1993 የLeaMcD ትምህርት ቤት ጅማሮ
ሰኔ 27, 1993
ከአሜሪካ ተነስቼ አዲስ አበባ የደርስኩት ረቡዕ 4 ነው። አመጣጤ አብርሃም የተባለውን ሰው ለማግኘት እንደመሆኑ መጠን ፍለጋዬን የተያያዝኩት ወዲያውኑ ነበር። ለዚህም ይረዳኝ ዘንድ መጀመሪያ የደወልኩት በመጥምቃዊያን ቤተ ክርስትያን አባል ለሆነ ለአንድ ዓይነ ስውር ሰው ነበር። ይህም ሰው በነገታው ረቡዕ ሰኔ 27 በቤተ ክርስትያኑ ወንጌላዊያን ማሰልጠኛ ኮሌጅ እንድንገናኝ ቀጠሮ ሰጠኝ። አብርሃምም በዚያው በኮሌጁ እንደማገኘው ተስፋ ሰጥቶኛል። ከዚህ ከስልክ ውይይት በኋላ ቀኑን በሙሉ ያሳለፍኩት ጥሩ እንቅልፍ በመተኛት ነበር።
ሰኔ 28, 1993
ሰኔ 28 ጠዋት ወደ 1 ፡00 ሰዓት ገደማ ከእንቅልፌ እንደነቃሁ የመጀመሪያ ስራዬ ያደረኩት ጌታ ባስተማረኝ መሰረት ፀሎት ማድረግ ነበር። ቀጥሎም ከመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ካነበብኩ በኋላ በዲ አፍሪክ ሆቴል ትንሽ ቆይታ አደረኩ። ቀጥሎም ወደ መጥምቃዊያን የወንጌል ማሰልጠኛ ኮሌጅ በመሄድ እስከ ከሰዓት በኋላ 11፡00 ሰዓት ድረስ ከአብርሃም ጋር ቆየሁ። ከዚያም ምሽት አከባቢ ከደመረ ጋር ተደዋውለን እራት አብረን ለመብላት ቀጠሮ ያዝን። በቀጠሮዬ መሰረት ማታ ወደ ደመረ ቤት አመራሁ። በደመረ ቤት እያለሁ በኃይሉ ከመስቀል አደባባይ ወደ ዋቤ ሸበሌ ስሄድ እንዳየኝ በመግለጽ በጭንቀት ተሞልቶ በስልክ ከደመረ ጋር ይነጋገር ነበር። ይህ ሰው እንደ ስጋት ያየኝ ነበር። ነገር ግን ደመረ ስለ ሁኔታዬ በፍጹም እንደማያውቅ ማለትም አዲስ አበባ ውስጥ እንዳለሁ እንደማያውቅ ነበር ለበኃይሉ የነገረው ። በኃይሉ ወደ አዲስ አበባ መመለሴን በማየቱ በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ገብቶ ነበር። ከዚህ ቀን በኋላ ደመረ ከባለቤቱ አምሳለ ጋር ወደ አምቦ በመሄድ እስከ ሚቀጥለው ረቡዕ ድረስ ቆይተው መጡ። እነ ደመረ ወደ አምቦ የሄዱበት ምክንያት በኃይሉ በሁለታችን መካከል ያለውን ግንኙነት እንዳያውቅ ፈልገው ይመስለኛል።
ሰኔ 29, 1993
በዚህን ቀን ጠዋት ከመስቀል አደባባይ ተነስቼ እስከ ሜክሲኮ አደባባይ የተጓዝኩት በእግሬ ሲሆን ሰመለስ ግን በሚኒባስ ነው። ስመለስ ለወጥ ቤት የሚያገለግሉ እንደ ማንኪያ፣ ቢለዋ፣ ሹካ እና ሳህኖች የመሳሰሉት ገዛዝቼ ነበር። ከዚህም ሌላ በየቀኑ ጠዋት ጠዋት ፍራፍሬ ለመጠቀም በማሰብ ብዙ ፍራፍሬዎችን ገዝቼ ተመለስኩ። ከሰዓት በኋላ ወደ 11 ሰዓት ገደማ አብርሃም ባለሁበት ቤት መጥቶ ጎበኘኝ። እርሱ ከሄደ በኋላ የብዙነሽ ወንድም ኢያሱም 12 ሰዓት ላይ ሊጎበኘኝ መጣ። አብረን ወደ ሆቴል በመውረድ እራታችን እንጀራ ከበላን በኋላ እየተጨዋወትን ቆንጆ ቆይታ አድርገን ወደ 1፡00 ሰዓት ገደማ ተሰናብቶኝ ሄደ።
ሰኔ 30, 1993
የዛሬ እቅዴ መስማት የተሳናቸው ማህበር ለመጎብኘት ቢሆንም ሀሳቤን ቀይሬ የቀድሞ ተማሪዎቼን ለማፈላለግ ወሰንኩ። ይህንን ለማድረግ ቀላል መንገድ ነው ብዬ ያሰብኩት በመጥምቃዊያን ቤተ ክርስትያን ባሉ መስማት የተሳናቸው ሰዎች በኩል ነው። እናም ወደዚያው ሄጄ ከአብርሃም ጋር የተወሰነ ሰዓት ካሳለፍኩ በኋላ ወደ ክፍሌ ተመለስኩ። ከዓርብ ጀምሮ ጤንነት ሰላልተሰማኝ ክፍሌ እንደ ደረስኩ መተኛትን ነበር የመረጥኩት። ዓርብ ሌሊቱንና ቅዳሜ ከሰዓት በተቅማጥ ስቸገር ነበር ያሳለፍኩት። ተቅማጡም በጣም ነበር ያደከመኝ።
ሐምሌ 1, 1993
የዛን እለት አምልኳችንን ለመፈፀም መካኒሳ ወደሚገኘው የመጥምቃዊያን ቤተ ክርስትያን ከአብርሃም ጋር ሄድን። ይህ ቤተ ክርስትያን መስማት የተሳናቸው አማኞች የሚገለገሉበት ነው። በቤተ ክርስትያኑም ያሳለፍነው የአምልኮ ጊዜ እጅግ በጣም ጥሩ ነበር። የቤተ ክርስትያኗ አባላት እራሴን እንዳስተዋውቅ በጋበዙኝ መሰረት ስሜን እና የመጥምቃዊያን ቤተ ክርስትያን አምላኪ መሆኔን ገለጽኩላቸው። እግረ መንገዴን በክርስቶስ ቤተ ክርስትያን በነበሩኩበት ጊዜ ያስተማርኳችውን የቀድሞ ተማሪዎቼን ለማግኘት እንደምፈልግም ጭምር ነገርኳቸው። እናም ፈልገው እንዲያገናኙኝ ጠየኳቸው። የአምልኮ ሰዓት ካበቃ በኋላ በሚቀጥለው ዓመት ትምህርቷን የምትጀምር አንዲት መስማት የተሳናት ሴት ቀርባ ተዋወቀችኝ። በምልክት ቋንቋ ከተነጋገርን በኋላ ሀሙስ ምሳ እንደምትጋብዘኝ ነገረችኝ። ሌሎችም መስማት የተሳናቸው ሰዎች መጥተው አነጋገሩኝ። አንዳንዶቹ ባፈናን እንደሚያውቁ ነገሩኝ። ከዚህ በኋላ ባፈናን በሚቀጥለው ቀን ማታ ከነልጇ እንደማገኛት ተስፋ አደረኩ። በመጨረሻም ከአብርሃም ጋር ወደ ዲ አፍሪክ ሆቴል በመምጣት ምሳችንን አብረን በላን። ከምሳ በኋላ ከአሜሪካ ስመጣ አውሮፕላን ላይ ያገኘኋቸውን ዲያነንና ፖል ገሪሰንን ደውዬ መምጣት ይችሉ እንደሆን ጠየኳቸው። ጥሪዬን ተቀብለው እኔ ዘንድ የደረሱት ወዲያው ነበር። የምግብ ግብዣ አድርገውልኝ ብዙ ስንጨዋወት ቆየን። በጫወታችን መካከል ስለ ባለቤቴ ኒል ብዙ ነገር ነገርኳቸው። የጓሮ አትክልት ማልማት እንደሚወድም አስረደኋቸው። በዚህን ጊዜ ገሪሰን የግብርና ፕሮጀክት ስለ ነበረውና የሚያግዘው ሰው ይፈልግ ስለነበር ስለ ኒል በነገርኩት ነገር እጅግ ተደሰተ። እናም ስለ ፕሮጀክቱ አስመልክቶ ለኒል ኢሜይል እንደሚያደርግለት ነገረኝ።
ሐምሌ 2, 1993
ቀኑን ሙሉ አብርሃምን ስጠብቀው ዋልኩ ሳይመጣ ስለቀረ ትንሽ ተኛሁ። አብርሃም ሳይመጣ ስለቀረ ብቻዬን ወደ አሜሪካ ኤምባሲ ሄድኩ። በዚህን ቀን በጣም ተረብሻለሁ። መንፈሴም የተረጋጋ አይደለም። ይህ ለምን እንደሆነ ባለውቅም ምናልባት እንግዳ በሆነ መንፈሳዊ ውጊያ ውስጥ ረዘም ላለ ጊዜ ስለቆየሁ ይሆናል። ወደ አሜሪካን ኤምባሲ የደረስኩት በታክሲ ሲሆን የከፈልኩትም 30 ብር ነው። በኤምባሲው እንደ ደረስኩ ተመዝግቤ ተራዬን አንድ ሰዓት ያህል ጠብቄ እንደ ደረሰኝ ስለ ተማሪዎች የቪዛ ጉዳይ ጠየኳቸው። ዓለማውም አብርሃም በትምህርት ምክንያት ወደ አሜሪካ እንዲሄድ ለማመቻቸት ቢሆንም እንደማይሳካለት ውስጤ በሚገባ ይነግረኝ ነበር። የኤምባሲ ሰራተኞችም ያረጋገጡልኝ ይህንኑ ነበር። ሌሊት ይሰማኝ የነበረው ይህ የአብርሃም ወደ አሜሪካ እንዳይሄድ መከልከሉ ስህተት እንደሆነ ይሰማኝ ነበር። እናም አብርሃም ይህንን የኤምባሲ ውሳኔ እንዲረዳ እግዚአብሄር እንዲረዳው እፀልይ ነበር። ፀባዩ ሌሎች መስማት የተሳናቸው ከሚያሳዩት በተለየ ሁኔታ እንዲሁም እኔ በምፈልገው ዓይነት ሳይሆን እንደ እግዚአብሄር ፈቃድ እንዲሆን አጥብቄ ፀለይኩ። አብርሃም ለትምህርት ወደ አሜሪካ እንዲሄድ እንዳልተፈቀደለት አምኖ ተቀብሏል። ነገር ግን ወዲያው የነገረኝ ነገር ቢኖር ወደ ሌሎች ሀገሮች ለመሄድ የሚያስችለውን እድሎች እንደሚሞክር ነው። ይህ ደግሞ በእጅጉ ተስፋ ያስቆረጠኝ እና እዚህ ያለኝ ስራዎቼን የሚረብሽ ነገር ነው።
ምክንያቱም እስከ አሁን ድረስ የ1980ዎቹ ሌሎች ህፃናትን መፈለግ የነበረብኝ ሲሆን እኔ ግን አላደረኩም። በራሱ በኩል እድሎችን ለመሞከር የመወሰኑ ጉዳይ ደግሞ በጀመረው መንገድ ላይረዳኝ ይችላል። የክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ዳይሬክተር ተብዬ ስለተሰየምኩ በዚህ ስያሜ ምክንያት የሆነ የእኔን ጉዳይ ከሰማም ለእኔ ስጋት ነው። ስለዚህ ይህ ጉዳይ ነገሮችን እንዳያወሳስብኝ ወደ አምላኬ ፀለይኩ። አምላኬ እባክህ ስህተቶቼን ሸፍንልኝ ይቅርም በለኝ። በዚህን ሰዓት በዙሪያዬ እየተከናወነ ያለውንም ነገር እባክህ አሳየኝ። አምላኬ እየሆኑ ያሉትን ነገሮች ለይቼ አውቅ ዘንድ፣ ከጭንቀቶቼም አርፍ ዘንድ እንዲሁም ከአንተ ያገኘሁት ሰላም እንዲመለስልኝ አድርግ። ከኤምባሲው ተመልሼ ወደ ነበርኩበት ሆቴል ስደርስ አብርሃም ለምሳ ወደ ቤቱ ሊወስደኝ ቁጭ ብሎ እየጠበቀኝ ነበር። ከዚያም ቤቱ እንደ ደረስንም እናቱ እና ወንድሞቹ ጋር አስተዋወቀኝ። ከዚያም ቆንጆ የዶሮ ወጥ ምሳ ተጋበዝኩ ከምሳ በኋላ ለቡና ቁርስ ፈንዲሻ ቀርቦ እጅግ ጥሩ ጊዜ አሳለፍኩ።
ከ9፡30 ሰዓት በኋላ ወደ ሆቴሌ ስመለስ ባፈና ከነ ልጇ ቁጭ ብለው ሲጠብቁኝ ደረሰኩ። ባፈናን እንደገና ለማግኘት በመቻሌ በጣም ደስ አለኝ። እንደተገናኘንም በለቅሶ ነበር የተቀበለችኝ። ቤተሰቦቼ በአደጋ የመሞታቸው ዜና በመስማቷም ለዓመታት ስታለቅስ እንደ ነበረች እያለቀሰች ነገረችኝ። በዚህም ምክንያት ዓይኖቿ ተጎድቶ ነበር። እኔም በተራዬ በኃይሉ በሚፈጽምብኝ የማግለል ስራ ምን ያህል እንደ ተጎዳሁ ዘርዝሬ ነገርኳት። አምላኬ ይህንን ነገር ዘርዝሬ ለባፈና መንገሬ ስህተት ይሆን? እባክህ ይህንንም ይቅር በለኝ። ባፈናን አፈላልጎ ያገናኘኝ መላኩ የተባለው መስማት የተሳነው ሲሆን ይህ ሰው በመጥምቃዊያን ቤተ ክርስትያን ያገኘሁት አዲስ ወዳጄ ነው። አብርሃም በዚህ በአዲስ አበባ ውስጥ መሆኑ በተለይም በስነ መለኮት ኮሌጅ ውስጥ መሆኑ ለእርሱ መልካም ሆኖ ታየኝ ነገር ግን እርሱ እዚህ መሆንን አልወደደም። ይልቁንም በሌላ ሀገር ውስጥ ሆኖ ትምህርቱን ለመከታታል ይፈልጋል። ይህ ምን ማለት ይሆን? እኔ እንደገባኝ ይህ ሰው ኢትዮጲያዊያን መስማት ተሳናቸውን በእውነት ለመርዳት አይፈልግም ብዬ ጠረጠርኩ። የእርሱ ፍላጎት ለራሱ ጥቅም ብቻ የሚሮጥ ይመስላል። ለማንኛውም አሁን በአብዛኛው
ከአብርሃም ጋር መስራት የነበረብኝ ህልሞቼ የተቋጩ ይመስላል። ለእርሱ የነበረኝ ህልም በኢትዮጲያ ውስጥ መስማት የተሳናቸውን ወገኖች እንዲመራ ነበር። ነገር ግን እርሱ ወደ ውጭ በሚያደርገው ጥረት ላይ ጠንካራ አቋሙን ስላሳየኝ በዚህ ረገድ የነበረኝን ህልም አመንምኖታል። ይህንን ህልሜን በተደጋጋሚ ሲያጣጥልብኝ በማያቴ ደስተኛ አይደለሁም። በዚህን ሰዓት ምንም እንኳ የተረበሽኩ ቢሆንም ድብቅ አጀንዳዎችን ለይቼ ለማስቀመጥ ተዘጋጅቻለሁ። እነዚህ አጀንዳዎቼ የተሳሳቱ ከሆኑ አምላኬ እንዲያጠራልኝ አሳልፌ ሰጥቸዋለሁ። በዚህ ጉዳይ ላይ ንሰሃ ገብቼ የአምላኬ ሰላሜን እንዲመለስልኝ እፈልጋለሁ። ይህንን በማስብበት ጊዜ ወደ አእምሮዬ የመጣው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል “… ባይገባው ሰላማችሁ ይመለስላችሁ።” የሚለው ነበር። እግዚአብሔር ዝም እል ዘንድ ዛሬ ሲያሳስበኝ ብዙ ነገሮችን ተናገርኩ፤ አሰብኩ። በኤምባሲው ውስጥ እያለሁም በክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ውስጥ በነበርኩበት ጊዜ ከሙስሊም ልጆች ጋር በተያያዘ ችግሮች እንደነበሩብኝም ተነግሮኛል። በክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ግቢ እያለሁ እነዚህን ነገሮች በምስጢር ነበር የያዝኩት።
