅር ለአንባቢው በትክክለ ማሳየት አልችልም ምክንያቱም ከማስበው በላይ በመሆኑ በውስጤ ያሉ ቃላቶች ምንም ያህል ቢሰባሰቡ በዚያን ቅጽበት የነበረኝን ስሜት በፍጹም ሊገልጹ አይችሉም።

 

በዚህን ሰዓት ይህንን ማስታወሻ ስጽፍ ዓይኔ በእንባ ተሞልቶ ነው። የተቻለኝ ያህል ቀረብኩኝና እነርሱ ባሉበት መደዳ በቀስታ ቁጭ አልኩ። በዚህን ሰዓት ልቤ ከእነርሱ ጋር ውድድር ውስጥ ነበር። በዚህ ሁኔታ ያለውን ልቤን እንዴት አድርጌ ልቆጣጠር? በተቻለኝ መጠን ስልት ብዬ የቀየስኩት ሀሳብ እንደገና ማጤን ጀመርኩ። እነርሱ የእውቅና ሰርትፍኬታቸውን ተቀብለው እየተመለሱ ባሉበት ጊዜ ፍጹም በሆነ ፍቅርና አድናቆት ተሞልቼ ዓይኔን ከእነርሱ ላይ ማንሳት አልቻልኩም ነበር። እነርሱም እንደ እኔው ሁሉ በእድሜ ስለመግፋታቸው ከፊታቸው ይነበባል። እንደገና ስለ አየኋቸው በጣም ደስ አለኝ። ከዚያም ቁራጭ ወረቀት ከቦርሳዬ አውጥቼ ይህንን ማስታወሻ ማስፈር ጀመርኩ። ” ደመረ እኔ ቤኪ ነኝ ካለህበት ትንሽ ራቅ ብዬ ነው ያለሁት። የለበስኩት ጥቁርና ቀይ አበባ ያለበት ቀሚስ ነው። በሀይሉ እዚህ መሆኔን ሳያውቅ በፊት ላይህ እፈልጋለሁ እናም በፕሮግራሙ መጨረሻ ላይ እንገናኝ። እወድሃለሁ ቤኪ”። የፃፍኩትን ማስታወሻ አጣጥፌ ለደመረ ስጪልኝ በማለት በጀሮዋ ነግሪያት አጠገቤ ለተቀመጠቸው አንዲት ሴት ሰጠኋት። በዚያን ሰዓት እዚያ ስለ መኖሬ ለበሀይሉ የመግለፄን ጉዳይ አደጋ ውስጥ መሆኑ ይታወቀኝ ነበር። ይህች ሴት በሀይሉ እና ደመረን የምታውቃቸው ቢሆንስ? አልኩኝ በልቤ። ሀሳቤ በሚሰጠው ትምህርት ላይ አልነበረም። የፕሮግራሙ ፍጻሜ አልደርስ አለኝ ፤ ሰዓቱ እጅግ ረዘመብኝ። የተጀመረው ነገር መፈፀሙ አይቀርምና ፕሮግራሙ እንዳለቀ ደመረ ወደ እኔ ዞር ብሎ ምልክት ሰጠኝ።

 

አሁንም ፎቶ ለመነሳት ወደ ፊት ይወጣሉ እግረ መንገዱንም ሊያገኘኝ ይፈልጋል። ከብዙዎች ጋር እየተቃቀፉ ፎቶ ይነሱ ስለነበር አሁንም የመገናኛ ጊዜያችንን እጅግ አረዘሙት። እኔ ግን በጣም ተጣድፌያለሁ። “ይህን ሁሉ ህዝብ ከእኔ አስበልጠው ሊያውቃቸውና ሊወዷቸው የቻሉት እንዴት ነው”ብዬ በቅናት መንፈስ  አሰብኩ። እኔም እንደ ሌሎቹ ሰዎች በዚያ ስፍራ ሆኜ ልስማቸውና እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት ፈልጌ ነበር። ነገር ግን ድፍረት ማግኘት አልቻልኩም። አሁን ሰዓቱ ደርሷል። ደመረን ላገኘው ነው። ምንም እንኳ በሀይሉ እንዳያየኝ ጥንቃቄ ባደርግም ከእይታው ልሰወር አልቻልኩም። በምልክት ቋንቋ ከደመረ ጋር እየተነጋገርኩ እየቀረብኩት ሳለሁ ነበር በእይታው ውስጥ የወደቅኩት። ይህ የሆነው ደመረ በምልክት ቋንቋ ሲናገረኝ አይቶ ወይም ደግሞ ሌላ ሰው ስለ እኔ በምልክት ቋንቋ ነግሮት ይሆናል። በጣም ጥንቃቄ እና ጥርጣሬ በተሞላበት ዓይኖቼ ዙሪያዬን ስቃኝ አየሁት። እንዳየኝ ስረዳ ለማስመሰል ብዬ በእርሱ አቅጣጫ ሌላ ሰው ሰው እንደሚፈልግ ሰው እየሆንኩ ነበር። ነገር ግን በትክክል አይቶኛልና ማስመሰሉ ምንም ዋጋ አልነበረውም። በዚያ ስፍራ ትሆናለች ብሎ ስለማይገምት አያየኝም ብየ ስለ አሰብኩ ትንሽ ራቅ ብዬ ቆምኩ። ስለዚህ ከሰው መካከል አይፈልገኝም ብዬ አሰብኩ። በመጨረሻም ቀድሞውኑ በዚያ ስፍራ እንደምኖር እንደሚያውቅ ተረዳሁ። ዋሽንግተን እያለሁ ቭርጂል እንደምመጣ ለደመረ እንዲነግረው ነገር ግን ለበሀይሉ እንዳያሳውቅ በስልክ ነግሬው ነበር።

