ኒል በኢትዮጵያ ያደረገው ጉብኝት
ከመጋቢት 20/2009 እስከ ሚያዝያ 4 /2009
ስሜ ኒል ይባላል። የኮቭናንት ድርጅት ሾፌር ነኝ። ከባለቤቴ ጋር በጋራ ሆነን ለዚህ ድርጅት በሾፌርነት ማገልገል የጀመርነው በ2003 ዓ.ም ነው። ከዚህ ዓመት ጀምሮ ለትርፍ ያልሆነ ሊመክዲ የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅታችን መስርተን ድርጅቱም በእጅጉ እየሰፋና እና እያደገ በመምጣቱ በሾፌርነት ገቢዬ ብቻ መደጎም እያቃተኝ መጥቷል። ይህ ድርጅት ህጋዊ ሆኖ በኢትዮጵያ እና አሜሪካ ወስጥ ፈቃድ አግኝተን የተመዘገበው በ2005 ነበር። በአሜሪካ ውስጥ የዚህ ድርጅት የምዝገባ ቁጥር ID#27-105006DLN17053179105026 ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥ የድርጅቱ የዕውቅና ቁጥር #2221 ነው። እውቅና ያገኘነው መስማት ለተሳናቸው ወገኖች ትምህርት ቤት መክፈት ሲሆን ይህም የማጠናከሪያ ትምህርት መስጠት፣ አንደኛ ደረጃ፣ ሁለተኛ ደረጃ እና ኮሌጅ ትምህርቶችን የሚያጠቃልል ነው።
በዚህም መሰረት በድርጅታችን ውስጥ የማጠናከሪያ ትምህርት ያገኙ ተማሪዎች 90% በጥሩ ሁኔታ የ8ኛ ክፍል የብሄራዊ ፈተና አልፈዋል። በድርጅታችን ውስጥ ያልተሳተፉ ተማሪዎች በአማካይ የ8ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ያለፉት ከ5% በታች ነው። ከዚህም በተጨማሪ አዋቂዎች ሆነው መስማት ለተሳሰናቸው ሰዎች መልሶ የማቋቋሚያ ፕሮግራም አለን። ከ14-15 የሚሆኑ ቋሚ ሰራተኞችም አሉን። ለተማሪዎቻችንም የመጓጓዣ፣ የዳቦና የሻይ ድጋፍ እናደርጋለን። ሪቤካ ለዚህ ስራ ወደ ኢትዮጵያ የሄደቸው ሰኔ/2007 ሲሆን ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ወደ አሜሪካ አልተመለሰችም።
ወደ ኢትዮጵያ ያደረኩት ጉዞ እንዲሁ በቀላሉ ለሽረሽር ራሴን ለማስደሰት አልነበረም። እጅግ ከባድ ነበር። ርቤካ ይዞ ይመጣል ብላ ያሰበችውን የገንብ መጠን ስላልነበረኝ ወደዚህ ወደ አሜሪካ ስመለስ በባዶ ኪስ ነበር። በኢትዮጵያ በቆየሁበት 3 ሳምንታት ገላዬን የታጠብኩት በቀዝቃዛ ውሃ ነበር። መብራትና ውሃ አንድ ጊዜ የሚመጣው በሳምንት ሶስት ቀናት ብቻ ስለነበር የሙቅ ውሃ ሻወር የወሰድኩት በሳምንት ሶስት ቀን ጠዋት ጠዋት ብቻ ነበር። የፍርድ ቤት ምልልስም ነበረብኝ። ርቤካ የፍርድ ቤት ክርክር ስለነበረባት ከደረስኩበት ቀን ጀምሮ በሳምንት 2 ወይም 3 ቀናት በፍርድ ቤት እመላለስ ነበር። ርቤካ እና ድርጅታችን በሁለት ጉዳዮች ስለተወነጀሉ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ የፍርድ ቤት ትግል ነበረብን።
ርቤካን እስከ ችሎት ቀን ድረስ ለሶስት ቀናት እስር ቤት የሚያቆየት አጋጣሚ ስለ ነበር ከፖሊስ ለማምለጥ አንድ ለሊት ያሳለፍነው በሆቴል ነበር። ለማንኛውም በፍርድ ሂደቱ ውስጥ ከባድ ትግል በማድረጋችን ርቤካም ወደ እስር ቤት አልተወሰደችም። በእርግጥ ለእስር ይቅረና ለክርክር የሚያበቃ ምንም ጥፋት አልፈጸመችም። ስለሆነም በክርክሮቻችን እንደምናሸንፍ ስለምናምን እግዚአብሄርን እናመሰግናለን። ወደ ከተማ ለእግር ጉዞ በወጣን ቁጥር መስማት የተሳናቸው ርቤካን እያስቆሟት በታላቅ ፍቅር ሰላምታ ይሰጧታል፤ ያነጋግሯታል። ከዚህም የተነሳ ርቤካ አንዳች የተቀደሰ እና መልካም ስራ እየሰራች እንደሆነ ተረዳሁ። መስማት የተሳናቸው የስራ እድል እንዲያገኙ ጭምር እየረዳች ነው። ለዚህም ስራ እንዲያፈላልግላቸው የመደበችው አንድ ሰው አላት። በዚሁ መሰረት ከ3 ወይም 4 ቀናት በፊት 50 መስማት የተሳናቸው ሰዎች በእንጨት ስራ ድርጅት ውስጥ እንዲቀጠሩ አመቻችታለች።