ምናልባት የነገርኩት ሰው ቢኖር ባፈናና ልጇ ብቻ ናቸው። ነገር ግን እግዚአብሔር በእምነት ሆኜ እንዲገልጥልኝ በጠየኩት መሰረት ነበር ሁሉንም ያሳየኝ። የእርሷ እኔን ለማግኘት ታደርግ የነበረውን ጥረቶች ስረዳ ደግሞ ነብሴ በውስጤ ፈሰሰች፤ እረፍት አጣች። የሚደርስብኝ መገለል የምወዳቸውን ሰዎች እንዳጣ አድርጎኛል እነዚህ የሚያገሉኝ ሰዎች ከወዳጆቼም እኔን በመለየት በኩል የሚሰሩት ስራ ተሳክቶላቸዋል። እዚህ ሀገር አብዝተው የሚወዱኝ ሰዎች ስለ መኖራቸው ማመን እጅግ ከበድ ነው። ባፈና እንደ ነብሷ ነው ምትወደኝ። ህይወቷ እና የኑሮ ውጣ ውረዷ ከበድ ያለ ቢሆንም እርሷ ግን ጠንካራ ሴት ነች። ይህች ሴት ምን ዓይነት የድንቅ! ድንቅ! የሆነች ሴት ነች? ባፈና ከነ ልጇ ከሄደች በኋላ ከአብርሃም ጋር ከቀኑ እስከ 9 ድረስ እንነጋገር ነበር። ስጋቶቼንና ምክሮቼን በፈጹም ሊቀበለኝ አልቻለም። ከእርሱ ጋር በማደርገው ንግግር የነበርኩበትን ሁኔታዎች በትክክል ሳልገነዘብ ቀርቼ ከግንኙነት ችግር የሆነ ከሆነ ሀላፊነቱ የእኔ ይሆናል። ነገር ግን ነገሮችን በትክክል ሳልገነዘብ በመቅረቴ ነው ወይስ ሁኔታዎችን በትክክል በመያዜ ነው አብርሃም እየተቃወመኝ ያለው? አምላኬ እባክህ ይህን ወጣት መስማት የተሳነው አብርሃምን ባርከው። ለእኔ የነበረኝንም ሰላም፤ ከአንተ ብቻ የሆነውን ሰላም መልስልኝ። አሁንም እንደ ትላንት ምሽት በዚህን ሰዓት ከእንቅልፌ ነቃሁ። እስከ ሌሊቱ 7፡00 ሰዓት ድረስ እንደነቃሁ ነበር። እግዚአብሔር ሆይ የጣፈጠ አንቅልፍ እንደምትሰጥ ተናግረሃል። ስለዚህ አምላኬ ሆይ እንደገና አርፌ እና ታድሼ ነገ በአግባቡ አገለግልህ ዘንድ ጥሩ እንቅልፍ ስጠኝ።
ሐምሌ 13, 1993
እንቅልፍ ብዙ ከራቀኝ በኋላ በመጨረሻ ጥሩ እንቅልፍ ተኛሁ። ጠዋት ስነሳ በጣም ርቦኝ ነበር። ከእቅልፌ ተነስቼ ኢሜሌንም አይቼ ቁርሴን ወደ መብላት ሄድኩ። የዛሬ ዓይነቱን ሁኔታ ግን እንደ ልማድ መወሰድ የለብኝም። ከዚያም በጠዋት ወደ ወንጌላዊያን ማሰልጠኛ ኮሌጅ ሄጄ ከአንድ ዓይነ ስውር ጋር ከሚሰራው ፓስተር ግርማ ከሚባል ሰው ጋር ውይይት አደረግሁ። ይህ ሰው ታላቅ የእግዚአብሔር ሰው ነው። በኢትዮጲያ ውስጥ መስማት ከተሳናቸው ወገኖች ጋር መስራትን በተመለከተ መልካም መሆኑን ገልጾ በርትቼ እንድገፋበት በጣም አበረታታኝ። ቀጥሎም ስለ አብርሃም በዚህ ስራ አለመተባበር እንዲሁም በኢትዮጲያ ውስጥ መቆየት እንደማይፈልግና በሌላ ሀገር ለመማር እንደሚፈልግ ነገርኩት። ፓስተሩም ሁኔታውን አዳምጦኝ እርሱ ራሱ ከሌሎች መስማት ከተሳናቸው ጋር የእኔን ዓይነት ልምድ እንዳለው እንዲሁም አብርሃምን ወደ ውጭ ለመላክ አለመፈለጌ ትክክል መሆኔን አረጋገጠልኝ።
ይህ ፓሰተር መስማት የተሳናቸው ወገኖች የወንጌል አገልግሎት ለማስፋፋት ሰፊ እድል እንዳለቸው ሊያሳየኝ ወደ የተለያዩ ቦታዎች ሊወስደኝ ይፈልግ ነበር። ነገሮች በዚህ ዓይነት ሁኔታ መቀየር መጀመራቸውን በማየቴ እጅግ ተደንቄያለሁ። ከፓስተር ግርማ ጋር እየተወያየሁ እያለሁ አብርሃም መጥቶ ሊያገኘኝ ይጠብቀኝ ነበር። አምላኬ ሁኔቶችን በግልጽ አሳይተኸኛልና አመሰግናለሁ። እባክህ አብርሃምን ምራው፤ አቅጣጫም አሳየው። እባክህ አንተ ለምትሰጠው መመሪያ ልቡን ክፈትለት! እናም ከአብርሃም ጋር ውይይት ጀመርን። ነገር ግን ንግግሩን መቋጫ የሌለው ሆነ፤ እድል ሊሰጠኝ አልፈቀደም። ለእኔም እድል እንዲሰጠኝ ብለምነውም ሊሰማኝ አልቻለም። ብዙ በተናገረ ቁጥር በእርሱ ውስጥ ይኖራል ብዬ የምጠረጥረውን ባህሪይ በግልጽ እመለከት ነበር። በጣም ያስጨንቀው የነበረው ስለ ራሱ የገነባው ዝና ነው።
በእኔ ላይም እጅግ በንዴት ይናገር ነበር። በመጨረሻም ከእርሱ ጋር የጀመርኩትን ንግግር አቋርጬ ወደ ኮሌጁ በመመለስ ከፓስተር ግርማ ጋር እንደገና ውይይቴን ጀመርኩ። ውድ አምላኬ እባክህ ይህንን ልጅ እርዳው። ቀጥሎም ከብዙነሽ እና ቤተሰቧ ጋር ምሳችንን በልተን ጥሩ ጊዜ አብረን አሳለፍን። ልክ 10፡00 ሰዓት ላይ ይመጣሉ ብየ ስጠብቃቸው የነበሩት ባፈና፣ ወርቅዬና ሂሩትም ሳይመጡ ቀሩ። አምላኬ በኃይሉ ከልክሏቸው ይሆን እባክህ መከፈት የሚገባቸው በሮች ሁሉ እንዲከፈቱ፣ መዘጋት የሚገባቸው በሮች ደግሞ እንዲዘጉ አድርግ። እባክህ አንተን በትዕግስት መጠበቅ እንድችል አስተምረኝ። ወደ 9፡00 ሰዓት አከባቢ ደመረ ደውሎልኝ ነበር። ከአዲስ አበባ ከወጣ ከ9 ቀናት በኋላ ነገ ማታ ወደ ቤቱ እንደሚመለስ ነገረኝ። አዲስ አበባ እንደ ደረሱ እኔ ወዳለሁበት ሆቴል ይመጣሉ ብዬ እገምታለሁ።
ሐምሌ 4, 1993
በድጋሜ ወደ ስነ መለኮት ኮሌጅ ተመልሼ የፓስተሮች አስተዳደር ከሆነው ከፓስተር ግርማ ጋር ሌላ ውይይት አደረግሁ። ከዚያም ከኮሌጁ ዳይሬክተር ከሆነው ስምኦን ከሚባለውም ሰው ጋር ተወያየሁ። ውይይታችን የነበረው ምናልባት በወንጌል ላይ ተጨማሪ ስልጠና አገኝ ዘንድ ነሃሴ ውስጥ ትምህርቴን በምጀምርበት ጉዳይ ላይ ነበር። ስለዚህ በኮሌጁ ውስጥ ትምህርቴን ለመጀመር የሚያስፈልጉ ነገሮችንም የማወቅ እድል አግኝቻለሁ። ነገር ግን የኒል ሀሳብ ምን ይሆን? ይህ መስማት ከተሳናቸው ወገኖች ጋር የወንጌል አገልግሎት ለመጀመር መልካም አጋጣሚ ስለሚሆን ለዚህ እዘጋጅ ዘንድ የኮሌጅ ትምህርቴን ልከታተል ነው። ራሄል በኮሌጁ ውስጥ ብቸኛዋ መስማት የተሳናት ተማሪ ነች። ይህች ሰው ትሁት የሆነ ባህሪይ አላት። አብሬያት ለመስራት የምትመች ሰው ስለሆነች ጥሩ የሆነ ውይይት አድርገናል። ወደ ሆቴሌ ተመልሼ ሳለሁ አብርሃም ከ12፡00 ሰዓት በኋላ መጣ። በዚህን ሰዓት እጅግ ደክሞኝ ስለ ነበረ አልጋዬ ውስጥ ገብቼ ነበር። ከእርሱ ጋር ለመወያየትም ፍላጎት አልነበረኝም። በእርሱ መፍረድ ባይሆንብኝም ምናልባት ከስህተቶቹ ይማራል የሚል ሀሳብ መጣብኝ። ነገር ግን ይህ ሰው አንገተ ደንዳና የሆነ፣ በራሱ ሀሰብ ላይ ብቻ ችክ ያለ፣ ለመስማት ያልተዘጋጀ እና ትዕዛዝ የማይቀበል ወይንም ተላላቆቹን የማይቀበል ሰው ይመስላል። ለዚህ ሁሉ ችግሮቹ መፍትሄ እንዲፈልግ እግዚአብሔር ፈቅዷል። የመዘጋጀቱ ጉዳይ ለእርሱ የተተወ ነው።
ሐምሌ 5, 1993
በጠዋት ተነስቸ ወደ ጎመጁ ቤት ሄድኩ። አንድ መስማት የተሳነው ሰው ከመጥምቃዊያን ቤተ ክርስትያን ሚሲዮናዊያን ጋር በመሆን በዚያ ነበር። ለዚህ መስማት የተሳነው ሰው በልቤ ያለውን ሁሉ አካፈልኩት። ይህም ሰው እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ አለ። አንቺን በዚህ ሰዓት ወደዚህ ቦታ የላከው አምላክ ይባረክ ይህ የፀሎቴ መልስ ነው አለ። እኔ ያካፈልኩት ሁሉ ለዓመታት ሲያልመው የነበረ ሀሳብ እንደሆነ ነገረኝ። ወዲያውም ምስክርነቱን አካፈለን። ምን ዓይነት የእግዚአብሔር ሰው ነው! እኔም ነገ በሆቴሌ መጥቶ እንዲያገኘኝ ጋበዝኩት። በዚያ ቤት ውይይታችን ቀጥለናል። እኔም መስማት የተሳነው የሚነገረውንም በምልክት ቋንቋ ለሌሎች አስተረጎማለሁ፤ ሌሎች የሚናገሩትንም እንዲሁ እተረጎምለታለሁ። ከዚህም በተጨማሪ ስለዚህ አገልግሎት እግዚአብሄርን እያመሰገንን ከባለቤቴ ኒል ጋር ይህን ያህል ርቄ በኮሌጅ ስለማደርገው ቆይታም እንፀልይ ነበር። እግዚአብሔር ሆይ እባክህ ነገሮችን ግልጽ አድርግልኝ፤ እባክህ በቶሎ መልስ ስጠኝ። የጉዞ ትኬቴንም በተመለከተ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ዛሬ ማታ ወይም ጠዋት አሳውቀኝ። ዛሬ ማታ ደመረ ቤት ሄጄ ጥሩ ቆይታ አድርጌያለሁ። በኃይሉም ሐምሌ ላይ ወደ አሜሪካ እንደሚሄድ ሰምቻለሁ። እግዚአብሔር ሆይ በኃይሉ ህይወት ውስጥ ፈቃድህ እንዲከናወን ይሁን፤ እባክህ ለፈቃድህ ልቡን እንዲከፍት እርዳው።
ሐምሌ 6, 1993
የአየር ትኬቴን መግዛት ባዘገይ ያለውን ጠቀሜታ እና ጉዳቱን ዘርዝሬ እየፃፍኩ እያለሁ ኢያሱ ስልክ ደውሎ ወደ ሆቴል ወርጄ እንዳገኘው ጠየቀኝ። ከእርሱም ጋር እየተወያየሁ ሳለሁ ወርቅዬ መጣ። ሞቅ ያለ ሰላምታ ነበር የሰጠኝ። ደጋግሞ ነበር እቅፍ ያደረገኝ። ጥቂት ቆይቶ ቢሄድም በምሳ ሰዓት ተመልሶ ምሳችንን በጋራ በምድር ቤት ባለው ክፍል ውስጥ አብረን ተመገብን። ስለ ጥንቱን እያወራንም ነበረ ምሳችንን የምንበላው። እርሱም ደጋግሞ በላይ በላዩ ያጎርሰኝ ነበር። የወሬያችን ርዕስም ጆን ኤድ እና በሀይሉ በእኔ ላይ ስለሚፈጽሙት በደል የተመለከተ ነበር። ወርቅዬ በደመረ ላይ የሚያነሳቸው ቅሬታዎች ደግሞ በእጅጉ አሳዘነኝ። ነገር ግን ወርቅዬ ከየት እንደመጣ በትክክል እረዳለሁ። እናም ከመቼውም ጊዜ በላይ ጥበብ የሚያስፈልገኝ፤ ከወትሮ በተለየ ሁኔታ በክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ማእከላዊ ስፍራ ላይ የቆምኩ ያህል ተሰማኝ። በወሬአችን መካከል ለወርቅዬ ስለ አየር ትኬቴ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ዛሬ መወሰን አለብኝ አልኩት። እርሱ ግን የመካኒሳ መስማት የተሳናቸው ዳይሬክተር ወደ ውስጥ አምጥቶ ሊያገናኘኝ እንደሚፈልግ ነገረኝ። ይህንን ለማድረግ የፈለገው ዛሬ ከሰዓት በኋላ ነው። ነገር ግን ደመረ ከእኔ ጋር እያለ እንደማያመጣ ተስፋ አለኝ። እኔ ግን በእነዚህ ሁሉ ምስጢሮች ተሰላችቻለሁ። እባክህ እግዚአብሔር ሆይ ደመረ በግልጽ ወደ ፊት መጥቶ ለእውነት እንዲቆም ጥንካሬ እና ድፍረት ስጠው።
የአየር ትኬትን በተመለከተ
ወደ አሜሪካ ልመለስ ወይስ ነሃሴ ውስጥ እዚሁ ቆይቼ ኮሌጅ ብከታተል ያለውን መልካምና መጥፎ ጎኖች
| እዚህ ብቆይ | ወደ አሜሪካ ብመለስ |
| መስማት ከተሳናቸው ጋር ስለ ትምህርታቸውና ተዛማጂ ጉዳዮች ላይ ብዙ ነገሮችን ማከናወን ይቻላል
በሀይሉም ስለማይኖር የተፈጠሩ ስህተቶችን የማስተካከል እድሎች ይኖራሉ እነዚህን ችግሮች ግን የእኔ ችግሮች አይደሉም የክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ችግሮች ናቸው እንጂ የሚያስተካክልም እኔ አይደለሁም፤ ነገር ግን ጌታ ይችላል:: |
ገንዘብ ይቆጠባል
ተመልሼ ለመምጣት ጥሩ የዝግጅት ጊዜ ይኖረኛል ከመስማት የተሳናቸው አብያተ ክርስትያናት ጋር በመነጋገር አጋር አገኛለሁ በሚቀጥለው ዓመት ት/ት ለመከታተል የተሻለ ልምድ አገኛለሁ |
እባክህ አምላኬ ምራኝ። ምን ማለትና ምን ማድረግ እንደምችል አውቅ ዘንድ ዛሬ ስለ ነገሮች መረዳት ስጠኝ። የጭለማ ሀይሎች ደጆችህን አይቋቋሙምና በእምነት መራመድ አስችለኝ። እኩለ ለሊት ላይ እዚህ መቆየት እንደሚገባኝ ስለ ተረዳሁ የጉዞ ትኬቴን ላለመግዛት ወሰንኩ። በዚሁ መሰረት ጠዋት ወደ ኢትዮጲያ አየር መንገድ የትኬት ቢሮ በመሄድ ጉዞዬን ወደ መስከረም 22 ማራዘሜን ነገርኳቸው። አሁን እግዚአብሔር በእኔ ተጠቅሞ ምን መስራት እንዳቀደ ለማወቅና ለመታዘዝ ተዘጋጅቻለሁ። አሁን እንግዲህ ኢትዮጲያ ከ20 ዓመት በፊት ከካርል ጋር ሆኜ እንዳደረገችብኝ አሁንም እንዳትደግመኝ መፍቀድ አልችልም። በዚህን ጊዜ በክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ሚሲዮን ውስጥ ብዙ ለውጦች ተደርጓል። እኔም ቢያንስ በአንድ ኮሌጅ ውስጥ መስማት የተሳነው ሰው በምን ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ሊኖር እንደሚችል ልምድ እያገኘሁ ነው። በእጅጉ ከጎኔ ያጠሁት እና የነፈቀኝ ሰው ቢኖር ባለቤቴ ኒል ብቻ ነው። አምላኬ ስለ ኒል ምን ማድረግ እንዳለብኝ አሳየኝ፤ እርዳኝ። ወርቅዬ ደግሞ አበበ የተባለውን የመከኒሳ መስማት የተሳናቸው ዳይሬክተር ይዞ መጣ። ከደመረ ጋር ያለኝን ግንኙነትን ጨምሮ በብዙ ጉዳዮች ላይ በስፋት ተወያየን። በእኔና በእርሱ መካከል የተፃፃፍናቸውንም ኢሜሎች አሳየሁት። አሁን ነገሮች ከምስጢርነት መውጣት ጀምሯል። ይህ ጉዳይ ደግሞ ደመረ ልቡ ቀና ካልሆነ ሊከዳኝ የሚጀምርበት ጊዜ ይሆናል።