 

በኋላ ደመረ እንደነገረኝ ገና ከዋሽንግተን ሳልነሳ ጉዳዩ ከቭርጂል አምልጦት ከጆሮው ገብቶ ኖሯል። ይህንን ሁሉ ሳላውቅ በተረበሸ አእምሮ ጥቂት ሜትሮችን ርቄያቸው ቆምኩ። አሁን ትክክለኛ ሰዓት መድረሱን ተረዳሁ። ደመረም የተቻለውን ያህል ተጠግቶኝ ከበሀይሉ እይታ ውጭ ወደምሆንበት ቦታ ወሰደኝ። ይህም ሊሰራ አልቻለም። እንዲያውም በሀይሉ ድምፁን ከፍ አድርጎ ተጣራ። ቤኪ ጠብቂን እንጂ ለምን ተሸሽናለሽ? አለ። በዚህን ጊዜ ቆምኩ። ወደ እነርሱ ዞሬ በፍርሃት እና ደስታ ተሞልቼ ሁለቱንም አቀፍኳቸው። ዝምታውን የሰበረው በሀይሉን በመሆኑ ድፍረቱን አደነኩ። ፍርሃቴን ወዲያ አሽቀንጥሬ ኢሜይሎችን በሙሉ ተቀብሎ እንደሆ ደመረን ጠየኩኝ። በአድናቆት ዓይን እያየኝ “በሙሉ” ነው ያልሽኝ አለኝ። ከአንቺ የደረሰኝ አንዲት አጭር ኢሜይል ብቻ ነው አለኝ። ወደ በሀይሉ ዞሬ እየጨበጥኩት ኢሜይሎቼን በሙሉ ለምን ለደመረ አላደረስክልኝም? ብዬ ጠየኩት። በዚህን ጊዜ እንባ እየተናነቀኝ ነበር። የመከላከል ይመስላል ወደ ደመረ ዞሮ በአማርኛ ከተነጋገረ በኋላ ወደ እኔ ተመልሶ ቆይተው እንደሚነጋገሩበት ነገረኝ። ቀጥሎም “ዛሬ ምሽት ለክብራቸው በተዘጋጀ የእራት ግብዣ ላይ ስለምንሳተፍ ከአንቺ ጋር ለመነጋገር ጊዜ የለንም” በማለት አብረን መቆየት እንደማንችል ማብራሪያ ብጤ ሰጠኝ። ይህ ንግግሩ በእጅጉ ውስጤን ጎዳኝ። በዚህ ግብዣ ላይ አለመሳተፌ ተሰማኝ። በዚህ ጊዜ ለቅሶዬ እየጨመረ በመምጣቱ ይህን ጉዳይ በቀጥታ ባላነሳም ከፊቴ ላይ በግልጽ ከሚያሳብቀው ስሜቴ ሳይረዱት አይቀርም።

 

 