አዲስ አበባ በሚገኘው በመኖሪያ ቤታችን አንድ ጥበቃ፣ አንድ ውሻ እና ድመት አለን። በየሳምንቱ እሁድ አምልኮ የሚፈጸምበት ቤተ ክርስትያንም በግቢያችን ውስ አለን። እሁድ እሁድ ጠዋት እኔና ርቤካ ለአምልኮ ወደ ሌላ ለመሄድ ሙከራ ብናደርግም መስማት የተሳናቸው ደስተኞች አልነበሩም። ስለሆነም በአምልኮ ሰዓት ርቤካህ እዚያው ግቢያችን ውስጥ ከእነርሱ ጋር ለመሆን ወስናለች። መስማት የተሳናቸው አዋቂዎች እና ወጣቶች በትምህርት፣ በመንፈሳዊ እድገትና ስራንም በማግኘት ረገድ እጅግ እየተበረታቱ ናቸው። በየቀኑ ጠዋት ጠዋት ከሰራተኞች ጋር አጭር የአምልኮ ጊዜ አለን። በየቀኑ የሚዋጉን ጣላቶችም ነበሩን። ጠላታችን ያው ዲያብሎስ እና ሰራዊቱ ሲሆኑ እኛን ለማጥቃት እና ቆሻሻ ስራውን ለመፈፀም የሚጠቀመው ተራ ሰዎችን ነው። እናም ስራውን ለማፍረስ በትግል ሜዳ መካከል ነን። በዚህ ትግልና መስማት በተሳናቸው ሰዎች ጋር የምናደርገው ስራ እንደሚሳካልን ያመንኩት ልባችን በእግዚአብሄር መንገድ ላይ ስላደረግንና እንደ ፈቃዱ ብቻ ስለምንቀሳቀስ ነው።
የዲያብሎስን ክፉ ስራ በተላያዩ ቦታዎች የለየንና ያወቅን ቢሆንም ከሁሉ የከፋው ስራውን ያየነው አሁን በዚህ ስፍራ ለመግለጽ በማልችልበት ቦታ ነው። የማይታመን ነው። ይህን ጉዳይ ባወራችሁ በፍጹም ልታምኑኝ አትችሉም። አሁን ለጊዜው በዝምታ ማለፍን መርጫለሁ። መጋደላችን ከደምና ከስጋ ጋር አይደለም ነገር ግን ሰማያዊያን ከሆኑት ስልጣናትና ሀይላት ጋር ነው እንጂ። ማስታወስ የሚገባን ግን “እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?” የሚለውን ነው። እኔ እና ርቤካ ብዙ ጊዜ ለፀሎት ለሊት እንነሳ ነበር። በፀሎታችንም ውስጥ በመልካምና ክፉ ስራዎች መካከል መቆማችን ለምን ይሆናል? እያልን አምላካችንን እንጠይቀው ነበር። ሁለታንም በደንብ የተረዳነው ነገር ቢኖር ክፉ ሰው እንዴት ያለ እንደሆነ ነው። ዲያብሎስ መስማት የተሳናቸውን እንዳይመሩ እና አላዋቂ ሆነው እንዲቀሩ ይፈልጋል። መስማት በተሳናቸው ላይ ብቻ አይደለም ነገር ግን ይህንን በሁሉም የእግዚአብሄር ፍጡራን ላይ እንዲተገበር ይፈልጋል።
በቁጥር የተደገፈ መረጃ በድርጅታችን በኩል የተከናወኑ ስራዎች
ቁጥርን በተመለከተ
170 መስማት የተሳናቸው በቋሚ እና በጊዚያዊ ሁኔታ አስቀጥረናል፤ አብዛኛዎቹ በአበባ ኢንዱስትሪ ውስጥ ነው።
50 መስማት የተሳናቸው ሰዎች በቻይና እንጨት ስራ ፋብሪካ ውስጥ ተቀጥረው በመስራት ላይ ናቸው።
20 መስማት የተሳናቸው ሰዎች በሰሌንና ወለል ምንጣፍ ስራ ተሰማርተዋል
120 መስማት የተሳናቸው ሰዎች በ9 የተለያዩ ቦታዎች ግንኙነት ተፈጥሮላቸው በመጠባበቅ ላይ ናቸው።
አንዳንድ ሰዎች ይህንን መስራት ለምን እንዳስፈለገን ሊጠይቁ ይችላሉ። አንተ እና ርቤካ ለዚህ ስራ መለየታችሁ ትክክል አይደለም የሚሉ ብዙ ናቸው። ባለቤትህ አንተ በማትኖርበት ቦታ ይህንን ስራ የምታከናውነው በምን ስልጣን ነው? ብለው የሚጠይቁኝ ብዙዎች ናቸው። እኔም እናንተ ምንም የማትሰሩት በምን ስልጣን ነው? ብዬ ተመሳሳይ ጥያቄ አነሳለሁ። ብዙዎች በዚህ ሁኔታ ተቃውሞ ያነሱብኛል፤ ነገር ግን ምንም በጎ ተግባር አይፈጽሙም። አነዚህ ሰዎች ትምህርት አላቸው፣ ችሎታ አላቸው እንዲሁም የብዙዎችን ህይወት ለመለወጥ ይችላሉ ነገር ግን ተቃውሞ እንጂ ተግባር የላቸውም።
እኔ እና ርቤካ ለምንሰራው ስራ እኛው ብቻ ፍጹማኖች አይደለንም። ይህንን ሁለታችንም ጠንቅቀን እናውቃለን። ሌሎች ከእኛ በተሻለ ሁኔታ ሊሰሩ እንደሚችሉ የምናውቅ ቢሆንም ይህንን ጥሪ አልተቀበሉም። ይህን ጥሪ ያላቸውና ታማኝ የሆኑ ሰዎች የጀመርነውን ስራ ከእኛ ተቀብለው እንዲያስቀጥሉ እንፈልጋለን፤ እንናፍቃለንም። እኔ እና ባለቤቴ የጀመርነውን ስራ ማስቀጠል እና ክፍተታችን ለሚሞላ ሰው ወይም ድርጅት በደስታ ለማስተናገድ ዝግጁዎች ነን። የሚረዳንን እግዚአብሄር እንዲልክልን በፀሎት እየጠየቅንና እያፈላለግን ነው። እስከዚያው ከእግዚአብሄር ፍርድ ለመዳን ስራችንን በማይመች ሁኔታ ውስጥ ሆነንም ለመቀጠል ወስነናል። ምክንያቱም በፍፃሜው ዘመን መስራት የሚገባንን ባለመስራተቻችን ፍርድ እንዳለብን እናውቃለንና። “ምጽዋትህና ፀሎትህ በፊቴ ይታወሳሉ” የሚለውን ቅዱስ ቃል ማስታወሱ ጠቃሚ ነው። እናም የዘወትር ፀሎቴ እኔና ርቤካህ በኢትዮጵያ ውስጥ በሰራነው እንጂ መስራት በሚገባን ነገር ግን ባልሰራነው እንዳይሆን ነው።