እባክህ አምላኬ በደመረ ልብ ላይ መስራት ጀምር። የቀና ልብ ስጠው። በሀይሉ እና ጆን ኤድ በእኔ ላይ የሚፈጽሙትን ደባ ለመቀልበስ ምናልባት ወርቅዬ፣ አበበ እና አጠቃላይ ሚሲዮኑ ከእኔ ጋር ይቆማሉ ብዬ አስባለሁ። እነዚህ ሁለቱ ሰዎች የሚሰሩት ሙስናና ማጭበርበር ለሁሉም ግልጽ የሆነ ነው። እናም እግዚአብሔር በዚህ ጉዳይ ላይ ይንቀሳቀሳል ብለን እየጠበቅን ነው። እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ እባክህ በትግዕስት እንድጠብቅ እርዳኝ። ወደ ራሴ መንገድ እንዳልቸኩል ነገር ግን የአንተን ሀሳብ ለመፈጸም እንድችል አግዘኝ። ፍርድህ የማይቀርና ትክክል ስለሆነ እባክህ በትዕግስት አንተን ብቻ መከተል እንድችል እርዳኝ። ነገሮችን በትክክል መለየት እንድችል አግዘኝ። በመገኘትህ ውስጥ አቆየኝ፤ የራሴን ፍላጎት እንዳላሳድድ፣ የተደበቀ ፍላጎቴን እንዳላራምድ፣ በሌሎችም ወጥመድ ውስጥ እንዳልወድቅ በታመኑ እጀችህ ውስጥ ያዘኝ፤ ጠብቀኝ። አሁን እየሆነ ያለው የአንተ ስራ ነው፤ አንተም እየሰራህ ነው። ጦርነቱም የአንተ ነው። እኔ የዋህ የሆንኩ አገልጋይህ ነኝ። እነሆ ላገለግልህም እዚህ አለሁ። ፍቅር የሆነ አገልግሎት ለሌሎች አገልጋዮችህም አብዝቼ ልሰጥ በዚህ መጥቻላሁና አምላኬ እርዳኝ። እባክህ አባቴ አታላዮች ከሆኑ ሰዎች ሸፍነህ ጠብቀኝ። በአንተ ታምኛለሁና ጠብቀኝ።
ሐምሌ 7, 1993
ከደመረ ጋር ቁርስ ከበላሁ በኋላ ከደመረ ይሆንብኛል ብዬ የጠረጠርኩትን ነገር መገንዘብ ጀመርኩ። ቆይቶም ደመረ ራሱ ምናልባት በጥቅሞቹ እና በስልጣኑ ላይ ስጋት የምሆን ከሆነ እንደማይታገሰኝ በግልጽ ነገረኝ፤ አስፈራራኝ። እኔ ደግሞ በጥቅሞቹ እና በስልጣኑ የመምጣቴ እድል ሰፊ ነው። ምንም እንኳን ሊያደርግብኝ የሚፈልጋቸውን ነገሮች ምልክቶች በግልጽ ቢያሳየኝም እኔ ግን አሁንም ከልቤ እንደ ወንድሜ እወደዋለሁ። ለማንኛውም ይህን ጉዳይ በእግዚአብሔር እጆች ላይ መተውን መርጫለሁ። አሁን ከሁሉም አንፃር ክህደቶችን እያየሁ ነው። አሁን ነገሮችን በምስጢር ይዤ እዚህ መቆየት ፈለኩ። በክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ካሉት ከሁሉም ሰዎች ተደብቄ መቆየትንም ፈለኩ። ማንን ማመንና ለማን መታመን እንዳለብኝ አላውቅም። ከክርስትያን ባህርይ አንፃር ስመለከታቸው ሁሉም ግራ የሚያጋቡ ናቸው። ስለዚህ ዝም ብዬ እፈጽመው ዘንድ እግዚአብሔር የፈለገውን ነገር ብቻ ልፈጽም። ይህን ሳደርግ ብቻ ነው ከችግሮችና ግራ መጋባቶች ውጭ የምሆነው። እግዚአብሔር ሆይ አንተ ዓለቴ ነህ፤ አንተ ጠባቂዬ ነህ። እምነቴን የማኖረው በአንተ ላይ ብቻ ነው። ሰው ይወድቃል አንተ ግን ዘለዓለማዊ ነህ። ሰው ይታለላል፤ አንተ ግን ሁሌም እውነትና ብርሃን ነህ።
ሐምሌ 7, 1993
አብርሃም መጥቶ የክፍሌን በር አንኳኳ ምንም መልስ አልሰጠሁትም ነገር ግን ከሆቴሉ አስተናጋጆች አንዷ መጥታ የሆነ ነገር አለችኝ። በክፍሌ ውስጥ በጥሩ ሁኔታ እንደምቀበለው አስቦ የመጣ ይመስላል። ይህን ያልኩት በፊት ይጠብቀኝ የነበረው በሆቴሉ ውስጥ ነበር። አሁን ግን ቀጥታ ወደ ክፍሌ ስለመጣ ነው። ለማንኛውም ለጥቂት ጊዜ ብቻ በሆቴሉ ውስጥ ተገናኝተን መወያየት እንደምንችልና ታች እንዲጠብቀኝ ነገርኩት። ምክንያቱም ልክ 5፡00 ሰዓት ላይ ከፍፁም ጋር ሌላ ቀጠሮ አለኝ። ከአብርሃም ጋር ተገናኝተን ትንሽ ከተነጋገርን በኋላ 5፡00 ላይ ከሌላ ሰው ጋር ቀጠሮ ስላለኝ ቶሎ እንዲሄድ ነገርኩት። እንደዚህ ማለቴ ጥሩ ስሜት ባይሰጠኝም ነገር ግን ሌላ አማራጭ አልነበረኝም። ምክንያቱም ከፍፁም ጋር በነፃነት ለማውራት አልችልም ነበርና። ስለዚህ ሰው የሚያስጨንቀኝ ነገር ምንድነው? እርሱ ነገሮችን ለማስተካከል እየጣረ ነው። እኔ ግን እድል ልሰጠው አልፈለኩም። አንዴ አብሮኝ እንዲሰራ አስቤ ነበር ነገር ግን በሚገባ ስለ ተገነዘብኩት አሁን ወደኋላ መመለስ አልችልም። አምላኬ እባክህ ባልተግባባንባቸው ጉዳዮች ይማር ዘንድ እርዳው። በቀጠሯችን መሰረትም ፍፁም 5፡00 ሰኣት ላይ መጣ፡፡ ከፍፁም ጋር ጥሩ ውይይት ነው ያደረግነው። ፍፁም መልካም የሚመስል የእግዚአብሔር ሰው ነው! በሚገርም ሁኔታ ነው ያበረታታኝ። ከ5፡00 አስከ 6፡30 ድረስ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሰፊ የሆነ ውይይት አድርገናል። ነገር ግን በልቡ ውስጥ ስላለውና መስማት ለተሳናቸው ወገኖች ምን ዓይነት ህልም እንዳለው በመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ ገና አልተወያየንም። ኢትዮጲያ የልቤ ሀገርና ራዕዬ ናት።
ፍፁም እግዚአብሄር በእውነት ለራሱ መልካም ተልዕኮ ወደዚህ አምጥቶሻል አለኝ። የእኛ አብሮነትና የእርሱ ሚና የመስማት የተሳናቸው የወንጌል ስርጭት ውስጥ ታላቅ ትርጉም አለው። ይህም ከክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ማለትም ከደመረ፣ በሀይሉ፣ ወርቅዬ እና አበበ የተለያዩ ውዥንብሮች እየመጣ ባለበት ወቅት ይህ ጊዜ መስማት የተሳናቸው ወገኖች እውነተኛ ቤተ ክርስትያን ትክክለኛ እምነት የምታስመሰክርበት ትክክለኛ ጊዜ ነው። ከክርስቶስ ቤተ ክርስትያን በሚጣለው ወጥመድ እና በቤተ ክርስትያኑ ፖለቲካ ውስጥ ወድቄ መያዝ የለብኝም። እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ ቀደም ብለህ ስላስተማርከኝ፤ አዲስ ትምህርት በዚህን ጊዜ ከዚህ እንዳልማር ስለአደረከኝ አመሰግንሃለሁ። የክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ከምትወድህ አስበልጬ እወድሃለሁ። ከሚወዳቸው ሰዎችም አስበልጬ እወድሃለሁ። በሕይወቴ ውስጥ አንተ ቀዳሚ ስፍራ አለህ። አንተ ጌታዬ ነህ፣ በሕይወት ዘመኔ ሁሉ ለአንተ ብቻ እገዛልሃለሁ። ከፍፁም ጋር እየተነጋገርኩ ባለሁበት በዚህን ሰዓት ወርቅዬ እንደገና መጣ። ወርቅዬ ወዳጄ ነው ብዬ አስባለሁ። ነገረ ግን የሆነ ነገር ወይም የሆነ ሰው ወይም የክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ውዥንብር ውስጥ እየከተቱኝ ነው። እግዚአብሔር ግን የውዥንብር አምላክ አይደለም። እነዚህ ሰዎች ደግሞ በውዥንብር መንገድ የተሞሉ ናቸው። ጌታ ሆይ ያለምንም ምክንያት በእውነት እና በንጽህና እንዲወዱህ መንገዱን አሳያቸው።
ሐምሌ 8, 1993
መስማት ከተሳናቸው ሰዎች ጋር ጥሩ የአገልግሎት ጊዜ ነበረን። አማረኛን ለመማር በጣም እፈልጋለሁ። በሰበካ ጊዜ አንዳንዶቹን ነገሮች መረዳት እንድችል አብርሃም ብዙ አግዞኛል። ከቤተ ክርስትያን ስመለስ ታደሰ አብሮኝ ወዳለሁበት ሆቴል መጣ። ቅዳሜ እኔ ዘንድ ለመምጣት እቅድ ነበረው ቢሆንም ይህንን ዕቅዱን ሰርዞ ዛሬ የመጣበት ምክንያት በእሁድ ፕሮግራም ላይ የሰበካ ፕሮግራም ስለ ነበረው ነው። እናም ዛሬ እስከ 10፡00 ሰዓት ድንቅ የሆነ የአብሮነት ጊዜ ይኖረናል። ስለ ኮሌጅ ጉዳይ መስማት የተሳናቸው ወገኖች ወደ ኮሌጅ በሚሄዱበት ጉዳይ ላይ እንዲሁም መስማት የተሳናቸው ወገኖች ያላቸው ፍላጎት ምን እንደ ሆነ በመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ በሰፊው ስንወያይ ነበር። ዛሬ ጠዋት መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች ለኮሌጅ የሚያስፈልጋቸውን ነገሮች በዝርዝር ሰጥቶኝ ነበር። ከኒልም ጋር ዛሬ ጠዋት በስልክ ለመነጋገር ችዬ ነበር። በዚህ የስልክ ንግግራችን ውስጥ ማድረግ ስለሚገባኝ ነገሮች መልስ ሊሰጠኝ በሳምንት ውስጥ እንደሚደውልልኝ ነግሮኛል። ይህ ማለት እንግዲህ ቀድሜ ወደ አገር ቤት ተመልሼ ለትምህርት ደግሞ ወደ ኢትዮጲያ ስለመምጣት ወይንም ደግሞ ገንዘብ ለመቆጠብ እዚሁ መቆየት እችል እንደሆን በሚሉ ጉዳዮች ላይ ተመልሶ ይደውልልኛል።
ሐምሌ 9, 1993
ዛሬ ቀኑን ያሳለፍኩት ከፍፁም እና ቤተሰቡ ጋር ነው። ከሚስቱ፣ ሁለት ሴት ልጆቹ፣ አዲስ የተወለደ ህፃን ልጅ እና የሚስቱ እህቶች አብረውት ነበሩ። በዚህን ቀን ፍፁም አዲስ ሀሳብ ይዞ ቀረበ። ይህም በጥቅምት ወር ውስጥ መስማት ለተሳናቸው ወገኖች ኮሌጅ መክፈት የሚል ነበር። ለዚህም የመኖሪያ ቤት መፈለግ ቅድሚያ የሚሰጥ መሆኑን ነገረኝ። ትምህርት የማስጀመሩንና የማለማመዱን ነገር በተመለከተ ፍፁምና ታደሰ ሊያስጀምሩ ይችላሉ። በእንግሊዝኛ እና በሌሎች ነገሮች እኔ ማገዝ እችላለሁ። የቤተ ክርስትያኑ የረዝም ጊዜ ዋና ረጂ (ስፖንሰር) ቪክ ምናልባት የገንዘብ እርዳታውን ሊቀንስ ስለሚችል ለቤተ ክርስትያን ጭምር የሚበቃ ቦታ ፈልጎ መከራየት ያስፈልጋል። ቪክ የቤተ ክርስትያኑን ስም እንዲቀይር ፍፁምን ቢጠይቀውም ፍፁም ግን ፈቃደኛ ሊሆን አልቻለም። ምክንያቱም መስማት የተሳናቸው ወገኖች የቤተ ክርስትያኑን ስም ቢቀይር ከቪክ ለሚያገኘው ደሞዝ ብቻ ብሎ ነው በማለት እንዳያስቡ ሰግቶ ነው። ፍፁም ሀቀኛ እና የተከበረ ሰው ትክክለኛ በሆነ ጉዳይ ላይ የማይደራደር በእውነት ትክክለኛ የእግዚአብሔር ሰው ነው። ከእርሱ ጋር መስራት በእጅጉ መታደል ነው። ይህ ሰው ሰዎችን የሚወድና ለሰው የሚያስብ ሰው ነው።
ሐምሌ 10, 1993
በዚህን ቀን መጽሐፍ ቅዱስ ለማጥናት መስማት የተሳናቸው መጥምቃዊያን ቤተ ክርስትያን ሄጄ ነበር። በዚያን ቀን የሚያስተምረው ፍፁም ስለ ነበረ ብዙ መስማት የተሳናቸው ሰዎች ከተለያዩ አብያተ ክርስትያናት መጥተው ነበር። ፍፁም የእግዚአብሔር ቅባት ያለው ሰው ነው። እናም እረዳውና አበረታታው ዘንድ እግዚአብሔር ወደዚህ የላከኝ እርሱ ነው ብዬ አምናለሁ። በአካል እዚህ የመገኘቴ ምክንያት ምንድነው ብዬ ጥያቄ ማንሳት ጀምሬያለሁ። ምናልባት ለአየር ገንዘብ ከማወጣ እዚሁ ካለሁበት ሆኜ ድጋፍ በማድረግ ታላቅ አገልግሎት ማድረግ እችል ይሆናል።
ሐምሌ 11, 1993
በጠዋት ለደመረ ደውዬለት አምሳለንና እርሱን ለቁረስ ጋብዤያቸው ነበር። ነገር ግን ደመረ ወደ ናዝሬት እየሄድን ነው በማለት እንደማይመቻቸው ነገረኝ ዳሩ ግን በቀናት ውስጥ ሲመለሱ እንደሚደውልልኝ ነገረኝ። እግረ መንገዴንም ስለ ደም ብዛቱ እና ልቡ ጉዳይ ስጠይቀው የልቡ ምት ባልተለመደ ሁኔታ መጨመሩን ነገረኝ። ይህ የሆነው እኔ እንደማስበው ትላንትና ማታ ባደረግነው ቆይታ ይመስለኛል። እኔም ሰውን ሳይሆን እግዚአብሔርን መፍራት እንዳለበት ነገሬው አበረታታሁት። በሀይሉንና ጆን ኤድንም መፍራት እንደሌለበት አስረግጬ ነገርኩት። በእውነት መፈናፈኛ በሌለው እጆች መካከል ተይዟል። በጣም ሸክም ሆኜበታለሁ እና ስለ እርሱ በፆም በለቅሶ በእግዚአብሔር ፊት መሆን አለብኝ። ከዚህ ስልክ ውይይት በኋላ መጀመሪያ የሄድኩት ወደ ወንጌላዊያን ኮሌጅ ነበር። ወደዚያም የተጓዝኩት በመንፈስ ተመርቼ ነው። ምክንያቱም አብርሃምን አግኝቼ በእውነት እንደምወደው መንገር እንዳለብኝ ውስጤ ይገፋኝ ስለ ነበር ነው። በመሰረቱ እንደ በፊቱ ከእርሱ ጋር ያልተገናኘሁት ከብዙ ሰው ጋር በመነጋገር ብዙ ስለ ተያዝኩ እንዲሁም ለጥቂት ጊዜ ከእርሱም ርቄ ሁኔታዎችን በግልጽ ለማያት እንዲችል በመወሰኔ መሆኑን ላሳውቀው ወደድኩ። እግዚአብሔር ታላቅ ነው። ይህ ሰው ተለውጧል። እንደተገናኘን የነገረኝ ነገር ቢኖር የኢሜይል መልእክቶቼን በሙሉ እያነበበ እንደሆነ የቀና ልብ እንዳለኝ እንደተገነዘበ እርሱም ከመሰረቱ እንደተሳሳተ በሰፊው ነገረኝ። እናም አሁን 100% ከእኔ ጋር መሆኑን አስረግጦ ነገረኝ። በጣም እንደ ተባረኩ ተሰማኝ። አሁን አዲስ በሚከፈተው የመስማት የተሳናቸው ኮሌጅ ውስጥ ለመማር እንደሚፈልግ ነገረኝ። በተጨማሪም በኢትዮጲያ ውስጥ የሚገኙትን መስማት የተሳናቸውን ለማገልገል ጉጉት እንዳለው ነገረኝ።