በሀይሉ እንደረሳኝ እህትነቴ እንደተረሳ ቤተሰቦቼን ማማ አባ ማለቱ የሀሰት እንደ ነበር ገብቶኝ ተስፋ ቆረጥኩበት። የቤተሰቦቼን የህልፈት ዜና እንደሰማን በጋራ ሆነን መሪር ሀዘን ውስጥ ተሰምቶን አብረን አንብተን ነበር። በሀይሉ የአባቴ የተለየ ጓደኛው ነበር። ለእናቴም ልዩ ፍቅር ነበረው። አባቴ ከሞተ በኋላ በኢትዮጲያ ላለው የቤተ ክርስትያን ተልዕኮ ዋና ዳይሬክተር ሆኗል። ከቤተሰቦቼ ጋር የነበረውን ሁኔታ አስታውሼ አሁን ሆን ብሎ ከሚያደርገው ሁኔታ ጋር አነፃፀርኩ። ያንን ሁሉ ባይረሳ ኖሮ ዛሬ በዚህ ሁኔታ በአደባባይ አያዋርደኝም፤ ጣል ጣል አያደርገኝም ነበር አልኩኝ። ልቡን በዚህ ሁኔታ በእኔ ላይ የሚያደነድነውና ጭካኔውን የሚያሳየኝ ዛሬ ብቻ አይደለም። የሆነ ሆኖ ዛሬም ጭምር የሚያሳየኝ ድንቁርናው በጣም አስገረመኝ። የአባቴን ቦታ በመያዙ በውኑ በቤተሰቦቼ ሞት ተደስቷል ማለት ነው? ብዬ ተገረምኩ። ከልብ ሆነ ፍቅር ለምን አያሳየኝም? ስለ እኔ እንኳን ባይሆን ስለ ቤተሰቦቼ ብሎ ለምን ርህራሄ አያሳየኝም? በ1960ዎቹ ውስጥ የኢትዮጲያ ስራ እንዲጀመር የረዳው ካርል ቶምፕሳን ለምስክርነት አለ። ይህ ሰው የእኔን ጭንቀት እና ጉዳት የሚረዳ  ነው ብዬ አሰብኩ። ከጥቂት ወራት በኋላ  ይህንን ሰው ኢትዮጲያ ውስጥ አግኝቼው ነበር። በዚያን ጊዜ ከእርሱ የሰማሁት ከገመትኩት በተቃራኒው ነበረ። ድምዳሜ ላይ ላደረሰው ለአስተያየት ግምገማ የወሰደው በፔፐርዳይን ከበሀይሉ ጋር የነበረኝን ምልልስ አይቶ ነው።

 

እናም ከዚህ ሰው ጋር ስንገናኝ ያለኝ “አንቸ ለበሀይሉ ክብር የለሽም፤ እንዲያውም የአእምሮ ችግር አለብሽ” ነበር ያለኝ። ይህም በሀይሉን ለመከላከል ሆን ብሎ ያደረገው ነገር ነው። ካርል ቶምፕሰን ከደመረ እና በሀይሉ ጋር ያለኝ የጥንት ግንኙት በጥንቃቄ ፈትሾ ቢሆን ኖሮ ዛሬ በዚህ ዓይነት አይዘልፈኝም ነበር። ነገር ግን የሚደንቀኝ ይህ ዘለፋውና የተጣመመው ምስክርነቱ ነገሮችን የቀየረ እንደሆነ ነው። በኢትዮጲያ ሳለን ካርል ቶምፕሰን የነገረኝ እኔን መስዋዕት በማድረግ ደመረ እና በሀይሉን እንደሚከላከላቸው ነው። ይህንን የሚያደረገው ወደ አሜሪካ ተመልሶ የአእምሮ ችግር እንዳለብኝ ለሚያገኛቸው አሜሪካዊያን በማወጅ እንደሆነ ነግሮኛል። በኢትዮጲያ ውስጥ የሚሰራውን የቤተ ክርስትያን ስራ ለማጥፋት እንደተነሳሁ በሀይሉ እንዳስረዳው ነግሮኛል። ካርል ቶምፕሰን በተጣመመ መንገድ እንዲተረጉም ያደረገው ይህ የበሀይሉ የውሸት ውንጀላ ብዙ እንዳስብ አድርጎኛል። እኔ በሀይሉን ስወደው እርሱ ደግሞ ብዙዎችን ጠላቴ በማድረግ በስውርና በይፋ እያጋጨኝ ነው። በሚቀጥለው ቀን ጠዋት ላይ በሀይሉ ከእኔ ጋር ያለውን አብሮነት በመሰረዝ ያገለለኝ እጅግ በፈጠነ ጊዜ ውስጥ ነበር። እኔ የእግዚአብሄር ሰው ነኝ በእግዚአብሄር ስራ በመያዜ ምክንያት ለአንቺ ጊዜ የለኝም አለኝ። የእኔም መልስ “በኢትዮጲያ ያሉትን ወንጌላዊያን እኔን በምትይዝበት ሁኔታ እንዲይዙ የምታሰለጥን ከሆነ የእግዚአብሔር ሰው ስለመሆንህ እጠራጠራለሁ” አልኩት።

 

 