1 አስተያየት. Leave new
Greetings of the day!
It is really amazing while you did all in the midst of life tied struggle. I understand and remember how Jennifer Merrit from UK did in Southern Ethiopia (Hossana), and latter extended to Nekemte )Western Ethiopia) from March 2001. Although she opened gates for the survival of many both in country and abroad through education to the extent of sending Deaf qualified former students to Gallaudet University in US and Bristol University in UK. I learned a lot from her life while she remained unmarried for sacrificial love to the Deaf.
Now she crossed 80 and staying back in UK since 2013 of her final to Ethiopia, and in the last five years from 2018 to June 2023 we had a good contact with her and once I invited her to come to Ethiopia again while I am serving in Nekemte School for the Deaf of the Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus-Development and Social Services Commission to let her see the progress.
Jenny’s life speaks a lot to me and to the Deaf at large. Following my presence in the School leadership she reconnected Crosslinks to continue supporting the School after 8 years.
Unfortunately because of corruption in the organization I decided to resign the EECMY-DASSC from June 20/2023 and Jenny got disappointed. I know that breaks her heart but if I did not decide like that means agreeing to the corruption and sabotage of the top leaders of the organization who are hunting money day and night with no care to the Deaf.
As to me being bare hand living with God makes a positive meaning than grabbing in the name of the Disabled Children.
I feel all what you spent and sense how it is difficult to lead in such horrify situation. But my worry is the upside down life of the Deaf who have been benefiting holistically from the organization and led astray.
As to me if God wills and you still have good heart to continue, better to rehabilitate and work on the ministry from the right time of God ahead. Still you need strong, faithful, qualified, and God fearing leader who continue the ministry with you.
Stay blessed,
Dereje Tilahun (Dr.)
Cell phone: +251947216564