ቀጥሎም ውይይት ያደረኩት ከግርማ ጋር ነበር። ዛሬ ከእርሱ ጋር ጥሩ ጊዜ አልበረኝም። ምክንያቱም ጌታ እየተናገረኝ ባለው ጉዳይ ላይ የጠራ ግንዛቤ ስላልነበረኝ እጅግ የከበደኝ ጊዜ ውስጥ ነበርኩ። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆኜ ነበር ግርማን ያገኘሁት። መስማት የተሳናቸው ትምህርት ቤት ወይም ኮሌጅ መጀመርን በተመለከተ እርምጃዬ ምን መሆን አለበት በሚለው ጥያቄ እየተብሰለሰልኩ እንዲሁም መፍትሄ ለመስጠት እየተጨነኩ ነገር ግን ምንም መፍትሄ መስጠት በማልችልበት ሁኔታ ውስጥ ሆኜ ነበር ግርማን ያገኘሁት። ለዚህም ምክንያቱ ዛሬ ጠዋት ከደመረ ጋር ከነበረኝ ጠንካራ የስልክ ንግግር የተነሳ ነው። ከዚህም ሌላ የኒል ናፍቆት፤ ወደ አሜሪካ የመመለሴ ጉዳይ ያለመቋጨቱ ነገሮች ሁሉ ለሚሰማኝ የተዘበራረቀ ስሜት አስተዋፅኦ ነበራቸው። ወደ አሜሪካ መመለስ እፈልጋለሁ ነገር ግን መመለስ አለብኝ? አምላኬ ሆይ እባክህ አጽናናኝ፤ እባክህ ምራኝ፤ ያዘጋጀህልኝ ነገሮች ቅደም ተከተላቸውን አሳየኝ። እባክህ የደመረንም ጤንነት ጠብቅ። ዛሬ እራቴን የበላሁት ከውርቅዬ ጋር ነው። በዚህን ወቅት ደመረ ያለኝን ሁሉ ዘርዝሬ ነገርኩት። ጆን ኤድ አበበ እንዲባረር እንዳዘዘ በዚህም ደመረ ደስተኛ እንደሆነ ከደመረ ሰምቻለሁ። ነገር ግን እነዚህን ለወርቅዬ አልነገርኩትም። የክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ግቢ የወንጀለኞች ግቢ ሆኗል። እግዚአብሄር ሆይ እባክህ እነዚህን ሰዎች እርዳቸው።
ሐምሌ 16, 1993
በኢትዮጲያ ውስጥ መስማት ለተሳናቸው ወገኖች ኮሌጅ ለመክፈት የርክካቤ የክንውን እቅድ
ወደ አሜሪካ በመመለስ አጋሮችን መፈለግ
ከክርስቶስ ቤተ ክርስትያን መስማት የተሳናቸው ትምህርት ቤት ተማሪዎችን መመልመል
ሰዎርድ መስማት ከተሳናቸው ኮሌጅ ጋር ሊያግዙ በሚችሉበት ጉዳይ ላይ መነጋገር
ሊረዱ የሚችሉ ተቋማትን ለይቶ ዝርዝር መረጃ አዘጋጅቶ መጨረስ
ለተማሪዎችን የደንብ ልብስ በመርዳት የሚያግዙ መስማት በተሳናቸው ወገኖች ላይ የሚሰሩ አብያተ ክርስትያናትና ድርጅቶችን መለየት እና ጌታ በሚመራኝ መሰረት የክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ሊያግዝ በሚችለው ጉዳይ ላይ ጥያቄ ማቅረብ
ኮምፒዩተሮችንና ሌሎች አስፈላጊ ግብዓቶችን ማፈላለግ
መስማት የተሳናቸውን ተማሪዎች ለኮሌጅ ብቁ ለማድረግ የጥናት ክፍለ ጊዜ በማመቻቸት ሊረዱን የሚችሉ አካላትን ማፈላለግ፡፡
እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ጥር ውስጥ ከኒል ጋር ተመልሶ ወደ ኢትዮጲያ መምጣት ይህም ለኒል በኢትዮጲያ ውስጥ ያለውን መስማት ለተሳናቸው ወገኖች የሚሰራውን ስራ እንዲሁም ባህላቸውን ለመመልከት ያስችለዋል። ከዚህም ሌላ ከበሀይሉ እና ጆን ኤድ ጋር ያለኝን ግንኙነት የላላ እና በክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ሚሲዮን ውስጥ የሚደረገውን ማጭበርበር ስራ አይቶ ስራቸውንም የረከሰ መሆኑን ለመረዳት ያስችለዋል። ከደመረ ጋር በስልክ ከተነጋገርኩ በኋላ ሊያገኙኝ ከሚጠብቁ ሌሎች መስማት ከተሳናቸው ሰዎች ጋር ለማነጋገር ወደ ሆቴሉ ወረድኩ። ከዚያም ቤተሰቦቿ ከእስላም የሆነች ነፊሳ የምትባል ሴት ወደ መስሪያ ቤቷ ወስዳኝ ስለ ነበረ እግረ መንገዴን ለስጦታ የሚሆኑ እቃዎችን የማግኘት አጋጣሚ አግኝቻለሁ። ተሾመ፣ ቅድስት እና እልፍነሽም እዚያ ሳለሁ ተገናኘን። እልፍነሽን እንደገና ማግኘት በመቻሌ ደስ ብሎኛል፤ ተቃቅፈንም ተላቀስን። ባፈና ግን ለምን ተመልሳ እንዳልመጣች ማወቅ አልቻልኩም። ጥርጣሬዬ ግን በሀይሉ ወይም በደመረ ምክንያት ሊሆን ይችላል። ለማንኛውም በመጨረሻው ቀን፤ በመጨረሻው ሰዓት እልፍነሽን ማግኘት በመቻሌ በጣም ደስ ብሎኛል።
ወደ አለሁበት ዲ አፍሪክ ሆቴል ከተመለስኩ በኋላ አንድ መስማት የተሳናት አርቲስት ብዙ ስራዎቿን ልታሳየን መጥታ ስለ ነበርና ሁሉንም ስለወደድኳቸው ሁሉንም ስራዎቿን ገዛኋት። ከዚያም ምሳ አብረን በልተን ተለያየን። ቀጥሎም ወርቅዬ መጥቶ ስለ ነበረ በምድር ቤት ውስጥ ጥሩ ጊዜ አሳለፍን። ወርቅዬ ከሄደ በኋላ ከነ ተሾመ ጋር መርካቶ ሄጄ ወደ አገር ቤት የማመጣውን በርካታ ነገሮችን ገዝቼ ተመለስኩ። በሚቀጥለው ቀን ከሰዓት በኋላ 10፡30 ወርቅዬ እና ተሾመ በታክሲ አየር መንገድ ድረስ ሸኙኝ። እዛው ቦሌ አየር ማረፊያ እያለሁም 11፡30 ሰዓት ላይ የብዙነሽ ቤተሰቦች ለብዙነሽ የሚልኩት እቃዎች ይዘው መጡ። እነዚህ ሰዎች የሚኖሩት ከክርስቶስ ቤተ ክርስትያን አጠገብ በመሆኑ በሀይሉን ያውቁታል። አሁን ጉዞ ወደ አሜሪካ ተጀምሯል። በጉዞዬም ላይ ለበሀይሉ ጥሩ ደብዳቤ ፃፍኩለት። በደብዳቤዬ ውስጥ ምንም እንኳ እርሱ ቢያገለኝም እኔ ግን መቼውም እንደምወደው ገልጬለታለሁ።
ሐምሌ 19, 1993
አሜሪካ ሲንሲናቲ አየር ማረፊያ የደረስኩት የዛን ቀን ሌሊት 6፡00 ሰዓት ላይ ነበር። ኒል ጠዋት 11፡30 ሊወስደኝ ወደዚያው ይመጣል። እናም በጣም ደስታ ተሰምቶኛል ምክንያቱም ከኒል ጋር የመገናኘቱ ጊዜ እጅግ ቅርብ በመሆኑ። ለማንኛውም በዚህን ሰኣት ሀገሬ አሜሪካ ውስጥ ነው ያለሁት። እናም ለብዙ ምክንያቶች ባህሪዬ ሊለወጥ ስለሚችል እርዳታ ያስፈልገኛል። ጌታ ግን ሁሉንም ያስተምረኛል። የሚያስፈልገው ነገር የእኔ ፈቃድ ብቻ ነው። ጌታ ሆይ ፈቅጃለሁና ልታስተምረኝ ና። በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ረቡዕና ሀሙስ ያሳለፍኩት በእንቅልፍ ነበር። በክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ውስጥ መሳተፍ በጀመርኩበት ጊዜ እግዚአብሔርን አገለግለው ዘንድ የሰጠኝ ስራ ነበር። ይኸውም መስማት የተሳናቸውን ወገኖች ማገልገል ነበር። ይህንንም በሕይወት ዘመኔ ውስጥ ዋነኛ ስራ አድርጌ ወሰድኩኝ። ይህንን አገልግሎት በማከናወን ወጣ ገባ ስል ስወጣ ስወርድ ዲያብሎስ በከፍተኛ ደረጃ ይቃወመኝ ነበር። ሰዎችን ይልቁንም የማምናቸውን ሰዎች ቤተሰቦቼ ሳይቀሩ ያነሳሳብኝ ነበር። ለምን እንደ ሆነ ባላውቅም። በፀሎትና አምልኮ ተግቼ ስራዬን እከታተላለሁ። በዘመኔ የደረሰብኝን ሁሉ በየእለቱ እየመዘገብኩኝ የነበረውን እውነተኛ ታሪክ የእግዚአብሔር ሰዎች ያነቡ ዘንድ አቅርቤያለሁ። ስለሆነም በተከታታይ የማቀርባቸውን እነዚህን እውነቶች እንዲያነቡ እጋብዛለሁ። እግዚአብሔር ይበርካችሁ።
መስከረም 21, 1994
ኒዮርክ የአውሮፕላን ጣቢያ ውስጥ ነው ያለሁት። በስሜት ተሞልቼ የበረራ ሰዓቴን እየተጠባበኩ ነው። ወደ ኢትዮጵያ የሚበረው አውሮፕላን የዘገየ መሰለኝ። አንዳች ነገር በውስጤ ይመላለሳል። ባለቤቴ ኒል አየር መንገድ አድርሶኝ ከተሰናበተኝ በኋላ ብቸኝነት ይሰማኝ ጀመር። ኒል ሳይሰናበተኝ በፊት እጅግ አበረታትቶኝና አፅናንቶኝ ነበር። ልለየው እንደሆነ የተሰማኝ ግን ከተሰናበተኝ በኋላ ነበር። ልጄ ጴጥሮስ ልቡን ለጌታ የሰጠ ልጅ ነው። እጅግ ስለሚያስብልኝና ስለሚረዳኝ እኮራበታለሁ። በጌታ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር ብቻ ለማድረግ የሚፈልግ ልጅ ስለሆነ እግዚአብሔር በእርሱ የባረከኝ ያህል ይሰማኛል። ከዲርም ብዙ የሚያበረክት ነገር ያለው ቢሆንም ግራ የሚያጋባ ልጅ ነው። ከዬት እንደመጣ አላውቅም። ጌታ ሆይ አንተ እንደምታውቀው እርሱና ጄይላን በፈፀሙት ድርጊት እስከ አሁን ውስጤ እያረረ ነው፤ እባክህ ምን ማድረግ እንዳለብኝ አንተው አሳየኝ አልኩ በውስጤ።
መስከረም 22, 1994
በአንድ አውሮፕላን እንጓዝ ስለ ነበር ከግልንዳ ዎረሌይ ጋር እንደገና ተገናኘን። ቀደም ሲል ጥሩ ቀረቤታ ስለ ነበርን ከእርሷ እና ባለቤቷ ጋር መልካም ግንኙነት ይኖረናል ብየ ተስፋ አደረኩ። አስብ እንደነበረው ከሀላፊ ጋር በመስራት ችግር አልገጠመኝም፤ ይህ አጋጣሚ ደግሞ ትልቅ እፎይታ ነው። የአዲስ አበባ ቆይታየ በተመለከተ እንደ ዓለም አቀፉ የወንጌል ማሕበር ሚስዮን የእንግዳ ማረፊያ ምቹ ቦታ የለም። ወደ ኢትዮጵያ ለመሄድ ባሰብኩ ቁጥር ለቆይታ ተስፋ የማደርገው ይህ ቦታ ነው። እናም አርፈበታለሁ ብዬ ከማስባቸው ቦታዎች ውስጥ ቀዳሚ እድርጌዋለሁ። ማረፊያን በተመለከተ ችግሬን የሚፈታልኝ ይህ ቦታ ነው። የማረፊያ ቦታዬን ካገኘሁ በኋላ ታደሰ ፍለጋ ሄድኩ። በዚያን ወቅት ታደሰ በኮሌጁ ቤተ መጽሐፍ ውስጥ ነበር። እጅግ አስፈላጊና መልካም የሆነ አጭር ቆይታ ካደረግን በኋላ በሚቀጥለው ቀን 9፡00 ሰዓት ላይ ወደ እኔ እንደሚመጣ ተቀጣጥረን ተለያየን። የቀጠሮአችን ዓላማም ከፍፁም ጋር መገናኘት ስለሆን በጉጉት የምጠብቀው ነበር። ጌታ ሆይ ለእኔ ያለህ እቅድ ምን ይሆን? በዚህ ዓይነት ቀኑ ተገባደደ። ከምሽቱ 12፡00 ላይ እራቴ በልቼ ወደ መኝታዬ ሄድኩ።
መስከረም 23, 1994
ማረፊያ ቤት መካኒሳ አከባቢ ይገኝ እንደሆነ ለማየት ብለን ከታደሰ ጋር ሄድን። እዚያ አካባቢ መኖር እጅግ እፈልግ ነበር። ሆኖም ግን ስላልቻልኩኝ ሌላ አከባቢ መፈለግ ግድ ነበር። ይህም ቆይታዬ ለሶስት ወራት ነበር። በዚህ ረገድ ታደሰ በጣም ረድቶኛል። የዛን ጊዜ ከፍፁም ጋር ገና መገናኘት አልቻልኩም ነበር። የምሳ ሰዓት ደርሶ ስለነበር ከታደሰ ጋር ምሳ ለመብላት ወደ ዓለም አቀፉ የወንጌል ማሕበር ሚስዮን ሄድን። ምሳ እየበላን ሳለ ከእኔ ራቅ ብሎ አብርሃም ተቀምጦ አየሁ። አብርሃምን ማየቴን ለታደሰ ስነግረው መስማት የተሳናቸውን ማስተማር ይችል ዘንድ ለአንድ ዓመት ስልጠና ወደ ኬኒያ ለመሄድ እቅድ እንዳለው ነገረኝ። ወደ አሜሪካ ለመግባት ሁኔታዎችን ጨርሶ አልነበረም? ያ ሁሉ ምኞቱ አልተሳካም ማለት ነው? አልኩኝ በልቤ። ለማንኛውም በፀሎት መርዳት እንዳለብኝ ተሰማኝ። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሳለሁ ፍፁምና ገነት መጡ። አሁን ከረፋዱ 5፡30 ገደማ ሆኖዋል። በጣም ደስ አለኝ። እየተጫወትን እስከ ምሽት ድረስ ቆየን። ፍፁምና ገነት መካኒሳ በሚገኘው እንግዳ ማረፊያ ይልቅ በዚህ ቦታ እንድኖር መከሩኝ። ምክንያታቸውም እንግዳ ማረፊያው ለበሀይሉ ቅርብ በመሆኑና ዘወትር የሚያየኝ ከሆነ መልካም እንዳልሆነ እንዲሁም በእንግዳ ማረፊያው የበለጠ ብቸኝነት ሊሰማኝ እንደሚችል ስለታሰባቸው ነው። ምክራቸው ምክንያታዊ ነበር። ቀጥሎም የዓለም አቀፉ የወንጌል ማሕበር ሚስዮን የእንግዳ ማረፊያ ሁኔታዎችን እንዲያመቻቹልኝ ለመጠየቅ ወስኜ ተለያየን።
መስከረም 24, 1994