ቀጥዬም እዚህ በፔፐርዳይን ያሉ ሰዎች እምነታቸው እንደ እኔው ነው። በሌሎች አብያተ ክርስትያናት ውስጥም ክርስትያኖች እንዳሉ እናምናለን አልኩት። እርሱም መልሶ ተሳስታችኋል አለኝ። በመጨረሻም “አንቺ የቤተ ክርስትያናችን አባል አይደለሽም። ስለሆነም ከአንቺ ጋር ምንም የለኝም”ብሎኝ ከእኔ ተለየ። በመጀመሪያ ደመረ ምንም ሳይናገር ዝም ብሎ ነበር የሚያደምጠን። በሀይሉ ሲሄድ ግን ደመረም በድንገት ብድግ ብሎ እዚያው ባለሁበት በከባድ የስሜት ስቃይ ውስጥ ትቶኝ ተከትሎት ሄደ። በዚያን ቀን ከዚያ ግቢ የወጣሁት ሊገለፅ በማልችል ሁኔታ ወዳጆቸ ነበሩ ሁለቱ ሰዎች አግልለውኝ በከባድ ሀዘን ውስጥ ሆኜ ነበር። እነዚህ ሁለቱ ሰዎች ኢትዮጲያ ውስጥ ቤተሰቦቸ በህይወት እያሉ ሲደክሙበት የነበረውን ስራ ነበር የተረከቡት። አሁን ግን የቤተሰቤ ቅሪት የሆነውን ታሪኬን ለማጥፋት እየሰሩ ናቸው። ይህንን ሁሉ መንገድ ተጉዤ የመጣሁት ከእነርሱ ውድ ከሆኑ ወዳጆቼ ጋር ተገናኝቼ ጥሩ የአብሮነት ጊዜ ለማሳለፍ ነበር። አሁን ግን በተሰበረ ልብ ወደ ቤቴ ጉዞ ጀመርኩ። ስመለስ በመንገዴ ላይ ያሉትን ዘመዶቼን እየጎበኘኋቸው ነበር። ቤቴ ስደርስ በሚደንቅ ሁኔታ ደመረ የሚገኝበትን የስልክ ቁጥር በኢሜይል ልኮ አገኘሁ። ምንም የተለየ ነገር ከእርሱ ባልጠብቅም ደወልኩለት። በሀይሉን ተከትሎ በክህደት መልክ ባለሁበት ትቶኝ መሄዱ እንደ መርዝ ነው የሆነብኝ። የሆነ ሆኖ ጥሩ የሚባል የስልክ ውይይት ካደረግን በኋላ በሀይሉን መቋቋሜን አድንቆ ደመረም እንደገና የሆነ ነገር ከእኔ ለመስማት እንደሚፈልግ ነገሮኝ ተለያየን።

 

ከዚህም በተጨማሪ በሀይሉን ተከትሎ የሄደበት ምክንያት ከእኔ ጋር መሆኑን በሀይሉ በአሉታዊ ጎኑ ወስዶ ለጆን ኤድ እንዳያቃጥርበት ሰግቶ እንደሆነ እኔን ለማግለሉ ደግሞ በሀይሉ ምንም ተጨባጭ ምክንያት እንደሌለው አስረድቶኛል። ከሁለት ሳምንት በኋላ ደመረንና ባለቤቱ አምሳለን ከነ ልጆቹ አትላንታ ውስጥ ጎብኝቻቸዋለሁ። ደመረ ስለ በሀይሉ ሆዴን የሚንጡ ብዙ ቁም ነገሮችን ነግሮኛል። እነዚህን መረጃዎች ሁሉንም ባይሆን የተወሰኑትን አውቃቸዋለሁ። እነዚህ መረጃዎች እውነት ለመሆናቸው በፔፐርዳይን ካሳየኝ በመነሳት መገመት ይቻላል። ቢሆንም ለበሀይሉ ያለኝን ፍቅር የሚቀንሱ አይደሉም። የሚያሳዝነው ነገር እርሱ መሸከም ከሚችለው በላይ ሀላፊነት መሰጠቱ ነው። ይህ የተሰጠው ሀላፊነት ለራሱ እንዲያደላ፣ በራሱ እንዲኮራ በሚያገለግላቸው ህዝቦች ላይ አምባገነን እንዲሆን አድርጎታል። ደመረ ግንኙነታችን በምስጢር እንዲሆን አጥብቆ ለምኖኛል። የልብ ችግር ያለበት በመሆኑ ብቻ ብዬ ልመናውን ተቀብያለሁ። ነገር ግን በዚህ ዓይነት ዘላቂ ግንኙነት እንዲኖረን ሳይሆን አሁን ካለበት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ መውጣት እስኪችል ብቻ ነው።

 

ከዚህ መውጣት እንዲችል መርዳት የምችልበት አንዱ መንገድ ደመረ እና አምሳለ ወደዚህ ወደ አሜሪካ መጥተው በቋሚነት እንዲኖሩ በማድረግ ነው። በመሆኑም እኔና ኒል እኛ ወዳለንበት ኦሃዮ መጥተው ከእኛ ጋር እንዲኖሩ ዝግጅት ማድረግ ጀምረናል። ደመረ የጆሮ ሃኪም ለመሆን ይመኝ የነበረው ህልሙ አሁን በእኔ እገዛ እውን ሊሆን ይችላል ማለት ነው። ነገር ግን አንድ ትክክል ያልሆነና መስተካከል ያለበት ነገር አለ። ይህም ደመረ በሀይሉ እና ጆን ኤድን ስለሚፈራ ለእግዚአብሄር እውነት ታመኝ መሆን አልቻለም። ይህ በግልጽ የሚታይ ነገር ነው። ከብዙ ወራት በኋላ በኢትዮጲያ ውስጥ የበሀይሉን ሸፍጥ ይፋ ለማውጣት ትክክለኛ ጊዜ ሲመጣ ዕውነትን ከመጋፈጥ ፋንታ ይሁዳ ጌታን እንደ ከዳ ደመረ እኔንም እውነትንም በመካድ ወደ ኋላ ተመልሷል። እውነታውን እንደ ካርል ቶፕሰን እና ጓደኞቹ በመሳሰሉ በአሜሪካዊያኖች ፊት መግለጥ ሲገባው ተቃራኒውን መርጦ ጀርባውን ሰጠኝ። የደመረ ታሪክ እንደ ወንድምና እህት የፍቅር ክህደት፤ እንዲሁም የበሀይሉ እና የጆን ኤድ ስልጣን ከፍርሃቱ ጋር ጥምረት ፈጥሮ ማንነቱንና ክብሩን እንዳስጣሉት የሚያሳይ ነው።

 

ማስታወሻ፡  አሁን ያለንበት ዓመት 2013ዓ.ም ሲሆን ይህንን ማስታወሻ ከጻፍኩኝ ከ19 ዓመታት በኋላ ማለት ነው። ይህም ማለት የደመረ፣ የበሀይሉ እኔ እና የፔፐርዳይን ትምህርታዊ ኮንፈረንስ ታሪክ ከተፃፈ ከ19 ዓመታት በኋላ ደመረ መስማት የተሳናቸውን የትምህርት ቤቱን ተማሪዎችን የአስገድዶ መድፈር ጥቃት ይፈጽምባቸው እንደ ነበር ታውቋል። ስለዚህ ደመረ እኔን የካደበት ምክንያት ከዚህ ስራው የተነሳ ነው። እውነትን ክዶ ወደ በሀይሉ እና ጆን ኤድ ስር የተወሸቀበት ምክንያት ይህንን እውነት የሆነውን ወንጀል ስለሚደብቁለት ነው።

 

ምዕራፍ 12 ከደመረ ጋር ዳግም ስለ መገናኘት ግንቦት 1, 1993

ውድ ደመረ

 

በስልክ መነጋገራችን እጅግ አስፈላጊ እና መልካም የሆነ ነገር ነው። በመነጋገራችን በጣም ተደስቻለሁ። አንተንና አምሳለን ወደ ኢትዮጲያ ሳትመለሱ እንደማገኛችሁ ተስፋ አለኝ። ልጆችህን እንደማያቸው ተስፋ አለኝ። ምናልባት ዊንዲ እና ባለቤቷ ከቤተሰቦችህ ጋር ይገናኛሉ ብዬ አስባለሁ። ከዚህ ጋር የላኩልህ ኢሜል ለበሀይሉ የሚደርስ ነው። እነዚያን ኢሜሎች አንተም እንደምታነባቸው ዓለማየሁ ቃል ገብቶልኛል። የፃፍኩት ብዙ በመሆኑና ለማንበብ ብዙ ጊዜ ስለሚወስድብህ ይቅርታ ልልህ እፈልጋለሁ። በክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ውስጥ ለመቆየት ያደረግነውን ተጋድሎ አንተና በሀይሉ እንድታውቁ እፈልጋለሁ። ይህም ለአንተ፣ ለበሀይሉ እና በኒውበርግ ስላሉት ሌሎችም ሰዎች ስላለን ፍቅር ነው። በሀይሉ እንደሚፈራኝ አውቃለሁ። ምክንያቱም በክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ውስጥ በሚመለከው ዓይነት ስለማላምን ነው። እኔንም ባልተገባ ሁኔታ የሚቀርበኝ ለዚሁ ነው። ነገር ግን ምንም ቢፈጽምብኝ ይቅርታ እንደማደርግለት እና እንደምወደው ንገርልኝ። የስልክ ቁጥሬ 509-486-0619 ነው። በቶሎ እደውልልሃለሁ።

እወድሃለሁ

ቤኪ

ምዕራፍ 13 አለመግባባት እና ሀዘን

ላቭላንድ ኦሃይዮ 45120

የስልክ ቁጥር 513-683-5199

መጋቢት 1994

ለኒውቤሪ የክርስቶስ ቤተ ክርስትያን

 