እስኪ ያልተለመደ ነገር ይጀመር! እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ በዚህ ቦታ በስራ ላይ ነህ? ብዬ በጥያቄ መልክ ተለማመንኩት፤ አምላኬ በእርግጥ እንዲረዳኝ በመማፀን። ከዚያም ወደ እንግዳ ቤቱ ቢሮ በመሄድ ለሶስት ወራት እዚህ መቆየት እንደምፈልግ ገልጬ ክፍል እንዲያዘጋጁልኝ ጠየኩ። ዓለም አቀፉ የወንጌል ማሕበር ሚስዮን የእንግዳ ማረፊያ ስራ አስኪያጅ ጋር ብዙ ከተወያየን በኋላ ለክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ቅርብ የሆነ የእናቱን ቤት እንደሚያከራየኝ ነገረኝ። እጅግ ደስ አለኝ። ይህ ምን ማለት ነው? የፍፁምን ምክር ተቀበልኩ ማለት ነው? የፍፁምን ምክር ከበሀይሉ እይታ ውጭ ለመሆን በመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ (የዓለም አቀፉ የወንጌል ማሕበር ሚስዮን የእንግዳ ማረፊያ) ውስጥ መቆየት አለብሽ የሚል ነበር። ነገር ግን አሁን ከክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ጎረቤት ሆኜ የመኖር አጋጣሚ ተፈጥሯል። ይህንን ቤት የፊታችን ቅዳሜ 11፡00 ላይ ከባለቤቱ ጋር ሆነን ልናየው ነው። ይደንቃል!! ከዚያም በቀጥታ ወደ ፍፁም ቤት ሄድኩ ። በብዙ ጉዳዮች ላይ ስንወያይ ዋልን። የውይይታችን ትኩረት የነበረው መስማት ለተሳናቸው ወገኖች የኮሌጅ ትምህርት እንዲቀጥሉ ባለን እቅድ ላይ ነበር። ፍፁም ይህንን ጉዳይ ለሪቻርድ ኦክ አስቀድሞ ማሳወቅ ነበረበት። እናም አሁን ፕሮግራሙን በቶሎ በመጥምቃዊያን ቤተ ክርስትያን ውስጥ መጀመርን በተመለከተ ስንወያይ ዋልን። ይህንን ጉዳይ አዲስ አበባ በነበረኝ ጉዞዬ ላይ ለግልንዳ ዎረሌይም አጫውቼያት ነበር። አሁን ግን ከፍፁም ጋር ሆነን ለቪክ ለማሳወቅና ለማማከር ቀጠሮ መያዝ እንዳለብኝ ተሰማኝ። አስቀድመን ግን እኔ ፍፁም እና አብርሃም መወያየት አለበን።
ጉዳዩን ከአብርሃም ጋር መወያት እንዳለብን ፍፁም ይፈልግ ነበርና ሀሳቡን ሳነሳለት ደስ አለው። እናም ቪክ በሀሳባችን ይሰማማል የሚል ተስፋ ይዘን በሚቀጥለው ቀን አርብ ከሰዓት በኋላ 10፡00 ለመገናኘት ተቀጣጥረን ተለያየን። ምናልባት ይህ ሰው ስለ ጉዳዩ አስቀድሞ የሚያውቅ ከሆነ እቅዳችንን ላይቀበለን ይችላል። ምክንያቱም በጉዳዩ ላይ ሁሉም ሰው አንድ ሀሳብ ላይ አልደረስንም ነበርና። ስለዚህ ይህንን የተከፋፈለ ሀሳብ የሚያውቅ ከሆነ እቅዳችንን ውድቅ ሊያደርግ ይችላል። እንዲህ ከሆነ በጉዳዩ ላይ ከታምራት ጋርም መወያየት ሊኖርብን ነው። የእለቱን ውይይታችን አጠናቀን ከፍፁም ቤት ስንመለስ መንገድ ላይ ለወርቅዬ ደውለንላት መጥታ ተገናኘን። ሰላምታ ተለዋውጠን ትንሽ አብረን ቆየን። ቆይታችንም መልካም ቆይታ ነበር። ወርቅዬን በማግኘቴ እፎይታ ተሰማኝ። ምክንያቱም እዚያው መካኒሳ መስማት የተሳናቸው ት/ቤት ውስጥ ይሰራ ስለ ነበር ስለ እኛ ምን እየታሰበ እንደሆነ ስለሚያሰማኝ።
መስከረም 25, 1994
እግዚአብሔር ሆይ ለአገልግሎት ስተጋ አንተ ግን ለዘመናት ለስቃይ ሰጠኸኝ፤ ከምወዳቸው ኢትዮጲያውያን በመለየቴ ሀዘን ወደቀብኝ። ነገር ግን ኢትዮጲያ ውስጥ ለመልካም አገልግሎት እንደ ጠራኸኝ አውቃለሁ። አዎ ጠላት ሊሰርቅ፣ ሊገድል እና ሊያጠፋ እንደሚመጣ ከቃልህ ተምሬያለሁ። ይህንን የጠላቴን ተግባር ለማየት ዓይኖቼ ተከፍቷል፣ በንቃትም እከታተላለሁ። በዚህ ማለዳ ላሰማኸኝ የማስጠንቀቂያ ደወል አመሰግነሃለሁ። እባክህ አምላኬ በውስጤ ስላስቀመጥከው ሸክም እርዳኝ። መወሰድ ስለሚገባኝ እርምጃና መከተል ስላለብኝ መንገድ ለፍፁም ሳስረዳው እንዲሰማኝ ልቡን ክፈተው፣ አዘጋጀው። አግዚአብሄር ሆይ በእጄ ውስጥ ያስቀመጥካቸውን ሀላፊነቶች እሸከማቸው ዘንድ አስችለኝ። በእነዚህ ጉዳዮች ላይ መረጃዎች ያስፈልጉኛል። ይህንንም ጉዳይ ለአብርሃም የማስረዳበትና የማሳምንበትን ፀጋ ስጠኝ። ይህን ሰው እንዴት መቅረብ እንዳለብኝ አሳየኝ። በዚህ ውስጥ ትክክለኛውን ሀላፊነት መውሰድ አልፈልግም። ለታይታ ብቻ የሚኖር ሰው ነው። ዝም ብሎ በፍፁም ፊት ከመጮህ ውጭ ጉዳዩን ለቪክ ለማስረዳት አይፈልግም።እንዲያው ለታይታ ብቻ ነው። ይህ ደግሞ የክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ፖለቲካ ነው። የዚህ ቤተ ክርስትያን ፖለቲካ ደግሞ ለህመም ዳርጎኛል። ጌታ ሆይ በዚህ ጠዋት በእኔ ሆነህ ታላቅ ስራ አከናውን። ስጋዬ በውስጤ እንዲሞት አይሁን! በመንፈስህ ሙላኝ፤ ድፍረትና ሀይልህን አጎናጽፈኝ።
መስከረም 26, 1994
ከደቡብ አፍሪካ ከመጣው አብርሃም ጋር ለመወያየት ብለን ከፍፁም ጋር ወደ ቤተ ክርስትያን ሄድን። በመንገዳችን ላይ ሳለን ለፍፁም ሰብዓ ሰገል የተነገረውን ማስጠንቀቂያ አስረዳው ነበር። እግዚአብሔር ለሰብዓ ሰገል የነገራቸው ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ “በሌላ መንገድ ሂዱ” የሚለው ነበር። እኔም በተለየ መንገድ መሄድ እንዳለብኝ ይሰማኛል። እናም መስማት የተሳናቸውን ወገኖች ለማገልገል በመጥምቃዊያን ቤተ ክርስትያን ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ መጀመር ሳይሆን በሌላ መንገድ መሄድ እንዳለብኝ ነው። ፍፁም ትሁትና ደግ ሰው ነው።እርሱን የጠራነው ሰርጉ በተቃረበበት ወቅት በመሆኑ ይቅርታ ጠይቀነው ከአብርሃም ጋር እየተጋገዙ እንዲሰሩ ነው። እንዲህ እንዲህ እያልን ነገሮችን እያስተካከልን ነው። ለአገልግሎታችንም ምቹ ይሆን ዘንድ በቂ ክፍሎች ያሉትን ቤት መፈለግ አለብኝ። ይህ ቤት ለመኖሪያ እና ለመማሪያ ክፍሎችም የሚያገለግል መሆን አለበት። ልክ ከክርስቶስ ቤተ ክርስትያን አጠገብ ቤት እንዳገኘሁና እዚያ እንደምኖር ያክል ደስታ ተሰማኝ። ነገር ግን ይህ ምን ማለት ነው? ከሰዓት በኋላ በመጥምቃዊያን ቤተ ክርስትያን መስማት የተሳናቸው ወገኖች መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ሚያጠኑበት ኮሌጅ ሄድኩ። በዚያም ብዙ የማውቃቸውና አዳዲስ መስማት የተሳናቸውን ተማሪዎች አገኘሁ። ታደሰ ደግሞ ሁሉንም አስተምሯቸው ወይም እያስተማራቸው ስለሆነ በሁሉም ዘንድ የተወደደ ሰው ነው። ሁሉም በትምህርቱ ተማርኳል። አብዛኛዎቹ ተማሪዎች የመጡት ከክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ነበር።
መስከረም 27, 1994
ከፍፁም ጋር ሆነን ለመከራየት የተጠቆምነውን ቤት ለማየት ብንሄድም ቁልፍ ስላልነበረ መጎብኘት አልቻልንም። የቤቱ ኪራይ በ400 ዶላር መሆኑን ተነገረን። እንዲቀንሱልን ከጠየቅን በኋላ ስለዚህ ጉዳይ በእግዚአብሔር ፊት በፀሎት ለመቅረብ ወስኜ ተመለስን። ከዚያም በቀጥታ የሄድነው ወደ ክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ግቢ ነበር። በዚያም ባፈና መኖሯን ከጠየቅን በኋላ ወደ ቤቷ ሄድን። እዚያም ጥቂት ከቆየን በኋላ ፍፁም ለቅሶ ኖሮበት ወደ ቀብር ሄደ። እኔ ደግሞ ባፈናንና ልጇን ምሳ ለመጋበዝ ተያይዘን ከግቢ ወጣን። ምሳ የበላነው በዓለም አቀፉ የወንጌል ማሕበር ሚስዮን ካፍቴሪያ ውስጥ ሲሆን ቀጥሎም ወደምኖርበት እንግዳ ማረፊያ ሄድን። ጥቂት አብረን እየተጫወትን ከቆየን በኋላ ባፈናና ልጇ በአውቶብስ ወደ ቤታቸው ሸኝቻቸው ተመለስኩ። ከዚህ ቀን በኋላ ጠዋት ወደ ክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ለመመላለስ ድፍረት አገኘሁ።
መስከረም 28, 1994
እሁድ ጠዋት ወደ ክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ሄድኩ። በኃይሉ በዚያ አልነበረም። ደመረ ግን ነበር። በአትሮኖስ ላይ ሆነው ስለ እኔ እንደሚናገሩ እርግጠኛ ነበርኩ። ሰዎች ወደ እኔ እንዳይቀርቡና በማንኛውም ሁኔታ ከእኔ ጋር እንዳይተባበሩ ንግግር እንደሚያደርጉ እጠብቅ ነበር። ይህ ነገር በውስጤ ተቋጥሯል። ነገር ግን በኃይሉ ሊያናግረኝ እንደሚፈልግ ደመረ ከነገረኝ በኋላ አንቺ ግን ቀድመሽ ልትደውይለት ይገባል አለኝ። ደመረ ከእኔ ጋር ያለው ግንኙነት በምስጢር ስለ ነበረ ይህንን ግንኙነታችንን ለማንም እንዳልናገር አጥብቆ ለመነኝ። ከእርሱ ጋር ብቻ ሳይሆን ከማንኛውም ሰው ጋር ያለኝ ግንኙነት በምስጢር እንዲሆን ጠየቀኝ። እኔም እርሱ ያለውን እንደማደርግ አረጋግጬለት በኃይሉን እምቀርበው በትህትና እንደሚሆን ነገርኩት። ደመረ በዚህ ንግግሬ እጅግ ተደስቶ በጥድፊያ ተለይቶኝ ሄደ። መገለል ቀላል አይደለም። በአንድ ወቅት ከብዙሃን ጋር ሆኖ ወዲያው ከማንኛውም ሰው ግንኙነት መታገድ እጅግ ከባድ ነው። ወርቅዬ ከጎኔ አልተለየም ነበር። በዚያ ቀንም ቢሆን ቤትሽን ልይልሽ ብሎኝ አብረን ጉዞ ጀመርን። እየተጓዝን እያለን የሆነ ሰው ከኋላ ይጠረዋል። እርሱም ዞር ብሎ ካየው በኋላ ሊያናግረው ወደ ኋላ ይመለሳል። እኔ ደግሞ ቆሜ መጠበቅ ጀመርኩ። ትንሽ ቆይቶ ፊቱን በሀዘን ከስክሶ ወደ እኔ መጣ ሰውዬውም እየተከተለው ከእኔ ጋር እንዳይሄድ ያስጠነቅቀው ነበር። በዚያን ጊዜ ቤተ ክርስትያኗ እኔን አግልላኝ የነበረ ቢሆንም ወርቅዬ ግን ሚስጢሩን አላወቀም ነበር። የሆኖ ሆኖ ወርቅዬ አብሮኝ ወደ ቤት መጣ። ከእኔ ጋር በመሆኑ ወርቅዬን ያስፈራሩት ይመስለኛል። እቤት ከደረስን በኋላ እግዚአብሔር እንዳይጥለኝና ጥበቃው እንዳይለየኝ ፀለየልኝ። የእግዚአብሔርንም ፊት እንድፈልግ መከረኝ፤ አበረታታኝ። ነገሩ የውጊያ ያክል ነው፤ መንፈሳዊ ውጊያ። ውስጤን ከበደኝ። ጌታ ሆይ እባክህ ጠብቀኝ፣ እባክህ ምራኝ።
መስከረም 29, 1994
እንደገና ተመልሼ ወደ ተከራየነው ቤት ተመልሼ ሄድኩ። አሁን ቁልፎቹንም ስለአገኘሁ ከፋፍቼ ክፈሎቹን ከቃኘሁ በኋላ ቆልፌ ስመለስ ለ13 ዓመታት ሆሳኢና ታስተምር የነበረ ጄሚ ከምትባል ሴት ጋር ተገናኘሁ። ከዚያም እሁድና ቅዳሜ አብረን ለማሳለፍ ተቀጣጥረን ተለያየን።
መስከረም 30, 1994
አሁን ወደ ተከራየሁት ቤት ገብቻለሁ። እናም በቤት ውስጥ ነኝ። በጣም ደስ አለኝ። ጌታ በእውነት ባርኮኛል። የመጀመሪያ ቀኔን በዚህ ቤት ማሳለፌ ነው። ቤቱን ለማፅዳት ብዙ ሰርቻለሁ። የቤት እቃዎችን፣ የመኝታ እቃዎችን ስገዛ ታደሰ እጅግ ረድቶኛል። በሚቀጥለው ቀን ደግሞ ብዙ የጽዳት እቃዎችን እገዛለሁ።
ጥቅምት 1, 1994
ፍፁምና ወርቅዬ ከጎበኙኝ በኋላ በሰጡኝ አስተያየት መሰረት “ያለሽው በጣም ሩቅ ነው። ከክርስቶስ ቤተ ክርትያን አጠገብ መኖር ነበረብሽ” አሉኝ። ይህ አስተያየታቸው በጣም አስፈራኝ። ጌታ ሆይ ስህተት ሰርቼ ይሆን? እባክህ አስተካክለኝ ብዬ ተለማመንኩት።
ጥቅምት 2, 1994
እንደገና ቤት ሊያከራዩኝ ከማናጀሩ ጋር ለመወያየት ወደ መካኒሳ ተጠራሁ። ነገር ግን ወርቅዬ ያለሁበት ድረስ መጥቶ እዚሁ መኖር አለብሽ በማለት ሌላ ሀሳብ አቀረበ፤ አበረታታኝም። እኔም ተስማምቼ የማፅዳቱን ስራ ቀጠልኩ። ትንሽ ቆይቶ ደግሞ ፍፁምና ታደሰ ጋር ሌላ ሀሳብ ይዘው መጡ። ከክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ራቅ ብለሽ መኖር አለብሽ። ሌላ ቦታ መፈለግ አለብሽ የሚለውን ሀሳብ አመጡ። ወርቅዬ እና አበበም እንደገና በመምጣት ይህንኑ ሀሳብ አፀኑ። ከክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ርቀሽ መኖር አለብሽ አሉ። አሁን ሌላ ቤት የመፈለጉን ስራ ለወርቅዬ ተሰጠ። እኔ በበኩሌ ሁሉንም ለሀያሉ እግዚአብሔር አሳልፌ ሰጠሁ። ከበኃይሉ ጋር ያለን ግንኙነት በተመለከተ የሆነ መልካም ነገር ሊከሰት ነው። ምናልባትም ሁሉም ሰው የተለየ ነገር አለመኖሩንና ነገሮች ወደ ነበረበት ጤናማ ግንኙነት መኖሩን ይረዱ የሆናል። በዚህም መሰረት እዚህ መኖር እንድችል ሁኔታችን ማመቻቸቴ ነበር። ይህ ነገር የሆንልኝ ዘንድ የእግዚአብሔርን ፊት በፀሎት እፈልግ ነበር። አንተ ምን ሊከሰት እንደሚችል በትክክል ታውቃለህ። እባክህ ጌታ ሆይ ጥፋት ሰርቼ፣ ከፈቃድህ ውጭ ሄጄ እንደሆነ ይቅር በለኝ፤ አካሄዴንም አስተካክልልኝ። በመንገዴ ሁሉ ምራኝ። አባት ሆይ ለፀሎቴ መልስ ስለ ሰጠኸኝ አመሰግንሃለሁ። ትመራኝ ዘንድ ሁል ጊዜ ወደ አንተ እመለከታለሁ፤ በአንተም ላይ እደገፋለሁ።
ጥቅምት 3, 1994
ለበኃይሉ ያደረኩት ፀሎት “”በሰማይ የምትኖር አምላኬ ሆይ የተወደደ ወንድሜ የሆነውን የበኃይሉን ጉዳይ ይዤ በአንተ በቅዱስ አባቴ ፊት እቀርባለሁ። እባክህ እንዲፀጸት አድርግ። እባክህ ልቡን ንካው። እባክህ፣ እባክህ፣ እባክህ ስለሚሰራው መልካም ያልሆነ ስራ ሀፍረት እንዲሰማው ንሰሃ እንዲገባ አድርግ። በመንግስት ታላቅ ሊሆን የሚወድ ሁሉ የሁሉ አገልጋይ መሆን እንዳለበት አሳስበው። እባክህ የሚኖረውን የግብዝነት ኑሮ እንዲያስተውል አድርግ። እባክህ አምላኬ ወደ አንተ እስኪመለስ ድረስ ለስቃይ ዳርገው። ትሁት አድርገው። ለራሱ ክብር የሚያሮጠውን ከንቱ ምኞት ከላዩ አንሳ። የትኛውንም ዋጋ ቢያስከፍለውም ወደ አንተ እንዲመለስ አድርገው። ስለ አደረሰብኝ ክፉ ነገርና መጥፎ አያያዙ ይቅር ብዬዋለሁ። እኔ በክርስቶስ ፍቅር እወደዋለሁ። ነብሱን ትድን ዘንድ ፍቅርህን አሳየው። እባክህ ጌታዬ በመንፈስህ ንካው። አባቴ እግዚአብሔር ሆይ በጌታ በኢየሱስ ስም ንካው። ከአመፃ መንገዱ እንዲመለስ ትሁት አድርገው። ስለ ስምህና ስለ ክብርህ ስትል ከልቡ ውስጥ ያለውን የማታለል መንፈስ ከውስጡ አውጣ። አንተ በምትፈልገው መንገድ ቅረበው በፍቅርህ ንካው። ከእርሱ ጋር የነበረኝን አብሮነት መልስ። አብሮነታችንም ከክፋት፣ ከምቀኝነት ከአመፃ እና ንዴት በፀዳ ሁኔታ እንዲሆን አድርገው። ይቅርታህንም አሳየው። እርሱም ታማኝና እውነተኛ ሰው መሆን እንዴት እንደሚችል አሳየው። አምላኬ እባክህ፣ እባክህ፣ እባክህ የምወደውን ወንድሜን በኃይሉን በመንፈስህ እንድትነካው እለምነሃለሁ። ሀጥያቱን በፊቱ እንዲመለከት አድርገው። ስለ ሀጥያቱንም እንዲፀፀት አድርገው። በአንተ ሁሉ ነገር ይቻላልና እባክህ፣ እባክህ፣ እባክህ ልቡን ወደ እውነተኛ መንገድ ቀይረው። “”
ጥቅምት 4, 1994
ወርቅዬ ቤት የማፈላለጉን ነገር ቀጥሎበታል። ፈልጎ ፈልጎ ከክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ግቢ ራቅ ካለ ቦታ አገኘልኝ። በፈለኩበት በመካኒሳ ውስጥ ለመኖር እድለኛ ልሆን አልቻልኩም። ይህ አዲሱ ቦታ መካኒሳ አከባቢ ከመኖር ጋር ሲነፃፀር በማንኛውም መልኩ ውድ ነው።
ጥቅምት 5 , 1994
በብቸኝነቴ ምክንያት ግራ ተጋባሁ። በዚህን እለት ጠዋት ተነስቼ ከገብረ ማሪያም ጋር ተነጋገርኩ። እርሱም ሁኔታዬን ተረድቶ ኖሮ ከእርሱ እና ከቤተሰቡ ጋር ለአምልኮ ወደ ክርስቶስ ቤተ ክርስትያን እንድሄድ አበረታታኝ። እዚያም ስንደርስ የግቢው ጥበቃዎች እንዳልገባ ከለከሉኝ። በዚህ ምክንያት ገብረ ማሪያም ቀኑን ሙሉ ከእኔ ጋር ዋለ። በምሳ ሰዓት ወርቅዬ እና ልጁ ያፌት ለምሳ ተቀላቀሉን። ቀጥሎም ከገብረ ማሪያም ጋር ወደ ቤቱ ሄደን ከቤተሰቡ ጋር ዋልን። በሚቀጥለው ቀን የኪራይ ቤቱን ውል የምንፈፅምበት ቀን ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። በመጨረሻም ማታ አካባቢ ገብረ ማሪያምና ወርቅዬ ወደ ቤቴ አደረሱኝ። በቤቴ ሆነን ከክርስቶስ ቤተ ክርስትያን አጠገብ መኖር የምችልበትን ሁኔታ አንስተን ብዙ ተወያየን።
ጥቅምት 6, 1994
ዛሬ ወርቅዬና ገብረ ማርያም ቤት አገኙልኝ። ይህ ደግሞ እጅግ ታላቅ ነገር ነው። የቤት ቁሳቁሶችም እንዲሁ ፈልገውልኛል። ወደ ውጤት የመቅረብ ያክል ተሰማኝ። እግዚአብሔር ሆይ ታላቅ ነህ። ለፀሎታችን መልስ ሰጥተሃል።ይህንን ቤት በማግኘታችን ፍፁምና ገነት እጅግ ተደስተዋል። አሁን በነፃነት መንቀሳቀስ እንችላለን።
ጥቅምት 7, 1994
የዛን ቀን ከገብረ ማሪያም ጋር ሁነን ቤቱን በሚገባ ስናጠና ቆየን። በጣም ተስማሚ ቤት ነው። መጠቀሚያ ቁሳቁሶች እንደ ሳህኖች፣ ብርጭቆዋች፣ ቴሌቪዥን ወዘተ ያሟላ ቤት ነው። ቡታ የሚባሉ ሽማግሌ ከቤቱ በጀርባ በኩል ይኖራሉ። የቤቱም ባለቤት እርሳቸው ናቸው። ስራችን መስማት ለተሳናቸው ወገኖች በመሆኑ የቤቱንም ኪራይ ዝቅ አድርገውልናል። እናም ሁላችን ተደስተናል። አምላኬ ሆይ ከሁሉም አቅጣጫ ድንቅ በሆና ሁኔታ በሮችን ከፍተህልኛል። በኃይሉ ገብረ ማሪያምን ስልክ ደውሎ ስለ እኔ ሁኔታ ጠይቆት ነበር። ከ30 ደቂቃ በላይ ነበር የተነጋገሩት። ይህ ለገብረ ማሪያም ያልተለመደ ነበር። ምክንያቱም በኃይሉ ከሰራተኞች ጋር የዚህን ያክል ረዘም ላለ ጊዜ የስልክ ንግግር አያደርግም ነበርና። ለጊዜውም ቢሆን በኃይሉ ተስፋ የቆረጠ ይመስላል። ምክንያቱም ብዙ ሰዎች ከእኔ ጋር መልካም ግንኙነት ስለ ነበራቸው ብቻዬን ሊያስቀረኝ የነበረው ምኞቱ ያልተሳካለት መሰለው። ፈርቶኝም ስለነበር ተጨማሪ ሰይጣናዊ እርምጃዎችን መውሰድ ስለ መጀመሩ ምንም ጥርጥር የለኝም። እግዚአብሄር ሆይ እባክህን ጥበቃህን አጠናክርልኝ።
ጥቅምት 8, 1994
ይህ ቀን በአዲሱ ቤቴ የመጀመሪያ ቀን ነው። የወርቅዬ ልጅ በሰራተኝነት እንድታገለግለኝ እፈልግ ነበር። ነገር ግን ወርቅዬ ይፈቅድ እንደሆነ እርግጠኛ አይደለሁም። ምናልባት ይቃወመኝ ይሆናል። በመጨረሻ ግን ከእኔ ጋር እንድትሆን ተወሰነ። ይህች ልጅ ሕፃን ልጅ አላት። ነገር ግን እኔ እምፈልገው ሙሉ ጊዜዋን በማዕድ ቤት ስራዬ እንጂ ከህፃን ልጇ ጋር እንድታሳልፍ አልፈልግም ነበር። አምላኬ ሆይ ምናልባት ራሴን ወድጄ ይሆን? ትንሹ ህፃን ልጅ እጅግ ያለቅሳል። ጌታ ሆይ ለእንዳንዷ ጥቃቅን ነገር ይቅርታህንና ምህረትህን እፈልጋለሁ። በኢትዮጵያ ውስጥ በሚኖረኝ ቆይታ ሁሉ ሰዎችን መርዳት እንድችል አግዘኝ። ጌታ ሆይ በኃይሉን በመንፈስህ እድትነካው እፀልያለሁ። እባክህ ጌታ ሆይ ይህ ሰው እንዲፀፀትና ስለ አንተ ሲል ዝቅ እንዲል አድርገው። እኔንም በማንኛውም ነገር በአግባቡ እንዳስብና እንድፀልይ እርዳኝ። ጥበብ እንድትሰጠኝ በእጅጉ እፈልጋለሁ።
ጥቅምት 11, 1994
ምንም እንኳን ብዙ ነገሮች የተለዋወጡ ቢሆንም ይህንን ማስታወሻ መጸፍ ከጀመርኩ ጥቂት ቀናት አልፏል። ብዙ ጊዜዬን የማሳልፈው ደግሞ ከገብረ ማሪያምና ከወርቅዬ ጋር ነበር። ሁሉቱም ሰዎች ይጠነቀቁልኝ ነበር። የወርቅዬ ሴት ልጅ 60 የአሜሪካን ዶላር በወር እየተከፈላት በወጥ ቤት ስራ ታገለግለኝ ነበር። በዚህ ቀን ከሰዓት በኋላ ፍፁምና ታደሰ ጋር ሆነን ስብሰባ ነበረን። በዚህ ስብሰባ የተወያየንበት ጉዳይ ለመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት ስለሚያስፈልጉ መጽሐፍት ነበር። ለዚህ ጉዳይ ያገለግላሉ ተብለው የተለዩትን መጽሐፍት እንዳገኙ ነገሩኝ። በዚህ ረገድ አንድ ነገረ ተሳክቷል ማለት ነው። በሚቀጥለው ቀን አርብ እንዲሁ የትምህርት ቀናት በስንት ሰዓት መጀመር እንዳለበት ከተወያያን በኋላ የስራ ሰዓት ብለን የወሰነው ሰኞ ከጥዋቱ 3፡30 – 6፡00፣ ረቡዕ ከ4፡00-6፡00 ቅዳሜ ደግሞ ከ8፡00 – 12፡00 እንዲሆን ወስነን ተለያየን። ለእነዚህ ሁለቱ አስጠኚዎች ክፍያ ጉዳይ የተለያዩ ሀሳቦችን አንስተን ከተወያየን በኋላ ወርሃዊ ክፍያቸው 100 ዶላር እንዲሆን ተስማምተናል። ገብረ ማሪያም በሁሉም ጉዳዮቼ ውስጥ እንደ ጠበቃም ሆኖ ይሳተፍ ነበር። በእውነት በሚያደርጋቸው ነገሮች ሁሉ እጅግ ደስተኛ ነበርኩ። በሁሉም ህግ ነክ ጉዳዮች ሁሉ እንደ ጠበቃ ሆኖ ለመቆም ይፈልግ ነበር። ለዚህ አገልግሎት እከፍለሃለሁ ብዬ ቃል የገባሁለት ነገር የለም። ነገር ግን እግዚአብሔር በሚያስፈልገው ሁሉ እንዲባርከው እና እንዲሰጠው እንደምፀልይለት ቃል ገብቼለታለሁ። እርሱን በተመለከተ ትንሽ ግራ ተጋብቻለሁ። እግዚአብሔር አባቴ ሆይ እባከህ መረዳትን ስጠኝ።
በዚህ ቀን ከወርቅዬና ቤተሰቡ ጋር ሆኜ በአጎቱ ልጅ ሰርግ ላይ ለመታደም ሄድን። በዚያ ሰርግ ላይ ብዙ ሕዝብ ነበር። ድንኳኑ በሰዎች ተሞልቷል። የሰርጉ ስነ ስርዓት እጅግ ደማቅ ነበር። በኋላ ደግሞ መስማት የተሳናቸው ሰዎች ወደሚያመልኩበት የመጥምቃዊያን ቤተ ክርስትያን ሄድኩ። ነፃ እና ተወዳጅ ቦታ ነው። ይህ መስማት የተሳናቸው ማህበረሰብ ለእኔ ተገቢ ቦታ እንደሆነ ከልቤ አምናለሁ። ከዚያም ከቤተ ክርስትያኑ መሪዎች ጋር ሆነን ምሳ ለመብላት ወደ ፍፁም ቤት ሄድን። በዚያም መልካም ጊዜ አሳለፍን። በመጨረሻም እቤቴ ስደርስ ደግሞ ገብረ ማሪያም ቀደም ብሎ ደውሎልኝ ስለነበረ እንደገና ደውዬለት ወዲያው ወደ ቤት መጣ። በሰፈር እያለሁ ኢንተርኔት ለማግኘት እፈልግ ነበርና አገኘሁ። እንደ ፍላጎቴ ሁሉ አምላክ በሰዓቱ ሰጠኝ። እናም ከባለቤቴ ከኒል ጥሩ የኢሜይል መልእክት ደረሰኝ። በፍቅር እና በሚያበረታታ ሀሳብ የተሞላ ነው። አምላኬ ሆይ ስለ ባለቤቴ ኒል እጅግ እመሰግንሃለሁ።
ጥቅምት 15, 1994
ቀናቶች እያለፉ ነው። ጥቂት በጥቂት የሚከናወኑ ነገሮችም እንዲሁ እየተከናወኑ ናቸው። እኔም በየዕለቱ መመዝገብ የሚገባኝ ነገሮች ከፃፍኩኝ አያሌ ቀኖች አልፏል። በመሰረቱ በዚህ ሳምንት የድጋፍ ጥናት ለመጀመር ሁሉንም ዝግጅቶች ጨርሰናል። የጥቁር ሰሌዳም ያገኘነው ዛሬ ነው። ይህንንም የሰጡን ታደሰና ብርሃኑ ናቸው። በአለም አቀፍ የወንጌል ኮሌጅ ውስጥ የሴቶችን የመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት ልንጀምር አሰብን። የመጽሐፍ ቅዱሱ ጥናት የምንጀምረው ስለ ሳውል ይሆናል። ይህን የትምህርት ክፍለ ጊዜ ከመጀመራችን ትንሽ ቀደም ብሎ የቤተ ክርስትያኑ መሪዎች ስለ እኔ ብዙ ጥያቄዎችን ያቀርቡልኝ ነበር። ይህ ሁሉ ጥያቄ ለምን? ብዬ እጠይቃቸው ነበር። ስለ ራሴ የነበረኝም ግንዛቤ የተሳሳተ መሰለኝ። ራሴንም ትልቅ ቦታ ያስቀመጥኩ መሰለኝ። ስለዚህም በሰዎች ላይ ከነበረኝ ቅሬታ ባሻገር ስለራሴም እፍረት ይሰማኝ ነበር። ቀኑን ሙሉ ደስተኛ አልነበርኩም። ጌታ ሆይ እባክህ ትንሽ ትንሽ መናገር፣ ብዙ ማዳመጥ እንድችል ጥበብ ስጠኝ። ራሴንም ማእከል አድርጌ እንዳልንቀሳቀስ እርዳኝ።
ዛሬ ከአብርሃም ረዳት ጋር ለመገናኘት አጋጣሚ አግኝቻለሁ። አብርሃም በኮሌጁ ውስጥ በወንጌላዊያንና በሚስቶች ጉዳይ ላይ እየሰራ ነው። በጣምም ያስደስታቸው ነበር። በዚህ እጅግ የተካና ሰው ነው። ነገር ግን መስማት በተሳናቸው ወገኖች ላይ ለምን እንደማይሰራ ጥያቄ ይሆንብኛል። ይህም መስማት በተሳናቸው ወገኖች አገልግሎት ላይ ትልቅ ጥርጣሬ እንዲኖረኝ አድርጓል። ለነገሩ ምንም ልፈርድ አልሻም፤ ግን ስለ እነርሱ እጨነቃለሁ። አመሻሽ ላይ ወርቅዬ እና ገብረ ማሪያም ከእኔ ጋር ነበሩ። ለእራትም አብረን ነበርን። ወርቅዬ በሳንባ ምች እየተሰቃየ ስለመሰለኝ ላሳክመው ወደ ሀኪም ቤት ወሰድኩት። ነገር ግን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይግባውና ከዚህ በሽታ ነፃ ሆኖ ተገኘ። እናም የምርመራ ውጤት ከሰማን በኋላ በጋራ ሆነን በእኔና በበኃይሉ መካከል ስላለው ጉዳይ ፀልየን ተለያየን። እኔም ጌታ በሰጠኝ ፀጋ እና ባስጀመረኝ ጉዳይ ወደ ፊት መግፋት እንዳለብኝ ተሰማኝ። ከዚህ ቀደም ሲል ስለ አገልግሎቱ ጌታ የከፈተልኝን አጋጣሚዎች አለመጠቀሜን ማሰላሰሉ ማቆም እንዳለብኝ ይሰማኛል። ምክንያቱም ጉልበቴ እና አቅሜ ሁሉ ከክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ጋር ወዳለው ችግር እየወሰደኝ ስለሆነ ነው። ስለ ወርቅዬና ስለ ገብረ ማሪያም አምላኬን አመሰግነዋለሁ። ምክንያቱም እነዚህ ሁለቱ ሰዎች በበኃይሉና በደመረ ፈንታ ተተክተውልኛልና። በዚህ አስፈላጊ በሆነ ጊዜ እነርሱን የሰጠኝ እግዚአብሔር ነው። ስለሆነም ሙሉ አቅሜን መስማት ለተሳናቸው ወገኖች አገልግሎት ላይ ማድረግ አለብኝ፤ ፍቅርን ሁሉ ላሳያቸው የገባኛል።
ጥቅምት 17, 1994
ዛሬ ገብረ ማሪያምና በኃይሉ በስልክ ስለ እኔ ለሰዓታት ያወሩ ነበር። ምን እንደ ተነጋገሩ ግን ሁሉንም ማወቅ አልቻልኩም። ምናልባት ነገ የተነጋገሩበትን ጉዳይ ሁሉንም አውቃለሁ ብዬ አስባለሁ። በዚህን ወቅት እጅግ እየጎዳኝ ያለው የደመረ ጉዳይ ነው። ደመረ በሚስጥር ከእኔ ጋር መልካም ግንኙነት ነበረው። እናም ብዙ ይዋሸኝ ነበር። በኃይሉ ግን ስለ ግንኙነታችም ምንም ፍንጭ የለውም። ሁሉም ነገሮች ግልፅ ሲሆኑ ደመረ እንደሚክደኝ ይሰማኛል። ምን ማድረግ አለብኝ? በምስጢር ከእኔ ጋር ያለውን አብሮነት ላጋልጥ ወይንስ ዝም ልበል? ዝም ብል ይሻላኛል። ትክክለኛ ማንነቴም ይህ ነው። ደመረ እንደ በግ ሊያርደኝ የሚያደርገውን ስራ ዝም ብዬ ማየቱ ይሻለኛል። እስኪ ያድርገው። ቶምሶን ሲመጣ ለነገሩ እንደሚመጣ ዛሬ አጣርቻለሁ ሁኔታው ምን መልክ እንደሚይዝ አያለሁ፡፤ የእነ ቶምሶን በዚህ አከባቢ መገኘት እነዚህን ችግሮች ይፈታል ወይንስ ችግሮችን ያባብሳል? እስኪ ልይ። አምላኬ ሆይ እባክህ ጥበብ ስጠኝ። እስኪ ለመታረድ የሚነዳ በግ ዝም ማለት እንዴት እንደሚቻል እባክህ አስተምረኝ። ጌታዬ ሆይ ምንም ሀጢያት ሳይኖርብህ ያለምንም ተቃውሞ ወደ መስቀል ተወስደሃል። በአንተ በመታመን የደመረን ሴራ በዝምታ ማለፍ እንድችል እርዳኝ። በኃይሉና ደመረ በፈጠሩብኝ በዚህ አስጨናቂ ጊዜ ውስጥ እንዳልፍ ስታመጣኝ ክብር ይሰማኛል። የእነዚህ ሰዎች እጅግ ክፉ የሆነ ባህርይ መመልከቱ በራሱ እጅግ ይጎዳል። አንድ ወቅት እንደ ቤተሰብ የሆኑኝ ሰዎች ሲያታልሉኝ፣ ሲዝቱብኝ፣ ሲክዱኝ እና ችላ ሲሉኝ ማየት እጅግ ጎድቶኛል።
ለዚያውም በሀገራቸው ውስጥ ብቸኛ ሆኜ ከልቤ ፍቅሬን እያሳየኋቸው ይህንን ሁሉ ሲፈፅሙብኝ ማየት እጅግ ጎድቶኛል። እነዚህ ሰዎች ስለሚፈፀምብኝ ድርጊት አንዱንም መረዳት አልችልም። ነገር ግን አምላኬ ሆይ ለዚህ ሁሉ አመሰግንሃለሁ። ከሚያደርሱብኝ ግፍ ሁሉ ጥሩ ትምህርት እንድማር እርዳኝ። ዛሬ አብርሃምን አይቸዋለሁ። ፓስተር ኦርናልድም አግኝቼው አናግሬው አለሁ። አብርሃም ከምን ጊዜውም የበለጠ ኩራት ተስምቶታል። ሊያየኝም አልፈለገም። ይህንንም ለፓሰተር ኦርላንድ ነግሬዋለሁ። በእኔ መጎዳት መኩራቱን ማቆም እንዳለበት ጠቅሼለታለሁ። በሚሆንብኝ ነገር ላይ ሆኖ ለሚያሳየኝ ፀባይ ሀላፊነት መውሰድ አለበት። የእርሱ ሁኔታ በያንን በእጅጉ አስታውሶኛል። ሁል ጊዜ በሰዎች ላይ በሚያደርሰው ማታለል ምክንያት መስማት ለተሳናቸው መንፈሳዊ ኮሌጅ ተሳታፊ እንዳይሆን ተደርጓል። አብርሃም አሁን የተጠመደበት ጉዳይ ቢኖር ከአውሮፓ የመጡትን ሰዎች እያሳሳቀ እና ለማስደስት እየሞከረ ወደ አሜሪካ ለመውጣት መንገድ እንዲያመቻቹለት ነው። እነርሱ ደግሞ የምልክት ቋንቋ ስለማይችሉ ከብዙዎች ርቋል ሊሳካለትም አልቻለም። ምናልባት አብርሃም የክፋት እይታውን በእኔ ላይ ሊያነጣጥር ይመስለኛል። ጌታ ሆይ ስለዚህ ወጣት ልጅ ተጠንቀቅለት፤ ጥበቃህን አብዛለት።
ጥቅምት 19, 1994
ገብረ ማርየም ትላንትና ከበሀይሉ ጋር ያደረጉትን የተራዘመ የስልክ ንግግር ይዘት ስለ ነገረኝ እጅግ ተበሳጭቻለሁ። ዛሬ በፍፁም ደስታኛ አይደለሁም። በሀይሉ እኔን በማጥላላትና የራሱን ክብር በማግዘፍ ብቻኛ ጠቃሚ ሰው መሆኑን በኩራት ይናገራል። በእርግጥ እኔን ለማናገር ጊዜ መውሰድ አይፈልግም። ሶስት ሳምንት አልፏል። ከእርሱ በኩል ምንም አልሰማሁም። ምን አይነት ሰው ነው? በእርግጠኛነት መናገር የምችለው የእግዚአብሔር ሰው አለመሆኑን ነው። አይደለም! ነገር ግን የእግዚአብሔር ሰው ነኝ፣ የእግዚአብሔር ባርያ ነኝ በማለት ለሰው የሚያውጀው እጅግ ብዙ ጊዜ ነው። ከዚህ በተቃራኒ እኔን ለህግ ለማቅረብ እንደሚፈልግ ለገብረ ማሪያም ነግሮታል። ከዚህም ሌላ ደመረ እና ወንድወሰን ለእኔ የሚሰሩ ከሆነ እንደሚያባርራቸው ጭምር ተናግሯል። በእኔ ፕሮግራም ውስጥ ተሳታፊ የሚሆኑትን ተማሪዎችንም እንደሚቀጣ ዝቷል። በአጠቃላይ መስማት ለተሳናቸው የማደርገውን ማንኛውንም በጎ ነገር ሁሉ ሊያወድም ጠንክሮ እንደሚሰራ አስምሮበታል። ይህንን ሁሉ በተራዘመ የስልክ ንግግሩ ውስጥ ለገብረ ማሪያም የነገረው ነው። ጌታ እግዚአብሔር ሆይ ወደ አንተ በተደጋጋሚ ጮህኩ፣ በተደጋጋሚ ተማፀንኩ፣ በተደጋጋሚ ወደ አንተ በለቅሶ ቀረብኩ አሁንም እለምንሃለሁ አባቴ ሆይ እባክህ ስማኝ። መታመኔ በአንተ ነው።አምላኬ አምንሃለሁ ይህ ነገር እንዳይቀጥል አድርግ። በሃይሉን ገስፀው።
እርሱ ሰይጣናዊ መንገድ መርጧል። ሁሌ የስይጣንን ስራ ያከናውናል። መልካም ስራዎችን ማውደምና ማጥፋት ላይ አትኩሯል። እባክህ አምላኬ አንድ ነገር አድርግ። እባክህ ወደ አንተ ሳለቅስ ስማኝ። አባቴ ሆይ መታመኔ በአንተ ነውና እለምንሃለሁ። ወርቅዬ ከለቅሶ ቤት ወደ ቤቱ ሲሄድ እግረ መንገዱን ሊያጽናናኝ መጣ። ገብረ ማሪያምም ከፊልጵስ ዩስ 4፡4-7 እና ቁጥር 13 በመጥቀስ አፅናናኝ። ዛሬ ብዙ ሳለቅስ ነው የዋልኩት። ምን ማለት እችላለሁ? እንባዬ ወዲያው የሚመጣው ለምንድን ነው? ጌታ ሁሉን ይቆጥራል። ሁሉንም በመዝገቡ ያኖራል። ጌታ ሆይ በወርቅዬ እና ገብረ ማሪየም በኩል ስለ አጽናናኸኝ አመሰግንሃለሁ። ለእኔ ያለህ ፍቅር እጅግ ታላቅ በመሆኑ እነዚህን ወዳጆች ላክልኝ። ደመረ እና በሀይሉ ያልሆኑትን ወርቅዬ እና ገብረ ማሪያም ሆነው ስለ ተገኙ አመሰግንሃለሁ። ወርቅዬ እና ገብረ ማሪያም የክርስቶስ ቤተ ክርስትያን አባል ሆነው ሳሉ ፍቅር አሳይተውኛል፣ ተጠንቅቀውልኛል። እግዚአብሔርም የሚፈሩ ሆነው ተገኝተዋል። እግዚአብሔርን የሚፈሩ፣ ሰው አፍቃሪና ሰው በመንከባከብ ቀዳሚ መሆን የነበረባቸው ዋናዎቹ የተባሉት በሀይሉና ደመረ መሆን ነበረባቸው። ነገር ግን ተገላቢጦሽ ሆኗልና አመሰግንሃለሁ። አንተ የምታበረታታና የምታድስ ታላቅ አምላክ ነህ። ታላቅ ምስጋና ይገባሃል። ጌታዬ አመሰግንሃለሁ፣ አመሰግንሃለሁ፣ አመሰግንሃለሁ! ፍፁምም ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ደውሎ አበረታትቶኛል።
ቀጥሎም ነገ ጠዋት ወደ ቢሮው እንድመጣ ከጋበዘኝ በኋላ ገብረ ማሪያምም አብሮኝ እንዲመጣ፤ ይህም የጋራ ፀሎት ለማድረግ መልካም እንደሆነ ነግሮኛል። ዛሬ ቀኑን ያሳለፍኩት ከጽጌ እና አበራሽ ጋር ነው። እነርሱም ሲያጽናኑኝ ነበር ቀኑን ያሳለፉት። ከዚህም ሌላ አብረን ወደ ቤተ ክርስትያን በመሄድ ሁሉንም መስማት የተሳናቸውን ልጆች ጎብኝተናቸዋል። እግዚአብሔር ሆይ ተጨማሪ ጓደኞችን ስለ ሰጠሀኝ አመሰግንሃለሁ። ይህም ፍቅር አይ ዘንድ እንዲሁም አሳይ ዘንድ ነውና አመሰግንሃለሁ። ይህን ያክል በሃይሉ የክርስትያናዊ ፍቅር ጠንቅ ሆኖ ብቅ ቢልም ብዙ መልካም አመታት ነበሩኝ። አምላኬ ሆይ የሰጠኸኝን ፍቅር ሁሉ አውጥቼ ለሰው ሁሉ አሳይ ዘንድ እርዳኝ። በምድር የሰጠሀኝን ስራ እንድፈፅም እርዳኝ። በዘመኔ እንዳከናውን የሰጥሀኝ ስራ ከማከናወን ውጭ ሌላ የሚያስጭነቀኝ ነገር የለም። ለተፈጠርኩለት እና የተለኩበትን ስራ ማከናወን እንድችል እርዳኝ። ሁሉም የሚሆነው በእኔ አይደለም በአንተ ሀይልና ጥበብ ነው። ትላንትና ክፍል ለመጀመር የጥያቄያችን ቀን ነበር። ዛሬ ደግሞ አበበ መጥቶ በሀይሉ እንዳባረረው ነገረኝ። አበበ የመካኒሳ መስማት የተሳናቸው ት/ት ቤት ዳይሬክተር ነበር። ነገር ግን በሀይሉ ያለ አግባብ ገንዘብ ማባከኑን (በሙስና ምክንያት) ለመንግስት ስለ ተናገረ ነበር የተባረረው።
ጥቅምት 20, 1994
ጥቅምት 28 ክፍል ለመጀመር ሲባል ለተማሪዎች የመጀመሪያውን ገለፃ የምንሰጥበት ቀን ነበር። በዚህ ቀን አበበ አበራ ከመካኒሳ መስማት ከተሳናቸው ት/ቤት በሀይሉ እንዳባረረው ነገረኝ። በሃይሉ በአስር የሙስና ጉዳዮች ተወንጅሏል። መንግስትም ይህንን ጉዳይ ይመረምራል። ደመረም በአንድ የሙስና ጉዳይ ተጠያቂ ነህ ተብሏል። በሀይሉ ሁሉንም የተጠየቀበትን ሙስና ወንጀሎች በሙሉ በአበበ ላይ አላዃል። በዚህን ቀን ከፍፁምና ታደሰ ጋር ሙሉ ቀን ያሳለፍን ቢሆንም ተማሪዎች ጥናት የምናስጀምርበትን ቀን ገና አልወሰንንም። ምክንያቱም በሀይሉም የተቻለውን ሁሉ በማድረግ ችግሮችን በእኔ ላይ በመፍጠር ስራዎቼን ለማደናቀፍ ዝቶ ነበርና። በሀይሉ በሚያደርጋቸውና በሚያሳብብኝ ክፉ ሀሳብ ደመቀ እጅግ እንደተናደደ ወርቅዬ መጥቶ ነገረኝ። ይህ የበሀይሉ ስራ ሁሉንም ሰዎች ሊያበሳጭ የሚችል ነው። ጌታ ሆይ የወርቅዬን ልብ እንደ ነካህ ሁሉ እባክህ ከመርፈዱ በፊት የበሃይሉንና የጆን ኢድን ልብ እንዲሁ ንካቸው፤ ወደ መልካምም ሀሳብ መልሳቸው።
ጥቅምት 1, 1994
ዛሬ መልካም ቀን ነው። እግዚአብሔር ፀሎቴን እንደመለሰልኝ ተሰምቶኛል። በሀይሉ መልካም ነገሮቼን ሊያቆም አይችልም። በዚህ ጉዳይ ላይ ጌታ አቅድ አለው። ይህን በተመለከተ ፍፁም ብዙ ነገሮችን ገልፆ ነግሮኛል። በእርግጥ ፍፁም የነገረኝ ከአብረሃም ታሪክ ጋር የሚመሳሰል ነው። አብረሃም በእምነት እግዚአብሔርን ታዘዘ፤ ዘመዶቹንና አገሩንም ትቶ ወደ ማያውቀው ሀገር ሄደ። ነገር ግን ወንድሙ ሎጥ አብሮት ነበር። ሎጥም መንገዱን እስኪመርጥ ድረስ እግዚአብሔር ምንም አልተናገረም ነበር። እግዚአብሔር ለአብርሃም ያለው እቅድ እንዳይፈፀም ሎጥ በመካከል ነበር። በኢትዮጵያ ውስጥ ካለችው የክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ጋር ያለኝም ግንኙነት እንዲሁ መልካም ነገሮች እንዳልፈፅም በማድረግ ላይ ነው። አሁን ወደ ኢትዮጵያ ከመጣሁ አንድ ወር ሆኖኛል። ነገር ግን የሰራሁት በጣም ጥቂቱን ነው። ለምን ቢባል በበሃይሉ ምክንያት ነው። ስለዚህም እኔ እግዚአብሔር ለላከኝ ስራ ከእነዚህ ሰዎች መለየት አለብኝ። በመሆኑም መስማት የተሳናቸውን ማስጠናቱን ስራ ተለይቼ መስራት ለመጀመር ዝግጅቱ ተጠናቋል። ይህ የእግዚአብሔር እቅድ ነው። የክርስቶስ ቤተ ክርስትያን በጉዳዬ ውስጥ ጣልቃ መግባት የለባቸውም፤ እግዚአብሔርም አይፈቅድላቸውም። እነርሱ የራሳቸውን እኔም የእግዚአብሔርን ዕቅድ ልፈፅም። ይህን ስራ ለመጀመር በመጥምቃዊያን መስማት በተሳናቸው አጠገብ አነስተኛ ክፍል ፈልገን እዚያ ለመጀመር ወስነናል። ለስራውም አንድ ሀላፊ ስለሚመደብ በእኔ ላይ ሰበብ የሚመጣ አይመስለኝም።ጌታ ሆይ ዝም ብዬ መስማት ለተሳናቸው በረከት ለመሆን የልቤ መሻት ይሄ ነው። በጠዋት ተነስቼ አልሰራ ብሎ የነበረው ቴሌቪዥን እንዲሰራልኝ ቁጭ ብዬ ፀሎት አደረግሁ። ቴሌቪዥኑ ወዲያው መስራት ጀመረ። ክብር ለጌታ ይሁን፤ አመሰግንሃለሁ አምላኬ።
ጥቅምት 22, 1994