ውድ ወንድሞች እና እህቶች

በመጀመሪያ ስሜን እንዳስተዋውቅ ይፈቀድልኝ። ስሜ ጄፍሪ ኤ ብራልይ ሲሆን የላቭላንድ ክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ወንጌላዊ ነኝ። ከሁለት ዓመት በፊት ርቤካህ ፔይን ወደ ቤተ ክርስትያናችን መጥታ ነበር። እስከዛሬ የዘለቀውን መልካም ግንኙነትና ምክክር የጀመርነው በሀዘን የተጎዱ ወገኖች አማካሪ መሆኔን ካወቀችበት ጊዜ ጀምሮ ነበር። ምንም እንኳ ለሀዘን የዳረጓት ብዙ ችግሮች ያሉና ልትረዳ የሚገባ ቢሆንም ከአንድ ችግር በስተቀር አብዛኛዎቹን ልትወጣ ችላለች። ርቤካህ ቤተሰቧ የሆነችውን ቤተ ክርስትያን በማጣቷ በጣም እያዘነች ነው። ይህንን ደብዳቤ የምፅፈው ርቤካህ ከቤተ ክርስትያኗ ለምን እንደተገለለች ለማጣራት ሳይሆን ከደረሰባት ሀዘን እንዲታገግም ለመርዳት ነው። በመሆኑም ይህንን ደብዳቤ በተሰበረ ልብ እንደምትቀበሉ ተስፋ አለኝ። ምክንያቱም ርቤካህ ካለችበት ጭንቀትና ሀዘን ትወጣ ዘንድ ይህ ትልቅ እርምጃ ነውና። ከእርሷ ጋር እንደገና ውይይት ለመጀመር እግዚአብሔር ልባችሁን ቢያነሳሳ በተቀረው ዘመኗ ውሰጥ የምታደርገውን የሕይወት ጉዞ በእጅጉ ይረዳል። ደግሜ ላረጋግጥላችሁ የምፈልገው ከቤተ ክርስትያኗ የተገለለችበትን ጉዳይ ለማጣራትና  ከእርሷ ጋር ለመወገን ሳይሆን አገልግሎት ፈልጋ ወደ እኔ በመምጣቷ አስፈላጊውን እርዳታ እንድታገኝ ከመሻት አንፃር ብቻ ነው። ጌታዬም ከዚህ ያነሰ አገልግሎት እንደማይጠብቅብኝ አምናለሁ። አማካሪ እንደ መሆኔ መጠን ይህ ደብዳቤ ለእናንተ መፃፍ የሚገባኝ ሲሆን ይህም ርቤካን ከመታደግ አንፃር አስፈላጊ መሆኑን አምናለሁ። በዚህ ጉዳይ ላይ ልታናግሩኝ ወይም ልትፅፉልኝ ብትፈልጉ በደስታ የምቀበላችሁ መሆኔን በዚሁ አጋጣሚ እየገለጽኩ የስልክ ቁጥሬ 513-683-0029 መሆኑን ለማሳወቅ እፈልጋለሁ። እግዚአብሔር ይባርካችሁ

ጄፈሪ ኤ ብራሊ

1566 ዌስት ላብላንድ አቫ

ላቭለላንድ ኦሃይዮ

የስልክ ቁጥር 513-683-5199

 

 

መጋቢት 21, 1994

ለሚመለከተው ሁሉ

 

ይህ ደብዳቤ የተፃፈው ርቤካህ ፔይን የቤተክርስትያናችን አባልና በዚህ ቤተ ክርስትያን ስትገለገል መቆየቷን ለማረጋገጥ ነው። ከርቤካህ ጋር የተዋወቅነው ከ3 ዓመታት በፊት ሲሆን አሁን እንግዲህ ለሶስት ዓመታት እንተዋወቃለን ማለት ነው። በእነዚህ ዓመታት ውስጥ በሞት ስለ ተለዩአት ቤተሰቦቿ ሕይወት እና በኢትዮጲያ ውስጥ ስለገጠማት ነገሮች ሁሉ ለተከታታይ ጊዜያት በሰፊው ስንወያይበት ነበር። ሀዘኖቿን በተመለከተ በእነዚህ 3 ዓመታት ውስጥ በርካታ ክፍለ ጊዜያትን በመውሰድ ብዙ የምክር አገልግሎት ጊዜ ነበረን። ከዚህም በመነሳት ከ4 ወይም 5 ወራት በፊት ጀምሮ ርቤካህ እና ባለቤቷ ኒል የቤተ ክርስትያናችን ቤተሰብ አባል ሆነው መደበኛ አምልኮ እየፈፀሙ ከቤተ ክርስትያናችን ቤተሰብ ጋር የቅርብ ግንኙነት እያጠናከሩ ይገኛሉ።በዚህን ጉዳይ ላይ ማብራሪያ የሚፈልግ ሁሉ በስልክ ቁጥር 513-683-0029 ብትደውሉልኝ በደስታ የምቀበላችሁ መሆኔን እገልፃለሁ።

ጄፍ ብራሊ

ለኒውበርግ ክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ሽማግሌዎች ከኒውበርግ ክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ማህበር አባል የተላከ ደብዳቤ ነሓሴ 18, 1994

ለሚመለከተው ሁሉ

 

ባለፈው ዓመት ትምህርት ቤት ሳይከፈት በፊት ካርል እና ቤኪን በቤታቸው ጎብኝቼ ነበር።በነገረችኝ መሰረት በዚያን እግዚአብሔር ወደ ኒውበርግ የመለሳት ቤተ ክርስትያን ትክክለኛ መንገድ ይዛ እንድትጓዝ ለመርዳትና በመንፈስ መሞላት እንዴት እንዳለብን ልታስተምረን እንደሆነ ነው። እግዚአብሔር ወደዚህ የመለሳት እራሷ እንድትማር ለማድረግ እንደሆነ ከግምት ውስጥ አስገብታ እንደሆነ ጠይቄያት ነበር። እንዳል ሆነ ከነገረችኝ በኋላ ቀጥዬም እዚህ ያሉ ሰዎች ይህንን ትምህርት ለመማር ወደ ቤተ ክርስትያን የሚመጡ እንደማይመስለኝ ነገርኳት። እርሷም ደጋግማ እንደነገረችኝ ፈሬድ ይህ ጉዳይ ስለ መንፈስ ትምህርት ጉዳይ በሀሳቡ እንዳለ እና እንደሚያሳስበው መናገሩን ገልፃልኛለች። ኒውበርግ ክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ወደ ኢትዮጲያ ለሚያደርጉት ጉዞ ያግዘናል ብዬ ተስፋ አድርጌ ነበር ስትለኝ ደግሞ ይህንን አንዳታስቢ ምክንያቱም ፍሬድ የድጋፍን ጉዳይ አስመልክቶ ለዋልት ስያወያየው ዋልት ለሳን ጆሴ ቤተ ክርስትያን ጉዳዩን ሲያማክራቸው እንደማያደርጉት ከዚህ በመነሳት ፍሬድም የእርሱም ቤተ ክርስትያንም እንደማትችል መነጋገራቸውን ነግሬያታለሁ። ወደ ኬኒያ ከመሄዳቸው በፊት ፍሬድ ከካርል እና ቤኪ ጋር ረጂም ንግግር እንዳደረገ እና በንግግሩም ውስጥ የእነርሱን እምነት በቤተ ክርስትያን ውስጥ ለማስረጽ እንደሚሞክር ነግሯታል። ከኬኒያ ሲመለሱም ይህንን የእነርሱን እምነት እንደተለማመደ አሳውቋታል።

ቤኪ በክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ዶግማ እንደማታምን ነግራኛለች።

 

የኒውበርግ ክርስቶስ ቤተ ክርስትያን በማግለሏ የተነሳ የተከሰተ ሀዘን ጥቅምት 22, 1998

ለተከበራችሁ ለኒውበርግ ቤተ ክርስትያን

 

አብረን አምልኮ ከፈፀምን ከብዙ ዓመታት በፊት ቢሆንም መራራቃችን የፈጠረብኝ ቁስል እስከ አሁን በአእምሮዬ አለ። ምናልባት እንደምታስታውሱት ከአባልነትም ሰርዛችሁኛል። በእርግጥ በዚያን ጊዜ እኔን ከአባልነት ስታስወግዱኝ ትክክል ሊመስላችሁ ይችላል። ነገር ግን በዚህን ሰዓትም እንደዚያው የምታስቡ ከሆነ እጅግ ይደንቀኛል። ከተሳሳትኩ ልታርሙኝ ትችላላችሁ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ከእናንተ ዶክትሪን በተለየ ሁኔታ ስለቆምኩ ነው። ይህም ማለት ከክርስቶስ ቤተ ክርስትያን በተለየ በጥምቀት ላይ ያለኝ እምነት እና “ከክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ውጭ ክርስትና የለም” የሚለው ራሱ ስህተት ነው ብዬ ስለማምን ነው። ከክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ውጭ ክርስትያን የለም የሚባለው ስህተት ነው ብዬ አምናለሁ። በእርግጥ በዚያን ጊዜ ይህንን አስተሳሰብ በማስተማሬ በቤተ ክርስትያን ውስጥ ለሰዎች መከፋፈል ምክንያት በመሆኔ ትክክል አልነበርኩም። ከዚህም ሌላ መንፈሳዊ እርዳታ በሚያስፈልገን ጊዜ ቤተሰቤን ማግለላችሁ አሁንም ትክክል መስሎ የሚታያችሁ ከሆነ እጅግ እደነቃለሁ። ታስታውሱ ከሆነ ካርል በካንሰር በሽታ ለሞት ቀርቦ ነበር። እኔ ደግሞ የሰባት ልጆች እናት መበለት ነበርኩ። ነገር ግን እኔ ስጋታችሁ አድርጋችሁ በመውሰድ እስከ አሁን ከነቤተሰቤ አግልላችሁኛል። ነገር ግን እኔ ስጋት አልሆንኩባችሁም። ዛሬ ማታ ከአስር ዓመታት በኋላ ደብዳቤዎቻችንን እና የማፅናኛ ካርዶቼን አውጥቼ እያየሁ ነበር።