በጠዋት ተነስቼ ገብረ ማሪያምን ለማናገር ሄድኩ። ገብረ ማሪያም አንድ እግሩ ከእኔ ጋር ነው። ሌላው እግሩ ደግሞ ከክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ጋር ነው። ስለዚህ ፍፁም እንደ መከረኝ ሁሉ ሁለት ቦታ መሆኑን ማቆም እንዳለበት ልነግረው ወሰንኩ። ምክንያቱም ሁለቱም አብረው ሊሄዱ የማይችሉ ነገሮች ናቸው። ደግሞም ጌታ ከክርስቶስ ቤተ ክርስትያን አጠገብ ቤት ሰጥቶኝ ነበር። ነገር ግን ለቀነው ሄድን። አሁንም እግዚአብሔር ሌላ ጥሩ ቤት ሰጥቶናል። ስራችንን በትክክል መጀመር እንችላለን። እንደ ገብረ ማሪያም ካሉት ከክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ሰዎች ጋር በግልፅ ተነጋግሮ ሚና እንዲለዩ በማድረግ ላይ ፍፁም የመከረኝ ትክክል ነው። እናም ምክንያት ስላልነበረው ወዲያው አቆመ። ሄኖክም መልሶ ቤቱን ለጥር እና ለየካቲት እንደገና እንደሚያከራየኝ ነገረኝ። ይህ ደግሞ እጅግ አስፈላጊ ነበር። አምናለሁ የጌታም እቅድ ነው። ነገር ግን ፍፁም አንድ ክፍል አለው ህንፃ የሚያገኝ ከሆነ ተመራጭ ይሆናል። የሆነ ሆኖ ፍፁም ወደሚከራየው ቤት ለመሄድ ፈቃደኛ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋሉ። እልፍነሽ ተመልሳ እንድትመጣ እፈልጋለሁ ምናልባት ባፈናም ብትሆን። እነዚህ ሴቶች ከበፊት ጊዜ ጀምሮ ስለማውቃቸው በጣም ያስፈልጉኛል
ጥቅምት 26, 1994
ዛሬም እንደ በፊቱ ሁሉ ቅር ቅር የሚለኝ ቢሆንም መልካም የሆኑ ነገሮች መከናወናቸውን ቀጥለዋል። እኔም ሁኔታዎችን በማስታወሻዬ ላይ ማስፈርን ማቆም የለብኝም። አንድ ቅዳሜ ቀን ፍፁም ወርነር የሚባል ጀርመናዊ ይዞልኝ መጣ። እኚህ ሰው የ62 ዓመት አዛውንት ናቸው። ወርነር በዓመት አንዴ ወደ ኢትዮጵያ እየመጣ ደሃ ለሆኑ መስማት ለተሳናቸው የመፅሐፍ ቅዱስና የገንዘብ ስጦታና ድጋፍ ያደርጋል። ወደ እኔ ከመጡበት ቀን ጀምሮ በቤቴ መኖር ጀምሯል። የማስጠናቱ ስራ እሁድ ቀን በቤቴ ማካሄድ እንችል እንደ ሆነ ፍፁም ጠየቀኝ እሺ ብየ እንደዚያም ሆነ
ቅዳሜ ጠዋት ግን ወርቅዬንና ጄይላንን አግቼያቸው ነበር። በዚህን ቀን ከወርቅዬ ጋር ጥሩ ቆይታ ነበር። ገብረ ማሪያም እኔን ለጠላቶቼ ይሰልለኝ ስለመሰለኝ ይህንን ጉዳይ ለወርቅዬ አወራሁት። በዚሁ ምክንያት አስፈላጊ ሲሆን በቤቱ ለመደበቅ ይፈቅድልኝ እንደ ሆነ ጠየኩት። ገብረ ማሪያም ሁል ጊዜ እየመጣ ምን እንደምስራ፣ ምን እንዳለኝ፣ ከማን ጋር እንደነበርኩ፣ የት እንደ ነበርኩ ይጠይቀኛል። ይህ ስራው እረፍት ነስቶኛል። ወርቅዬ ደግሞ ይህ የገብረ ማሪያም ባሕሪይው እንደሆነና ለጉዳት የሚሰጥ እንዳልሆነ ነገረኝ። ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ ከአበበ አበራ ጋር ተገናኝተን ቶምሶንን እሁድ በቤተ ክርስቲያን ጠርቶት እንዲያገናኘን ነገርኩት። እሺ ይለው እንደሆነ በኢሜል እንዲያሳውቀኝ ኢሜሌን ሰጠሁት። አበበም እሺ አለኝ፤ ቶምፕሶንም እንደሚመጣ ነገረኝ። እኔም ይህ ሰው ፃድቅ እንዲሆንና ለጠራሁት ጉዳይ ምቹ እንዲሆን ወደ እግዚአብሄረር ፀሎት አደረስኩ። ሰኞ ጠዋት ፍፁም ደውሎልኝ ከስዎርድ (Sword) መስማት የተሳናቸው ኮሌጅ ፈተና እንደ ተዘጋጀልኝ ነገረኝ። እኔም ጠዋት እንደምገኝ ነግሬው ሰውነቴን ከታጠብኩ በኋላ ለፈተናዬ ማጥናት ጀመርኩ።
ጥቅምት 27, 1994
የክርስቶስ ቤተ ክርስትያንን ለዋርነር ለማሳየት አብረን ሄድን። ሰዓቱም ተማሪዎች የሚወጡበት ሰዓት ነበር። መንገድ ላይ እየሄድን ስለ ራሴ እያጫወትኩት ነበር። ሁሉም ሰው በእኔ ላይ ስለላ ያካሂዳል። በሕይወቴ ብዙ ድካም ሳይኖርብኝ አይቀርም ካልኩት በኋላ በውስጤ ወደ እግዚአብሔር ፀለይኩ እንዲህ በማለት፤ እግዚአብሔር ሆይ ስህተቶቼ ሁሉ ስህተት ሆነው በፊትህ ከታዩ እባክህ ሁሉንም ስህተቶቼን ሸፍንልኝ፤ ይቅርም በለኝ። ወደ ቤተ ክርስትያኑ እንደ ደረስን ወደ ግቢ ገባን። ዋርነር ወደ በር ሄደ። እኔ ደግሞ ራቅ ብዬ ቆሜያለሁ። ዋርነርም በመግቢያው ላይ ከአንድ መስማት ከተሳነው ተማሪ ጋር ይነጋገር ነበር።እኔ በቆምኩበት አካባቢ የግቢ ካፌ ነበር። የሚያልፉ ተማርዎች ብዙዎቹ ወደ እኔ መጥተው ሊያነጋግሩኝ ይፈልጉ ነበር። እኔም አያቸው ነበር። ወደ ካፌው ዞር ስል በፊት ተማሪያችን የነበረች መስማት የተሳናትን አልማዝን አየኋት። አልማዝ በካፌው ውስጥ በአስተናጋጅነት ታገለግላለች። በቀጥታ ወደ ካፌው ሄድኩና ቦታ ይዤ ሻይና ኬክ አዘዝኩ። የቤተ ክርስትያኑ የነበረ ነጩ መኪና አልፎን ወደ ውጭ ወጣ። በውስጡ ያሉት አፍጠው ወደ እኛ ይመለከቱ ነበር። ቀጥሎም ዘወትር እንደምናደርገው ወደ ወርቅዬ ቤት ሄድን። ሁል ጊዜ ማምሻው ላይ ወደ ወርቅዬ ቤት ሄደን ትንሽ እንጫወት ነበር። ዛሬ ግን እንዳጋጣሚ ሆኖ ወርቅዬ ሌላ ቀጠሮ አለበት ስለ ተባለ መቆየት አልቻልንም። ከዚያም አቋራጩን መንገድ መርጠን ወደ ቤታችን ሄድን። በመንገዳችን ላይ የባፈናን ልጅ ዳዊትን አገኘነው። ዳዊት አብሮን ከእኛ ጋር ወደ ቤቴ በመምጣቱ የምኖርበትን ቤት የማየት አጋጣሚ አገኘ። በኋላም በ12፡00 ላይ ከእናቱ ከባፈና ጋር ተመልሶ መጣ። እራት አብረን በልተን ተለያየን። ከዛን ቀን ጀምሮ ከባፈና ጋር በምስጢር እንገናኝ ነበር። እኔ ጋ ለመምጣት ስትፈልግ ለግቢው ዘበኛ የታመመ ጓደኛ እንደምትጠይቅ በመንገር ነበር።
ጥቅምት, 28, 1994
ዛሬ የማስጠናት ፕሮግራማችንን በይፋ ጀምረናል። መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች የደስታ ፊት ይታይባቸዋል። በእነርሱ መደሰት እኔም በጣም ደስ ብሎኛል።
ህዳር 13, 1994
እኔ የምኖረው ለክርስቶስ ነው። ሞቴም እንዲሁ ለእርሱ ነው። ኢየሱስ የእኔ ነው። ይህ ዘላለማዊ የሆነ የፃድቃን ማረጋገጫ ነው።ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔ ምክንያትም ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ። ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ ሀሴትም አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያት እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና። ጌታዬ ክርስቶስ ያለፈበት ነውና በዝተው በእኔ ላይ የተጫኑትን የስቃይ መንገዶቼን እከተላለሁ። ይህንንም የማደርገው በደስታ ነው። የተላኩበትን ተሸክሜ ጌታዬን እከተላለሁ። እርሱ ሁሉ በሁሉ የሆነ ነውና ሁለመናዬን ለእርሱ አሰረክባለሁ።
ህዳር 16, 1994
ትላንትና አንድ መልካም ዜና ሰማሁ፤ ሚኪ ቤታችንን የመልቀቁን ዜና። ይህ የራስ ምታቴ ምንጭ ነበርና እውነትም ትልቅ ዜና ነው። ከሁሉም በላይ በዚህን ጊዜ መሆኑ ድንቅ ነው። ሰኞ ቀን በኃይሉ ፍርድ እንደሚያገኝ አበበ ነገረኝ። በኃይሉ ሙሰኛ ነው። የመንግስት ሀላፊዎች በአጭር ቀናት ውስጥ በበሀይሉ ላይ የሚወስዱትን እርምጃ እንደሚያሳውቁ እንዲሁ መረጃ ሰጥቶኛል። የመጀመሪያው ባለቤቴ ከርል የሞተው ከ13 ዓመት በፊት በዛሬው ቀን ነው።
ህዳር 27, 1994
ምንም እንኳ ምን ዓይነት ቅጣት በበሀይሉ ላይ እንደሚወሰድ ባያውቅም አበበ በጠዋት መጥቷል። በሀይሉን መልካም እንደማይጠብቀው አበበ ይናገራል። ነገር ግን ምንም እንዳልተሰማው እንደተገነዘበ አበበ ነግሮኛል። አምላኬ ሆይ ይህ ሁሉ ወዴት እንደሚያመራ አላውቅም። ነገር ግን አንተን አምናለሁ፤ ህይወቴን በእጆችህ ላይ አደራ ሰጥቻለሁ። አንተ ምራኝ፣ ጥበብ ስጠኝ። አምላኬ አመሰግናለሁ፤ ስምህን ከፍ ከፍ አደርጋለሁ። አብዛኛዎቻችን ክፍሎቹን ለማየት ሄድን። ትናንት ማታ በቤተ ክርስትያኑ የተባለውንም ጉዳይ ሰምተናል። ክፍሎቹን ለማየት ስንሄድ ባፈና ከእኔ ጋር ነበረች። ሁለቱ የበሀይሉ ጓደኞች እኔን፣ ባፈናንና ሌሎቹንም በጋራ ሆነን ስንሄድ አይተውናል። እርግጠኛ ነኝ ወዲያው ሄደው እንደሚነግሩት አልጠራጠርም። ነገር ግን ከአሁን በኋላ ምን ሊያደርግ ይችላል? አበበ እንደ ነገረኝ የመንግስት ሀላፊዎች በሰራተኞች ላይ ምንም ዓይነት እርምጃ እንዳይወስድ እንዳስጠነቀቁት ነግሮኛል። አምላኬ ሆይ ለበኃይሉና ደመረ ያለኝን ፍቅር ልተው አልችልም። እባክህ በመንፈስህ ንካቸው፤ የሚራራ ልብም ስጣቸው። ለንሰሃም አነሳሳቸው።
ታህሳስ 9, 1994
ዛሬ ከአበበ ጋር ተገናኝተን ስለ እሱ ስንወያይ በቦታው ላይ ሊመለስ እንደሚችል ነገረኝ። ምክንያቱም በሀይሉ የእርሱን ቢሮ ህገ ወጥ በሆነ ሁኔታ እንዳሸገ አምኗል ብሎኛል። ይህንን ህገ ወጥ ስራውን በፅሁፍ አረጋግጧል።
ታህሳስ 10, 1994
መስማት ለተሳናቸው መጠቀሚያ የሚሆን ክፍሎች ልደታ አከባቢ በኪራይ አግኝተናል። በ4፡30 ላይ እነዚህን ክፍሎች ለማየት ቀጠሮ ይዣለሁ። ዛሬ ስለ ክርስቶስ ቤተ ክርስትያን የሰማሁት የለም።
ጥር 1, 2002 መልካም አዲስ ዓመት!
ታህሳስ 24, 1994
ዛሬ አበበ አበራ እኛን ለማስማማት ከበሀይሉ ጋር 3 ሰዓታት የፈጀ ስብሰባ አድርጓል። ከዚህ ረጂም ውይይት በኋላ በሀይሉ ከእኔ ጋር ምንም መስራት እንደማይፈልግ ገልፆለታል። ዛሬ ጥሩ አይሰማኝም። በሀይሉ ለባለስልጣናት የሚረጨውን የጉቦ መጠን ስሰማ እጅግ ደነገጥኩ። ለሁሉም ጉቦ ይሰጣል። ግቢ ውስጥ ለሚኖሩትም ገንዘብ በመስጠት ደግነቱን እያሳየ ነው። ይህ ሁሉ ያልነበረውን መልካም ግንኙነት በገንዘብ ሀይል ለመመለስ እየጣረ መሆኑን ያሳያል። እኔን በተመለከተ ደግሞ በክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ስራ ውስጥ ያለአግባብ ጣልቃ እየገባሽ ስለሆነ ለሚትፈጥሪው ችግር ፍርድ ታገኚያለሽ በማለት ይዝትብኛል። ዛቻውንም የሚያደርሰኝ በገብረ ማሪያም በኩል ነው። ይህንን የሚናገረው በድፍረት ነው። ምክንያቱም ጭፍንና ማየት በማይችሉ የአሜሪካን ክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ላይ እምነቱን አድርጓልና ከልቡ ተማምኗቸዋል። እነሱም አስተማማኝ ድጋፍ ሰጥተውታል።
ታህሳስ 25, 1994
አበበ በመባረሩ ምክንያት በመካኒሳ መስማት የተሳናቸው ትምህርት ቤት የሚገኙ ተማሪዎች እጅ ቅር ተሰኝተዋል። በዚህም ምክንያት ዛሬ ሁሉም ተማሪዎች ከትምህርት ቤት ቀርተዋል። አበበ እንዲመለስላቸው ይፈልጋሉ። ትምህርት በማቆም በበሀይሉ ላይ ያላቸውን ቅሬታ ገልጸዋል።
ታህሳስ 26, 1994
ምንም እንኳን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ሀይማኖት ዘንድ የዓመት በዓል ቢሆንም የመካኒሳ መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች ዛሬም ወደ ትምህርት ቤት አልተመለሱም። በሀይሉ ባልተገባ ሁኔታ የትምህርት ቤቱን ዳይሬክተር የነበረውን አበበን በማባረሩ ቅሬታቸውን በመግለፅ ላይ ናቸው። በዚህ ምክንያት በሀይሉ ዛሬ ማታ ከአበበ ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ይህ ካልሆነ ደግሞ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጉዳዩን አስመልክቶ ለሀይሉ ቃለ-መጠይቅ እንደሚያደርግ ሰምተናል። ቃለ-መጠይቁም የፊታችን ረቡዕ በትምህርት ቤቱ ግቢ ወስጥ እንደሚሆን ይጠበቃል። ይህ ከሆነ ደግሞ ለበሀይሉ ታላቅ ውርደት ነው። ይህ በድብቅ የሚደረገው ሩጫ ለሕዝብ ይፋ ሊሆን ነው ማለት ነው? ጌታ ሆይ እኔ በአንተ ብቻ እታመናለሁ። አንተን ብቻ አምናለሁ። ሀያልነትህን አሳይ። ፍትህ የሚገኘው ከአንተ ነውና ፍርድ ስጥ። ሳይዘገይ እባክህ የበሀይሉን ልብ ንካ። የቤተ ክርስትያኑ ንብረት የሆነችው ሰማያዊ ቀለም ያላት መኪና ጉዳይ በተመለከተ ከአለን ጋር እየተፃፃፍኩ ነው። ይች መኪና የተሸጠበትን ገንዘብ የወሰደው በሀይሉ ነው። ሙስና የጀመረው በዚህ ይሆን? ስለዚህ ጉዳይ ምን ማድረግ አለብኝ?