 

በእርግጥ ከኒውበርግ ማህበረሰብ እና ጥቂት ከክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ግለሰቦች ፍቅርና ማፅናናትን ነበር ያገኘሁት። ከክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ቢያንስ ሁለት ሰዎች የይቅርታ ካርድ ልከውልናል ምክንያታቸውም በሀዘንሽ ጊዜ ከአንቺ ጋር መቆም ነበረብን ነገር ግን ከአንቺ ጋር አልነበርንም፤ ይህ የሆነበት ምክንያትም ለሁሉም አባላት ቤተ ክርስትያኗ ከእርሷ ጋር እንዳትተባበሩ በማለቷ ነው ብለውኛል። እንደዚህ ማድረጋችሁ አሁንም ትክክል ነን ብላችሁ የምታስቡ ከሆነ እጅግ እደነቃለሁ። ምናልባት ይህን ጉዳይ ከአእምሯችሁ ጠፍቶ ይሆናል። ነገር ግን በእነዚህ አስር አመታት ውስጥ ከባለቤቴ እና ከእናትና አባቴ ሞት በላይ ይህ ድርጊታችሁ ታላቅ ሀዘን ፈጥሮብኛል። እንደዚህ የምልበት ምክንያት ክፉና መራራ ሰው ሆኜ ሳይሆን ስለምወዳችሁና ቤተሰቤም ስለነበራችሁ ነው። ምንም እንኳ ሊደርሱልን የሚችሉ ብዙ ጓደኞች ቢኖሩንም እኛ የፈለግነው እናንተን፤  በኒውበርግ የምትገኙት ቤተ ክርስትያን ነበር። በዚህ ባለፉት አስር አመታት ሕይወቴ የተመሰቃቀለ እና በሀዘን የተሞላ ነበር። ለሁለታችንም ይህን ጉዳይ ማስተካከል ከባድ ጉዳይ ሆኖ ቆይቷል። እኔ ግን ሁሌም አስታውሳለሁ። ሰባት ልጆችን ከእነዚህም ውስጥ አምስቱ የጉዲፈቻ ናቸው ለብቻዬ ማሳደግ ከባድ ጫና ፈጥሮብኛል።

 

እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ያጣኋቸውን ቤተሰቤ እና በመገለል ምክንያት የራሴን ማንነት ማጣትና ከባድ ሀዘን ፈጥሮብኝ ነበር። በእውነት ከመንፈሳዊ አንፃር ስመለከተው ይህ የማያባራ የሀዘን ድንግዝግዝ፣ መጠራጠርና ወንጀለኛነት ስሜት የሚፈጥር እንዲሁም በራስ መተማመንን የሚያሳጣ ሁኔታ ነው። በዚህ በምኖርበት ኦሀይዮ ውስጥ አንድ አነስተኛ የክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ማህበር ጎብኝቼ ነበር። የቤተ ክርስትያኑ ወንጌላዊ በሀዘን ለተጠቁ የምክር አገልግሎት የሚሰጥ ነው። ታሪኬን ሁሉ ልነግረው ወስኜ ስዘጋጅ ተመልሼ እንደማገኘው ነገርኩት። ታሪኬ ሁሉ ደግሞ በቀጥታ ከእናንተ ጋር የሚገናኝ ነው፤ ይህም ፍቅራችሁን ማጣቴ ነው። በእርግጥ ጥቂቱን የነገርኩት ሲሆን የተቀረውን ጊዜ በለቅሶ ነበር ያሳላፍኩት። መገለልን በእጅጉ እጠላለሁ። ምናልባት ከእናንተ እንደተገለልኩ ሁሉ ከእነዚህ አነስተኛ ቤተ ክርስትያንም ተመሳሳዩ እንዳይገጥመኝ ስጋት አለኝ። ይህንን ደብዳቤዬን በተዛባ ሁኔታ እንዳትረዱት እለምናችኋለሁ። እኛ በተስተካከለ የጫወታ ሜዳ ውስጥ ነን። እንደከዚህ ቀደሙ በልበ ሙሉነት እምላችሁ ነገር የለም። በፍፁም ስጋት ለመሆንም አይደለም። እንዲያው ከእኔ ጋር መነጋገር እና መልዕክት እንድንለዋወጥ እና አንዳንድ መልስ ለሚሹ ጥያቄዎቼ እንድትሰጡኝ ፈልጌ ነው እንጂ።

በክርስቶስ እህታችሁ

ርቤካህ ፔይን (ማክዶናልድስ)

 

 

 

Leave a Reply

Discover more from LeaMcD Deaf Ethiopia

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading